ቴክኖ የመጀመሪያ ኤአይ አጋዥ ቴክኖሎጂውን በ #አዲስ_አበባ አስተዋወቀ
ቴክኖ ቋንቋን መተርጎም፣ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየርን ጨምሮ ተያያዥ ስራዎችን በማከናወን የለት ዕልት ክንውንን ያቀላሉ ያላቸውን ኤአይ አጋዥ ቴክኖሎጂን በአዲስ አበባ አስተዋወቀ።
ኩባንያው ትናንት ባዘጋጅው የኤአይ መርሓ ግብር የቴከኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊከ ቴክኖ #ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚናን እየተጫወተም እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ቴክኖ ኢትዮጵያም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እንዲሁም ማህበረሰቡ አለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመድ መትጋቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
አዲሱ የቴከኖ ኤ አይ አጋዥ ቴከኖሊጂ የዕለት ተዕለት ኑሩን በእጅጉ ከማቅለሉም በላይ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመከወን የሚያስችል አጋዥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴከኖሎጂን ተካቶለታል ተብሏል፡፡
የቴኖሎጂ ኤክስፐርቱና የቴክ ፕሮግራም አዘጋጅ አቶ ሰለሞን ካሳ ስለ ኤአይ( ሰው ሰራስ አስተውሎት) የሰዎችን ህይወት በማቅለል ረገጅ ያላቸው ጠቀሜታነት ቀላል አለመሆኑን ተናግረዋል። ለአብነትም ሰዎች የሚመገቡትን ምግብ የካሎሪ መጠን በቴክኖ ኤአይ አጋዥ ቴክኖሎጂ ማወቅ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ቴከኖ ለዓለም ያስተዋወቀው የቴከኖ ኤ አይ አጋዥ ቴክኖሎጂው በአዳዲሶቹ የፋንተም V2 ስልኮች ላይ መካተታቸው ተገልጿል።

የ #አንካራ ስምምነትን ተከትሎ የ #ሶማሊያ ልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ #አዲስ_አበባ ይገባል
በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር የተመራ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጉብኝቱ በአንካራው ስምምነት መሰረት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲል የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የልዑካን ቡድኑ በጋራ ጥቅም እና ትብብር ላይ የተመሰረተ አጋርነት ለመፍጠር የለውጥ ዕድሎችን በማሰስ ላይ እንደሚያተኩር ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የሶማሊያ መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሉዓላዊነት እና በግዛት አንድነት መርሆዎች ላይ የጸና ግንኙነት ለመፍጠር ባለው ራዕይ ቁርጠኛ መሆኑ ተመላክቷል።
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በባሕር በር ሳቢያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ታህሳስ 2/ 2017ዓ/ም በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በአንካራ ስምምነት መፈጸማቸው ይታወሳል።

#ኢትዮጵያ የአንካራውን ስምምነት ‘ሙሉ በሙሉ’ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች
ከአንካራው ስምምነት በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝታቸው በ#አዲስ_አበባ እያደረጉ ከሚገኙት የ #ሶማሊያ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት መደረጉን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኢትዮጵያ የአንካራውን ስምምነት ‘ሙሉ በሙሉ’ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጹ።
የሶማሊያ የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር እና አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በዛሬው ዕለት ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል በተርክ አሸማጋይነት ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም የተፈረመውን ስምምነት ተግባራ ለማድረግ ተስማምተዋል።
በተጨማሪም ሚኒስትር ደዔታዎቹ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር መስማማታቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የሶማሊያ ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ሽብርተኝነትን በመከላከል በቀጣናው ሰላም ለማስፈን ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። አክለውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።
የሶማሊያ የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር ከወንድሜ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ማለታቸው ተገለጿል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እልባት ለመስጠት በተርክዬ አሸማጋይነት ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የአንካራውን ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐመድ በአንካራ መፈረማቸው ይታወሳል።

ዜና፡ ግዙፉ የ #ቻይና ኤሌክትሪክ መኪና አምራች ቢዋይዲ በ #ኢትዮጵያ በአምስት የኤሌክትሪክ ሞዴሎችን ለሽያጭ አቀረበ
የቻይናው የመኪና አምራች ቢዋይዲ (BYD) አምስት የኤሌክትሪክ ሞዴሎችን በማቅረብ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በይፋ መግባቱን አከፋፋዩ ሞኤንኮ አስታውቋል።
በኤሌክትሪክ ተስከርካሪ አምራችነት ዘርፍ ታዋቂ የሆነው ኩባንያው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የመኪና አከፋፋዮች አንዱ ከሆነው ሞኤንኮ ጋር በመተባበር ወደ ገበያ መግባቱን በ #አዲስ_አበባ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ አስታውቋል።
በተጨማሪም ቢዋይዲ ለደንበኞቹ የመኪና ሽያጭ እና የጥገና አገልግሎቶችን ለማቅረብ በአዲስ አበባ #ቃሊቲ ማሳያ ክፍልና የድህረ ሽያጭ አገልግሎት ማዕከል ከፍቷል። #መገናኛ አካባቢም አዲስ የተሽከርካሪ ማሳያ ክፍል በይፋ መክፈቱን አስታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6276

Addis standard
ግዙፉ የቻይና ኤሌክትሪክ መኪና አምራች ቢዋይዲ በኢትዮጵያ በአምስት የኤሌክትሪክ ሞዴሎችን ለሽያጭ አቀረበ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16/ 2017 ዓ/ም፦ የቻይናው የመኪና አምራች ቢዋይዲ (BYD) አምስት የኤሌክትሪክ ሞዴሎችን በማቅረብ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በይፋ መግባቱን አከፋፋዩ ሞኤንኮ አስታውቋል። በኤሌክትሪክ ተስከርካሪ አምራችነት ዘርፍ ታዋቂ የሆነው ኩባንያው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የመኪና አከፋፋዮች አንዱ ከሆነው ሞኤንኮ ጋር በመተባበር ወደ ገበያ መግባቱን በአዲስ አበባ በተካሄደው የማስጀመሪያ…
ቢሮው በመዲናዋ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ያለታሪፍ ጭማሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ አሳሰበ
በ #አዲስ_አበባ ከተማ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ያለታሪፍ ጭማሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ባካሄደው 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ የትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ እንዲሰጥ እና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ መወሰኑ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በውሳኔው መሠረት አውቶቡሶች፣ ሚድ ባስ እና ሚኒ ባሶች መደበኛ በሚሰሩበት መስመርና ቀን ላይ በሚከፈለው ሕጋዊ ታሪፍ መሠረት አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስቧል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይህን በሚገባ በመረዳት እስከምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ በመግለጽ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እና የሚመለከታችሁ አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላችሁን ሚና እንዲወጡ ጠይቋል፡፡
=================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

#አዲስ_አበባ ድረስ ንዝረት ያስከተለ ተደጋጋሚ የ #አዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጥ ቤቶችና መንገድ ላይ ጉዳት አደረሰ
ባሳለፍነው ቅዳሜ እና ዕሁድ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች በሬክተር ስኬል 5 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ መኖሪያ ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና በመንገዶች እንዲሁም ማሳዎች ላይ የመሰነጣጠቅ ሁኔታ መከሰቱን ተገልጿል።
በዚህም ጉዳት በደረሰባቸው እና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
በአካባቢው ያለው የቅልጥ ዓለት ድንጋይ (ማግማ) እንቅስቃሴ አሁንም በመቀጠሉ በአዲስ አበባ ድረስ የመሬት ንዝረት ያስከተለ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እንዲከሰት ማስቻሉን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም ተናግረዋል።
በዚህም ቅዳሜ ረፋድ 4 ሠዓት ከ43 ላይ በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን ትናንት እሁድ ማለዳ 12 ሠዓት ከ57 ላይ 4 ነጥነብ 9 እንዲሁም በዚሁ ዕለት ምሽት 2 ሠዓት ገደማ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን እና ሌሎችም ክስተቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አደጋው በዚህ ቀን ይከሰታል ወይም አይከሰትም ማለት ስለማይቻል፤ የአካባቢው አሥተዳደርም ሆነ ሕብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ማድረግ እንዳለበት ተመላክቷል

የ #አዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሬት መንቀጥቀጥ ቅድመ ጥንቃቄ የሚረዱ ጥናቶችን ለማድረግ የባለሙያዎች ግብረ ሃይል ለማደራጀት ተስማማ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭነት ያላት በመሆኑ የቅድመ ጥንቃቄ የሚረዱ ጥናቶችን ለማድረግ የባለሙያዎች ግብረ ሃይል ለማደራጀት መስማማቱን አስታወቀ።
አስተዳደሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም እንዲሁም ከጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከመጡ ምሁራን ጋር ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች ስለተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ንዝረት እንዲሁም አጠቃላይ ስርጭቱን በተመለከተ ትናንት ተወያይቷል።
በውይይቱ ወቅት ምሁራኑ ባቀረቡት ጥናቶቾች በአዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት በአፋር እና አካባቢው እያጋጠመን ካለዉ የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳ የመሬት ንዝረት እያጋጠመ መሆኑን እና ንዝረቱ ሲያጋጥም መደናገጥ እና መረበሽ ሳያስፈልግ በባለሙያዎች የሚሰጡት ምክር በመከታተል መረጋጋት እንደሚገባ ማስረዳታቸውን የከተማ አድተዳደሩ መረጃ አመላክቷል።
በዚህም የባለሙያዎች ግብረ ሃይል በማደራጀት ተገቢውን ጥንቃቄ ከወዲሁ ለማድረግ እንዲያስችል ለአንዳንድ ቅድመ ጥንቃቄ የሚረዱ ጥናቶችን ለማድረግ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።
ሰሞኑን ንዝረቱ አዲስ አበባ ድርስ የሚሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቋል። ቅዳሜ ዛሬ ሌሊት 9:52 ሰዓት ላይ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአቦምሳ የተከሰተ ሲሆን ይህም በመዲናዋ በርካታ አካባቢዎች ከፍ ያለ ንዝረትን አስከትሏል።

የ #አዲስ_አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ካሉት 41 ባቡሮች እየሠሩ ያሉት 16ቱ ብቻ እንደሆኑ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ወደ ስራ ሲገባ 41 ባቡሮች የነበሩት ቢሆንም አሁን አገልግሎት እየተሰጡ ያሉት ባቡሮች ቁጥር 16 ብቻ ነው ሲሉ የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብርሀን አበባው ለጋዜጣ ፕላስ ገልጸዋል፡፡
ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባቡሮች አገልግሎት የማይሰጡት በብልሽት ምክንያት መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።
ባቡሮቹ ብልሽት በሚያጋጥማቸው ጊዜ የጥገና ዕቃዎች ገበያ ላይ የሉም ያሉት ኃላፊው፤ ችግሩን ለመፍታት ከአንዱ ባቡር እየተነቀለ ወደ ሌላኛው ሲገጠም መቆየቱ ተናግረዋል።
የባቡሮቹን ሶፍትዌር ለመጠቀም ፍቃድ አለመኖሩም ለባቡሮቹ መቆም ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተበላሽተው የቆሙ ባቡሮችን ወደ ስራ ለማስገባት፣ የተሻለ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ዘርፉ አሁን ካለበት የውጤት መቀዛቀዝ ለማውጣት የሪፎርም ስራዎች መጀመራቸውን አብራርተዋል፡፡
በዚህም እስከ መጪው ሰኔ ድረስ አምሥት ባቡሮች ወደሥስራ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የሁለት ባቡሮች የጥገና ስራ መጠናቀቁን ጠቁመው፤ እነኝህ ባቡሮች በቀጣይ ሶስት ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ አብራርተዋል።
(ኢፕድ)

በ #አዲስ_አበባ ከ88 ሺ በላይ ህገወጥ ማስታወቂያዎችን የለጠፉ ተቋማትና ሌሎች ደምቦችን የተላለፉ ግለሰቦች መቀጣታቸው ተገለጸ
በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት ከ27ሺ በላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች፣ ከ88 ሺ በላይ ህገ ወጥ ማስታወቂያዎችን የለጠፉ ተቋማት እና ከ2400 በላይ ህገወጥ ግንባታዎች ያከናወኑ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገለጸ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በእነዚህና በሌሎች ደንብ ጥሰቶች በተወሰደ እርምጃም ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸው፤ በቀጣይ የደንብ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ላይ ባደረገው ግምገማ ላይ የተገኙት አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው፤ በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ግንባታን የሚመጥን የህግና ህግ ማስከበር የሚችል ተቋም የመገንባት ስራው በትኩረት እየተሰራበት ነው ብለዋል።
ተቋሙ ከጊዜ ወደጊዜ የመፈጸም የማስፈፀም አቅሙ እየጨመረ መምጣቱን ያነሱት ቢሮ ሀላፊዋ፤ የደንብ ጥሰትን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር እያከናወነ ያለው” አበረታችና የከተማዋን የልማት እንቅስቃሴ የሚመጥን ነው” ብለዋል።
አክለውም በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚገኙ የመጠጥ፣ የጫት፣ የሺሻ ቤቶችና ሌሎችንም ህገወጥ ተግባር በማከናወን ላይ የሚገኙ ከ3400 በላይ ደንብ ተላላፊዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል። እየተከናወኑ የሚገኙ ህግ የማስከበር ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉም የቢሮ ሀላፊዋ አመላክተዋል።

የባለቤቱን አካላት በመቆራረጥ የተከሰሰው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
በ #አዲስ_አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ባለቤቱን በመግደል አካላቷን “አድቅቆ በመቆራረጥ” ሽንት ቤት ውስጥ በመጨመር ወንጀል የተከሰሰው ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ግለሰቡ ወንጀሉን የፈጸመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ ሲሆን ባለቤቱን በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን ስታ እንድትሞት ማድረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ተከሳሹ ሟችን እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት "አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ መቆራረጡን" ሚኒስቴሩ በመግለጫው ገልጿል።
በተጨማሪም "ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ” ሽንት ቤት ውስጥ በመጨመር የቆረጠውን እግሯ ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ አስቀምጧል ብሏል።
በመቀጠልም እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኋላ ለ15 ቀናት ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቷል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0etG7kJMDGF29xYi14nM1tPo939vKXnwTaf2KfkDA6YbmJQpKBvujzNSmTMAisZLul

ቢሮው አመራሮችን ጨምሮ ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑ የመንግስት ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሊያጣራ መሆኑን ገለጸ
የ #አዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት ቢሮ የሠው ሀብት ሥራ አመራር ዘርፍ አመራሮችን ጨምሮ ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑ የመንግስት ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ ሊያከናውን መሆኑን አስታወቀ።
በቢሮው የሰው ሀብት ሥራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መላኩ ታምሩ በከተማ አስተዳደሩ ከ90 ሺህ በላይ የሚሆነው የመንግስት ሠራተኛ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም በየጊዜው የሚታየውን የሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ መበራከትን ለማስቀረት ከተቋማት ጋር በመቀናጀት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ሥራው በአፋጣኝ እንደሚጀመር ቢሮው የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ ለማከናወን ከተቋማት ከተውጣጡ የሠው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተሮች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ተናግረዋል፡፡
የቢሮው የሠው ሀብት ክትትል፣ ድጋፍና ኦዲት ዳ/ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን በበኩላቸው በተቋማት የሚገኙ የሥራ ሂደቶች በትክክለኛ መልኩ የተማረ የሠው ኃይል መያዛቸውን ለማረጋገጥ የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት የማረጋገጥ ሥራ በልዩ ትኩረት እንደሚከናወን መግለፃቸውን ከቢሮው የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ባሳለፍነው አመት ግንቦት ወር የትምህርት ማስረጃ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ከተሠራላቸው 10 ሺህ 238 ሰራተኞች መካከል ትክክለኛውን መስፈርት ያሟሉ 1 ነጥብ 6 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ማስታወቁ ይታወቃል።

#ኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ድርጅቶች በ #አዲስ_አበባ ውይይት ማካሄዳቸው ተገለፀ
የኤርትራ መንግሥትን ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ሰኞ ጥር 19 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።
በውይይቱ ላይ እስከ “ሁለት ሺህ እና ከዚያም በላይ” የሚሆኑ ኤርትራዊያን መሳተፋቸውን ከተሳታፊ ድርጅቶች አንዱ ለዶቼ ቬለ ገልጿል።
የተደረገውን ውይይት በተመለከ “የኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅና ሳይኖረው አልሆነም” ሲሉ የኤርትራን መንግሥት ለመለወጥ የሚንቀሳቀሰው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ የሱፍ አብደላ ተናግረዋል።
አቶ የሱፍ አብደላ የፖለቲካ ትግላቸው ማጠንጠኛ የኤርትራ መንግሥት ኤርትራ ውስጥ በሚገኙ አፋሮች ላይ የሚፈጽመው ያሉትን "በደል" እና "ግፍ" ማስቀረት ነው። ለዚህም ሲባል የኤርትራ መንግሥትን ከሌሎች የኤርትራ "ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ለመቀየር" ከኤርትራ ውጪ እንደሚንቀሳቀስ እና በትግል ላይ የሚገኙ መሆኑን ገልፀዋል።
"ሰማያዊ ማዕበል" የሚባለው ንቅናቄ ያዘጋጀው በተባለው በዚህ "ሴሚናር" ወይም ውይይት ላይ ከተለያየ የዓለም ክፍል የተውጣጡ ኤርትራዊያን የተሳተፉበት መሆኑን መግለጻቸውን ዶቼ ቬለ ዘግቧል።

ቢሮው ተገቢ ባልሆነ ቦታ ላይ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን ለማስተካከል መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ገለጸ
በሀገሪቱ ተገቢ ባልሆነ ቦታ ላይ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን ለማስተካከል እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የ #አዲስ_አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።
የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው የአደባባይ ስብከቶችን በሚገባቸው ሐይማኖታዊ ቦታዎች እንዲደረጉ ከሐይማኖት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሐይማኖታዊ ነጻነትን በማይጋፋ እና ህገ ወጥነትን መከላከል በሚያስችል መልኩ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
አቶ ገብሬ ዳኘው ይህን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል።
አማካሪው በወቅቱ እንደተናገሩት በመዲናዋ ተገቢ ባልሆነ ቦታ ላይ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን መቀነስ ችሏል።
ለአብነትም በ #ሜክሲኮና በ #መገናኛ አደባባዮች የሚደረጉ ስብከቶች ላይ በተከታታይ የግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም መታረም የሚገባቸውን በማረም የችግሩ መጠን ከነበረበት ቀንሷል ብለዋል።
በመመሪያ ማውጣቱ ሂደት ቢሮውን ጨምሮ የሐይማኖት፣ የተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙበትም አክለው አስረድተዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
በሀገሪቱ ተገቢ ባልሆነ ቦታ ላይ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን ለማስተካከል እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የ #አዲስ_አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።
የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው የአደባባይ ስብከቶችን በሚገባቸው ሐይማኖታዊ ቦታዎች እንዲደረጉ ከሐይማኖት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሐይማኖታዊ ነጻነትን በማይጋፋ እና ህገ ወጥነትን መከላከል በሚያስችል መልኩ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
አቶ ገብሬ ዳኘው ይህን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል።
አማካሪው በወቅቱ እንደተናገሩት በመዲናዋ ተገቢ ባልሆነ ቦታ ላይ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን መቀነስ ችሏል።
ለአብነትም በ #ሜክሲኮና በ #መገናኛ አደባባዮች የሚደረጉ ስብከቶች ላይ በተከታታይ የግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም መታረም የሚገባቸውን በማረም የችግሩ መጠን ከነበረበት ቀንሷል ብለዋል።
በመመሪያ ማውጣቱ ሂደት ቢሮውን ጨምሮ የሐይማኖት፣ የተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙበትም አክለው አስረድተዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ፖሊስ “በደንብ መተላለፍ” ያሰራቸውን ግለሰቦች በደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነፍስ ወከፍ 2 ሺህ ብር እንዲቀጡ ማደረጉን ገለጸ
የ #አዲስ_አበባ ፖሊስ ትናንት ባወጣው መግልጫ “በደንብ በመተላለፍ” ህገ ወጥ ተግባር ሲፈፅሙና ሲያስፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነፍስ ወከፍ 2 ሺህ ብር እንዲቀጡ ማደረጉን ገለጸ።
ፖሊስ በመግልጫ በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች ሰሞኑንም የወንጀል መንስኤ እና የህብረተሰቡ የፀጥታ ስጋት የሆኑ አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ቤቶች ውስጥ የተገኙ ግለሰቦች በሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል ብሏል።
በተጨማሪም በህጋዊ የንግድ ሽፋንን ለህገ ወጥ ተግባር በማዋል ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም አዋኪ ድርጊት ሲፈፀምባቸው የተገኙ የተለያዩ ሆቴሎች፣ ቪላ ቤቶች፣ የሌሊት ጭፈራ ቤቶች እና ሌሎች የንግድ ተቋማት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ማህበራዊ ድረ ገፆች “ፖሊስ የደህንነት ስጋት ትፈጥራላችሁ በሚል የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለ አግባብ ካሰረ በኋላ በነፍስ ወከፍ ያለ ደረሰኝ 2 ሺህ ብር በጉቦ መልክ እየተቀበለ እንደሚለቅ በመግለጽ” የተሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም ሲል አስተባብሏል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0at65jfJAfPzYDgUZyDCCyE4882b1kLZiWU2dYRHEWHXzXVmEByGdDnBwTYCE1Xt3l

የ #ኢሕአፓ አባልና የአዲስ አበባ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ይሳቅ ወልዳይ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ፓ) አባል እና የ #አዲስ_አበባ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ይሳቅ ወልዳይ፣ ትናንት የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ።
አቶ ይሳቅ ወልዳይ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች የተያዙበት ምክንያት እስካሁን እንዳልተነገራቸውም ፓርቲው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።
በተጨማሪም ኢሕአፓ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ፤ የፓርቲው አባል አቶ ይሳቅ ከዚህ በፊት“ከመንግሥት ጋር ቁርኝት ባለው ግለሰብና ማንነታቸው ካልታወቁ ተባባሪዎች ጋር በአዲስ አበባ ተይዘው ለሰዐታት ታስረው መለቀቃቸውን” አስታውሷል።
“ዛቻዎችም እንደደረሰባቸው” የገለጸው ድርጅቱ፤ “ብልጽግ ፓርቲና መንግሥት ዜጎችን በማሰር፣ በማሰቃየትና በመሰወር ድርጊት” ወቅሷል። ይህም ድርጊት የሰበዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ደጋግመው ያረጋገጡት “ዛሬ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩት ዕውነታ ነው” ብሏል።
“በሰበብ አስባቡ ዜጎችን ማሰር፣ ጥቃት ማድረስ፣ የመጻፍና የመናገርን መብት መግፋት እንዲሁም በሕጋዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ላይ የሚደርሰው እስር” እንዲያበቃ ያሳሰበው ፓርቲው አባሉ አቶ ይሳቅ ወልዳይ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ፓ) አባል እና የ #አዲስ_አበባ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ይሳቅ ወልዳይ፣ ትናንት የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ።
አቶ ይሳቅ ወልዳይ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች የተያዙበት ምክንያት እስካሁን እንዳልተነገራቸውም ፓርቲው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።
በተጨማሪም ኢሕአፓ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ፤ የፓርቲው አባል አቶ ይሳቅ ከዚህ በፊት“ከመንግሥት ጋር ቁርኝት ባለው ግለሰብና ማንነታቸው ካልታወቁ ተባባሪዎች ጋር በአዲስ አበባ ተይዘው ለሰዐታት ታስረው መለቀቃቸውን” አስታውሷል።
“ዛቻዎችም እንደደረሰባቸው” የገለጸው ድርጅቱ፤ “ብልጽግ ፓርቲና መንግሥት ዜጎችን በማሰር፣ በማሰቃየትና በመሰወር ድርጊት” ወቅሷል። ይህም ድርጊት የሰበዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ደጋግመው ያረጋገጡት “ዛሬ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩት ዕውነታ ነው” ብሏል።
“በሰበብ አስባቡ ዜጎችን ማሰር፣ ጥቃት ማድረስ፣ የመጻፍና የመናገርን መብት መግፋት እንዲሁም በሕጋዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ላይ የሚደርሰው እስር” እንዲያበቃ ያሳሰበው ፓርቲው አባሉ አቶ ይሳቅ ወልዳይ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ የ #አዲስ_ አበባ ገቢ ያለ ታክስ ሬት ጭማሬ በሰባት አመታት ውስጥ በስምንት እጥፍ መጨመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ
ከንቲባ አዳነች አቢቤ የአዲስ አበባ ገቢ ባለፉት ሰባት አመታት ስምንት እጥፍ መጨመሩን ገለጹ። ይህ እድገት የተገኘው "የትኛውንም አይነት ታክስ ሬት ሳይጨመር" በተደረጉ ጥረቶች ነው ብለዋል።
ከንቲባዋ ትናንት የካቲት 12 ባካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም አራተኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ከሰባት አመት በፊት የከተማዋ በጀት 30 ቢሊዮን ብር ከነበርበት ዛሬ ላይ በ6 ወራት ብቻ 111.5 ቢሊዮን መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል። ይህም የሆነው የግብር ምህዳሩን በማስፋት የታክስና የኦዲት አሰራርን በማዘመን ነው ብለዋል።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት በአጠቃላት 125.5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከዚህ ውስጥ 111.5 ቢሊዮን ብር ማለትም ከታሰበው 90 በመቶ በተሳካ ሁኔታ ተሰብስቧል።
ይህ እድገት የታየው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ላይ የተሻሻለ የግብር መጠን ተግባራዊ ካደረገ ከአንድ ዓመት በኋላ ሲሆን ይህም በቤት ባለቤቶች መካከል ሊፈጥር ስለሚችለው የገንዘብ ተፅእኖ ሰፊ ክርክር እና ስጋት አስነስቷል።
ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6931

የአዲስ አበባ ገቢ ያለ ታክስ ሬት ጭማሬ በሰባት አመታት ውስጥ በስምንት እጥፍ መጨመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13/ 2017 ዓ/ም፦ ከንቲባ አዳነች አቢቤ የአዲስ አበባ ገቢ ባለፉት ሰባት አመታት ስምንት እጥፍ መጨመሩን ገለጹ። ይህ እድገት የተገኘው “የትኛውንም አይነት ታክስ ሬት ሳይጨመር” በተደረጉ ጥረቶች ነው ብለዋል። ከንቲባዋ ትናንት የካቲት 12 ባካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም አራተኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ከተማዋ ከፍተኛ የበጀት ማስፋፊያ ማድረጓን…
የ #ናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ጉባዔ በ #አዲስ_አበባ ተካሄደ
የ #ግብፁ የውሀ ሚኒስትር ሀኒ ሳሁሌ እና ሌሎች የተፋሰሱ የአባል ሀገራት ሚኒስትሮች የተሳተፉበት የናይል ተፋሰስ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ጉባዔ ትናንት የካቲት 14 ቀን በአዲስ አበባ ተካሄዷል።
በጉባዔው የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን ስለሚቋቋምበት አግባብ፣ በተፋሰስ አገራቱ የልማት ትብብር እና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጓል ተብሏል፡፡
በጉባዔው ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) የሚቋቋመው የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን ለአባል ሀገራቱ የጋራ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
አክለውም ኮሚሽኑ የተፋሰሱ ሀገራት የልማት ትብብር በህግና ስርዓት እንዲመራ ከማድረጉ በተጨማሪ ለጋራ ጥቅም የሚውሉ ተጨማሪ ግድቦችን ለመስራት እድል እንደሚከፍት ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ አጠቃቅምና ቀጣናዊ የጋራ ብልጽግና መረጋገጥ የማይናወጥ አቋም አላት ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ፍሎሬንስ አዶንጎ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የጉባዔው ቁልፍ ጉዳይ የተፋሰሰ ሀገራቱን የልማት ትብብር ማጠናከር ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም በጉባዔው የተፋሰሱ ሀገራት በጋራ ለመልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን መግለጻቸው በዘገባው ተመላክቷል።
19ኛው የናይል ቀን የናይል ቤዚን ኢኒሺዬቲቭ አባል ሀገራት በተገኙበት ከዛሬ ጅምሮ በአዲስ አበባ በሳይንስ ሙዚየም እንደሚከበር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አስታውቋል።

ዜና፡ የተሻሻለው የ #ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግሥት ተፈጻሚ እንዳይሆን የጠየቁ ክልሉ የምክር ቤት አባል በቁጥጥር ስር ዋሉ
በቅርቡ የተሻሻለው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግስት ተፈጻሚ እንዳይሆን አቤቱታ ያሰሙት በክልሉ ምክር ቤት የተቃዋሚው #ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ተመራጭ አቶ ዮሐንስ ተሰማ ትናንት እሁድ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አቶ ቢቂላ ቦሮ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
አቶ ዮሐንስ ወደ #አዲስ_አበባ ለመሄድ በ #አሶሳ ህዳሴ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የጉዞ እገዳ ተጥሎባቸው ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ የገለጹት የፓርቲው ዋና ጸሐፊ፤ ቤታቸው ከገቡ በኋላ ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ “በክልሉ አድማ በታኝ ተይዘው” ወደ አሶሳ ወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=7165

ዜና፡ #ትግራይ ውስጥ ‘ከሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን ከሚሉ ወገኖች አንዱ የ #ኤርትራ መንግሥት ነው’ ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በ #አዲስ_አበባ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ “ትግራይ ውስጥ ከሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ፤ የኤርትራ መንግሥት አንደኛው እንደሆነ አውቃለሁ” ሲሉ ተናገሩ።
“የኤርትራ መንግሥት ከፌዴራል መንግሥት ጋር የመጀመሪያ ግጭት ውስጥ የገባው #ፕሪቶርያን ከተስማማን በኋላ ነው” ሲሉ የተለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ “ከኤርትራ መንግሥት ጋር ሰላም እንፍጠር ማለት ኤርትራ በትግራይ ላይ የፈጸመችውን ጭፍጨፋ እንካድ ማለት አይደለም” ብለዋል።
አቶ ጌታቸው፤ “ክልሉ ወደ ሌላ ጦርነት መግባት የለበትም። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ አካል ነው። የፌዴራል መንግስቱ አግባብነት ያለው ሃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል” ሲሉ ተደምጠዋል።
ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=7206

“ትግራይ ውስጥ ከሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን ከሚሉ ወገኖች አንዱ የኤርትራ መንግሥት ነው” ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ - Addis standard
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017 ዓ/ም፦ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአዲስ አበባ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ “ትግራይ ውስጥ ከሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ፤ የኤርትራ መንግሥት አንደኛው እንደሆነ አውቃለሁ” ሲሉ ተናገሩ። “የኤርትራ መንግሥት ከፌዴራል መንግሥት ጋር የመጀመሪያ ግጭት ውስጥ የገባው ፕሪቶርያን…
ዜና: ቢሮው በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ የወጣውን ደንብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምር አስታወቀ
#አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ “በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ያወጣውን ደንብ” ከዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ።
ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ደንብ በመዲናዋ ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቢያንስ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ክፍት እንዲሆኑና አገልግሎት እንዲሰጡ ያስገድዳል።
ከዛሬ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ደንቡን ለህብረተሰቡ የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል ብሏል።
“በደንቡ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ማብራሪያ በሁሉም የሚዲያ አውታሮች አማካኝነት ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው እንደሚደረግ እና ደንቡን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ” አመላክቷል።
በመዲናዋ ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቢያንስ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ክፍት እንዲሆኑና አገልግሎት እንዲሰጡ የአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መወሰኑን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።
ንግድ ቢሮው ለአስራ አንዱም ክፍለ ከተማዎች ሰኔ 7 ቀን 2016 በጻፈው ደብዳቤ፤ ለንግድ ማበረሰቡ ውሳኔውን በማስገንዘብ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ቢሮው ዛሬ ባወጣው መግለጫ የስራ ባህልን ይበልጥ ለማዳበር፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን፣ የከተማዋን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ቀን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በምሽት የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ደንቡ መውጣቱን አስታውሷል።