Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
97.9K subscribers
8.91K photos
405 videos
18 files
21.3K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
ማይክሮሶፍት በታሪኩ ትልቅ ግዥ መፈጸሙ ተገነረ


ማይክሮሶፍት ለሁለት አመት የቆየ ፉክክር በማድረግ ነው "አክቲቬሽን ብሊዛርድ" የተባለውን ኩባንያ መግዛት የቻለው።
https://am.al-ain.com/article/microsoft-makes-largest-purchase-its-history
እስራኤል በደቡብ ጋዛ ተኩስ የማቆም ፍላጎት እንደሌላት ገለጸች

የግብጽ የደህንነት ሹማምንት እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ላይ የምታደርገውን የቦምብ ድብደባ ለማቆም መስማማቷን መግለጻቸውን ተከትሎ ነው እስራኤል ምንም አይነት ተኩስ አቁም አልተተገበረም ያለችው።

በግብጽ ቁጥጥር ስር ባለው የራፋህ ድንበር ማቋረጫ የውጭ ሀገር ፓስፖርት የያዙ ሰዎችን ለማስወጣት ይከፈታል መባሉንም የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት አስተባብሏል።

ሃማስም ተደረሰ ስለተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት ማረጋገጫ አልሰጠም።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/isrral-denies-ceasefire-deal-gaza
“ሁለተኛ ሀገራችን እየደማች ነው” - በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን

18 ሺህ የሚጠጉ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያን በእስራኤል የሚኖሩ ሲሆን፤ የሃማስን ጥቃት ተከትሎ በድጋሚ ከመኖሪያቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን ተናግረዋል።

በጦርነቱ ምክንያት ከደረሰው የንብረት ውድመት ባሻገር የተወሰኑ ኤርትራዉያን የገቡበት እንደማይታወቅም ነው በእስራኤል የሚኖሩ ኤርትራውያን በጋራ በሰጡት መግለጫ የገለጹት።

“እስራኤል ሀገራችን ናት፤ ሁለተኛ ሀገራችን እየደማች አንታገስም” ማለታቸውም ተዘግቧል።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/eritrean-asylum-seekers-israel
አሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከቧን ወደ እስራኤል ያስጠጋችው ለምንድን ነው?

የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስቴር ሁለት የጦር ጄት ተሸካሚ የሆነ ግዙፍ መርከብና ድጋፍ ሰጪ መርከቦችን ወደ ምስራቅ ሜዲትራኒያን ባህር ልኳል።

ፔንታጎን የጦር መርከቡን ወደ እስራኤል ማስጠጋቱ ግጭቱ ቀጠናዊ መልክ ይዞ እንዳይስፋፋ በማሰብ መሆኑን ሲገልጽ ይደመጣል።

የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስና የቀጠናው አጋሮቹ ግን የጦር መርከቡ ቴል አቪቭ በጋዛ የምትፈጽመውን ጥቃት ለማገዝ የተሰማሩ መሆናቸውን ያምናሉ።

አሜሪካ ከወቅታዊው የሃማስና እስራኤል ጦርነት አስቀድማም በቀጣናው በርካታ የጦር መርከቦች፣ አውሮፕላኖች እና ወታደሮች አሰማርታለች።

እነዚህ ግዙፍ መርከቦች ወደመካከለኛው ምስራቅ ምን ይዘው መጡ? ተከታዩን ሊንክ በመጫን ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦https://am.al-ain.com/article/what-us-war-ships-bring-middle-east
እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመው ጥቃት ካልቆመ ቀጣናዊ ውጥረቱ እንደሚባባስ ኢራን አስጠንቅቃለች

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያን "የጽዮናዊያን ጥቃቶች ካልቆሙ በቀጠናው ያሉ የሁሉም እጆች የጥይት ቃታው ላይ ናቸው" ብለዋል።

እስራኤልን በጋዛ ሰርጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ፈልጋለች በማለት የከሰሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ጥቃቱ በመካከለኛው ምስራቅ አዲስ የተቃውሞ ግንባር እንደሚከፍት አብራርተዋል።

ጋዛን ለሚያስተዳድረው ሃማስ ድጋፍ የምታደርገው ቴህራን በወቅታዊው የፍልስጤምና እስራኤል ጦርነት ምን አቋም ይዛለች? ሊንኩን ተጭነው ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/iran-warns-israel-hamas-war-may-escalete
ኤርትራ ስለባህር በር የሚደረጉ ንግግሮች ግራ አጋቢ እንደሆኑባት አስታወቀች

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀይ ባህርን ለመጠቀም ንግግር እንደሚያስፈልግ በተናገሩ ማግስት የኤርትራ መንግስት መግለጫ አውጥቷል።

መግለጫው በውሃ፣ በባህር በር እና ተያያዥ ጉዳዮች ንግግሮች መብዛታቸውንና ግራ የሚያጋቡ መሆናቸውን ከመግለጽ ውጭ በስም የጠቀሰው አካል ግን የለም።

የኤርትራ መንግስት በእንደዚህ አይነት መንገዶች እንደማይጠለፍ እና የሚመለከታቸው ሁሉ ጉዳዩን እንዳይነኩትም አሳስቧል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/eritrea-water-access-sea-discources-perplexing
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እስራኤልን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለጸ


አሜሪካ ከጥቃቱ በኋላ የመጀመሪያውን ተግባራዊ ምላሽ የሰጠችው የጦር ጀቶቾን መሸከም የሚችሉ ግዙፍ የጦር መርከቦችን ወደ እስራኤል በማስጠጋት ነበር።
https://am.al-ain.com/article/biden-visit-israel
ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተወያዩ

መሪዎቹ የኢትዮጵያ እና ቻይናን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል።

https://am.al-ain.com/article/ethiopian-pm-meets-xi
በእስራኤልና ሀማስ ጦርነት ጉዳይ ምን አዲስ ነገር አለ?


ግብጽና አሜሪካ ግጭቱ የአከባቢውን ጸጥታ አደጋ ላይ እንዳይጥል ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
https://am.al-ain.com/article/new-updates-hamas-israel-war
ፑቲን የሩሲያና ቻይና “ገደብ የለሽ” ትብብርን ለማጠናከር ቤጂንግ ገብተዋል

ፕሬዝዳንቱ በአለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዛዣ ከወጣባቸው በኋላ ሁለተኛውን የወጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በቻይና እያደረጉ ነው።

https://am.al-ain.com/article/putin-visits-dear-friend-xi
እስራኤል የሚጠበቀውን የምድር ጦር ዘመቻ ከመጀመሯ በፊት በሽህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ጋዛን ለቀው ለመውጣት ድንበር ላይ ተሰብስበዋል።

ከግብጽ ጋር የሚዋሰነው የራፋ ድንበር እንዲከፈትና ዜጎች ከጋዛ እንዲወጡ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ቀጥለዋል።

ነገር ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንበሩን ለመክፈት የተደረገው ድርድር ምንም አይነት ፍሬ አልተገኘበትም ብሏል።

ካይሮ በበኩሏ እስራኤልን ባለመተባበር ወቅሳለች።

ለሀማስ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት እስራኤል የአየር ድብደባዋን ስትቀጥል፤ ከጋዛ የሚወጡ መንገዶች በሙሉ ዝግ ናቸው።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ሰኞ እስራኤል ገብተዋል።

ብሊንከን በስድስት የቀጣናው የአረብ ሀገራት ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ነው ወደ እስራኤል የተመለሱት።
https://am.al-ain.com/article/new-updates-hamas-israel-war
አሜሪካ 2ሺ የባህር ኃይል ወታደሮቿን ወደ እስራኤል ላከች


የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ልሎይድ ኦስቲን ባለፈው ቅዳሜ ሁለተኛዋን የጦር መርከብ ወደ ምስራቅ ሚዲትራኒያን ባህር መላኳን አስታውቀው ነበር።
https://am.al-ain.com/article/usa-sends-2thousand-marines-israel
በ2024 ለገበያ የሚቀርቡ አይነግቡ ተሽከርካሪዎች

የጀርመኖቹ ቮልስዋገን እና መርሰዲስን ጨምሮ ታዋቂ ተሸከርካሪ አምራቾች በ2024 አዳዲስ ምርቶቻቸውን ያቀርባሉ።

https://am.al-ain.com/article/5-most-powerful-cars-2024
ከፍተኛ የአሜሪካ ጀነራል በእስራኤል ይፋዊ ያልሆነ ጉብኝት ማድረጉ ተገለጸ

አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ጀነራል በእስራኤል ይፋዊ ያልሆነ ጉብኝት ማድረጉ ተገልጿል።

ጉብኝት ያደረጉት ጀነራል የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ የሆኑት ጀነራል ሚካኤል ኩሪላ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

በመካከለኛው ምስራቅ ያሉትን የአሜሪካ ኃይሎች የሚቆጣጠሩት እኝህ ጀነራል ባለፈው ማክሰኞ እለት በእስራኤል በመገኘት በጸረ- ሀማስ ዘመቻ ዙሪያ መክረዋል።

የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ እስራኤል እየተመላለሱ ናቸው።

ፕሬዝደንት ጆ ባይደንም እስራኤል ራሷን ለመከላከል ምን እንደምትፈልግ ለመጠየቅ ወደ እስራኤል ያመራሉ ተብሏል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
አል ዐይን ኒውስ ከቻይና ሴንተራል ቴሌቪዥን (CCTV+) ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረመ

በስምምነቱ መሰረት ተቋማቱ ዘገባዎችን፣ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችንና የቀጥታ ስርጭቶችን ጨምሮ የተለያዩ ይዘቶች ይለዋወጣሉ። በሰራተኞች መካከል የልምድ ልውውጥ እና የጉብኝት መርሃ ግብርም የስምምነቱ አካል ናቸው።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/alain-news-cctv-cooperation-agreement
የአለማችን ፈጣኑ ራፐር ኤሚነም በስሙ ያስመዘገባቸው ክብረወሰኖች ምንድን ናቸው?

“የራፕ ሙዚቃ ንጉስ” ነው የሚባልለት አሜሪካዊው ሙዚቀኛ በሰከንድ 7 ነጥብ 5 ቃላትን በማውጣት በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ሰፍሯል።

https://am.al-ain.com/article/eminem-guinness-world-records
የዓለም የጤና ድርጅት ለሰብዓዊ አቅርቦት በአስቸኳይ የጋዛ መንገድ ይከፈትልኝ አለ



ቴላቪቭ ባለፈው ሳምንት በደቡባዊ የእስራኤል ከተሞች በደረሰ ጥቃት አንድ ሽህ 300 ሰዎችን የገደሉባትን የሀማስ ታጣቂዎች መደምሰስ ላለመ የምድር ጥቃት እየተዘጋጀች ነው።

https://am.al-ain.com/article/who-appeals-opening-corridor-enter-gaza
እስራኤል በሆስፒታል ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ በትንሹ 500 ሰዎች ሞቱ

እስራኤል ማምሻዉን በጋዛ ባፕቲስት ሆስፒታል ላይ ድብደባ ፈጽማለች። የዓለም ጤና ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት ቱርክ፣ ኢራንና ኳታርን ጨምሮ በርካቶች ጥቃቱን እያወገዙ ነው።
ምን አዳዲ ነገሮች ተከስተዋል? ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/about-500-killed-in-hospital-airstrike
እስረኤል በጋዛ ሆስፒታል ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ በተለያዩ የዓለም ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች እየተደረጉ ነው

እስራኤል በሆስፒታሉ ላይ በፈተጸመችው የአየር ድብደባ በትንሹ 500 መሞታቸው እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው የጋዛ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ይህንን ተከትሎም የፍልስጤሟ ዋና ከተማ ራማላህ ከፍተኛ የሆን ህዝባዊ ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ሰልፈኞች ፕሬዝዳንት መሃሙድ አባስ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። ተቃዋሚዎች ከጸጥታ አካላት ጋር ተጋዘጭተው የመሳሪያ ድምጾችም እየተሰሙ ነው።
በጆርዳን ዋና ከተማ አማን የሚገኘውን የእስራኤል ኤምባሲም ተቃዋሚዎች ሰብረው መግባታቸው ተስመቷል። በቱኒዝያዋ ዋና ከተማ ቱኒዝም በርካቶች ቁጣቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል።
ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል? ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/about-500-killed-in-hospital-airstrike