AGEW TV
Photo
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር የቀድሞ ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በ13 ዓመት እስራት ተቀጡ
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር የቀድሞ ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ በኮሚሽኑ የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን የተለያዩ የእርዳታ ዓይነቶችን ከመጋዘን ወጪ በማድረግ ለተረጂዎች ሳይደርስ ተሽጦ ለግል ጥቅም መዋሉን አስረድቷል፡፡
በዚህም የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 3 የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እንዲሁም 33 እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ምንጩን ደብቆ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም ተመስርቶባቸው ነበር፡፡
አቶ ምትኩ ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን ዳይሬክተር የማነ ወ/ማሪያምና ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ያልተገባ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር በሺዎች በሚቆጠሩ ተረጂዎች ስም እንዲሁም የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ለበርካታ ጊዜ የምግብ ቁሳቁሶች ከኮሚሽኑ መጋዘን በማውጣት ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች ግለሰቦች በመሸጥ ሕገወጥ ጥቅም ሲያገኙ እንደነበር በክሱ ተመላክቷል፡፡
በዚህም በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ክልል (የቀድሞ) ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የግብረሰናይ ድርጅቱ ማዕከላት ለተረጂዎች ሳያደርስ በመሸጥ ለግል ጥቅም ማዋል፣ ብድርና ድጋፍ በሚል ሰበብ በሕገ ወጥ መንገድ ከኮሚሽኑ በ100 ሚሊየን የሚገመት ለእርዳታ ድርጅቱ በገንዘብ መልክ መሰጠቱ ዐቃቤ ሕግ አስረድቷል፡፡
ለዚህም በአቶ ምትኩ ካሳ ቤተሰቦች ስም ከኤልሻዳይ ድርጅት በተለያዩ ጊዜ ክፍያ መፈጸሙንም ነው በክሱ የተመላከተው፡፡
በተለይም ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ፣ ከ41 ሺህ ኩንታል በላይ በቆሎ፣ ከ78 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት፣ 3 ሺህ 999 ኩንታል ሩዝ ከተራድኦ ድርጅቱና ከኮሚሽኑ ጋር በመመሳጠር እርዳታውን አዳማ ለሚገኝ የዱቄት ፋብሪካ መሸጡ ተጠቅሷል።
በ2ኛ ክስ ደግሞ ከ472 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ በድጋፍ መልክ በ1ኛ ተከሳሽ አቶ ምትኩ ካሳ ፈቃጅነት በ2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ክፍያ እንደተፈጸመና በ3ኛ ተከሳሽ ወጪ አድራጊነት ለግል ጥቅም በመዋሉ በመንግስት ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰ መሆኑ ተገልጿል።
በአቶ ምትኩ ልጆችና ባለቤታቸው ስም ተገዝተው የተገኙ ተሽከርካሪዎችና መኖሪያ ቤቶች መኖራቸው በክሱ የተጠቀሰ ሲሆን ፥ በሕገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ በሌሎችም ተከሳሾች ላይ በየደረጃው የወንጀል ተሳትፏቸው በክሱ ተዘርዝሮ ተካትቷል።
ተከሳሾቹ አቶ ምትኩ ካሳ፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል፣ ልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ የወንጀል ድርጊት መፈፀማቸውን ተከትሎ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፏል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት የዐቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃና የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ ካደመጠ በኋላ አቶ ምትኩ ካሳ በ13 አዓት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል፡፡
በተጨማሪም በአቶ ምትኩ ካሳ ባለቤት ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ላይ የ8 ዓመት ከ4 ወር እስራትና 3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲሁም ልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ 5 ዓመት እስራትና 3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል። በሲፈን መኮንን
.
@AGEWTV

❤1
AGEW TV
Photo
አገው ምድር እንጅባራ
#agewtv እንጅባራ ከተማ ከአዲስ አበባ 445 ኪ.ሜ፣ ከባሕር ዳር 113 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝ የአገው አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና ከተማ ናት፡፡ ዓይንን በሚያጠግብ ልምላሜ ተከባ የምትገኘው እንጅባራ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንዲሁም በምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ የመስህብ ሀብቶችን ለመጎብኘት አማካኝ ቦታ ላይ ምትገኝ ድንቅ ከተማ ናት፡፡
በአገው አዊ ዞን በባንጃ ወረዳ፣ በከሳ ቸውሳ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ዝምተኛው ዋሻ በሚል መጠሪያ ስሙ የሚገኝ ዘንገና ሀይቅም ይገኛል፡፡ ከአስፋልቱ ወደ ሐይቁ በመኪና ወይም በእግር ዘና እያሉ በግራና በቀኝ በሚያምር የጥድ ዛፍ ታጅበው ትንሽ እነደተጓዙበውብና ማራኪ እጽዋት የተከበበውን ሰው በራሱ እጅ እንደሰራው ተፈጥሮ ያዘጋጀውን አስገራሚ ሐይቅ ከምድር እንደ መስታወት የሚያንጸባርቅ ፀጥ ረጭ ያለ በጎድጓዳ ስፍራ ላይ ያረፈ ሀይቅ ሲመለከቱ ተዓምር ይላሉ፡፡
የሀይቁ አማካይ ጥልቀት ከ150-169 ሜትር ጥልቀት አለው፡፡ ርዝመቱ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ 930 ሜትር፣ ከሰሜን ወደ ደቡብ 970 ሜትር ሲሆን፣ 0.54ኪ.ሜ² ስፋት አለው፡፡ ውሃው በበጋ በክረምት 1.30ሜትር የህል ልዩነት ያሳያል፡፡ሐይቁን ከላይ ሁነን ስንመለከተው አረንጓዴ ሰማያዊ ቀለም አለው፡፡ ይህም እንዲሆን ያደረገው በዙሪያው ያሉት አረንጓዴ ዕጽዋት ነፀብራቅ ነው፡፡በሐይቁ ዙሪያ የተለያዩ እፅዋት፣የዱር እንስሳትና አዕዋፍ ይገኛሉ፡፡
በአገው አዊ ውስጥ ከሚገኙ ተፈጥሯዊ መስህቦች መካከል ዱራ፣ አዮ፣ አምን፣ ፈጣም፣ ግዛኒ አርዲኖ የመሳሰሉ ወንዞችን፤ ትስኪ፣ ፋንግ፣ ጋርቾ፣ ዶንዶር፣ ኳሽኒ፣ ልብሲ ቢምብላ የመሳሰሉ ፏፏቴዎችን፤ ዘንገና እና ጥርባ ሀይቆችን፣ የባኩሳ ብሔራዊ ፓርክን፣ የተለያየ ከፍታና ቅርጽ ያላቸው እንደ ዝርሂ እና አሰም ተራራዎችን እና ዋሻዎችን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡
የአገው የፈረሰኞች ማህበር በዓል፣ የአዊት ድጋግ/የአዊ ጃንጥላ፣ ባህላዊ የቅርቀሃ ውጤቶች፣ ጭራ፣ የአገው ግምጃ ቤት ማርያም ፣ ጉም እየሱስ ገዳም ፣ ወለተ ጴጥሮስ ገዳም፣ አኘኒ ሚካኤል፣ ዙርዙር ኪዳነ ምህረት፣ ከሳ ደብረ ጽዮን ማርያምን ደግሞ በባህላዊና ታሪካዊ መስህብነት በአገው ምድር የምናገኛቸው ፀጋዎች ናቸው፡፡

💯4❤1
AGEW TV
Photo
የትግል ጥሪ ለአገው ፖለቲከኞች፣ ለማህበረሰብ አንቂዎችና ለአፍሌን በሙሉ ፤ በእጃችን ያለንን ሙሉ አቅማችንን በመጠቅም ትኩረታችንን አዊ ዞን ላይ እንድንናደረግ እጠይቃለሁ:-
አዲሱ መኮንን(PHD)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የተለያዩ የዓለም ሀገራት የታሪክ ድርሰናት እና መዛግብት እንደሚያስረዱን የነፃነት ዋጋን ውድነት ቢሆንም ለነፃነት የሚደረገው ትግል በጨቋኝ እና በጨፍላቂ አካላት የተነፈጉ ማህበረሰቦች (ሀገሮች) ነፃነታቸውን ለመጎናፀፍ በሌሎች መስዋትነት ሳይሆን በራሳቸው ቁርጠኛ እና ተናባቢ ትግል መሆኑን ያስረዳል።
እኛ አገዎችም የዓላም ነፃነት ታጋዮች አካል እንደመሆናችን ከጨቋኝና ከጨፍላቂ እንዲሁም ከፀረ-አገው አካላት በቅርብ ጊዜያት ነፃነታችንን ለመጎናፀፍ የተለያዩ ነፃነትን ከተጎናፀፉ ሀገራትና ማህበረሰቦች ትምህርትና ልምድ በመቀሰም እና ወደ ራሳችን በመቀየር ሙሉ ትኩረታችንንና አቅማችንን የአገው ህዝብን እያፈነ፣ እያሰረ፣ እያሳደደ፣ እያፈናቀለ፣ እያስገደለ እና እየገደለ ያለው የአዊ ዞን ተላላኪ አመራር ላይ በማሳረፍ ዕውቀታችንንና ጥበባችንን ተጠቅመን ዘመኑን የሚመጥን አገዋዊ ስትራቴጂ ነድፈን ትግላችንን በትንሽ መስዋትነት ከፀሀይ ብርሃን በላይ በማፍጠን በቅርብ ጊዜያት "የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን" ዕውን ልናደርግ ይገባናል።
የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን ዕውን ለማድረግ እኛ በሀገር ውስጥ ምንኖር እና በተለያዩ ውጭ ሀገራት የምትኖሩ የህዝባችን በደልና እልቂት የሚያንገባግባችሁ የአገው ተወላጅ ዲያስፖራዎች ወቅቱ የሚፈልገውን ትግል ልናካሄድ ይኖርብናል።
አሁን ላይ ወቅቱ የሚፈልገው አገዋዊ ትግል ለማድረግ መሰባሰብ፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ መግባባት እና መቻቻል የሚኖርብን ሲሆን እነዚህን መርሆች በመከተል አታጋይ የትግል ስልቶችን ማርቀቅ፣ ተራመጅ ሃሳቦችን ማፍለቅ፣ አገዋዊ የነፃነት ትግሉ የሁላችንንም የአገው ተወላጆች ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል።
ይህ የተጀመረው የነፃነት ትግላችን ዕውን እንዲሆን የአገው ፖለቲከኞች፣ ማህበረሰብ አንቂዎችና አፍሌን የሚቀሩን የቤት ስራዎች ስላሉብን በአፋጣኝ ቀሪ የቤት ስራዎቻችንን መስራት ይኖርብናል። እነዚህም፦
1. እኛ የተሻለ ግንዛቤ ያለን አካላት ማህበረሰባችን በአገዋዊ ማንነት እንዳይደራደር ልዩ ትኩረት በመስጠትና በቀላሉ በሚረዱት መንገድ ደጋግመን በአዊ ዞን ተልዕኮ ተቀባይ አመራር በህዝባችን ላይ እያንጃበበ ያለውን አገውን አማራ የማድረግ ዕሳቤ በምናገኝበት ቤተ ክርስቲያን፣ ትምህርት ቤቶች፣ በሌሎች ስራ ቦታዎች፣ በዕድር፣ በዕቁብ እና በሌሎች ህዝባችን በሚሰባሰብባቸው ተቋማትና ቦታዎች በድፍረት ለህዝባችን ግንዛቤ በመፍጠር እምቢ ለነፃነቴ እንዲል ማድረግ፣
2. ከእኛ የሚጠቀው ሌላኛው አንኳር ተግባር ለማህበሰሰባችን ግንዛቤ ስንፈጥር መጠቀም ያለብን ቋንቋ እንደየ አካባቢዎች ፣ ቀበሌዎችና ወረዳዎች ማህበረሰባችን ለመግባቢያነት የሚጠቀምበትን ሲሆን ይህንን ማድረግ የተፈለገው ዋናው ዓላማ ህዝባችን በቀላሉ ሃሳብን በራሱ ቋንቋ መረዳትና መግለፅ እንዲችል ስለተፈለገ ነው፣
3. ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለን የአገው ልጆች እርስ በእርሳችን እየተናበብንና የእየተደጋገፍን ትኩረታችንን የነፃነት ትግላችን ላይ ብቻ ማድረግ፤ አገዋዊ ስነ-ልቦና የሌለው የአዊ ዞን አመራርን በተናበበ እና በበሰለ የትግል ስልጥ ከስልጣን እንዲወገድ በማድረግ አገዋዊ ስነ-ልቦና ያላቸው እውነተኛ የአገው ተወላጆች ወደ ስልጣን እንዲመጡና የጀመረነው የነፃነት ትግላችን በተባበረ ትግል ዕውን እንዲሆን ዕድል መፍጠር፣
4. ከጨቋኞችና ከጨፍላቂዎች እንዲሁም አገዋዊ ስነ-ልቦና ከሌላቸው የአዊ ዞን ተልዕኮ ተቀባዮች ህዝባችን ተላቆ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ሲችል ማህበረሰባችን በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚሆንበት ዕድሉ ሰፊ መሆኑን ለህዝባችን ማሳያዎችን በምሳሌ እያጣቀስን ደጋግመን በማስተማር በማስረዳት ህዝባችን ለአገዋዊ መብቱ መከበርና ጥቅሙ መጠበቅ እንዲታገል አስቻይ የትግል ሆኔታዎችን መፍጠር።
5. ከእኛ የተሻለ የትግል ልምድ፣ ዕውቀት፣ ክህሎትና ግንዛቤ ካለን የአገው ተወላጆች የሚጠበቀው ተለዋዋጭና አዳዲስ የትግል ስልቶችንና ታክቲኮችን በመጠቀም አደረጃጀታችንን ከሃሳባዊነት እና ከማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚነት በተጨማሪ መሬት ላይ በማውረድ በህዝባችን ዘንድ በቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን መንግስታዊ አደረጃጀቶች (መምህራንን፣ የጤና ባለሙያዎችን፣ የግብርና ባለሙያዎች ወዘተ...) እና መንግስታዊ ያልሆኑ እንደ ዕድር፣ ዕቁብ የመሳሰሉ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የጀመርነውን የነፃነት ጉዞ አጠናክረን ነፃነታችንን በቅርብ ጊዜ ለመጎናፀፍ በፅናትና በቁርጠኝነት አገዋዊ ትግሉን ማስኬድ።
6. ማህበረሰባችን የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን ጥቅም ልይቶ በደንብ እንዲያውቅ ከህፃናት እስከ አዛውንት፤ ከኃይማኖት አባቶች እስከ ሀገር ሽማግሌዎች፤ በተለይ የነፃነት ኃይልና ሞተር እንዲሁም የለውጥ አምባሳደር ለሆኑ ወጣቶች (አፍሌን) የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ በዕውቀት ላይ የተመሠረት ትንተና በማድረግ የነፃነቱን ጠቀሜታ ደጋግሞ ማሳወቅ እና ከጫፍ እስከ ጫፍ አንድ ላይ እንዲቆሙ ማድረግ።
7. ሁሉም የአገው ማህበረሰብ ከሊቅ እስከ ደቂቃ የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉዳይ የአገው ህዝብ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት (የህልውና ጉዳይ) መሆኑን አውቆ በየፑል ቤቶች፣ በየሻይ ቤቶች፣ በየእርሻ ቦታዎች፣ በየመዝናኛ ቦታዎች፣ በየማህበራዊ ኩነቶች፣ በየቢሮዎች፣ በየንግድ ቦታዎች፣ በየትምህርት ቤቶች፣ በየጤና ኪላዎች እስከ ሆስፒታሎች እና ህዝባችን የዕለት ተለት ተግባራትን በሚያከናውንባቸው ቦታዎች ሁሉ ከአንደበቶቻችንና ከአንደበቶቻቸው መውጣት ያለበት ቃል "የአገው ክልል እና ክልል እንሆናለን" የሚሉ ቃላቶችን መጠቀም መሆን እንዳለባቸው የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ ወዘተ...ናቸው።
በመጨረሻም የጀመርነው አገዋዊ ትግላችን ዳር እንዲደርስ (ግብ እንዲመታ) ፅናት፣ ማስተዋል፣ የመስመርና የዓላማ አንድነት፣ ቁርጠኝነት እና ስትራቴጂያዊነት ከአገው ፖለቲከኞች፣ ከማህበረሰብ አንቂዎች እና አፍሌን ይጠበቃል። ይህ ትልቅ አገዋዊ ዓላማ ዕውን እንዲሆን በድጋሜ ለአገው ፖለቲከኞች፣ ለማህበረሰብ አንቂዎች እና ለአፍሌን ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
የአገው ህዝብ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ በቅርብ ጊዜ የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን በቅርብ ቀን ዕውን ያደርጋል ሲሉም አዲሱ መኮንን(PHD) ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
፨፨፨፨ አገውነት ወይም ሞት!!! ፨፨፨፨

❤2
የቁንጅና ውድድር ማስታወቂያ
የአገው አዊ ብሔረሰብ ዞን ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ለ86ኛ ጊዜ ለሚከበረው የአገው የፈረሰኞች በዓል ወይዘሪት አዊን በመምረጥ የአዊ የባህል አምባሳደር ለማድረግ አስቧል፡፡
ስለሆነም እንደ እንጅባራ ከተማ አስተዳደር ወይዘሪት እንጅባራን በመምረጥ ለዞኑ ማቅረብ እንዲቻል ከታች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ስለምናወዳድር መስፈርቱን የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
#የማዎዳደሪያ_መስፈርት
1.8ኛ ክፍልና በላይ
2.ቁመት 1.65 ሜትር እና በላይ
3.እድሜ ከ17-30 ዓመት
4.ክብደት እስከ 55 ኪሎ ግራም
5. የብሄረሰቡን ባህልና ወግ የምታውቅና በዓግባቡ መግለፅ የምትችል እስከ 15/05/2018 ዓ/ም ድረስ እንጅባራ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 _ ድረስ መጥታችሁ እንድትመዘገቡ እንገልፃለን፡፡

ልብ ሰባሪ ዜና ዳንግላ ዶክተሯን አጣች
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
ይህች በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን ዶ/ር ሜሪ አበበ ትባላለች ትውልድና እድገቷ አገው ምድር ዳንግላ ከተማ ነው።
ወላጆቿ መምህራን ሲሆኑ የትምህርትን ሁለንተናዊ ፋይዳ አጥብቀው የተረዱ በመሆናቸው በሰጡት ትኩረት የተነሳ ዶክተር ሜሪና መንትያዋ ዶ/ር ሳምሪ በትምህርታቸው እጅግ የተመሰከረላቸው ጎበዝና ምግባረ ሰናይ ተማሪዎች በመሆን ከወላጆቻቸውም አልፈው ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና ለአካባቢያችን ምሳሌና ዓርዓያ መሆን የቻሉ ድንቅ ተማሪዎች እንደነበሩ ያስተማሯቸው መምህራኖች በእምባ ታጅበው ያስረዳሉ።
ዶ/ር ሜሪና መንትያዋ ዶ/ር ሳምሪ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ከፍተኛ የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት በማምጣት ወደ ጎንደር ዩንቨርስቲ በህክምና ትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዚህ ዓመትም ከ 3 ወር በኋላ እንደሚመረቁ ያገኜነው መረጃ ያመለክታል።
ሙሉ ትምህርታቸውን ጨርሰው በጥናትና ምርምር እንዲሁም በምረቃ ዝግጅት ላይ የነበሩት መንትዮቹ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ትላንት ጥር 07/2018 ዓ.ም ዶ/ር ሜሪ አበበ በድንገት ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል።
የሟች አስከሬንም ዛሬ ጥር 08/2018 ዓ.ም ከጎንደር ወደ ትውልድ ቦታዋ ዳንግላ እንደሚመጣና በአጉንታ ደብረ ምህረት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብሯ እንደሚፈጸም ይጠበቃል።
ይህ እጅግ መሪር ሀዘን ነው....ለምረቃ መርሃ ግብር ለሚዘጋጅ ቤተሰብ ይህን ያክል ጊዜ ልጅን ለወግ ማዕረግ ለማብቃት ለሚተጋ ለሚወጣና ለሚወርድ ቤተሰብ ምን ይውጠው ይሆን ብለን ስናስብና የአሟሟቷን ሁኔታ ስናስብ ሀዘኑን የበለጠ መሪር ያደርገዋል።
እንግዲህ ምን ይደረጋል አፈሩ ይቅለልሽ፣ነፍስሽን ይማረው..ለቤተሰቦቿ ጽናቱን ይስጥልን😭
.
@AGEWTV1

😭6😢4
ጥያቄችንን ስለመለሳችሁልን ከልብ እናመሰግናለን!!
ሚድያችን ከወራት በፊት ጀምሮ የ85ኛዋን የአገው አምባሳደር ክብርት ቤቴልሔም አዳሙን በድጋሜ ልትሆንልን ይገባል በሚል በተደጋጋሚ በጠየቅነው መሰረት "የአገው ፈረሰኞች ማህበር" እና "የአገው ባህልና ቱሪዝም" ጉዳዩን በጥሞና በመመልከት ክብርት አምባሳደራችን በድጋሜ የ86ኛው የአገው ፈረሰኞች ባህል አምባሳደር አድርገው ስለመረጡ ከልብ እናመሰግናለን።
ክብርት አምባሳደር ቤቴልሔም አዳሙ በርካታ ታሪካዊና ባህላዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ የቱሪስት ቦታዎችን ለህዝብ በሰፊው እያስተዋወቀች የምትገኝ ኮኮብ አምባሳደራችን ናት።
አምባሳደር ቤቴልሔም አዳሙ በሚድያችን ስም እና በአገው ህዝብ ስም እንኳን ደስ አለሽ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልሽ ምኞታችን ነው።
ወደኋላ ተመልሰን ስንቃኝ ያገኘናቸው በጥቂቱ እነዚህ እና ሌሎችም አሉበት
https://www.facebook.com/share/r/166w5vdbkK/
https://www.facebook.com/share/r/17p6emZWXb/
https://www.facebook.com/share/r/1CKexg2Ct4/
አገው ቲቪ ለአላማ ለቆሙት ሁሉ ለእውነት ይሞግታል!!
.
AGEW TV 🔗 AGEW TV Fans

❤4👍2