አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ Afro Soccer Ethiopia
215 subscribers
1.03K photos
2 videos
608 links
የኢትዮጵያን የእግር ኳስ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች እናስተዋዉቃለን
https://www.youtube.com/@afrosoccerethiopia3884
Download Telegram
የአሰልጣኝ ስዩም አስደናቂ መንገድ

አንጋፋው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ብሔራዊ ቡድኑን እያዘጋጀ ይገኛል። አሰልጣኙ ቡድኑን ከተረከበ ጀምሮ በተለያዩ ሀገራት በመሰልጠን ላይ የሚገኙ ታዳጊዎችን እየሰበሰበ ነው። እስካሁን 5 ታዳጊዎች ቡድኑን ተቀላቅለዋል።

👉 አእላፍ አያሌው (ከኦስትሪያ ቪየና ክለብ)
👉ኦልያድ ተስፋይ (ከካናዳው ቫውጋን)
👉ናትናኤል አረጋዊ (ከኤሚሬትስ TFC ክለብ)
👉ቢንያም ደስታ (ከኤሚሬትስ TFC ክለብ)
👉ይበልጣል ኤልያስ (ከስፔን B1 Soccer Academy)

ሥዩም ከበደ ይህንን በማድረጉ
👉ታዳጊዎቹ በታላላቅ የአውሮፓ ክለባት መልማዮች እይታ ውስጥ ይገቡልናል
👉ብሔራዊ ቡድናችንን በአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ከቋሚ ተሸናፊነት ወደ አሸናፊነት የሚያሸጋግሩልን አማራጭ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ይበዙልናል።

እንደሀገር ታዳጊዎችን በዘመናዊ ስልጠና ማፍራት ባንችል እንኳን እንዲህ በየቤተሰባቸው ጥረት እና በህዝብ ርብርብ ያደገውን ሀገር ዘመናዊ ስልጠና ማግኘት ለቻሉት እድል መስጠት እጅግ የሚበረታታ እና ለእግርኳሳችን እድገት የሚበጅ ነው ።
የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ መንገድ እጅግ የሚበረታታ እና ቀጣይነት ሊኖረው የሚገባ ነው።
አሰልጣኝ ስዩም ከበደ 👏👏👏

👉የአፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ ቻናሎች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👉https://t.me/afro_football_marketing

👉https://t.me/afrosoccer

👉ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064088501389

👉ዩቲዩብ https://youtube.com/@afrosoccerethiopia3884?si=_dlDBX5aP7GWPYO_

👉ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZMMMmXtE7/

👉https://t.me/afrosoccer
👍1
አምሳሉ ጥላሁን ባህር ዳር ከተማን ተቀላቀለ

ከአፄዎቹ የምንግዜም ምርጥ ተርታ የግራ መስመር ተከላካዩ አምሳሉ ጥላሁን አንዱ ነው ።አምሳሉ ከመከላከል ባሻገር ጎሎችን ያስቆጥራል ፤ በተለይ የግራ እግር ጠንካራ ምቶቹ መለያዎቹ ናቸው።ከፋሲል ከነማ ታዳጊ ቡድን በመነሳት ለአውስኮድ እና ዳሽን ቢራ ክለቦች ተጫውቶ እራሱን በማሳየት ወደ አሳዳጊው ክለብ ተመልሶ አይረሴ ግልጋሎት ሰጥቷል። ከአፄዎቹ ጋር በርካታ የዋንጫ ክብሮችን ማሳካት የቻለው አምሳሉ ጥላሁን(ሳኛ) በመጨረሻም ውሉ በማለቁ ምክኒያት ከአፄዎቹ ተለያይቶ ባህር ዳር ከነማን ተቀላቅሏል።
ማስታወቂያ ለ ታዳጊዎች

መድን የእግር ኳስ ክለብ ለታዳጊዎች ምልመላ ማስታወቂያ አውጥቷል

መስፈርት

* ዕድሜ ከ 20 አመት በታች
* ፆታ ወንድ
* ከዚህ ቀደም በኢትዬጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርመራ MRI ምርመራ አድርጎ ማረጋገጫ ያለው
* የMRI መረጃ የሌላቹ የልደት ሰርተፊኬት ፣ የ 8ኛ ክፍል አልያም የ 10ኛ ክፍል ወይ ደሞ የ 12 ክፍል መረጃ ማቅረብ ትችላላችሁ
* ምልመላ ጊዜ ከ ጥቅምት 01 ቀን 2017 ከ ጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 4 የሚቆይ ሲሆን ለአራት ቀናት የሚቆይ ምልመላ ይደረጋል

አድራሻ አቃቂ

የሚገኘው 07 ቀበሌ የመድን እግር ኳስ ክለብ መሰልጠኛ ሜዳ ላይ ሲሆን መልካም ዕድል ለታዳጊ ተጨዋቼች እያልን ይህንን መልእክት ለታዳጊዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንዲደርስ እናስተላልፍ ።
"ምርጡ አሰልጣኝ እኔ ነኝ "

አዎ በኢትዮጵያ አንጋፋ እና ምርጡ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ነው። የሀገራችን አሰልጣኞች ሲቪ እና ብቃት ቢመዘን ከየትኛውም አሰልጣኝ የተሻለው የስዩም ነው። ችግሩ ስዩም በየክለቡ ለተሰገሰጉ ሙሰኞች አይመችም። ለደላላ ጋዜጠኞችም በሩ ዝግ ነው። በያኔው በተጨዋችነት ዘመኑ በለመደው የንፅህና መንገድ ዛሬም ለመጓዝ ይታገላል ፤ የዛሬዎቹ ፈላጭ ቆራጭ ሙሰኞች ደግሞ "ቅድሚያ ለሀገር እግርኳስ እድገት " ማለትን አያቁም እና አያሰሩትም ፤ ሴራ ጠምጥመው ያደናቅፉታል።
በራሱ አንደበት "ከሀገሪቱ ምርጥ ሶስት አሰልጣኞች መሃል አንዱ እኔ ነኝ ሁለቱን ብትጠሩም አለሁበት " ያለው እውነት ነው። በተጫዋችነትም በአሰልጣኝነትም ኢትዮጵያ ፤ የመን ፤ ሱዳን ሌላም ሀገር ያስመዘገቡው ድል ታላቅ ምስክር ነው። በሲቪው ይታይ ፤ በልምዱና በብቃቱ ይመዘን ። ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነት ብቁ መሆኑን እነ ባህሩ ቃኘው "ካለመነፅር" ካዩት ይታያቸዋል።
አሱልጣኙ "የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ከሀገር ውስጥ አሰልጣኝ ከፈለገ ለማሰልጠን ዝግጁ ነኝ ሲቪዬን አስገብቼ ለአሰልጣኝነት እወዳደራለሁ " ብሏል።
👎1
ውበቱ v  ሰውነት v ገብረመድን

ገብረ መድህን ፡"ሽንፈቱን የዓለም ፍጻሜ አታድርጉት፤ ጊኒን የገጠምነው ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ይዘን ነው "

ውበቱ :  "ሊቢያዎች ጨዋታውን ማሸነፍ ይገባቸዋል ፣ የነበርንበት ምድብ ከባድ ነበር ማለት እንችላለን"

ሰውነት : " ተጋጣሚህ ብራዚልም ይሁን ፣  በተለይ ጎል አካባቢ አዳነ እንዳትምር ! ሳላ ! ጌታነህ! መረቡን ወዝውዘው  - ድል የጠማው ህዝብ እየጠበቀን ነው ! ጎል አስቆጥር ! አሸንፍ !!!"


በእናንተ እይታ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተሻለው አሰልጣኝ የቱ ነው ?
ሰኢድ ኪያር ስለ አስራት

አስራት ሀይሌ በኢትዮጲያ እግር ኳስ የወደር የለሽ ስኬታማነት ተምሳሌት ነው፡፡በተጫዋችነት የ10ኛው አፍሪካ ዋንጫ አባል ነበር፡፡

በክለብ አስራት የቅዱስ ጊዮርጊስ ምልክት ነው፡፡በክፋ ቀን የደረሰ ጀግናም ጭምር!!
አስራት ጫማ ሰቅሎ ማሰልጠን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በዋንጫ ያሸበረቀ የአሰልጣኝነት ህይወት ነበረው፡፡ በድምሩ  የ30 ዋንጫዋች ስኬት ምክንያት ነው፡

በብሂራዊ ቡድን ሴካፋን በሩዋንዳ እና ኢትዮጲያ አሸንፎ ኢትዮጲያን አስፈንጥዝዋል!!

በአሁኑ የኢትዮጲያ እግር ኳስ የሚጫወቱ፣የሚያሰለጥኑ አያሌ የሱ ፍሬዎች አሉ፡፡

👌አስራት ተጽፎ የማያልቅ ድንቅ ታሪክ፣የማያወላዳ ስብእና እና የኢትዮጲያ እግር ኳስ የግማሽ ምእተ አመት ሁለንተና ሆኖ አልፍዋል፡፡ጎራዴው ወደ ሰገባው ተመልስዋል፡፡ መጽናናትን ለሁሉም እመኛለሁ!!!"

ስፖርት ጋዜጠኛ ሰኢድ ኪያር
👍2
ኢድ ሙባረክ

በሀገር ውስጥ እና በመላው አለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ1446 ተኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ::

ሚዲያችን በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል ።

መልካም በዓል!
ኢድ ሙባረክ!

Afro Football Marketing
Afro Soccer Ethiopia/አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ

👉https://t.me/afro_football_marketing

👉https://t.me/afrosoccer

👉ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064088501389

👉ዩቲዩብ https://youtube.com/@afrosoccerethiopia3884?si=_dlDBX5aP7GWPYO_

👉ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZMMMmXtE7/

👉https://t.me/afrosoccer

👉 ኢንስታግራም https://www.instagram.com/afro_soccer_ethiopiaa?igsh=eXR1cXI4a281NW9w
አምባሳደሮቹ

ስማቸውን ተጠቅመው ለሰብአዊ ድጋፍ አምባሳደር መሆናቸው ያስመሰግናቸዋል ። ሌሎችም የናንተን ፈለግ ቢከተሉና ባቅራቢያቸው ለሚገኙ የበጎአድራጎት ተቋማት ፤ ትምህርት ቤቶች ፤ የስፖርት አካዳሚዎች ፤ ስታዲየሞች የመሳሰሉ ለህብረተሰባችን ጠቃሚ ነገሮች ላይ ቢሳተፉ መልካም ነው ።

👉በአፍሪካም ሆነ በዓለም በበጎ አድራጎት ስራቸው የሚታወቁ የህዝባቸው አለኝታ የሆኑ ተጫዋቾችን ጥቀሱ?



👉https://t.me/afro_football_marketing

👉https://t.me/afrosoccer

👉ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064088501389

👉ዩቲዩብ https://youtube.com/@afrosoccerethiopia3884?si=_dlDBX5aP7GWPYO_

👉ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZMMMmXtE7/

👉https://t.me/afrosoccer

👉 ኢንስታግራም https://www.instagram.com/afro_soccer_ethiopiaa?igsh=eXR1cXI4a281NW9w
ጠቁሙን

👉"በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ የምንግዜም ምርጡ አማካይ ተጫዋች ምርጫ ውስጥ እነማን መካተት አለባቸው ? ጠቁሙን
👉በዚህ ውድድር ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው በክለብም ሆነ በብሄራው ቡድን ከፍተኛ ብቃት ያሳዩ የአማካይ ስፍራ ተጫዋችን ጠቁሙን።
👉ከቀደምቱም ሆነ አሁን ካሉት የምታውቁትን ጠቁሙን ።


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.facebook.com/100064088501389/posts/pfbid0292fsWyTSGwZjvi1u8THc63zchA5WgDVN3gbCJUSBonZ5SqHsf7N7dBYJfhFZgmKyl/?app=fbl
ሙሉጌታ ምህረት ፡ አመለ ሸጋው ኮከብ

ገረሱ ሸመናን ና አዳነ ግርማን ጨምሮ በርካታ ኮከቦችን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ያበረከተችልን ሀዋሳ ከተማ የሰጠችን ሌላው ፈርጥ አመለ ሸጋው ሙሉጌታ ነው
በክለብ
👉ሙሉጌታ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ሶስት ጊዜ ሻምፒዮን ሆኗል
👉ይህ የአማካይ ተጫዋች ሀዋሳ ከነማ በ1996 የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማንሳት ቀዳሚው የክልል ክለብ ሲሆን ፥ ሙሉጌታ ደግሞ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
👉በቀጣዩ አመትም ክለቡ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ባለቤት ሲሆን፥ የአምበሉ ሙሉጌታ ሚና ላቅ ያለ እንደነበር ይታወሳል
👉በ1998 ወደ ጊዮርጊስ በማቅናት ከክለቡ ጋር የፕሪሚየር ሊግ እና የጥሎ ማለፍ ዋንጫን አሳክቷል፡፡
👉በ1999 ወደ ሀዋሳ ከነማ በመመለስ ክለቡ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሲያሸንፍ ሙሉጌታ የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመሆን በድጋሚ ተሸልሟል፡፡

ብሄራዊ ግልጋሎት
👉ሙሉጌታ ለዋሊያዎቹ 13 ጊዜ ተሰልፏል ። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋርም የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሴካፋ ዋንጫን አሳክቷል ።

ልዩ ባህሪ
👉ሙሉጌታ ከኳስ ብቃቱ ባልተናነሰ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ የሚወሳ የመልካም ፀባይ ባለቤት ነው
👉በ16 አመታት የክለብና የብሔራዊ ቡድን የተጫዋችነት ቆይታው አንድም ቀይ ካርድ አላየም
👉የሙሉጌታ የተጫዋችነት ጥብቅ ዲሲፕሊን በአሰልጣኞቹና በቡድን አጋሮቹ ጭምር የተመሰከረለት ነው፡፡ የእግርኳስ ሙያ በሚፈልገው ልክ እራሱን የዲሲፕሊን ተገዥ በማድረጉ ለበርካታ አመታት አቋሙን ጠብቆ መዝለቅ ችሏል
በአሰልጣኝነት
👉ሀዋሳ ከተማን፣ ወልቂጤ ከተማንና ሀዲያ ሆሳዕናን በዋና አሰልጣኝነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ምክትል በመሆን አገልግሏል።ይህ ኮከብ በአሁን ጊዜ ሀዋሳ ከተማን በአሰልጣኝነት እየመራ ነው
1
ሰብስክራይብ በማድረግ ብቻ እንተጋገዝ

የኢትዮጵያን ቀደምት ተጨዋቾች ብቃት ለማየት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@afrosoccerethiopia3884?si=2yohb8GPeYarnzRa

የኢትዮጵያን ቀደምት ክዋክብት እያነገስን፤ አዲሶቹን እያሳደግን፤ ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን