Addis Ababa Police Official
13.7K subscribers
3.77K photos
5 videos
561 links
Addis police
Download Telegram
ሎተሪ ደርሶናል በማለት ከአንዲት ግለሰብ 50 ሺብር በማታለል የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች ሊያመልጡ ሲሉ እጅ ከፈንጅ ተይዘው ምርመራው መጀመሩን የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 01 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ግለሰቦቹ በሎተሪ የማታለል ወንጀሉን በመፈጸም ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ/ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ሳዕሊት ምህረት ከሚባል አካባቢ ነው።

እንግዳ ሰው ደምሴ፣ ምንተስኖት መንበረ እና አንድነት አለሙ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ወደ የግል ተበዳይ በመቅረብ ሎተሪ ደርሶን ቅድመ ክፍያ ስላለ እሱን ክፈይልን እና ገንዘቡን ስናወጣው ለልጆችሽ ስጦታ እንሰጣችኋለን በማለት ያሳምኗታል፤ የግል ተበዳይም 50 ሺ ብር ከአዋሽ ባንክ እንድታወጣ ካደረጓት በኋላ ኮድ 1 አ/አ 30514 በሆነ ታክሲ ተሽከርካሪ ተጠቅመው ሊያመልጡ ሲሉ ብዙም ሳይርቁ በፖሊስ እና በአካባቢው ህብረተሰብ መያዛቸውን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የላምበረት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ፈጽመው እንዳያመልጡ ህብረተሰቡ ያደረገው ትብብር የሚመሠገን መሆኑን ያነሳው ጣቢያው ከፖሊስ ጋር በመተባበር ወንጀል የተፈጸመበትን ተሽከርካሪ ተረባርቦ በማስቆም እና ተጠርጣሪዎችን አንገት ለአንገት ተናንቆ በመያዝ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረግ ተችሏል ብሏል።

የግል ተበዳይ ወደ ፖሊስ በመምጣት ክስ የመሰረተች ሲሆን በተጠርጣሪዎቹም ላይ ተጨማሪ ማስረጃ የማሰባሰብ እና ምርመራ የማስፋት ስራ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ማንኛውም ግለሰብ ለእንደዚህ ዓይነት የማታለል ወንጀሎች ተጋላጭ ላለመሆን ሎተሪ ደርሶ በአየር ላይ የሚከፈል ቅድመ ክፍያ አለመኖሩን አውቆ መሰል ጥያቄ በሚቀርብለት ወቅት ምንም አይነት ገንዘብ ባለመስጠት ይልቁንም አጠራጣሪ ጉዳይ ካጋጠመም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ወንጀልን መከላከል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
*
ዘገባ፦ ም/ሳጅን መልካሙ ዜና
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
23👍8
በአሽከርካሪነት ሙያ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ድርጅት የተሰጠውን ተሽከርካሪ በመሰወር 10 ጎማዎቹን ሸጦ የተሰወረን ግለሠብ ከእነ ግብረ አበሩ በቁጥጥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 01 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተከሳሽ ቢያብል ታረቀኝ፤ ሠለሞን በየነ ከተባለ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 መስቀል ፍላወር አካባቢ ከሚገኝ የግንባታ ድርጅት ግቢ ውስጥ ነው።

ተጠርጣሪው በድርጅቱ ውስጥ በአሽከርካሪነት ሙያ ተቀጥሮ እየሰራ ሳለ ለስራ የተሰጠውን ኮድ 3 - 32 9 19 ኢት የሆነ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ወደ አስኮ አካባቢ በመውሰድ ግምቱ ከ8መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ 10 የተሽከርካሪውን ጎማዎች እና 2 ባትሪዎችን በመፍታት ከሸጠ በኋላ ወደ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ከተማ በመሄድ ይሰወራል።

ፖሊስ ከግል ተበዳይ መረጃ በመነሳት ባደረገው ብርቱ ክትትል እና ከቢቸና ከተማ ፖሊስ ጋር በመተባበር ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ማዋልም ችሏል።

አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላም በተከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ አንድ ግብረ አበሩን እና አስሩን ጎማዎች ገዝቷል የተባለን ላመስግን ቀሬን በቁጥጥር ስር በማዋል ተሽከርካሪውን እና የተሸጡ ጎማዎችንም ማስመለስ መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።

ሦስቱም ተጠርጣሪዎች ላይ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብና የምርመራ መዝገቡንም በማደራጀት በዐ/ህግ በኩል ክስ እንደሚመሠረትም ተገልጿል።

በድርጅቶች ላይ የሚፈጸሙ መሠል የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ሠራተኞች ሲቀጥሩ በቂ እና ትክክለኛ ዋስትና ማቅረባቸው መረጋገጥ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል።
*
ዘገባ፦ ም/ሳጅን ዓለም ልጅዓለም
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
👍2214😱4
ከ250 በላይ ወጣቶችን በቅድመ ወንጀል መከላከል ዙሪያ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን የአራዳ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፒያሳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በወረዳ 01 ከወንጀል ነፃ የሆኑ በግል ስራ የተሰማሩ ወጣቶችን አደራጅቶ በማሰልጠን " ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የአካባቢያችንን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ እናደርጋለን!" በሚል መሪ ቃል ወደ ስራ አስገብቷል።

ወጣቶቹ ለአስራ አምስት ቀናት ስለ ወንጀል አስከፊነት፣ በወንጀል መከላከል እና መረጃ አሰጣጥ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በየ አካባቢያቸው ከግል ስራቸው ጎን ለጎን ወንጀልን እንዲከላከሉ አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ ማስገባቱን የፒያሳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ኢዮብ ተከተል ገልፀዋል፡፡

ፒያሳ አካባቢ የከተማዋ ዋና ማዕከል እንደመሆኗ መጠን በአካባቢው በርካታ ህዝብ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከዚህ በፊት ይፈፀሙ የነበሩ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን ከህብረተሰቡ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት መቀነስ እንደተቻለ ኃላፊው አስታውሰው፤ ወንጀልን በመከላከል ሂደት ውስጥ የህብረተሰቡ ሚና የጎላ ሲሆን በተለይ ደግሞ ወጣቶችን በማስተባበር ከወንጀል የፀዳ አካባቢ ለመፍጠር በትኩረት መስራት አስፈላጊ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ወጣቶቹም ከወሰዱት ስልጠና ስለ ወንጀል ምንነት እና አስከፊነት በቂ ግንዛቤ ያገኙ መሆኑን ገልፀው ከመደበኛ ስራቸው ባሻገር በአካባቢያቸው ወንጀል እንዳይፈፀም ከፖሊስ ጎን በመሆን ወንጀልን ለመከላከል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ዜጎች በመኖሪያቸውም ሆነ በስራ አካባቢያቸው የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen engagement application ) በመጠቀም ጭምር የመዲናችንን ሠላምና ጸጥታ አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
*
ዘገባ፦ ም/ሳጅን ፍሬወይኒ ገብረ ፃዲቅ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
👍109👎1
የይዞታ ካርታ አዘጋጃለሁ በሚል ከአንድ ግለሰብ 50ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለን የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ባለሙያ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 ሠዓት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቤተል አካባቢ ነው።

ተከሳሽ ሳምሶን ፍስሀ በክ/ከተማው የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ባለሙያ ሲሆን የግል ተበዳይ የሆኑት አቶ ባይሳ ሚልኬሳ በፍርድ ቤት በነበራቸው የፍትሐብሔር ክርክር ጉዳይ በማሸነፋቸውና ሲከራከሩበት የነበረው መሬት 397.58 ካሬ የይዞታ ካርታ እንዲዘጋጅላቸው በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ተሠጥቷል።

ግለሰቡም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ይዘው ወደ ጽ/ቤቱ ባለሙያ በመቅረብ ካርታው እንዲሠራላቸው ቢያደርጉም ባለሙያው ግን የይዞታ ካርታውን 342 ካሬ አድርጎ በመስራቱ ፍርድ ቤቱ እንዲሰራ ያዘዘው 397.58 ካሬ ባለመሠራቱ ተስተካክሎ እንዲሠራ ተለዋጭ ትዕዛዝም ይሠጣል።

የግል ተበዳይ ይህንን ተለዋጭ ትዕዛዝ በመያዝ ወደ ጽ/ቤቱ ሲመለሱ በተከሳሽ በኩል ካርታውን ለማስተካከል 50ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸው ለፖሊስ በሠጡት ጥቆማ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ሊውልም ችሏል።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ተገቢውን የምርመራ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጿል።

ሙስናን በመታገል ዜጎች መብታቸውን በገንዘብ እንዳይገዙ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት በመሆኑ ህብረተሰቡ መሠል ድርጊቶች ሲያጋጥሙት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen engagement application ) በመጠቀም ወይም በ991 ነጻ የፖሊስ የመረጃ ስልክ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
23👍17👏3