Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
92.7K subscribers
8.31K photos
401 videos
18 files
19K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
አብን የጠራው ሰልፍ በአማራ ክልል ዕውቅና ተነፈገው

“ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና አልተሰጠም”-የአማራ ክልል
“ሰልፉ በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል”-አብን
አብን ሰልፉን በተመለከተ በነገው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ እሰጣለሁ ብሏል፡፡
https://am.al-ain.com/article/the-amhara-regional-gov-t-says-the-peaceful-demonstration-called-by-nama-is-not-recognized
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ኩባንያዎችን የመገምገም ሂደት ተጠናቆ ሲያልቅ ኩባንያዎቹ በቀጥታ ወደ ገበያ እንደሚገቡ ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሩ ሁለቱ ብቃት ያላቸው ተጫራቾች በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋሉ ብለዋል ፡፡https://am.al-ain.com/article/two-telecom-companies-is-set-venture-ethiopian-market-in-march-april
አሜሪካ የኢራንን የነዳጅ ዘርፍ ኢላማ ያደረገ አዲስ ማእቀብ ጣለች

አሜሪካ በኢራን ላይ ጫና ለማሳደር በማሰብ የኢራንን የፔትሮሊም ሚኒስቴንር ጨምሮ ከነዳጅ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ዘርፎች ላይ አዲስ ማእቀብ መጣሏል አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው ማእቀብ የተጣለው በኢራን የነዳጅ ዘርፍ ቁልፍ ሚና ባላቸው ሲሆን አሜሪካ ማእቀቡን ለመጣል እንደ ምክንያት ያቀረበችው ቁድስ የሚባሉትን ኃይሎች መርዳታቸው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትር ምኑችን ኢራን የፔትሮሊም ዘርፉን ለሽብር እንቅስቃሴ ይጠቀሙበታል ብለዋል፡፡ ማእቀቡ በኢራን የነዳጅ የውጭ ንግድ ላይ ተጽእኖ ማሰደሩ ተገለጿል፤ አሜሪካም ከኢራን ነዳጅን የሚገዙ ሀገራት ገቢው መካከለኛው ምስራቅ ሽብር ለሚፈጥረው ጦር ማገዝ መሆኑን ማወቅ አለባቸው ብለዋል፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጠራ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የተከሰሱት ግለሰቦች ተፈረደባቸው

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጠራ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት ያጠፉ ግለሰቦች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት ያጠፉ አምስት ግለሰቦች በተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ከ5 ዓመት እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጥተዋል።
በሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ በኔዘርላንድስ ፖሊስ ተያዘ

የኔዘርላንድስ ፖሊስ እ.ኤ.አ በ 1994 በሩዋንዳ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳትፏል በሚል የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
የቀድሞው የባንክ ጸሐፊና በመዲናዋ ኪጋሊ የፋርማሲ ባለቤት የነበረው የ 71 ዓመቱ አዛውንት ፣ የሚገደሉ ቱትሲዎችን ስም ዝርዝር በማዘጋጀት ተከሷል፡፡
በተጨማሪም ግለሰቡ በቱትሲዎች ላይ በተፈጸሙ ሌሎች ጥቃቶች ላይም ተሳትፏል ተብሏል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ሩዋንዳ ተላልፎ እንዲሰጣት ጠይቃ የነበረው ግለሰቡ እ.ኤ.አ. በ 2000 በኔዘርላንድስ ጥገኝነት ጠይቋል፡፡
ለ 100 ቀናት በቆየው የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ወቅት 800,000 ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር አልቡርሃን ወደ ካይሮ አቀኑ

አልቡርሃን ወደ ካይሮ ያቀኑበት ምክንያት ምን እንደሆነ አልተገለጸም፡፡ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን የሚያደርጉት የሶስትዮሽ የግድቡ ድርድር ዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡https://am.al-ain.com/article/sudan-s-al-burhan-left-for-cairo-egypt
አብን መግለጫ እንዳይሰጥ መከልከሉን ገለጸ

ኢዴፓ በአማራ ክልል የተጠራውን ሰልፍ የክልሉ መንግስት መከልከሉን አውግዟል፡፡
የክልሉ መንግስት አብንለነገ ለጠራው ሰልፍ እውቅና አልሰጠሁም ማለቱ ይታወቃል፡፡
https://am.al-ain.com/article/national-movement-of-amhara-announces-that-police-denied-it-to-give-statement
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በወረባቦ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ሰብላቸውን ላወደመባቸው አርሶአደሮች ድጋፍ ማቅረብ ተጀመረ

በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ የበረሃ አንበጣ ሰብላቸውን ላወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አስቸኳይ የዕለት ቀለብ ድጋፍ ማቅረብ መጀመሩን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡
የፌዴራል መንግስት ያቀረበው ስንዴና የምግብ ዘይት በቀጥታ ለተጎጂዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ገልጿል፡፡
በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ በወረባቦ ወረዳ በ13 ቀበሌዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
በወረዳው 9ሺህ 682 ሄክታር ሰብል ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ በተጨማሪም 2ሺህ 267 ሄክታር የግጦሽ መሬትና 22 ሺህ 289 ሄክታር ደን እና ቁጥቋጦ ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡
በዚህም ከ10 ሺህ በላይ የቤተሰብ ሀላፊዎች ተጎጂ ሲሆኑ በአጠቃላይ ከ61 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ለችግር ተጋልጠዋል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የፊፋ ፕረዝዳንት በኮሮና ተያዙ

የዓለምአቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ ፕረዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተዘገበ።
የፕሬዝዳንቱን በቫይረሱ መያዝ ያረጋገጠው የዓለምአቀፉ እግርኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ፕሬኢንቱ ኢንፋንቲኖ የቫይረሱ ቀላል ምልክቶች እንደታዩባቸው እና ራሳቸውን ማግለላቸውንም ገልጿል።
ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በድርድሩ አካሄድና ጊዜ ሰሌዳ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ተግባቡ

ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉት ድርድር ዛሬ የጀመረ ሲሆን ሀገራቱ በድርድራቸው፣በድርድሩ አካሄድና በጊዜ ሰሌዳ ላይ ሰምምነት ላይ ለመድረስ መግባባታቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይና ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።
ሀገራቱ ልዩነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር የውጭ ጉዳይና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው እንደሚገናኙ መግለጫው ጠቅሷል።

የመጀመሪያው ስብሰባ በሱዳን ሰብሳቢነት ይካሄዳል ተብሏል።
በኢትዮጵያ አለመሰማማት ምክንያት የአሜሪካው ድርድር ከተቋረጠ በኋላ ድርድሩ በሶስቱም ሀገራት ሰምምነት በአፍሪካ ህብረት መእቀፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በአፋር ተገደሉ

የትምህርት ሚኒስቴር ሁለት ባልደረቦቹ በአፋር ክልል ለሥራ በሄዱበት ወቅት ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀ፡፡ አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ለይቶ ማቆያ ገቡ

ከፕሬዝዳንቱ ጋር የነበረ ግለሰብ በኮሮና መያዙ በመረጋገጡ ነው ፕሬዝዳንቱ ራሳቸውን የለዩት፡፡
ሲሪል ራማፎዛ የሕዳሴ ገድብ ድርድርን በመምራት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
https://am.al-ain.com/article/south-african-president-isolates-himself-after-an-individual-with-him-tests-positive-for-covid-19
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሞሮኮ ደቡባዊ ግዛት ቆንስላ በመክፈት የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ሆነች