የታማኝነትን ጥግ ያሳየው ወጣት❗️
ከ80,000 ብር በላይ ወድቆ ያገኘው ወጣት ሞተረኛ ገንዘቡን ለአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህግ ክፍል በማስረከቡ ህግ ክፍሉ ለባለቤቱ በታማኝነት በአካል ገንዘቡን እንዲረከብ አድርጓል።
አፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ህዳር 21 ቀን 2018ዓ.ም
ነገሩ እንዲህ ነው...
ታደሰ መንግስቴ ይባላል ነዋሪነቱ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በአንኮበር ወረዳ ጎርጎ ዙሪያ ቀበሌ ነዋሪ ነው።
ቀኑ ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 20 /2018 ዓ.ም የገበያ ቀን በመሆኑ ልክ እንደወትሮው ሁሉ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ገበያ ያቀናል። ታዲያ ይህ ግለሰብ ለግብይት የሚውል መጠኑ 83,300 ብር የሆነ ገንዘብ ይዞ ጉዞውን ወደገበያ በሞተር ሳይክል አድርጓል። የዕለት ጉርሱን ለልጆቹ ሸማምቶ ለመግባት በከፍተኛ ጉጉት ወደ አሰበው ገበያ ደረሰ። ልክ ገበያ እንደደረሰ ያ ለብዙ ነገር የተጠበቀ ገንዘቡ ወድቆ ጠፍቷል፣የተጠቀለለበት ፊስታል ቢኖርም ገንዘቡ ግን የውሀ ሽታ ሆነ።
ታዲ ይህ ባለንብረት ምንም ጊዜ ሳያጠፋ ገንዘቡ እንደጠፋበት ለሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አንኮበር ቀጠና ለሚገኘው የጎርጎ ህግ ክፍል ያሳውቃል። ህግ ክፍሉም በቀጥታ ወደ ተግባር ገባ ገንዘብ ጠፍቷልና ያገኛችሁ ሰዎች ብትመልሱልን ወሮታውን እንከፍላለን የሚል ጥሪ ለማስተላለፍ የድምፅ ማጉያዎችን ተጠቅሞ መልክቱን ለማስተላለፍ ሽር ጉድ ማለት ጀመረ።
ነገር ግን መልዕክቱ ከመተላለፋ በፊት አንድ ሰው ወደ ህግ ክፍል እየተጣደፈ መጣ "የወደቀ ብር አግኝቻለሁ ባለቤቱ እስኪገኝ አንተጋ ታስቀምጠዋለህ የኔ ነው የሚል ከጠፋ ደግሞ ለአቅመ ደካሞች እንሰጣለን" በማለት በስልክ ተደውሎ ተነግሮኛል። ገንዘብ የጠፋው ካለ ገንዘቡ ተገኝቷል፣ በማለት ጥቆማ ሰጠ።
ማመን ከባድ ነበር እውነታውን ከባለቤቱ ለማረጋገጥ ብፍጥነት አግኝቻለሁ ወደሚለው ግለሰብ ተደወለ "ገንዘብ አግኝተሃል? አዎ ከሰላሳ ደቂቃ በኃላ እመጣለሁ መጠነኑን ተናግሮ መውሰድ ይቻላል" በማለት በልበ ሙሉነት አረጋገጠ። ያ ልባም ወጣት ተስፋዬ ይባል። የታማኝነት ጥግ የታየበት ተስፋዬ የሞተር አሽከርካሪ ነው። የተለመደውን ስራውን ሲያከናውን ነበር ይህን ገንዘብ ያገኘው።
የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለሚፈልጉ ይህ ትልቅ ገፀበረከትና እድል ነው ለተስፋዬ ግን ፤ምንም ማለት አይደለም የራስ ያልሆነ ገንዘብን መውሰድ ነውር ነው። ለተስፋዬ ገንዘብ የሚገኘው ላብን በማፍሰስ እንጂ የሰውን ሀቅ በመውሰድ አይደለም። ይህ ወጣት በአማራዊ ወግና ባህል ተኮትኩቶ ያደገ፤ መልካም ቤተሰብ ያሳደገው ምርጥ ዘመናዊ ወጣት በመሆኑ ይሕን መልካምና የተቀደሰ ድርጊት ፈፅሟል።
አማራ ባለፉት አስርት አመታቶች ውስጥ በመጤ ባህሎች ምክንያት ብዙ ነገሮቹን አጥቷል። ለአማራ ጠቃሚ የሆኑ ባህሎች፣ ወጎች፣ እሴቶችና ልምዶች አለም ወደ አንድ መንደር በመምጣቷ ምክንያት እየተሸረሸሩ መጥተዋል። እንዳንዶቹም በመንግስት ፓሊሲ ጭምር ክልከላ ተደርጎባቸዋል። የሰው ገንዘብ መውሰድ በአማራ ዘንድ ነውር ነው። በማህበረሰቡ ውስጥ ያስገልላል፣ ያዋርዳል፣ ያስፀይፋል፣ የተጠላና የተናቀ ያደርጋል። ገበያ ውስጥ ሌባ የተገኘ እንደሆነ "ሌባ ሌባ" እየተባለ ሁሉም ሰው ሌባውን ያሳድዳል፤ ከተያዘም በኃላ "እኔን ያየህ" ተቀጣ እያለ ገበያውን በማዞር ሁሉም ሰው እንዲውቀውና እንዲጠነቀቅ ይደረጋል።
የአማራ ፋኖ ትግል ከጀመረ ጀምሮ በርካታ የአማራ እሴቶች እየተመለሱ ነው። በህላዊ የእርቅ ስርዓት፣ የእደር ህጎች፣ እኔን ያየህ ተቀጣ የመሳሰሉ የአማራ እሴቶች እየተተገበሩ ነው። በዚህ ምክንያት ወንጀሎች በእጅጉ ቀንሰዋል።
ተስፋዬ ቃሉን ጠብቆ በሰዓቱ መጣ። ምንም ሳይሸራርፍ በህግ ክፍል በኩል ገንዘቡን ለባለንብረቱ ተመላሽ አድርጓል፣አማራነት ይህ ነው፣ ታማኝነት በወጣቶች አንደበት እጅግ ይበረታታል።
ተስፋዬ የታማኝነት ጥግ ነው። ለብዙ ወጣቶች አርዓያና ምሳሌ የሚሆን ወጣት ነው። የወጣት ተስፋዬን አይነት መልካም ሰዎች ያብዛልን።
በመሆኑም የበጎ ስራ ባለቤት ከሆነው ወጣት ተስፋዬ ባደረገው ዓዕርያነት የተሞላበት ተግባር ብዙውች ይማሩበት ዘንድ መረጃውን በምስል አስደግፎ ለአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ያደረሰንን የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የፖለቲካ ክፍል አመራር የሆነውን አርበኛ ኢንጅነር ሀብታሙ ብዙአየሁን በኮሩ ስም ከልብ እናመሰግናለን።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት‼️
ድል ለአማራ❗️ድል ለፋኖ ❗️
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል

https://www.youtube.com/@amharamediacentre
https://t.me/AmaraMediaCenter
https://www.facebook.com/share/v/1AhhVgkDWd/
http://tiktok.com/@amharamediacenter19.1
ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት መስጠት እንዲሁም መረጃ መላክ ለምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች ባለው ስልክ ቁጥር በዋት አፕ መላክ የምትችሉ መሆኑን ብትህትና እንገልጻለን!! +256759313671

በሰሜን አማራ ቀጠና በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት ያለቀበትና በርካታ መሳሪያ የተማራከበት ከባድ አውደውጊያ ተከሄደ ።
የአፋብሀ ስሜን አማራ ቀጠና ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዕዝ የራስ አሞራው ውብነህ ፫ኛ ኮር ስር የሚገኙ ክፍለጦሮች ለሳምንታት የዘለቀ ከባድ አውደ ውጊያ እያካሄዱ ይገኛሉ።
ሰፊውን የሰሜን ቀጠና ያከለለው አውደ ውጊያ ፣ ከጃናሞራ እስከ እንቃሽ፣ ከድብ ባህር እስከ አጅሬ ጃኖራ፣ከደጋ መረባ እስከ ወቅን ድረስ የዘለቀ ሲሆን ፣ ዳባት ወረዳ ላይ አረቡር፣አባ ዮሀንስ ፣አብጠራና ጭና የሚባሉ አካባቢዎች ላይ የአገዛዙ ሰራዊት ፣በተዘጋጀለት ቀለበት ሰተት ብሎ በመግባት በኢንጂነር አርበኛ ጻዲቀ ዋለልኝ በሚመራው በደጃች አያሌው ብሩ ተሰማ ክፍለጦር አናብስቶች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ በርካታ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማስተናገዱን ከቦታ የተገኙ መረጃዎች ያመልክታሉ።
የተሽኘው ተሽኝቶ የተማራከው ሲማራክ ቁስለኛውን ወደ ዳባት ጤና ጣቢያና ወደ ደበርቅ ሆስፒታል እያመላለሰ ይገኛል ተብሏል።
በዚሁ ዳባት ወረዳ ላይ ዳባት ገብብርኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የአገዛዙ ጓዝ ተሽካሚና አጓጓዥ የሆኑ አጋሰስ ሚሊሻዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውንም የመረጃዎች ምንጮች አክለዋል።
በተመሳሳይ በሌላኛው የዳባት ቀበሌ በሆነው አይደፈሬው እንቃሽ ቀበሌ በእነ አርበኛ ባየ ቀናው የሚመራው ሰራዊት ከላይ ደጋማው አካባቢ ተንደርድሮ ወደ ቆላማማው እንቅሽ ሰርጦች የገባው የአገዛዙ ጉግማንጉግ ሰራዊት በእንቅሾቹ አናብስቶች በእሳት ነበልባል በባሩዱ ቋያ ተለብልቦ ወደ መጣበት ተመልሶ የፈረጠጠ ሲሆን የአናብሶቹን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ሰራዊት በሩቁ ሆኖ በሞርተርና በዲሽቃ የንጹሀን ህጻናትንና ሴቶችን እንደለመደው ጨፍጭፎ ሂዷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በአጅሬ ጃኖራ የአገዛዙ ምስለኔ ሰራዊት በአካባቢው የገብሬ ቤት ለቤት እየገባ ሴቶችን የፋኖ ሚስት ናችሁ፣ የፋኖ ልጆ ናችሁ፣ የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ እያለ ማህበረሰብ ሲያስቸግር መሰንበቱ ተጠቅሶ ይሄንን የማህበረሰብ እንግልት ያየው ፋኖ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን መረጃዎች አክለው ገልጸዋል።
በሌላ መረጃዎች ደግሞ በአርማጭሆ መሽሀ ላይ ሞት የጠማው ተቅበዝባዙ የአገዛዙ ሰራዊት ፣ ተንደፋድፎ እንደ መግባት ተንደርድሮ መውጣት ከባድ የሆነበት ዙፋን አስቀጣዩ ሰራዊት ከባድ ጉዳትን አስተናግዶ እንደተመለሰ አካባቢው ላይ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።