Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
97.8K subscribers
8.91K photos
405 videos
18 files
21.3K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
ማንቸስተር ሲቲ ድሉን ከደጋፊዎች ጋር ሲያከብር

ማንቸስተር ሲቲ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ ሶስት ዋንጫዎችን አንስቷል። የሶስትዮሽ ዋንጫን ያሳካው ቡድን በትናትናው እለት በክፍት አውቶብስ እየተንቀሳቀሰ ደስታውን ከደጋፊዎቿ ጋር አጋርቷል።
ቪዲዮውን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ https://am.al-ain.com/article/manchester-city-celebrate-victory-parade
የሱዳንን ግጭት ለመፍታት የኢትዮጵያን ጨምሮ የአራት ሀገር መሪዎች ከተፋላሚዎች ጋር ሊመክሩ ነው

መሪዎቹ በቀጣይ 10 ቀናት ከሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ጋር በአካል ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሏል። ኬንያ ሊቀ-መንበርነት የሚመራው ስብስብ በሱዳን ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተነግሯል ።
ተጨማሪ ዝርዝር ያንብቡ፤ https://am.al-ain.com/article/igad-ethiopia-kenya-sudan-war
ዝቅተኛ የነፍስ ወከፍ እለታዊ ገቢ ያላቸው ሀገራት

የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን ሀገራት ያሉበትን የኢኮኖሚ ደረጃ ለመለካት የሚያስችል አንዱ መስፈርት ነው።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦
https://am.al-ain.com/article/countries-lowest-percapita-income
ኒውዮርክ ከተማ የመስመጥ አደጋ እንዳንዣበበባት ተገለጸ

በኒውዮርክ በየዓመቱ የሚካሄዱ የግንባታ ስራዎች ለከተማዋ መስመጥ ምክንያት ይሆናሉ ተብሏል። የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆችው ኒውዮርክ የመስመጥ አደጋ እንዳንዣበበባት የከርሰ ምድር ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር ያንብቡ፤ https://am.al-ain.com/article/sinking-city-new-york-america
አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር የክብረ ወሰን ባለቤት መሆኑን ተረጋገጠ

የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር የገባበት 7፡23.81 የዓለም ሪከርድ መሆኑን ማረጋገጫ ሰጥቷል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ ውድድሩነ በፈረንጆቹ የካቲት 15 2023 በመወዳደር ያሸነፈ ሲሆን፤ የዓለም አትሌቲክስ የዶፒንግ ሌሎች ምርመራዎችን ካጣራ በኋላ በዛሬው እለት ሰዓቱ የዓለም ሪከርድ መሆኑን አረጋግጦለታል።

በዚህም ለሜቻ ግርማ ለ25 ዓመታት በኬንያዊው ዳንኤል ኮመን እጅ የቆየውን የ3000 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር 7፡23.81 በመግባት የግሉ አድርጎታል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ ባሳለፍነው አርብ ፈረንሳይ ፓሪስ ዳይመንድ ሊግ 19 ዓመታት ሳይደፈር የቆየውን የ3000 ሜትር መሰናክል የዓለም ሪከርድን መስበሩ የሚታወስ ነው፡፡

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ልዩ ትኩረት የሰጡት ውዱ ሃብት - ሊቲየም

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ ተፈላጊነት እየጨመረ በመሄዱ ሀገራቱ የሊቲየም ባትሪ መስሪያ ፋብሪካዎችን እየገነቡ ነው። ቺሊ፣ ብራዚል፣ አርጀንቲና እና ቦሊቪያ ከፍተኛ የሊቲየም ሃብት አላቸው።
ተጨማሪ ዝርዝር ያንብቡ፤ https://am.al-ain.com/article/south-america-lithium-nationalization
የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማን ያነሳልʔ

በዝናብና በስታዲየም ችግር የተፈተነው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ መገባደዱ እየተቃረበ ነው። የደረጃ ሰንጠረዡን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲመራው ባህርዳር ከተማ 2ኛ ላይ ይገኛል።
የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ማን ያነሳልʔ በተከታዩ ሊንክ በመግባት ግምትዎን ያስቀምጡ፤ https://am.al-ain.com/article/who-will-win-ethiopia-pl
"እየሱስን ለማግኘት" በሚል ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 80 ኡጋንዳዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አማኞቹ ኢየሱስን ለመገናኘት ለ40 ቀናት እንዲጾሙም መደረጉ ተነግሯል። የኡጋንዳው ፓስተር ኦፖሎት ድርጊት አማኞችን እስከ ሞት እንዲጾሙ ካዘዙት ኬንያው ፓስተር ፖል ማኬንዚ ጋር ተመሳሳይነት አለው ተብሏል
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ያንብቡ፤ https://am.al-ain.com/article/ugandans-jesus-repatriation-ethiopian
ኢ-ሲጋሬት በከፍተኛ መጠን ጥቅም ላይ የሚውልባቸው ሀገራት

ኢ-ሲጋሬት በኤሌክትሮኒክስ ቴክኒክ ቶባኮ ለማጨሻ ጥቅም ላይ የሚውል መሳሪያ ነው።
https://am.al-ain.com/article/countries-where-e-cigarette-used-most
ሜሲ በቤጂንግ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በፖሊሶች ለምን ተያዘʔ

አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በቤጂንግ ለሁለት ሰዓት ያክል መጉላላቱ ተነግሯል። ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ከአውስትራሊያ ጋር ባላት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ለመሳተፍ በመጓዝ ላይ እያለ ነው በቻይና ፖሊሶች የተያዘው።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ https://am.al-ain.com/article/messi-stopped-chinese-border-control
ኤርትራ ከ16 አመት በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባልነቷ ተመለሰች

በትናንትናው እለት በጂቡቲ በተካሄደ ስብሰባም ኤርትራ የኢጋድ መቀመጫዋን ዳግም መረከቧን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ባለፉት 16 አመታት ከምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ተነጥላ የቆየችው ሀገር ለቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋትና ትብብር በቁርጠኝነት እንደምትሰራም ነው ያስታወቁት።

ተጨማሪ ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ https://am.al-ain.com/article/eritrea-rejoins-igad-after-16-years
ሩሲያ የዩክሬን ፕሬዝዳንት የትውልድ ከተማን በሚሳይል መታች
በጥቃቱ የ10 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በትውልድ ከተማቸው የደረሰውን ጥቃቱን አውግዘዋል።
ተጨማሪ ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ https://am.al-ain.com/article/russia-attack-ukraine-president-hometown
ዓለም በታሪክ ውስጥ እጅግ ውስብስብ የሆነ የፕላስቲክ ቀውስ ገጥሟታል ተባለ

ከደቂቃዎች እስከ ሰዓታት የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ምርቶች በአካባቢ ለብዙ መቶ ዓመታት ይቆያሉ። የፕላስቲክ ብክለት የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት እምብዛም ውጤታማ ባልሆነባቸው በእስያ እና አፍሪካ ሀገሮች ጎልቶ እንደሚታይ ተነግሯል።

ተጨማሪ ይመልከቱ https://am.al-ain.com/article/getting-rid-of-plastic
የኢትዮጵያን ጨምሮ የአራት ሀገር መሪዎች በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ ከሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ጋር ሊመክሩ ነው

የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ለመፍታት የአራት ሀገር መሪዎች ከካርቱም ተቀናቃኞች ጋር እንደሚወያዩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) አስታውቋል።

ኢጋድ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ደቡብ ሱዳንን መሪዎች ያካተተ የአራትዮሽ ስብስብ ከጀነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃንና ከጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ጋር ይወያያሉ ብሏል።

ተጨማሪ ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ https://am.al-ain.com/article/igad-ethiopia-kenya-sudan-war
በኢኳዶር “ሞተዋል” ተብለው ሊቀበሩ የነበሩት የ76 አመት አዛውንት በአስከሬን ሳጥን ውስጥ በሃይል እየተነፈሱ ተገኝተዋል

በኢኳዶር የ76 አመቷ ቤሊያ ሞንቶያ ህይወታቸው አልፎ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቧል።ልጃቸው ጊልበር ሮዶልፎም “ሟች” እናቱን ማጣቱ አንገብግቦት በሀዘን ስብር ብሎ ተቀምጧል።

ሞንቶያ “ህልፈታቸው” በሀኪሞች ተረጋግጦ ቤተሰቡ ከተረዳ ከአምስት ስአት በኋላ ግን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ። አዛውንቷ የተቀበሩበት የአስከሬን ሳጥን አካባቢ ድምጽ መስማት ጀመረ።

ተጨማሪ ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ https://am.al-ain.com/article/dead-woman-found-breathing-coffin
ሜሲ በቤጂንግ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በፖሊሶች ለምን ተያዘʔ

አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በቤጂንግ ለሁለት ሰዓት ያክል መጉላላቱ ተነግሯል።

ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ከአውስትራሊያ ጋር ባላት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ለመሳተፍ በመጓዝ ላይ እያለ ነው በቻይና ፖሊሶች የተያዘው።

ሜሲ በቻይና ፖሊሶች ተይዞ በአውሮፕላን ማረፊ ውስጥ የተጉላላው ከፓስፖርት ጋር በተያያዘ እንደሆነም ተነግሯል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ https://am.al-ain.com/article/messi-stopped-chinese-border-control
ኒውዮርክ ከተማ የመስመጥ አደጋ እንዳንዣበበባት ተገለጸ

በዘመናዊ ከተማ ታሪክ የብዙ የዓለማችን ምሳሌ የሆነችው ኒዮርክ ከተማ የመስመጥ አደጋ እንዳንዣበበባት የከርሰ ምድር ጥናት ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ከሆነ በኒዮርክ ከተማ በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 7 ትሪሊዮን ቶን በላይ ጠጣር የግንባታ ግብዓቶች፣ ብረቶች እና መስታዋት ግንባታ ይካሄዳል።

ይህ ከፍተኛ ክብደት መጠን ያላቸው ምርቶች አጠቃላይ መሬቱ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።

ተጨማሪ ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ https://am.al-ain.com/article/sinking-city-new-york-america
የዓለም አቀፍ ስደተኞች ቁጥር 110 ሚሊዮን መድረሱን ተመድ ገለጸ

የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ እንደገለጸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በግዳጅ የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 110 ሚሊዮን ደርሷል።

በሱዳን እና በዩክሬን የተቀሰቀሰው ጦርነት የስደተኞችን ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ተመድ ገልጿል።

ተመድ አሁን ያለው አለም ሁሉም ውጥረቶች በሂደት የሰብአዊ ቀውስ የሚያስከትሉበት ጊዜ ነው ብሏል።

የሶሪያ ቀውስ ከመቀስቀሱ ሁለት አስርት አመታት በፊት የዓለም የስደተኞች ቁጥር 40 ሚሊዮን ገደማ ነበር ብሏል ተመድ።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic