Amazing Pictures & poems ✍
83 subscribers
29 photos
2 videos
9 files
112 links
Download Telegram
"~ይድረስ ለወንድሜ ለማላውቅህ"

አበበ ባልቻ ".... አሁን ያለውን ዘረኝነት ከነ መንስኤውና ሙሉ ችግሩ ጋሽ ጸጋዬ ከ 50 አመት በፊት  በዚህ ግጥም ገልጾታል..."

ሚካኤል ሽፈረው "...ወቅቱ የብሔር ብሔረሰብ ጉዳይ የሚቀነቀንበት ወቅት ነበር ጋሽ ጸጋዬ ይሄን አጀንዳ ከየት አመጣችሁት ብሎ በሌላ መንገድ ነበር የሚያየው..."
°
"...ይድረስ ለወንድሜ ለማላውቅህ..."

°
ይድረስ ላንተ ለማላውቅህ
ለወንድሜ ሩቅ ለማልፍህ
ለምታውቀኝ-ለማላውቅህ፥ ለምታየኝ-ለማላይህ. . .
ማነህ ባክህ?
ሳትወደኝም ሳታምነኝም፥ አጢነህ ለምትፈራኝ
ስናገርህ አጠንቅረህ፥ አተኩረህ ለምትሰማኝ….
ይድረስ ለክቡር ወንድሜ፥
ለአረህ ዟሪው ለገታሩ
ለሩቅ ገጠሬ ነባሩ
ለማላውቅህ ለዳር ዳሩ፥….
ማነህ
ከሩቅ የምታስተውለኝ
የማልለይህ-የምትለየኝ
ተግተህ የምትገምተኝ፥
ያላየኸኝ አስመስለህ
አቀርቅረህ ተግ ብለህ
ባንደበትህ የእርግማን መርዝ፥
በልብህ ትእዝብት ቋጥረህ…
የፀጥታው የዋሻው ሱቅ
ማነህ አንተ የቅርቤ-ሩቅ
ማነህ….
ከረን ነህ መለሎ ብሌን
ከአሰብ ወደብ እስከ ስሜን
ስትሳብ ስትሰበሰብ
ሽንጠ ሰንበሌጠ-መርገብ
ከኡመ-ራ ነህ ከመረብ
አኑአክ ወይስ ገለብ
ከዘር ተገፍተህ ተሰደህ
በሐሩር ሰደድ ተጥለህ
በንዳድ መቀመቅ ታጥረህ
በእልቂት አፋፍ ፈፋ ያለህ
ማነህ
‘አጋው’ ነህ ወይስ ሺናሻ
ቅማንቴ ነህ ወይ ፈላሻ
ስምህ የሆነብን ግርሻ፥
ግራ ጐንደር ነህ መተከል
ባላዋቂ የምላስ ቅርስ፥ የዘር ንፍገት ስትቀበል
ያለዕዳህ ስምህ ሲበከል
እምትችል እምትቀበል፥ እማትሞት እማትነቀል
ማነህ
ቆለኛ ሸክላ ሠሪ ነህ
ያገር ዕድል ያገለለህ።
ለጥበብህ እንደመካስ
በደባትር ትንታግ ምላስ
ዘለዓለም ልብህ የሚላስ
ማነህ
ገባር ነህ የሙክት ሳቢ
እረኛ ነህ የከብት አርቢ
አራሽ ነህ ያገር ቀላቢ
አማል ነህ የግመል ሳቢ….
ባክህ ማነህ ወንድምዬ፥ አንድም ቀን የማንወያይ
በውል፥ በጣይ፥ ባደባባይ
በፎቶ ግራፍ ዓይን እንጂ፥ ዓይን ለዓይን የማንተያይ
እኔ ለወሬ አንተን መሳይ፥ አንተ ለጭንቅ እኔን መሳይ።
ማነህ እኮ የማላውቅህ
ማዶ ለማዶ ሩቅ ለሩቅ፥ በመኪና ዓይን የማይህ
የማትቀርበኝ የማልቀርብህ
ጠረንክን የምጠየፍህ
በጋዜጣ በመጽሔት፥ ወሬህን የምተርክህ
ሥዕልክን ፎቶግራፍክን፥ ላገር ጎብኚ የምሸጥህ፥
ማነህ አንተ ወንድምዬ፥ የማላውቅህ የምታውቀኝ
ሶዶሬ ማዶ እምታልፈኝ
በዝምታህ የምትከሰኝ
ባይንህ ጦር የምትገሥፀኝ
የሆድክን የማልጠይቅህ፥ የሆድክን የማተነግረኝ፥
ማነህ
ቦረን ነህ አባ ጋናሌ
የኛዻ ጠር አባ ጣሌ
ወይ ‘ሳፋር’ ንጥረ ሶማሌ፥
ከረን ነህ ወይስ ዳንካሌ
አፋር ነህ አባ ቱማታ
ማታሐራ ወይ ከምባታ
ወይስ ኩናማ አባ ዱታ፥
ማነህ ጐበዝ ማነህ አያ
ኢማኑ ነህ አባ ራያ
ወይስ ኢቱ አባ ሎቲ
የአዳል ሞአ የአዳል ሞቲ፥
እኮ ማነህ ሩቅ ያለኸው
ማንነትክን የማላውቀው
እማልሰማ እማልጠይቅህ
እማትነግረኝ እማላውቅህ፥
ማነህ ጐበዝ ላስተውልህ፥ አተኩረህ ጭጭ እምትል
እማትጣጠፍ ቅምጥል
መሃል አገር ያልሸተተህ
ባሻገር ዙር ድንበር ያለህ
የእህል ደላላ እሚበላህ
ባለሚዛን እሚያዋካህ፥
ማነህ
የዝምታ መደብር ነህ?….
እኮ ማነህ ስምህ ማነው
የዘር ግንድህ የሰየመው
ተበጥሶ ያልተቀጠለው
ሥርህ ማነው?….
በልቦናህ የምታማኝ
ታዝበህ የምትሰማኝ
ባትወደኝም ባታምነኝም፥ አጢነህ የምትፈራኝ
ማክበር እንጂ እማታስጠጋኝ፥
ማንነትክን ምንነትንክን፥ ላልሰማህ የምጠይቅህ
ለጉልበት ለላብህ በቀር፥ ላንተነትህ የማልቀርብህ
ከዓይነ-ጥላዬ እምትሸሸኝ፥ ከዓይነ-ጥላህ እማልርቅህ
ላፌ እንጂ ለልቦናዬ፥ የማትመስለኝ የማልመስልህ
ከመንፈሴ እምገልልህ
ከሕሊናዬ እማሸሽህ
ቦታህን የማትረሳ፥ ቦታህን የማስታውስህ….
ማነህ
ይድረስ ለክቡር ወንድሜ፥ ሕመምከን ለማታዋየኝ
በጸጥታህ ለምትወቅሰኝ
ጐፈሬህን እንደአባትህ፥ እንደሞያህ አጐፍረህ
በወለባ አንቆጥቁጠህ
ሎቲ አጥልቀህ ጦር አንግበህ
በመኪና እግር እማልፍህ
የማትጠራኝ የማላውቅህ፥
ማነህ
በየቱሪስቱ ካርድ ላይ
ከቦህ ሰማያዊ ሰማይ
አተኩረህ የምትታይ
ውሸትክን ፈጠህ ሳቅሁ ባይ፥
እንደቴክኖክራሲ አግቦ
ዙሪያህ በሀሰት ጌጥ ታጅቦ
እፎይታ ያቀፈህ መስለህ
ትእዝብት በዓይንህ ጦር አዝለህ
ርቀህ ተቀብረህ ሰንብተህ
የቱሪስት ካርድ የሳበህ
አንተ ማነህ?
እኮ ማነህ ወንድምዬ፥ ደራሲ የሚቀኝብህ
ሠዓሊ የሚነድፍብህ
ቀሲስ የሚቀሰስብህ
የቱሪስት የጋዜጠኛ፥ ካሜራ እሚጋበዝብህ
የሚተች የሚተረጉም፥ የሚነድፍህ የማንም እጅ
የማነህ ደም የማነህ ቅጅ?….
አንተ የማማ ኢትዮዽያ ልጅ
እኔማ ሆኜብህ ፈረንጅ
አሳብ ለአሳብ ለተጣጣን
ምን አጣላን ማን አጣላን
ማን እንዳንወያይ ገራን
እንደባቢሎን ኬላ ግንብ፥ ለመተላለፍ የቀባን
አንተን የዘልማድ ዘላን፥ እኔን የመኪና ዘላን
እንድንሆን የገፋፋን?
ማነው ምንድነው ወንድሜ፥ ሆድ ለሆድ የሚያናክሰን
ሳንርቅ የሚያራርቀን፥ ሳናኮርፍ የሚያኳርፈን!….
ይድረስ ለክቡር ወንድሜ፥ ለምትሳብ ናዳ ጥጉን
ፈፋ ዙሪያ ሸንተረሩን
ሸለቆውን ፈረፈሩን
ዳር ድንበሩን ሩቁን-ሩቁን፥
ከዘር ተገፍተህ ተሰደህ
በሐሩር ሰደድ ተጥለህ
በንዳድ መቀመቅ ታጥረህ
በእልእቂት አፋፍ ፈፋ ላለህ….
እኛ መሀል ለሌለኸው
ታሪክህ ለተሸፈነው
ሁሉን ከሩቅ አብሰልስለህ፥ አጠንቅረህ ለምታየው….
ይድረስ ለክቡር ወንድሜ፥ ለምታየኝ ለማላይህ
ለምታውቀኝ ለማላውቅህ
ማነህ ባክህ….
ማነህ

(ለበጌምድር ወይጦ ባላገር –፲፱፻፷፫ – ደባርቅ)
(ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን ከእሳት ወይ አበባ )

https://t.me/albotube
👍2
Forwarded from 🚸....🦋️📱
Forwarded from 🚸....🦋️📱
🎚🎚((ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው))

🎚በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣

🎚አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ  ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፥፥

✅አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፥

✅ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው፥

✅አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፣

✅በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን  የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፣

✅ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣

✅ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ

🎚እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል

🎚በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም ፣

🎚የ1️⃣ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው ፣

🎚ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና  አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣

🎚ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣
,
…የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል

🎚አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል  ቁልቁል ትወርዳለህ፣

🎚እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፥፥
ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ ፣

✅5️⃣ ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …

🎚ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፥፥ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፣

🎚ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ ፣

🎚የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፣
,
🎚"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፥

🎚ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፣

🎚በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ ፣

🎚በዓለም ላይ ያሉ🔢ቱ ፈዋሽ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው…
✅የፀሃይ ብርሃን
✅እረፍት
✅ስፖርት
✅ምግብ
✅በራስ መተማመን እና
✅ጓደኛ

እነዚህን አጥብቀህ ያዝ፥፥ ደስተኛ ህይወትን አጣጥም!!


ምንጭ ➖Science Cafe
ሰሞንኛ፤

(የሚያስተክዝ ወግ)፤

(በእውቀቱ ስዩም)፤
እንዴት ሰነበታችሁ? እኔ በተቻለኝ መጠን በእጄ እሚገኘውን ጥሬ እቃ በሙሉ በመጠቀም ለመደሰት  እየሞከርኩ ነው፤  አንዳንዴ ፥ለመደሰት  ካለኝ ቁርጠኝነት የተነሳ በአክሊሉ ስዩም ዘፈን ሳይቀር ከመደነስ ወደ ሁዋላ አልልም፤

ስሙኝማ!   አሜሪካ ለሶማልያ ኮማንዶዎች የምታደርገውን የምግብ እርዳታ አቋረጠች እሚል ዜና “ዋዜማ “ ገጽ ላይ አነበብኩ፤ ምክንያቱ ደግሞ ኮማንዶዎቹ በልገሳ የሚያገኙትን  ልዩ ምግብ ገበያ ላይ አውጥተው ጆሮውን ስላሉት ነው፤

አሜሪካ  ግን ምን ነካት? ሀያል አገር አልነበረችም እንዴ?  የሶማሌ ኮማንዶዎች ከምግብ የላቀ ፍላጎት እንዳላቸው አታውቅምን?  አንድ የሶማሌ ኮማንዶ አሜሪካ ሂሳብ የዘጋችበትን  ክትፎ ሸጦ፥ መለስተኛ ቅቅል በልቶ ፥ በተረፈው ፥  አንድ ዙርባ ባህርዳር በብብቱ  ስር እንደ ቴርሞሜትር ሻጥ አድርጎ  ወደ ምሽጉ መግባት አለበት፤ እነ ባይደን ፥ የአራራውን ነገር  ከግንዛቤ  እስካላስገቡ ድረስ ኮማንዶዎቹ በዚህ ብቻ አይመለሱም፤ ገና  ታንኩን  አወላልቀው ስፖኪዮውን ለብቻ ፥ አፈሙዙን ለብቻ ገነጣጥለው ለገበያ ያቀርቡታል፤

ባልተያያዘ ዜና፥ ባለፈው የከተማ መጸዳጃ ግንባታ መዋጮ ሲጠየቅ ጓደኞቼ አቃቂር ማውጣት ጀመሩ፤ ለምሳሌ ምኡዝ  " ሀብታም አጥር ስር  መሽናት፥ ድሆች ቅሬታቸውን የሚገልጹበት  ወጭ -ቆጣቢ አብዮት ነው፤ ችግሩን ሳናስወግድ ምልክቱን ማዳፈን የለብንም” ብሎ ደሰኮረ፤

እኔ ግን  የማስተባበርያው ቢሮ ደወልኩና ተቀባይዋን  “ ከደመወዜ ላይ አምስት  መቶ ብር ልልክላችሁ ወስኛለሁ፤ ብዙም ባይሆን ለሁለት ጉድጓድ መቆፈርያ ይሆናል ” ስላት የመለሰችልኝ መልስ ሞራል ይነካል፤

“ለችግኝ ጉድጓድ ነው?”
ልብ ብላችሁ ከሆነ፥ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ የምግብ እቃዎች መጠናቸው እያነሰ ነው ፤  የሆነ ሱቅ ፊትለፊት “የሚሸጥ ምጣድ “ የሚል ተዘርግቶ አይቼ ተከዝኩ ፤ ምጣዱ ከማነሱ የተነሳ  በስናይፐር እንኳ ብትጋግሩበት መሀሉን  ትስቱታላችሁ!  ምጣድ ድሮ ቀረ ወዳጄ!  ድሮ እኛ ቤት የነበረው ምጣድ  በጣም ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ እናቴ  በበቅሎ እየዞረች ነበር የምትጋግርበት፤

በመጨረሻ የእለቱ መልእክቴ "ለአላማ እንኑር " የሚል ነው፤ ለአላማው በየትኛውም ሁኔታ ያለውን ተሰጥኦ የሚጠቀም ሰው አደንቃለሁ፤ ባግባቡ ከተጠቀምክበት ጉራም ስጦታ ነው፤

በቀደም እኛ ሰፈር በሚገኘው የገንዘብ መሸምጠጫ ማሽን (ኤቲኤም ) ላይ ወረፋ ይዣለሁ ፤ከፊትለፊቴ ያለው ጎረምሳ ካርዱን ማሽኑ ውስጥ ከከተተ በሁዋላ አጠገቡ ያለቺውን ዘናጭ ሴት” ኢምፕረስ “   ለማድረግ  ፈለገ፤ ኤቲኤሙ ጠረር አርጎ የተፋለትን   ሁለትሺህ ብር   ቆጥሮ ወደ ኪሱ ከተተና  የማሽኑን ትከሻ መታመታ እያደረገ ምን አለ፤

  “ መልሱን ያዘው ! “

https://t.me/albotube
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!!!

በዓሉ.........
የሠላም ፣ የፍቅር እና ደስታ የሞላበት በዓል እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!!!!

..............መልካም በዓል ይሁንላችሁ!!!!

ለወዳጅ ዘመድዎ በመላክ መልካም ምኞትዎን ይግለፁ.....!!


https://t.me/albotube
ምሽት በረንዳ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)

አገር ምድሩ መሽቶ
ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ 
የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን 
ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን
ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ
አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ
የሌት አይኔን ሲሳይ

በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ
የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ   
በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ
ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ
አንዲት ሴት እያየሁ
አሰላስላለሁ ፤

“ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ
በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ
ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው
የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው
ፍቅር ሲያጣጥሙ
ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ
ይች ወገን አልባ
የሌሊት አበባ
በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች
የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?”

እያልሁ አስባለሁ፥ 



ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ
የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ

በግልጥ  ይታየኛል
“ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል
በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል"
የሚል ይመስለኛል  ፤

በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት  ስምሪት
ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት
አይቼ ማልዘልቀው
ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው
መከራና ውበት የሚያፈራርቀው ።

https://t.me/yafrica21
"The donkey said to the tiger:"The grass is blue."
The tiger replied: "No, the grass is green."

The discussion heated up, and the two decided to go to the lion, the king of the jungle.

Already before reaching the forest, where the lion was sitting on his throne, the donkey began to shout:

"His Highness, is it true that the grass is blue?"
The lion replied: "True, the grass is blue."

The donkey hurried and continued:"The tiger disagrees with me and contradicts and annoys me, please punish him."

The king then declared:

"The tiger will be punished with 5 years of silence."

The donkey jumped cheerfully and went on his way, content and repeating: "The grass is blue!"

The tiger accepted his punishment, but he asked the lion: "Your Majesty, why have you punished me? After all, the grass is green."

The lion replied: "In fact, the grass is green."

The tiger asked: "So why are you punishing me?"

The lion replied: "That has nothing to do with the question of whether the grass is blue or green.

The punishment is because it is not possible for a brave and intelligent creature like you to waste time arguing with a donkey, and on top of that come and bother me with that question."

The worst waste of time is arguing with the fool and fanatic who does not care about truth or reality, but only the victory of his beliefs and illusions.

Never waste time on arguments that don't make sense...

There are people who, no matter how much evidence and evidence we present to them, are not in the capacity to understand, and others are blinded by ego, hatred and resentment, and all they want is to be right even if they are not.

When ignorance screams, intelligence is silent. Your peace and quietness are worth more."

https://t.me/yafrica21
👍1
እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!❤️
በጨዋታ መሃል ፦

<<በራስህ አትተማመንም አይደል>> አለቺኝ ?

እንዴት ልበ ሙሉነት የተጠናወተኝ ሰው እንደሆንኩ ከራሴ ጋ እየተሻማው አወራሁ... አብራራሁ... ዘበዘብኩ

በእርጋታ ከሰማቺኝ በኃላ
<<እንዴት እንደዚህ አልሽ ብትለኝ እና ያስተዋልኩትን ብነግርህ  አይሻልም?>> አለቺኝ

<<ቀጥይ>> አልኳት ደስ ባላለው ፊት እያየኃት

<<ስላለህ፣ ስላስደመምከው  ፣ስላደረከው ነገር ብዙ ሰአት ሁል ግዜ ታብራራልህ ።  የተጣላኸውን የጠላኸውን ያናደደህን  ሰው ስህተት እና ያንተን ቅድስና ታስረዳለህ ፣

ሰው ስለራሱ ሲያወራህ ቀጥለህ እኔ.. እኔም.. ብለህ ስለ ራስ ታወራለህ ምንም ነገር ስትሰማ ከራስህ ጋ እያወዳደርክ ነው መሰለኝ ።

ሰው ሲቃወምክ ስለምታወራው ነገር ሳይስማማ ሲቀር ቅር ይልሃል... ብዙ ታብራራለህ ። ያመንከው እና የሆንከውን እንዲመሰከርልህ እንዲጨበጨብልህ ጉንጭህ እስኪዝል ታስረዳለህ  ።

ስላደረከው እና ስለሆንከው ነገር አስተያየት ትጠይቃለህ ደስታህ የሰው አስተያየት ላይ ተንጠልጥሎል።

እምቢ ማለት ይከብደሃል ። እምቢ ከማለት መዋሸት ትመርጣለህ ። ባላሳቀህ ነገር ትስቃለህ ፣

የአዲስ ሰው ቀልብ ለመሳብ እሱ የሚወደውን ነገር ለማውራት ለመሆኑ ጥረት ስታደርግ ብዙ ግዜ ያስተዋልኩ ይመስለኛል ።

ሰው እንዳይቀየም ስትል መጠየቅ ያለብህን አጠይቅም ።

ያበደርከውን ብደር እንኳን ስትጠይቅ ችግር እንዳጋጠመክ አብራርተህ ነው ።

ራስህን አታከብርም መሰለኝ እራስን አለማክበር  አንደኛው  በራስ ያለመተማመን ውጤት ነው !!

ከጠላት ሁሉ ጠላት  የሚከፋው የውስጥ ጠላት ነው ። ከራስህ ጋ የታረክ  ግዜ አለም ቢጣላህ እንኳን አትሸበርም ።

ስታወራ ረጋ ብለህ  ተናገር !
ለመወደድ ስቃይ አትብላ !
ሰው አክብር  እንጂ አክብደህ አትይ !
ሁሉንም እቅድህን ለሁሉም አታውራ!
የተሰማህን ሁሉ አትናገር !
እምቢ አልችልም ማለት ልመድ !
ስለተሳካልህ ነገር ሂደት በየሜዳው አታብራራ !

ያልተቀበልከው ማንነት ካለ የበታችነት ስሜት የሚያሰማህ ሁነት ካለ ረጋ ብለህ አጥናውና መላ ፈልግለት ።

ብቻህንም መሆን ልመድ ሁሌ አብሮ ሰው እንዲሆን አታስስ

ዝም ብዬ አየኋት ።

ልክ ካልሆንኩ፣ ያልኩት እውነት ከሌለው እንደቀባጠርኩ ከተሰማህ አፉ በለኝ
ካወራውት ፍሬ ነገር ካገኘህበት ደሞ ደግ >>

አሁንም ዝም አልኳት ።  ዝምታዬ ውስጥ ግን መደነቅ እና ድብርት  ነበረበት

https://t.me/amaz_pic
👍1
`` አለቃ ማለት ስትቀድመው አርፍዶ የሚመጣ፤ ስታረፍድ ቀድሞ የሚመጣ ሰው ነው። `` 🤗   -ጆርጅ በርናርድ ሾው



https://t.me/amaz_pic
ሲጎልብን የሚያስቡልን ፣ የሌለንን ሆን ብለው የማያስታውሱ ፣ ጨለማችንን ለማብራት የሚተጉ፣ ብታገባ   ፣ብትሰራ ፣ ቢሻለው ፣ ቢያገኝ እያሉ የጎደለንን የሚያዩልን እንዲሞላልን የሚጥሩ ፦

የሚወዱን ፣ እንደዋዛ የማያዩን፣ ከላይ ሆነው የማይፈርዱብን ፣ ያደረግነውን ጥንጥ ነገር የሚቆጥሩልን ስሜታችን ደንታ የሚሰጣቸው ........

https://t.me/amaz_pic
እያንዳንዱ ትውልድ ተረኛ ነዋሪ ነው❗
የነገ ሟች የዛሬ ሟችን ይቀብራል...❗
ከ150 ዓመታት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 ዓመታት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም ፈፁመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡

እስኪ ወደ ኋላ 150 ዓመታት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡

ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡

አስታውሳለሁ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝን ዝና ቀርቶ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 ዓመታት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡

አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 ዓመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡

ማጠቃለያው ህይወትን ቀለል አድርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሆነው ተረስተዋል፡፡

ከ150 ዓመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡ ለዚች ምድር ዘላለማዊ ሳይሆን ተረኛ ነዋሪ ነን፣ነገ የምናልፍ፣ከተመቻችሁ ሼር አድርጉት።


https://t.me/albotube

https://t.me/amaz_pic
❤2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Hey everyone,

First off, I want to apologize for my recent absence. I've been on a break these past few months, and I truly appreciate your patience and continued presence in the group.
I've noticed a significant number of you have been leaving recently, and I genuinely want to understand why. Your feedback is incredibly important to me.
Please, tell me:
What are your reasons for leaving the group?
What kind of content would you love to see more of?
My goal is to create a vibrant and valuable space for all of you, and I can only do that with your honest input. Based on your suggestions, I'm committed to consistently uploading the content you want to see.
Thank you for being a part of this community. Let's make it even better together!


https://t.me/albotube
❤1
የተካደ ትውልድ
(በእውቀቱ ስዩም)
የተካደ ትውልድ
አይዞህ ባይ የሌለው
ታዳጊ የሌለው
ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው
ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤

የተካደ ትውልድ

አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ
ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ
እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት
አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤

ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍት የተቀማ
አልጋው ያጋም እሾህ፥ ምኝታው የሳማ፤

የተካደ ትውልድ

ሞቶ እንኳን ሬሳው፥ አይላላለት ቀንበር
በዘብ እጅ ተገድሎ ፥ በሹም የሚቀበር
ከጡት አስጥል በላይ፥ ኑሮ የመረረው
እንዳይሄድ ጎዳናው ፥ የተደናገረው
ድል ያልሰመረለት ፥ትግል ሳይቸግረው: :

የተካደ ትውልድ
በስጋ በነፍሱ
በቀልቡ በገላው
ከቶ ምንድን ይሆን?
ምንድን ይሆን መላው?

(የማለዳ ድባብ፥ 28)
❤3
እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሳቹ አዲሱ ዓመት የሠላም፣የፍቅር፣የጤናና የስኬት ከነመላው ቤተሰብ ይሁንልህ!መልካም በዓል!!!
👌2
Amazing Pictures & poems ✍ pinned «#አሰሪ፦ ዓሳውን በደንብ አጥበህ ጥበሰው #ሰራተኛ፦ ህይወቱን ሙሉ ውሀ ውስጥ የኖረን እንስሳ ማጠብ ግፍ አይሆንም 😎»
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

በአሉ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የብልፅግና  የአንድነት ፣ የመተሳሰብ ፣ ይሁልንላቹ።

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ለሀገራችን ጤና እና ሰላም ፣ ለህዝቦቿ ፣ ፍቅርና አንድነት ፣ የተራቡ የሚጠግቡበት፣ የተቸገሩ የሚትረፈረፉበት ፣ ያዘኑ የሚፅናኑበት ፣ የታመሙ የሚድኑበት ፣ የተጨነቁ ከጭንቀታቸው የሚላቀቁበት የትንሳኤ በአል ይሁንላችሁ።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

መልካም የፋሲካ በአል ይሁንልን!
            
        
❤1