Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
94.5K subscribers
8.39K photos
402 videos
18 files
19.4K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
የሱዳኑ አልቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ

ከሰሞኑ በካይሮ ጉብንት አድርገው የነበሩት የሱዳን የሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ አል ቡርሃን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አል ቡርሃን በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና በተለያዩ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
ፎቶ ፋይል
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የሕዳሴ ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት በዛሬው ቀን አል-ቡርሃን ኢትዮጵያ ገብተዋል
የሱዳን የሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አል-ቡርሃን በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፍራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉት ውይይት ይጠበቃል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሕዳሴው ግድብ ላይ ኢትዮጵያን ያስቆጣ አስተያየት ከሰጡ በኋላ አል-ቡርሃን ቀድመው ግብፅን ጎብኝተዋል፡፡ https://am.al-ain.com/article/lt-gen-abdel-fattah-al-burhan-arrives-in-ethiopia-for-2-day-visit
ኮሮና እንግሊዝን ዳግም እገዳ እንድትጥል አስገደደ

ሰዎች ለተፈቀደላቸው ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከቤታቸው እንዳይወጡ የ 4 ሳምንታት እገዳው ይከለክላል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ ያገረሸውን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሌሎች የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራትም እገዳዎችን እየጣሉ ነው፡፡
https://am.al-ain.com/article/england-to-start-new-four-week-lockdown
በቱርክ የ 70 ዓመት አዛውንት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከፍርስራሽ ውስጥ ወጡ

አርብ ዕለት የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በቱርክ ኢዝሚር ከተማ እየተካሔደ ባለው የነፍስ አድን ስራ የ 70 ዓመት አዛውንት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከፍርስራሽው ውስጥ መውጣታቸውን ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡
ቱርክን እና ግሪክን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን በትንሹ 60 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ900 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከሟቾቹ 58ቱ ቱርካውያን ናቸው፡፡ የነፍስ አድን ስራው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎችን ከህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማውጣት ተችሏል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 414 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 935 ሰዎች አገገሙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,901 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 414 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 935 ሰዎች ሲያገግሙ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 336 ሰዎች በጽኑ ታመዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ 96,583 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 53,452 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,478 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሦስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ በበይነ መረብ ተካሂዷል

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ በድርድሩ ቀጣይ አካሄድና የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሶስቱ ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሞያዎችን በመሰየም በድርድሩ አካሄድ እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሞያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሪፖርት እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የባለሙያዎች ስብሰባ ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን የደረሰበትን ጉዳይም በጥቅምት 24 ለሚካሄደው የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ድርድር ያቀርባል እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በምእራብ ወለጋ ዞን ኦነግ ሸኔ የሽብር ጥቃት መፈጸሙን ክልሉ አስታወቀ

ትናንት በምእራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በፈፀመው የሽብር ጥቃት ሰላማዊ ዜጎችን በጭካኔ ህይወታቸውን ማጥፋቱን የኦሮሚያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ገልጿል፡፡
የክልሉ መንግስት በኦነግ ሸኔ ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/the-oromiya-regional-state-announced-that-a-terrorist-attack-had-taken-place-in-the-west-welega-zone
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት መፈጸሙን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ

ፓርቲው ትላንት ምሽት በወረዳው በአማራው ላይ የቡድን ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
በዘለቄታዊ መፍትሄው ላይ እንደ አማራ ለመምከር በቅርቡ ሁሉን አሳታፊ የሆነ የሕዝብ መድረክ እንደሚዘጋጅም ገልጿል፡፡
https://am.al-ain.com/article/amhara-prosperity-party-says-racially-motivated-attack-took-place-in-guliso-woreda-west-welega-zone
የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ ራሳቸውን ለይተዋል

የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክክ እንዳላቸው ከተለዩ በኋላ ራሳቸውን መለየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ ምንምእንኳን የቫይረሱ ምልክት ባይታይባቸውም በዓለም ጤና ድርጅት ፕሮቶኮል መሰረት ራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩና ከቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic
ታንዛኒያ ምርጫን ተከትሎ የዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪን አሰረች

ተቃዋሚዎች ምርጫው መጠነ ሰፊ ማጭበርበር ታይቶበታል በማለት ምርጫው እንዲደገም፤ ፕሬዘዳንት ማጉፉሊ 84 በመቶ በማግኘት በድጋሚ ወደ ስልጣን ያመጣውን የምርጫ ውጤት ለመቃወም ጥሪ አቅርበዋል፡፡https://am.al-ain.com/article/tanzania-arrested-leader-of-main-opposition-leader
“የጸጥታ አካላት ጥቃቱ ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሠማርተው እርምጃ እየወሰዱ ነው”-ጠ/ሚ ዐቢይ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በምእራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡
“ሁኔታው እንደ መሪም እንደ ዜጋም ልብ ይሰብራል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
https://am.al-ain.com/article/pm-abiy-ahmed-says-security-forces-are-deployed-in-the-area-where-the-attack-took-place
አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ነገ የመጨረሻ ድምጽ ይሰጣሉ

ከዋናው የድምጽ መስጫ ቀን በፊት እስካሁን 94 ሚሊዮን ሰዎች ድምጻቸውን መስጠታቸው ተገልጿል
የሁለቱ ተቀናቃኞች የመጨረሻ ቅስቀሳ እና የእስካሁኑ ሂደት ምን ይመስላል?👇
https://am.al-ain.com/article/americans-will-go-to-the-polls-tomorrow-to-elect-their-next-president
አልጀሪያ አዲስ ህገመንግስት አጸቀች

የአልጀሪያ ህገመንግስት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች ከፈረንጆቹ 1962 ወዲህ ለ8ኛ ጊዜ ተሻሽሏል፡፡ኃላፊው እንደገለጹት እንዲጸድቅ በአዎንታ ድምጽ የሰጡት 3.3 ሚሊዮን ወይም 66.8 በመቶ ናቸው ብለዋል፡፡https://am.al-ain.com/article/algeria-approves-new-constitution-in-referendum
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 359 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 953 ሰዎች አገገሙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,726 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 359 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 953 ሰዎች ሲያገግሙ 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 353 ሰዎች በጽኑ ታመዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ 96,942 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 54,405 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,489 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው