ዜና፡ በምዕራብ ኦሞ ዞን በተከሰተ የአባ ሠንጋ በሽታ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፣ በሽታው የቤት እንስሳትንም ገድሏል
በደቡብ ምዕራብ #ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን በተቀሰቀሰ የአባ - ሠንጋ በሽታ ሰባት ሰዎችን ጨምሮ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የዞኑ መስተዳድር አስታወቀ፡፡
የአባ - ሠንጋ በሽታው በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ ኮካ በተባለ ቀበሌ ውስጥ የተከሰተው ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከዞኑ የአርብቶ አደር እና የጤና መምሪያ የተውጣጣ ቡድን ሚያዚያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በሽታው ታይቶበታል ወደተባለው አካባቢ መድረሱን የምዕራብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደር መምሪያ አስታውቋል።
ቡድኑ ባደረገው ምርመራ በሽታው አባ-ሠንጋ / አንትራክስ / መሆኑን ማረጋገጥ መቻሉን የመምሪያው ሃላፊ አቶ በለጠ ግርማ መናገራቸውን ከጀርመን ድምጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በሽታው እስከአሁን በሰው ሕይወትና በእንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱንም ሃላፊው ገልጸዋል ያለው ዘገባው “በበሽታው 7 ሰዎች እና 15 የቤት እንስሳት መሞታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል“ ማለታቸውንም አካቷል።
በሽታው ወደ ሌሎች አጎራባች ወረዳዎች እንዳይስፋፋ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑን እና “አሁን ላይ በባለሙያዎች የህክምና መድኃኒት የመስጠት እና የእንስሳት ክትባት ሥራ መጀመራቸውን የአርብቶ አደር መምሪያ ሃላፊው መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል።
የዞኑ መስተዳድር በሽታውን በራሱ አቅም እየተከላከለ እንደሚገኝ እና በቀጣይ ሂደቱን በመገምገም ከክልል ድጋፍ የምንጠይቅበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል ሲሉ መናገራቸውን አመላክቷል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3

ዜና፡ ፖሊስ ከ #አዲስ_ስታንዳርድ የወሰዳቸውን የኤሌክትሮኖክስ መሳሪያዎች በአፋጣኝ እንዲመልስ ሲፒጄ ጠየቀ
በፖሊስ በተወሰዱት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል ስጋቱንም ገልጿል
ፖሊስ በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ባደረገው ብርበራ በወሰዳቸው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ተቋም (ሲፒጄ) ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ስጋቱን አስታወቀ።
በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን ምርመራ እንዲያቋርጥ የጠየቀው ሲፒጄ የተወሰዱት የተቋሙ የኤሌክትሮኖክስ መሳሪያዎችንም በአፋጣኝ እንዲመልስ አሳስቧል።
“የአዲስ ስታንዳርድ ላይ የተፈጸመው ብርበራ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት ነፃ ሚዲያዎችን ዝም ለማሰኘት እያካሄደው ያለው ዘመቻ አካል ነው፤ የተቋሙን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች መውሰዱ በውስጣቸው የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚቻልበት እድል ከፍተኛ ነው” ሲሉ የሲፒጄ አፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ ስጋታቸውን መግለጻቸውን አስታውቋል።
ስድስት የደንብ ልብስ ያልለበሱ የፖሊስ አባላት መሆናቸውን የገለጹ ሰዎች ሚያዝያ 9 ቀን2017 አ.ም የአዲስ ስታንዳርድን ቢሮ መበርበራቸውን፣ የዜና ክፍል ኃላፊውን እና የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊውን ለምርመራ ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መውሰዳቸውን የድርጅቱ መስራች ፀዳለ ለማ ለጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ተቋሙ (CPJ) ተናግረዋል።
ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳላቸው ቢናገሩም ግልባጭ ሳያሳዩ ወደ ተቋሙ ቢሮ ዘው ብለው መግባታቸውን፤ የተቋሙ ጋዜጠኞች ሁከት ሊያስከትል የሚችል ዘጋቢ ፊልም በማዘጋጀት ተጥርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እንደነገሯቸው ፀዳለ ተናግረዋል፤ አክለዉም ክሱ ሀሰት መሆኑን እና ድርጅቱ ዘጋቢ ፊልሞችን የማዘጋጀት አቅም እንደሌለው መግለጻቸውን ሲፒጄ በመግለጫው አካቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7618

Addis standard
ፖሊስ ከአዲስ ስታንዳርድ የወሰዳቸውን የኤሌክትሮኖክስ መሳሪያዎች በአፋጣኝ እንዲመልስ ሲፒጄ ጠየቀ - Addis standard
በፖሊስ በተወሰዱት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል ስጋቱንም ገልጿል አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15/ 2017 ዓ.ም ፦ ፖሊስ በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ባደረገው ብርበራ በወሰዳቸው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል የጋዜጠኞች መብት…
ዜና፡ በፕሬዝዳንት #ታደሰ ወረደ የተመሰረተው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ “አካታችና አቃፊ ባለመሆኑ አንቀበለውም፣ በጉልበት የመጣ ነው” - ሶስት የክልሉ ፓርቲዎች
#በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረዳ የተቋቋመው ካቢኔ አካታችና አሳታፊ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ትላንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
በሌተናል ጄነራል ታደሰ የተመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ስልጣን የመጣው በጉልበት ነው ብለው እንደሚያምኑ ሶስቱ ፓርቲዎች የትግራይ ነጻነት ፓርቲ (ውናት)፣ የአረና ትግራይ ለዲሞክራሲ (አረና)፣ ባይቶና ትግራይ (ባይቶና) በጋራ በሰጡት መግለጫ ተገልጿል።
በክልሉ በቀደመው የጊዜያዊ አስተዳደሩ የተመሰረተው የጊዜያዊ ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ታደሰ ወረዳ ለሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር እውቅና እንደማይሰጠው፤ በክልሉ እንዲካሄድ በፕሬዝዳንት ታደሰ የተጠራውን ብሔራዊ እርቅ እንደማይቀበለው የትግራይ ነጻነት ፓርቲ (ውናት) ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገበ ገልጸዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7628

በፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ የተመሰረተው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ “አካታችና አቃፊ ባለመሆኑ አንቀበለውም፣ በጉልበት የመጣ ነው” - ሶስት የክልሉ ፓርቲዎች - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16/ 2017 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረዳ የተቋቋመው ካቢኔ አካታችና አሳታፊ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ትላንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ። በሌተናል ጄነራል ታደሰ የተመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ስልጣን የመጣው…
ዜና፡ #በአማራ ክልል በትምህርት ቤት ዙሪያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች አስታወቁ
በአማራ ክልል ምሥራቅ #ጎጃም ዞን ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርት ቤት ዙሪያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች አስታወቁ።
ጥቃቱ የደረሰዉ በዞኑ እናርጅ እናውጋ ወረዳ ገደብ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሲሆን የትምህርት ቤት አጥር ለማጠር እና ቤት ለመሥራት 'ለልማት ሥራ' የወጡ "ሰላማዊ ሰዎች" በጥቃቱ መገደላቸው ተገልጿል።
ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ ቅርብ ርቀት ላይ ነበርኩ ያሉ አንድ የዓይን እማኝ እንደተናገሩት ጥቃቱ በተፈጸመበት ቅጽበት ጩኸት፣ ግርግር እና ድንጋጤ መፈጠሩን ጠቁመው "የሆነውን አናውቀውም" ሲሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም እሳቸውን ጨምሮ ሥራ ላይ የነበሩ ሰዎች ጥቃቱ ወደተፈፀመበት አካባቢ ሲጠጉ "ሰው የሚባል አይለይም" ሲሉ ስለ ጉዳቱ ተናግረዋል።
"እንዳለ በሙሉ ጥቁር ነገር ነው የሆነው። አካባቢው በሙሉ ሰው የሚባል ነገር የለም። ከወደቀው ውስጥ የሚጮህ አለ፤ የሚንከባለል አለ። የተፈጠረው ነገር ይዘገንናል። ሰው ለሆነ እጅግ የሚዘገንን ድርጊት ነው" ብለዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ አስከሬን ስለማንሳታቸው የተናገሩ ሌላ እማኝ ደግሞ አብዛኛው የጥቃቱ ተጎጂዎች ወዲያው ሕይወታቸው ማለፉን ገልፀው፤ ሟቾቹ በአብዛኛው ወጣቶች ናቸው ማለታቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0S8xcwYmjK2oYQmXP88447bS6nFAF4fu1qAyrpnN9esLL7BL9UTfmEDndyL7QT6odl

ዜና፡ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ “ከቀያቸው ተፈናቅለው በአስከፊ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን መመለስ ነው” - ፕሬዚደንት #ታደሰ ወረደ
#በትግራይ ክልል ከቀያቸው ተፈናቅለው በከፋ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የመመለስ ጉዳይ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ ነው ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያስታወቁት የአፍሪካ ህብረት #የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት መከታተል፣ ማረጋገጥና ማክበር ተልእኮ ከፍተኛ ሀላፊ ሆኖው የተመደቡትን ሜጀር ጀነራል ሳማድ አክሶዴ ትላንት ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
ፕሬዚደንቱ አክለውም ተፈናቃዮችን ለመመለስ፣ የትግራይ ሰራዊት ወደ ህብረተሰቡ የማቀላቀልና መልሶ የማቋቋም በአጠቃላይ በፕሪቶርያው ስምምነት አፈፃፀም ዙርያ ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀራረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
ሜጀር ጀነራል ሳማድ አክሶዴ በበኩላቸው በፕሪቶርያው ስምምነት አፈፃፀም፣ ተፈናቃዮች መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በዲዲአር አፈፃፀም ሂደት ለመወያየት መምጣታቸውን በመጠቆም ለፕሪቶርያው ስምምነት የተሟላ ትግበራ የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚሰሩ መግለፃቸውን የፕሬዝዳንቱ የጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7634

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ “ከቀያቸው ተፈናቅለው በአስከፊ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን መመለስ ነው” - ፕሬዚደንት ታደሰ ወረደ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17/ 2017 ዓ/ም፦በትግራይ ክልል ከቀያቸው ተፈናቅለው በከፋ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የመመለስ ጉዳይ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ ነው ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያስታወቁት የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት መከታተል፣ ማረጋገጥና ማክበር ተልእኮ ከፍተኛ ሀላፊ ሆኖው የተመደቡትን…
ዜና፡ “ሲም ካርድ በመጠቀም ፈንጂዎችን ለማፈንዳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ይዣለሁ” ሲል #የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ “ሲም ካርድ በመጠቀም ፈንጂዎችን በማፈንዳት የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሶስት ተጠርጣሪዎች” ይዣለሁ ሲል ገለጸ።
"ተጠርጣሪዎች ገበያ ስፍራዎች በትምህርት ቤቶችና እንዲሁም ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ፈንጂዎችን በማጥመድ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ዝግጅት እንደነበራቸው" ባካሄድነው ምርመራ አረጋግጠናል ሲሉ የመምሪያው ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም ትላንት ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
"ፍንዳታውን የሚያካሂደው በፈንጂው ላይ በሚታሰር የሞባይል ቀፎና ሲም ካርድ በመታገዝ ወደ ሲም ካርዱ በመደወል ፍንዳታውን በርቀት ሆነው እንደሚያካሂዱ" ተደርሶበታል ብለዋል፡፡
የመምሪያው ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም በመግለጫቸው "ተጠርጣሪዎቹ ከቀናት በፊት ምሽት ላይ በከተማው አንድ ፖሊስ ጣቢያና በክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ላይ ፈንጂ በማፈንዳት ተሰውረው የቆዩ ናቸው" ማለታቸውን ከከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
"የፀጥታ መዋቅሩ ባደረገው ጥብቅ ክትትልና ስምሪት ተጠርጣሪዎቹ ሌላ የሽብር ተልእኮ ለመፈጸም በአንድ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በድብቅ ካዘጋጁዋቸው የፈንጂ መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል" ማለታቸውንም መረጃው አካቷል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና፡ #የሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች “በፓርቲው ጽህፈት ቤት ሲካሄድ የነበረ የሴቶች ስብሰባን አደናቅፈዋል፣ ጉዳቶችና እስሮችም ተፈጽመዋል” ሲል ኦብነግ ክስ አቀረበ
በሊቀመንበሩ አብዲራህማን ማህዲ የሚመራው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (#ኦብነግ) የሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች #በጅግጅጋ ከተማ በጽ/ቤቱ ሲካሄድ የነበረን የሴቶች ስብሰባን አደናቅፈዋል፣ ጉዳቶችና እስሮችም ተፈጽመዋል ሲል ክስ አቀረበ።
ድርጊቱ በሶማሌ ክልል ዉስጥ በሚገኙ በፓርቲው ደጋፊዎቹ እና በፖለቲካ ምህዳሩ ላይ እየተካሄደ ያለው “የሰፋ ጭቆና” አካል ነው ሲል ገልጿል፤ በተጨማሪም "ለሶማሌ ህዝብ ቃል የተገባው የፖለቲካ ምህዳር በግዴታ እና በኃይል ሆን ተብሎ እየተዘጋ ነው" ሲል ከሷል።
ቡድኑ "ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን" ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቆ "ህዝባችን ሲጠቃ እና ወንጀለኛ ተደርጎ ሲቆጠር ዝም አንልም" ብሏል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7641

የሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች “በፓርቲው ጽህፈት ቤት ሲካሄድ የነበረ የሴቶች ስብሰባን አደናቅፈዋል፣ ጉዳቶችና እስሮችም ተፈጽመዋል” ሲል ኦብነግ ክስ አቀረበ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17/ 2017 ዓ/ም፦በሊቀመንበሩ አብዲራህማን ማህዲ የሚመራው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) የሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች በጅግጅጋ ከተማ በጽ/ቤቱ ሲካሄድ የነበረን የሴቶች ስብሰባን አደናቅፈዋል፣ ጉዳቶችና እስሮችም ተፈጽመዋል ሲል ክስ አቀረበ። ድርጊቱ በሶማሌ ክልል ዉስጥ በሚገኙ በፓርቲው ደጋፊዎቹ እና በፖለቲካ ምህዳሩ ላይ እየተካሄደ ያለው “የሰፋ ጭቆና” አካል…
ዜና፡ “በቅርቡ የጸደቀው መመሪያ አይመለከተንም፣ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እስኪሰጠን ድረስ ጥያቄያችን ማቅረብ እንቀጥላለን” - #የመቀሌ ነዋሪዎች
“እንድንደራጅ በተደረገበት መመሪያ መሰረት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እስኪሰጠን ድረስ ህጋዊ እና ሰላማዊ የሆነው ጥያቄያችን ማቅረብ እንቀጥላለን” ሲሉ በመቀለ ከተማ 70 ካሬ የመኖሪያ ቦታ ለመውሰድ የተመዘገቡ ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ ትላንት ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ባካሄዱት ሰልፍ በቅርቡ የጸደቀው መመሪያ 9/2017 አይመለከተንም፡ ተመዝግበን እና ገንዘብ በመቆጠብ እንድንደራጅ በተደረግንበት መመሪያ 4/2011 ነው ልንዳኝ የሚገባን ሲሉ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
አዲሱ መመሪያ ወደ ኋላ ተመልሶ እኛ ላይ ተፈጻሚ ሊሆን የሚያስችል ምንም አይነት የህግ አግባብ የለም ሲሉ አስታውቀዋል።
በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ጥያቄዎቻችንን እንኳ በሰላማዊ ሰልፍ እንዳንቀርብ ገድቦን ነበር ያሉት አቶ ሓጋዚ የፖለቲካ ችግሩ አሁን ላይ ለጊዜውም ቢሆን መፍትሔ አግኝቷል ብለን እናምናለን፣ ለዚህም ነው ፕሬዝዳንቱ ጋር ጥያቄያቸንንም ለማቅረብ የተገኘነው ሲሉ አስታውቀዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7638

“በቅርቡ የጸደቀው መመሪያ አይመለከተንም፣ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እስኪሰጠን ድረስ ጥያቄያችን ማቅረብ እንቀጥላለን” - የመቀሌ ነዋሪዎች - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17/ 2017 ዓ/ም፦ “እንድንደራጅ በተደረገበት መመሪያ መሰረት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እስኪሰጠን ድረስ ህጋዊ እና ሰላማዊ የሆነው ጥያቄያችን ማቅረብ እንቀጥላለን” ሲሉ በመቀለ ከተማ 70 ካሬ የመኖሪያ ቦታ ለመውሰድ የተመዘገቡ ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ ትላንት ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ባካሄዱት ሰልፍ በቅርቡ የጸደቀው…
ዜና፡ #ኢትዮ ቴሌኮም “ካቀረበው አክስዮን ሽያጭ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የተከፈለ ገንዘብ” መሰብሰብ መቻሉን ገለጸ
“ከ47 ሺ በላይ ሰዎችም” ተሳትፈዋል ብሏል
ኢትዮ ቴሌኮም ከጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በቆየው እና #ለኢትዮጵውያን ለሽያጭ ካቀረበው የ10 በመቶ ድርሻ “3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የተከፈለ ገንዘብ” መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ።
ለ121 ቀናት በተካሄደው አክስዮን ሽያጭ 47 ሺ 377 ሰዎች መሳተፋቸውን እና 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን አክስዮኖች መግዛታቸዉን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ጠቁሟል።
በአጥቃላይ 100 ሚሊዮን አክስዮኖች ለሽያጭ መቅረባቸውን ያወሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አንድ ግለሰብ የሚገዛው የአክሲዮን ዋጋ ከአንድ ሚሊዮን እንዳይበልጥ ተደርጎ ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።
ባንኮች እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዉያን የአክስዮን ገበያው ላይ ለመሳተፍ ጥያቀ ማቅረባቸውን የጠቆሙት ፍሬሕይወት ታምሩ በቀጣይ ሂደቱ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
በ121 ቀናት የአክስዮን ሽያጭም ጥሩ የዲጂታል ባህል መገንባቱን አንስተው ይህም ለተቋሙ ብቻ ሳይሆን ለሃገሪቱ አዲስ ልምምድን የፈጥረ መሆኑን አመላክተዋል፤ የኢትዮ ቴሌኮም መደበኛ አክሲዮኖች የግዢ በዲጂታል መንገድ በማከናወን ብር 3.2 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብት ለማሰባሰብ ችሏል ብለዋል፡፡
የተሸጡ አክሲዮኖች ድልድል በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የማጽደቅ ሂደት ከተከናወነ በኋላ ውጤቱን አሳውቃለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ቀሪ አክስዮኖችን በተመለከተ አክሲዮን የገዙ ባለድርሻዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ በቀጣይ በዝርዝር የሽያጭ ሂደቱ ይገለጻል ብሏል።

ዜና፡ #የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሶማሊያ ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ ሰራዊት ላዋጡ ሀገራት ምስጋና አቀረቡ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለአፍሪካ ኅብረት #የሶማሊያ ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ሰራዊት ላዋጡ ሀገራት ምስጋና አቀረቡ።
#በዩጋንዳ ኢንቴቤ በአውሶም ዙሪያ የመከረው ልዩ ስብሰባ የተጥናቀቀ ሲሆን በስብሰባው የተገኙት የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር፤ ሰራዊት በማዋጣት መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙ ሀገራት አድናቆታቸውን በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል።
ህብረቱ በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በቁርጠኝነት የሚደግፍ መሆኑንም አመላክተዋል።
በዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ጋባዥነት በተካሄደው ስብሰባ #ኢትዮጵያ፣ #ግብፅ፣ #ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ #ጂቡቲ እና ሶማሊያ ተሳትፈዋል።
በመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በጉባኤው ተሳትፏል።
የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የሶማሊያ መንግስት እስከ አሁን የሄደበትን መንገድ አድንቀው፣ የፀጥታ ተቋማትን የማጠናከርና የማቀናጀት ስራ ላይ አበክሮ መስራት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የሶማሊያ የጸጥታ ኃይል በራሱ አቅም ግዳጆችን የመወጣት አቅም ላይ እስኪደርስ ድረስ ድጋፏንአጣናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።
አክለውም አፍሪካውያን በሶማሊያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የጋራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዜና፡ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት #በአማራ ክልል በበድሮን በመታገዝ የሚደረጉ ጥቃቶችን አወገዘ
በአማራ ክልል ምሥራቅ #ጎጃም ዞን ባሳለፍነው ሳምንት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸው እና ድርጊቱ እጅግ እንዳሳሰባቸው #የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌይ አስታወቁ።
በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርት ቤት ዙሪያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ማስታወቃቸውነ የተመለከተ ዘገባ መቅረቡ ይታወሳል።
“ይህ የከፋ ጥቃት በቅርብ ወራት ውስጥ ተፈጽመው የበርካቶችን ህይወት የቀሰፉ ተግባራት ተጨማሪ ማሳያ ነው፤ በርካታ ንጹሃንን የቀሰፉ የድሮን ጥቃቶችመ እ.አ.አ በ2024ትመ ተፈጽመዋል” ሲሉ ዋና ጸሃፊው መናገራቸውን ምክር ቤቱ ትላንት ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
“የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በንጹሃን በብዛት በሚኖሩባቸው አከባቢዎች የሚፈጸሙ መሰል ጥቃቶችን በእጅጉ ይኮንናል” አመላክቷል።
በተጨማሪም ዋና ጸሃፊው ፒሌይ ተዋጎ ያልሆኑ ሰዎችን ከጥቃት በጠበቀ መልኩ እንዲሁም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህጎችን በጥብቅ ሳይከተሉ በግጭት አካባቢዎች የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል።
ፒሌይ የሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ሰላማዊ መፍትሄን እንዲከተሉ አሳስበዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02u7iqAczdEgmt9VemS93aPVjCfy16f74Ey7oxt2Ni9J9LdzXEqwBM7waiPkCdDHiMl

ዜና፡ ግንቦት አምስት በኋላ እንደሚሰረዝ በምርጫ ቦርድ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው #ህወሓት አሁንም እንደ አዲስ እንደማይመዘገብ አስታወቀ
ህጋዊ እውቅናየ አለመመለስ በስምምነቱ ላይ አደገኛ መዘዝ ያስከትላል ብሏል
በምርጫ ቦርድ በተቀመጠው ቀን ገደብ መሰረት ህልውናው ሙሉ በሙሉ ሊሰረዝ ሁለት ሳምንታት የቀሩት ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)፤ በድጋሚ “ምንም አይነት” ምዝገባ እንደማያካሂድ አስታወቀ።
ፓርቲው ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ “አደራዳሪዎች፣ የአፍሪካ ህብረት ፓነል እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሀትን ህጋዊ እውቅና አለመመለስ በስምምነቱ ላይ የሚያስከትለውን አደገኛ መዘዝ ተረድተው የድርሻቸውን እንዲወጡ” ሲል ጠይቋል።
በፌደራል መንግስት እየተደረገ ያለው “#የፕሪቶርያ ስምምነትን የሚጥስ አካሄድ በተመለከተ ህወሓት ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ህብረት ፓኔል መውሰዱን” ያስታወቀሰው መግለጫው “ፓኔሉም የህወሓት ህጋዊ ሰውነት እንዲመለስ እና እንደአዲስ መመዝገብ እንደማይገባው በመግለጽ ውጤቱም እስከ ቀጣዩ የፓኔሉ ስብሰባ ተጠናቆ እንዲቆይ ሃሳብ ሰጥቶበታል” ብሏል።
“ነገር ግን ፓኔሉ እስካሁን ባለመሰብሰቡ በአጠቃላይ የስምምነቱ አፈጻጸም ሆነ የሚታዩ ጥሰቶችን መግምገም አለመቻሉን” አመላክቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7647

ዜና፡ ግንቦት አምስት በኋላ እንደሚሰረዝ በምርጫ ቦርድ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ህወሓት አሁንም እንደ አዲስ እንደማይመዘገብ አስታወቀ - Addis standard
ህጋዊ እውቅናየ አለመመለስ በስምምነቱ ላይ አደገኛ መዘዝ ያስከትላል ብሏል አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20/2017 ዓ/ም፦ በምርጫ ቦርድ በተቀመጠው ቀን ገደብ መሰረት ህልውናው ሙሉ በሙሉ ሊሰረዝ ሁለት ሳምንታት የቀሩት ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)፤ በድጋሚ “ምንም አይነት” ምዝገባ እንደማያካሂድ አስታወቀ። ፓርቲው ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ “አደራዳሪዎች፣ የአፍሪካ…
ዜና: ኮሚሽኑ በመጀመሪያ ዙር 75 ሺ የቀድሞ #የትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ህብረተሰቡ ለመመለስ ቢያቅድም እስከ አሁን የተመለሱት 17 ሺህ ብቻ ናቸው ተባለ
በአማራ ክልል ከ3ሺህ በላይ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ማሕበረሰቡ ተቀላቅለዋል ተብሏል
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን በትግራይ ክልል እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንደሚጠናቀቅ በተገለጸው በመጀመሪያ ዙር ለ75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ ቢያቅድም እስከ አሁን የተመለሱት 17 ሺህ ብቻ መሆናቸውን አስታወቀ።
ባለፈው ኅዳር ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም በብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን ተጀምሮ የነበረው እንስቅስቃሴ ብዙ ሳይዘልቅ ለወራት ተቋርጦ መቆየቱን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን ኮምሽነር ተመስገን ጥላሁን ተናግረዋል።
"በትግራይ ክልል በወቅቱ የነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለሥራችን ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ነበረ" ያሉት ኮምሽነሩ አክለውም "የቀድሞ ተዋጊዎችን መረጃ ማጥራት፣ ከትጥቅ ርክክብ እና የትጥቅ ሁኔታ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ማጥራት ያለብን ጉዳዮች ስለነበሩ በዚሁ ምክንያት ልናቋርጥ ተገደን ነበረ" ብለዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7650

ኮሚሽኑ በመጀመሪያ ዙር 75 ሺ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ህብረተሰቡ ለመመለስ ቢያቅድም እስከ አሁን የተመለሱት 17 ሺህ ብቻ ናቸው ተባለ - Addis standard
በአማራ ክልል ከ3ሺህ በላይ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ማሕበረሰቡ ተቀላቅለዋል ተብሏል አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20/2017 ዓ/ም፦ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን በትግራይ ክልል እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንደሚጠናቀቅ በተገለጸው በመጀመሪያ ዙር ለ75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ ቢያቅድም እስከ አሁን የተመለሱት 17 ሺህ ብቻ መሆናቸውን አስታወቀ።…
ዜና፡ #የሰላም ሚኒስትር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ “ከ18 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማወያየት ችያለሁ” ሲል ገለጸ
የሰላም ሚኒስትር በበጀት አመቱ “25 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማወያየት አቅዶ ከ18 ሚሊዮን የሚልቁትን ማወያየት ችሏል” ሲሉ ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ መናገራቸው ተገለጸ።
ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት የተቋማቸውን የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት መሆኑን ከህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሚኒስትሩ “18 ሚሊየን የማህበረሰብ ክፍል” በምን፣ እንዴት እና የት እንዳወያዩ በሪፖርታቸው ስለማካተታቸውም ይሁን አለማካተታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያለው ነገር የለም።
ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ “የፌዴራልና የክልል መንግስታትን እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር በርካታ ስራዎች ሰርቷል” በሚል ከቋሚ ኮሚቴው አድናቆት ተችሮታል ሲል ምክር ቤቱ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ፌስቡክ ገጹ ባገራው መረጃ አስታውቋል።
መረጃው በተጨማሪም ቋሚ ኮሚቴው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “ለግጭት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን አስቀድሞ በመለየት የግጭት ምንጮችን ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በትብብር የማጋለጥ ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ አቅጣጫ እንደተቀመጠለት አመላክቷል።
አቶ መሐመድ፣ “በየአካባቢው የሚከሰቱ ጥቃቅን ግጭቶችን ላይ ላዩን የብሄርና የሃይማኖት መልክ ያለው በማስመሰል በተዛባ ግንዛቤ ግጭቱን ከማስፋፋት ይልቅ፣ የግጭቱን እውነተኛ መንስኤ መፈለግና መፍትሄ መስጠት የተሻለ” ነው ሲሉ ጠቁመዋል ብሏል።
ሚኒስቴሩ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት “ከሃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ተቋማት እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል” ሲሉ አቶ መሐመድ አስረድተዋል ብሏል።

ዜና፡ በየመን በስደተኞች መኖሪያ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት #ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 68 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
#በየመን በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ኢትዮጰያውያንን ጨምሮ 68 ስደተኞች መገደላቸው ተገለጸ፤ የአየር ጥቃቱን የፈጸመችው አሜሪካ ነች ሲሉ የየመን ሁቲዎች አስታውቀዋል።
በሁቲዎች የሚተዳደር ነው የተባለ የየመን የቴሌቪዢን ጣቢያ ጥቃቱ በተፈጸመበት ቦታ የቀረጸው ቪዲዮ ላይ ከፍርስራሹ ውስጥ የሚወጣ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት ስደተኛ በአማርኛ “ወይኔ እናቴ” የሚል ድምጽ ያሰማል ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ባስነበበው ዘገባው አመላክቷል።
በአየር ጥቃቱ 47 ስደተኞች ቆስለዋል ያለው ዘገባው በጥቃቱ ከወደመው መጠለያ ማዕከል ህንጻ ፍርስራሽ ስር የተቀበሩ የበርካታ ሰዎች አስከሬኖችን የሚያሳዩ አሰቃቂ ምስሎች በቴሌቪዢን ጣቢያው መቅረባቸውን አስታውቋል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ሳዑዲ አረብያ ለሚያደርጉት ህገወጥ ጉዞ የመን ዋነኛ ማቋረጫቸው መሆኗን የጠቆመው የዜና አውታሩ “ሳዳ” በሚል በሚጠራው የህገወጥ ስደተኞች መጠለያ ማዕከል በተፈጸመው የአየር ጥቃት ስደተኞቹ ላይ ዘግናኝ የሚባል ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።
በአሜሪካ የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም በተባለው የአየር ጥቃት የሞቱት አጠቃላይ 68 ሰዎች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ኢትዮጵያውያኑ ምን ያክል መሆናቸውን ዘገባው ያለው ነገር የለም፤ በመጠለያው ማዕከል ላይ 115 ስረተኞች ይኖሩ ነበር ሲል ገልጿል።
አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ባለሥልጣን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሃይል በየመን በተፈጸመው ጥቃት በሲቪሎች ላይ የደረሰውን ጉዳት እንደሚያውቅ እንደነገሩት ሮይተርስ በዘገባው አስታውቋል።

ዜና፡ የንግድ ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ ከ250 ሺህ በላይ ነጋዴዎች መቀጣታቸውን ሚኒስቴሩ አስታወቀ
ዘንድሮ በተጀመረው የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መሠረት ከመጠነኛ ስህተት እስከ ከባድ የንግድ ጥሰት ያከናወኑ ከ250 ሺህ በላይ #ነጋዴዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጋቸውን ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) በነጋዴዎች የተወሰደው የንግድ ፈቃድ እየዋለ ያለው ለምን አይነት ተግባር ነው በሚል የንግድ ፈቃድ ቁጥጥር (ኢንስፔክት) መደረጉን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል፡፡
በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሚሆን የንግድ ማኅበረሰቡ ላይ የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን ማከናወን ተችሏል ብለዋል፡፡
የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን ሥራ ከፍቃድ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮችን ማስተዋል ተችሏል ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዚህም ከ250 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል ሲል ሚኒስትሩ ገልትሰዋል፡፡
ድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን የሚደረገው ዋናው ምክንያት አጭበርባሪነት፣ ሌብነትን እና በዚህ ደረጃ የሚደረጉ የንግድ ማጭበርበሮችን ማስወገድ ስለሚያስችል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
እንደ ሚኒስትሩ ካሣሁን (ዶ/ር) ገለጻ፤ ይህ አሠራር በ2016 በጀት ዓመት ላይ ያልነበረ እና በ2017 በጀት ዓመት ላይ የተከልነው የንግድ ፈቃድ ኢንስፔክሽን የተወሰዱት ፈቃዶች ለምን አገልግሎቶች እየዋሉ ነው የሚለውን የመለሰ ትልቅ ሥራ ነው። ይህ የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን ሥራ ከፈቃድ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ዜና: #በኢትዮጵያ የከተማ ወባ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሶስት ከተሞች ላይ ያተኮረ የምርምር ፕሮጀክት ተጀመረ
#በጅጅጋ፣ #ሰመራና #ሎጊያ ከተሞች አደገኛ የከተማ ወባ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችል፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የምርምር ፕሮጀክት ተጀመረ።
የጥናት ፕሮጀክቱ ለሶስት አመታትን እንደሚካሄድ የተጠቆመ ሲሆን ከሰሜን #አሜሪካ ኤምሪ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ምርምሩን በዋናነት የሚያካሂዱት፣ የአዲስ አበባ እና ጅጅጋ ዩንቨርስቲዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ ከጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘው የሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ይካሄዳል የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያ አደገኛ የሆኑ የከተማ ወባ አማጪ ትንኞችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ርካሽ የሆነ ዘዴን ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑ የጀርመን ድምጽ ባስደመጠው ዘገባ ጠቁሟል።
ከጣቢያው ጋር ቆይታ ያደረጉት በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የዚሁ ፕሮጀክት ተባባሪ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሰሎሞን ያሬድ እንደተናገሩት ባለው ነባራዊ የቁጥጥር ዘይቤ፣ የትንኝ ዕጭ ቁጥጥር የነበረው፣ የብዙ የሰው ኃይል የሚያስፈልገው እና ወጭውም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ለመለየት ቀልጣፋና ትክክለኛ የሆነ መረጃን መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ በማዋል ስርጭቱን ለመቆጣጠር መታሰቡን አመልክተዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የዚህ ፕሮጀክት ሌላኛው ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር አርአያ ገብረሥላሴ በበኩላቸው "ኢኖሬሌስ ስቴፌንሲ" የተሰኘችው የወባ ትንኝ በተለይም በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙ ከተሞች መስፋፋቷን ገልጸዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0C4BPZCwu5CcwsHMHxhf4CyUWnkNmij9NDQQTrzhpkvJWBEa2QSqNzH4ARp9zvzCEl

በፎቶ፤ በ #ጁቡቲ የ #ኢትዮጵያ ኢምባሲ በፍቃደኝነት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የሚሹ ዜጎችን እየመዘገበ መሆኑን ገለጸ
የጂቡቲ መንግስት በህገ-ወጥ መንገድ በጂቡቲ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ለቀው እንዲወጡ መመሪያ መስጠቱን ተከትሎ በጁቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በፍቃደኝነት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የሚፈልጉ ዜጎችን እየመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።
የሀገሪቱ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዚያ 24 2017 ዓ/ም ድረስ በፍቃደኝነት እንዲወጡ፤ ይህን የማይከተሉ ከሆነ በሀይል እንዲወጡ እንደሚደረግ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከጁቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ባደረገው የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ቀነ ገደቡ እንዲራዘም ያቀረበው ጥሪ አለመሳካቱን ገልጿል።