የ2017 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ የፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ
AMN - መጋቢት 30/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የ1ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ 6ኛ ክፍል ፤ የመካከለኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ 8ኛ ክፍል እና የ12ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና የሚሰጥበትን ከተማ አቀፍ የጊዜ ሰሌዳን ይፋ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የማህበራዊ የትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአንድ ጊዜ 16 መኪናዎችን ቻርጅ ማድረግ የሚያስችሉ የኤሌትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያዎች ተመረቁ
AMN - መጋቢት 30/2017 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጊዜ 16 መኪናዎችን ቻርጅ ማድረግ የሚያስችሉ የኤሌትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን አስመርቋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በአዲስ አበባ ገርጂ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ የኤሌትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ወይም ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን ስራ አስጀምረዋል፡፡
ፍሬህይወት ታምሩ ኢትዮ ቴሌኮም ህይወትን እያቀለለ እና እያዘመነ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ 16 መኪናዎችን በአንድ ጊዜ ቻርጅ ማድረግ እንደሚያስችል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አንስተዋል።
ከዚህ ባሻገር ኢትዮ ቴሌኮም ኑሮን ከማዘመን እና ከማቅለል ባሻገር የስነ-ምህዳርን ጤንነት በመጠበቅ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
በመጀመሪያው የኤሌክትሪክ መኪኖች ባትሪ መሙያ ጣቢያ እስካሁን 14 ሺህ 680 መኪናዎች ቻርጅ ማድረጋቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።
በንጉሱ በቃሉ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል ከ ብሬንትፎርድ የሚደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
AMN-ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም
አርሰናል ከአስደናቂው የቻምፒየንስ ሊግ ድል በኋላ ዛሬ በሊጉ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል፡፡ መድፈኞቹ አሁንም በሂሳባዊ ስሌት የሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ ናቸው ፡፡ ነገር ግን ሚካኤል አርቴታ የበለጠ ለቻምፒየንስ ሊጉ ቅድሚያ በመስጠት የተወሰኑ ተጫዋቾችን ሊያሳርፍ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
በተለይ ሪያል ማድሪድን 3ለ0 በረቱበት ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት የገጠማቸው ዴክለን ራይስ እና ቡካዮ ሳካ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ላይገቡ ይችላሉ ተብሏል፡፡ አርሰናል ምሽት 1፡30 የሚጀምረውን ጨዋታ ካሸነፈ ለጊዜውም ቢሆን ከሊቨርፑል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት ያጠባል፡፡
በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች 8፡30 ላይ ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ክርስታል ፓላስን ያስተናግዳል፡፡ በ52 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙት ሲቲዎች በቀጣይ ዓመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የግድ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ብራይተን ከ ሌስተር ሲቲ ፤ ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ኤቨርተን እንዲሁም ሳውዛምፕተን ከ አስቶንቪላ ይጫወታሉ፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ

የፋይዳ ልዩ ቁጥር በማጋራት የሚፈጠር ስርቆት አይኖርም
AMN-ሚያዚያ 04/2017 ዓ.ም
ባለ 12 አሀዝ የፋይዳ ልዩ ቁጥር በህይወት ዘመን አብሮ የሚቆይ የማይቀየር ቁጥር ሲሆን የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (16 አሀዝ) ቁጥር የሚባለው ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የሚቀየር ቁጥር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር አንድ ግለሰብ ትክክለኛት ለማረጋገጥ አገልግሎት የሚያገለግል ነው፡፡
ነገር ግን ይህ ቁጥር በባዮሜትሪክ መረጃ የተደገፈ ልዮነትን የሚገልፅ በመሆኑ የአንድን ሰው ፋይዳ ልዩ ቁጥር በማጋራት የሚመጣ ምንም አይነት የማንነት ስርቆት ወይም ሌላ አገልግሎት ተመሳስሎ የሚገለገልበት አግባብ አለመኖሩን ከብሄራዊ መታወቀያ ፕሮግራም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጣልያን ሴሪ አ ኢንተር ሚላን አሸነፈ
AMN- ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም
በ32ኛ ሳምንት የጣልያን ሴሪ አ መሪው ኢንተር ሚላን ድል አድርጓል። በሜዳው ሳንሲዬሮ ካሊያሪን ያስተናገደው ኢንተር 3ለ1 አሸንፏል።
አስደናቂ የውድድር ዓመት እያሳለፉ የሚገኙት ኢንተሮች ከተከታዩ ናፖሊ ያላቸውን ነጥብ ወደ ስድስት አስፍተዋል።

የታይታኒክ መርከብ ስጥመት እና "ታይታኒክ" ፊልም!
AMN-ሚያዚያ 05/2017 ዓ.ም
ግዙፏ ታይታኒክ መርከብ የሰጠመችው እ.አ.አ በ1912 ኤፕሪል 14 ነበር።
ከዛሬ 113 ዓመታት በፊት ከበረዶ ግግር ጋር ተላትማ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የሰጠመችው መርከቧ 269 ሜትር ርዝመት እና ከ47 ሚሊዮን ኪ.ግ በላይ ክብደት ነበራት።
መርከቧ በ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በ3 ዓመት ወስጥ ነበር የተገነባችው።
ታይታኒክ ከእንግሊዝ ተነስታ ወደ ኒውዮርክ ጉዞ ከጀመረች ከ4 ቀን በኋላ ነበር በዛሬዋ ዕለት እኩለ ሌሊት አካባቢ 30 ሜትር ቁመት ካለው የበረዶ ግግር ጋር የተጋጨችው።
በአደጋው ወቅት ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች መርከቧ ውስጥ እንደነበሩ ይነገራል። ከእነዚህ ውስጥ ከ1500 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በህይወት የተረፉት ደግሞ 706 ሰዎች ብቻ ናቸው።
ከውቅያኖስ በታች በ3 ሺህ 840 ሜትር ጥልቀት የሰጠመው የታይታኒክ መርከብ ፍርስራሽ የተገኝው አደጋው ከደረሰ ከ73 ዓመታት በኋላ ነበር።
ከዚህ ጭብጥ በመነሳት የተሰራው የጀምስ ካሜሮን "ታይታኒክ" ፊልም 200 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የወጣበት እና እጅግ ተወዳጅ የሆነም ነበር። ፊልሙ በ11 ዘርፎች አካዳሚ አዋርድን አሸንፏል።
የታይታኒክ ፊልም መሪ ተዋናዮች ኬት ዊንስሌት እና ሊዮናርዶ ዲ ካፔሪዮ በተውኔት ዘረፍ ኦስካር አለማሸነፋቸው ብዙዎችን ያስገርማል።

https://www.instagram.com/addismedianetworkamn/profilecard/?igsh=cnloYWJ1ajByczJp
Join us on Instagram and guess the Arsenal vs Madrid game to win gifts

ይገምቱ ይሸለሙ
በነገው ዕለት ዕረቡ ሚዚያ 08/2017 ዓ.ም ሪያል ማድሪድ በሜዳው አርሰናልን ያስተናግዳል።
በመልሱ ጨዋታ አርሰናል በሜዳው ያገኘውን ድል ለማስጠበቅ ማድሪድ ደግሞ በቤርናባው አዲስ ታሪክ ለሠስራት ይፋለማሉ።
ይህንን ጨዋታ ማን ያሸንፋል??
ይገምቱ እና ይሸለሙ!!
ግምትዎን ለማስቀመጥ ከጥሎ ባለው ሊንክ ኢንስታግራም ቻናላችንን ብቻ ይጠቀሙ!!
https://www.instagram.com/p/DId2uQwIFYL/?igsh=MXc2enp1OGN6aDBrag==

አርሰናል በመልሱ ጨዋታ ሪያል ማድሪድን 2ለ1 አሸነፈ
መድፈኞቹ በድምር ውጤት ሪያል ማድሪድን 5 ለ 1 አሸንፈው ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፈል።
በሳንቲያጎ ቤርናባኦ አርሰናልን ያስተናገደው የውድድሩ ባለ ሪከርድ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ በአርሰናል በድምር ውጤት 5 ለ1ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል።
የአርቴታው ቡድን በብዙ ተጠብቆ የነበረውን ጨዋታ በድል በመወጣት ታላቅ ታሪክ ፅፏል። 2 ለ 1በተጠናቀቀው ጨዋታ ቡካዩ ሳካ እና ማርቲኔሊ ለአርሰናል ቪኒሽየስ ጁንየር ለ ማድሪድ ጎቦቹን አስቆጥረዋል።
በመጀመሪያው አጋማሽ በቫር ውሳኔ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ቡካዮ ሳካ ሳይጠቀምበት መቅረቱ እና በሌላ መልኩ በዳኛ ለማድሪድ የተወሰነለትን ፍፁም ቅጣት ምት በቫር መሻሩ የምሽቱ ጨዋታ ሌላ ገፅታ ነበር።