Amen Electrical Technology Official®
22.9K subscribers
955 photos
21 videos
18 files
591 links
We provide professional #training with Job creation supported by workshop and on-site training which is unique in its kind.
Website: www.amenelectrical.com
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
📱0991156969
📱0939555510
Download Telegram
#NEMA Vs #IEC Standards
=======================
👉ሰላም ውድ የአሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ስለኮንታክተር፣ ስለ ሪሌይ፣ ስለ ሞተር ማስጀመሪያ ዘዴዎች (motor starting methods) እና ሰለሞተር ኮንትሮል (motor control) በቀጣይ በሰፊው እናያለን። ነገር ግን ከዛ በፊት ብዙ ሰዎችን ስለሚያደናግሩት ሁለቱ ስታንዳርዶች ቀድመን ብናይ በቀጣይ የምናያቸውን ትምህርቶች በቀላሉ ለመረዳት ይረዱናል። እነሱም:-
🔹IEC- International electrotechnical Commission
👉ለሁሉም የኤሌክትሪክ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ስለተዛማጅ ቴክኖሎጂዎች አለም አቀፍ ደረጃዎችን የሚያዘጋጅና የሚያትም አለም አቀፍ የደረጃዎች ድርጅት (ኤሌክትሮቴክኖሎጂ ) በመባል የሚታወቅ ሲሆን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኮንግረስ እ.ኤ.አ. በ 1881 በፓሪስ ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኤክስፖ ተካሂዷል ፡፡ በዚያን ጊዜ ስለዓለም ኤሌክትሪክ እና ማግኔቲክ አሃዶች ስርዓትም ተስማምተዋል ፡፡
👉ከዛን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ጊዚያት ማሻሻያዎችን እያረግና የተለያዩ ሀገሮችን በአባልነት እያካተተ ያለ አለም አቀፍ የደረጃዎች ድርጅት ሲሆን የኛዋ ሀገር #ኢትዮጵያም በተባባሪ አባልነት/ በውስን የድምፅ አሰጣጥ እና የአስተደደር መብቶች(Associate Member) ሆና ተካታለች።
👉ከኋይል ማመንጨት፣ ከማስተላለፍ እና ከማሰራጨት እስከ የቤት ውስጥ መገልገያ መሳሪያዎች፣ የቢሮ ቁሳቁሶች፣ ሰሚኮንዳክተሮች፣ ፋይበር ኦፕቲክስ፣ ባትሪ፣ የፀሐይ ሀይል፣ ናኖ ቴክኖሎጂ እና ሌሎችንም በርካታ የቴክኖሎጂ አይነቶችን ይሸፍናል።
🔸NEMA-National Electrical Manufacturers Association
👉 ብሔራዊ ኤሌክትሪክ አምራቾች ማህበር (NEMA) በሰሜን አሜሪካ ውስጥ በተለይ በኢንዱስትሪ ቦታዎች ለሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ኤሌክትሪክ መተግበሪያዎች የሚያገለግሉ ደረጃዎችን የሚያወጣ ማህበር ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰረተውም እ.ኤ.አ በ1921 ነው።
👉ደረጃዎችም በአደገኛ ክፍሎች፣ የግል ተደራሽነት እና ተጨማሪ በአይነት ላይ ተመረኮዞ የአካባቢ ሁኔታዎችን ለመከላከል የሚወጡ ናቸው ፡፡
👉ለዩነታቸው እንደሚከተለው ቀርቧል።
🔹IEC
▪️ዋጋቸው ዝቅተኛ ነው።
▪️ለአንድ አላማ ብቻ የሚያገለግሉ ናቸው።
▪️መጠናቸው አነስተኛ ነው።
▪️ለአለም አቀፍ ገበያ ያቀርባል።
▪️ኦቨርሎድ ሲፈጠር ፈጣን ምላሺ ይሰጣሉ።
▪️ሴፍቲ ከቨር አይፈልጉም።
🔸NEMA
▪️ዋጋቸው ውድ ነው።
▪️ለተለያዩ አገልግሎት ይውላሉ።
▪️መጠናቸው ትልቅ ነው።
▪️ለሰሜን አሜሪካ ገበያ ያቀርባል።
▪️ሾርት ሰርኪዩት ሲፈጠር ፈጣን ምላሺ ይሰጣሉ።
▪️ሴፍቲ ከቨር ይፈልጋሉ።
👉ስለዚህ በዚህ መሰረት አንድ የኤሌክትሪክ እቃ ስንገዛ የየትኛው ስታንዳርድ ነው የሚለውን መለየትና መግዛት እንዲሁም በስታንዳርዱ መሰረት መስራት አስፈላጊ ነው።

👉#ስለምትከታተሉን_እናመሰግናለን🙏

👉#ለሌሎችም_ያጋሩ❗️

🔹ለቴሌግራም ቻናላችን:-
👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE2DpDe9fPGCTupqTg

🔹ሀሳብ ለመስጠት
👇
https://t.me/electricexpert

"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን!"
🔹🔸🔹ለወዳጅዎም ያጋሩ!🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹እናመሰግናለን!🔹🔸🔹