ዜና፡ በከፍተኛ ሁኔታ ሰላም ከራቃቸው የአለማችን ሀገራት መካከል #ኢትዮጵያ አንዷ ነች፣ ከጎረቤቶቿ ጋር ያላት ግንኙነትም መልካም አይደለም - ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ
- ኤርትራ በአንጻራዊነት ከኢትዮጵያ በተሻለ 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
በአለም አቀፍ ደረጃ የሀገራትን የሰላም ሁኔታን በመገምገም፣ በደረጃ የሚያስቀምጠው ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ ባወጣው የ2025 አመታዊ የሀገራት የሰላም ሁኔታ አመላካች ደረጃ ኢትዮጵያ ከ163 ሀገራት መካከል 138ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣላች፤ ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገራት ናት ተብላለች።
23 መመዘኛዎችን በመጠቀም የአለም ሀገራትን ሰላማዊነት በደረጃ የሚያስቀምጠው ግሎባል ፒስ ኢንኤክስ ኢትዮጵያ በተለይም የእርስ በርስ ግጭት፣ መንግስታዊ የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ሽብር (Political Terror Scale) በሚሉ መመዘኛዎች ከአምስት ነጥብ አምስት በማምጣት የከፋ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ሲል አመላክቷል።
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ነጥብ ካስመዘገበችባቸው መመዘኛዎች መካከል ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ሲሆን ከአምስት ነጥብ አራት በማስመዝገብ ግንኙነቷ መልካም አይደለም ሲል ገልጿታል፤ በፖለቲካ አለመረጋጋት መመዘኛ ከአምስት ነጥብ አራት ነጥብ 25 በማስመዝገብ ያልተረጋጋ ፖለቲካ ያለባት ናት ብሏታል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=9032

Addis standard
ዜና፡ በከፍተኛ ሁኔታ ሰላም ከራቃቸው የአለማችን ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፣ ከጎረቤቶቿ ጋር ያላት ግንኙነትም መልካም አይደለም - ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ - Addis standard
ኤርትራ በአንጻራዊነት ከኢትዮጵያ በተሻለ 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19/ 2017 ዓ/ም፦ በአለም አቀፍ ደረጃ የሀገራትን የሰላም ሁኔታን በመገምገም፣ በደረጃ የሚያስቀምጠው ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ ባወጣው የ2025 አመታዊ የሀገራት የሰላም ሁኔታ አመላካች ደረጃ ኢትዮጵያ ከ163 ሀገራት መካከል 138ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣላች፤ ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገራት ናት ተብላለች። ኤርትራም…
ዜና: ማህበሩ ጋዜጠኞችን ለቀናት ሰውረው ያቆዩ አካላት በግልፅ እንዲታወቁ እና በሕግ ፊት እንዲቀርቡ ጠየቀ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጋዜጠኞችን ያሉበት በማይታወቅበት ሁኔታ ከ10 ቀናት በላይ ሰውረው ያቆዩ አካላት በግልፅ እንዲታወቁ እና በሕግ ፊት እንዲቀርቡ ጠየቀ።
ማህበሩ በአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 FM ሬዲዮ የቅዳሜ ገበያ ፕሮግራም አዘጋጅ ጋዜጠኛ አብዱሰመድ ከ12 ቀናት በኋላ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዮናስ ደግሞ ከ10 ቀናት ስወራ ነጻ ወጥተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ማረጋገጡን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሑፉ አስታውቋል።
ጋዜጠኞቹ ያሉበት በማይታወቅበት ሁኔታ ከ10 ቀን በላይ ተሰውረው መቆየታቸው “ሕገ ወጥ ተግባር ነው” ያለው ማኅበሩ፤ የድርጊቱ ፈጻሚዎች በግልፅ ታውቀው በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ይህን ያስታወቀው የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ እና በአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 FM ሬዲዮ የቅዳሜ ገበያ ፕሮግራም አዘጋጅ ጋዜጠኛ አብዱል ሰመድ መሀመድ እንደተለቀቁ መገለጹን ተከትሎ ነው።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=9033

ማህበሩ ጋዜጠኞችን ለቀናት ሰውረው ያቆዩ አካላት በግልፅ እንዲታወቁ እና በሕግ ፊት እንዲቀርቡ ጠየቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 19/ 2017 ዓ/ም፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጋዜጠኞችን ያሉበት በማይታወቅበት ሁኔታ ከ10 ቀናት በላይ ሰውረው ያቆዩ አካላት በግልፅ እንዲታወቁ እና በሕግ ፊት እንዲቀርቡ ጠየቀ። ማህበሩ በአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 FM ሬዲዮ የቅዳሜ ገበያ ፕሮግራም አዘጋጅ ጋዜጠኛ አብዱሰመድ ከ12 ቀናት በኋላ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዮናስ ደግሞ ከ10 ቀናት…
በትግራይ ክልል በደረሰ የመኪና አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የመኪና አደጋው የደረሰው ዛሬ ንጋት 11፡00 ላይ ሴሮ ቀበሌ ልዩ ስሙ መቐልሕ በሚባል አካባቢ እንደሆነ የወረዳው የጸጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ሻምበል ገ/ትንሳዔ ገ/ገርግስ ለፋና ዲጅታል እንዳሉት፤ አደጋው የደረሰው ከእገላ ወረዳ ወደ እንትጮ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ነው።
አውቶቡሱ ከዋናው መንገድ በመውጣት 80 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ውስጥ በመግባቱ በደረሰ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ነው ያሉት። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን ገልጸው፤ የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ ነው ብለዋል።
(ኤፍ ኤም ሲ)
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ከ #ቼክ_ሪፐብሊክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ #ኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህጻናት ሙዚየም በ #አዲስ_አበባ ሊገነባ ነው
በ #ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የህጻናት ሙዚየም በአዲስ አበባ ሊገነባ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ሙዚየሙ የቼክ ሪፐብሊክ መንግሥት በሚያደርገው የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚገነባም ተገልጿል።
ዛሬ የቼክ ሪፐብሊክ ርእሰ መዲና በ #ፕራግ በተካሄደ ስነ-ስርዓት፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳ ከቼክ ብሔራዊ ሙዚየም እና ከቼክ ዲቨሎፕመንት ኤጀንሲ ኃላፊዎች ጋር ሙዚየሙን ስምምነት ለመገንባት የሚያስችል ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት፣ ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳ እንደገለጹት፣ ሙዚየሙ ልጆች ስለ ሀገሪቱ ታሪክ እና ባህል በቀላል መንገድ እውቀት እንዲያገኙ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ፣ በፈጠራ፣ በትምህርት እና በእውቀት እንዲጎለብቱ እድል ይፈጥርላቸዋል ። ለሙዚየሙ ግንባታ የሚያስፈልገውን የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ላደረገው የቼክ መንግሥትም ምስጋና አቅርበዋል።
ሙዚየሙ አዲስ አበባ በሚገኘው የወዳጅነት ቁጥር 2 ፓርክ ውስጥ እንደሚገነባ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል። የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ዓላማ ህጻናት የቱሪዝም ሀብቶችን እንዲያውቁና ለዘርፉ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ መርዳት እንደሆነም ተገልጿል።

በ #ጃፓን ካሳማ ከተማ ለአትሌት #አበበ_ቢቂላ የመታሰቢያ መንገድ ተሰየመ
በጃፓን ካሳማ ከተማ አትሌት አበበ ቢቂላን ለማስታወስ የግማሽ ማራቶን መንገድ በስሙ መሰየሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የስያሜ ስነ-ስርዓቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበልን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራን፣ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌን እና የካሳማ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት በተገኙበት ተከናውኗል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ይህ የመታሰቢያ ስያሜ ለአትሌቱ ክብር ከመስጠት በተጨማሪ በኢትዮጵያ እና በጃፓን መካከል ያለውን ጥብቅ ወዳጅነት እና የባህል ትስስር የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል።
አትሌት አበበ ቢቂላ በ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ያገኘው ድል ኢትዮጵያን ያስጠራ ብቻ ሳይሆን በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነትም አጠናክሯል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አምባሳደር ደባ ደበሌ በበኩላቸው ጃፓናውያን ይህንን ቀን ለዘመናት እንደሚያስታውሱ እና የአትሌት አበበ ቢቂላ ድል በጃፓን ማህበረሰብ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንዳለው መግለጻቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የካሳማ ከተማ ከንቲባ ሻንጁ ያማጉቺ ይህ የመታሰቢያ መንገድ በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

ዜና: በጎርፍ ተወስዶ ላለፉት 11 ቀናት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ የነበረው የጌደብ ወንዝ ድልድይ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ተገለጸ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ በጎርፍ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የጊደብ ወንዝ ድልድይ በተገጣጣሚ ብረት ድልድይ እንደገና ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ሃላፊ ዶ.ር ጋሻው አወቀ ገለጹ።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከፍተኛ የቴክኒክ ቡድን እና የደብረማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ባለሞያዎች በጋራ በመሆን በተገጣጣሚ የብረት ድልድይ የመልሶ ግንባታ ስራው መጠናቀቁን የገለጹት ሃላፊው አክለውም ላለፉት 11 ቀናት ተስተጓጉሎ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ከነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መስተካከሉን ተናግረዋል።
አያይዘውም ለመልሶ ግንባታ ስራው መሳካት የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር አካላት፣ የ403ኛ ክፍለጦር የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እና የአካባቢው ጸጥታ አካላት ላደረጉት ሁሉ አቀፍ ትብብር እንዲሁም አሽከርካሪዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ለስራው መፋጠን ላሳዩት ትዕግስት ምስጋና አቅርበዋል።
በተጨማሪም አሽከርካሪዎች አላስፈላጊ እሽቅድድምን እንዲያስቀሩ እና፣ ድልድዩ መሸከም የሚችለው 40 ቶን ክብደት ድረስ በመሆኑ እና ሁለት ተሽከርካሪ በአንድ ጊዜ ደርቦ ማስተላለፍ ስለማይችል በመጠባበቅ እና ፍጥነት በመቀነስ እንዲያሽከረክሩ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በደብረ ማርቆስ ባህር ባሕር ዳር መስመር አማኑኤል ከተማ የሚገኘው የጌደብ ወንዝ ድልድይ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት በጮቄ ተራራ ዙሪያ የጣለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ መፍረሱን መዘገባችን ይታወሳል።