የሳምንቱ አንኳር ዜናዎች
እሁድ ሐምሌ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ)
1) በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ በቼ እና ዲዳ በተባሉ ቦታዎች፤ ሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እና ዕሁድ ሐምሌ 16/2015 የታጠቁ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ከሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እስከ ሐምሌ 17/2015 ድረስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት እንደደረሳቸው ጠቅሰው፤ “በቂ የጸጥታ አካላት ወደቦታው ልከናል” ጉዳዩ እየተጣራ ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
2) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች በፈረቃ ለመስራት የሚፈልጉትን የሥራ ፈረቃ መርጠው ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ማስገባታቸውን አዲስ ማለዳ ከሠራተኞች ሰምታለች። ይሕም የሆነው መንግሥት ለሠራተኞች ደመወዝ እንደማይጨምር ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ማስታውቁን ተከተሎ የትርፍ ሰዓት ሥራ በመስራት ገቢያቸውን የሚደጉሙበት አሰራር እንዲኖር በማሰብ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሶ፣ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የአመራርና የሠራተኛ ውይይት መካሄዱን ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።
3) በጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ላለው ግጭት፤ የክልሉ መንግሥት ተጠያቂ መሆኑን የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።
የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ሳይመን ቱት፤ “በክልሉ በሚገኙ የኑዌር እና አኝዋክ ብሄረሰቦች መካከል በየጊዜው የሚፈጠረውን ግጭት እያባባሱት ያሉት የክልሉ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችና የከተማ መስተዳድሩ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡ በዚህም ሰኞ ሐምሌ 17/2015 አስር ሰዓት አካባቢ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሁልዴን በተባለ ቀበሌ በተቀሰቀሰ ግጭት 12 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።
4) ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው የቡና ምርት መጠን ከባለፈው ዓመት መቀነሱን የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡
የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ግዛት ወርቁ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ለዓለም ገበያ ያቀረበችው የቡና መጠን 302 ሺሕ ቶን መሆኑን ጠቅሰው፤ በዘንድሮ ዓመት ግን 240 ሺሕ ቶን ብቻ ማቅረቧን እና ይህም ከባለፈው ዓመት ለዓለም ገበያ ከቀረበው የቡና ምርት ጋር ሲንጻጸር በ62 ሺሕ ቶን መቀነሱን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
5) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን፣ ጌራ ወረዳ ቦርጮ ዴካ ቀበሌ ግብር ከፍለው ደረሰኝ የጠየቁ አርሶ አደሮች በወረዳው የመንግሥት ሥራ አመራሮች እና የጸጥታ አካላት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው አዲሰ ማለዳ በቦታው ከነበሩ የዓይን እማኞች ሰምታለች።
በቁጥር አራት የሚሆኑ አርሶ አደሮች በሕጋዊ መንገድ ግብር ከከፈሉ በኋላ ደረሰኝ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው እና ደረሰኝ ሲከለከሉ ጉዳዩ ወደሚመለከታቸው አካላት ሄደው ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ነው የተገለጸው፡፡
6) አርብ ሐምሌ 21/2015 በመቀሌ ከተማ ድጋፍ እንዲደረግላቸው እና ጥቅማ ጥቅም እንዲከበርላቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተሰባሰቡ ከስድስት ሺሕ በላይ አካል ጉዳተኛ የሕወሓት ታጣቂዎች፤ በፖሊስ ኃይል እንዲበተኑ መደረጋቸውን ትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።
ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ወደ ተለያዩ የክልሉ ቦታዎች ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው በሚደረግላቸው ድጋፍ የሚኖሩና በጦርነቱ ወቅት ቆስለው የአካል መጉደል ያጋጠማችው ወጣቶች፤ በመቀሌ ከተማ ሃያ ኹለት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን እና ፖሊስ ሠልፈኞቹን በኃይል እንዲበተኑ ማድረጉን የትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ አደራጅ ጊደሰና መድኅን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
7) በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር በዋናነት በመተማ በኩል የሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሕገወጥ ንግድ መባባሱ እና የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጭምር ተሳታፊ መሆናቸውን የአይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ የግጭትና የኃይማኖት ዕምነት ጉዳዮች የሥራ ሂደት ኃላፊ ዮናስ ጋዲሳ፤ ባለሃብቶች በንግድ ፈቃድ አማካኝነት ከተለያዩ ቦታዎች ገዝተው የሚያመጡትን ዕቃ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሱዳን እያስወጡ መሆኑን ተከትሎ ሕገወጥ ንግዱ ተባብሷል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ከሕገወጥ ንግዱ በተጨማሪ ግጭቱን ተከትሎ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎችን ጉቦ የሚቀበሉ የተወሰኑ የጸጥታ አካላት፤ ኬላ ላይ ሳይፈተሹ እንዲያልፉና በጸጥታ አካላት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲገቡ የሚያደርጉ መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
__
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተዛውረው የተመረቁ ተማሪዎች መመረቂያ ዲግሪያቸው እንዳልተሰጣቸው ገለጹ
እሁድ ሐምሌ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ከአክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው በዘንድሮው ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የመመረቂያ የምስክር ወረቀት (ቴምፖ) ሳይሰጣቸው ከግቢው እንዲወጡ መደረጉን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎቹ "የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 13/2015 ተማሪዎቹን አስመርቆ የመመረቂያ ወረቀት በመስጠት የሸኘ ቢሆንም፤ ከአክሱምና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለመጣን ተማሪዎች ግን "እንድናስተምር እንጂ ቴምፖ እንድንሰጥ የሚያስገድደን አካል የለም።" የሚል ምላሽ መስጠቱ ትልቅ ቅሬታ አሳድሮብናል።" ሲሉ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ ንባብ -> http://addismaleda.com/archives/34583
__
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
እሁድ ሐምሌ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ከአክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው በዘንድሮው ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የመመረቂያ የምስክር ወረቀት (ቴምፖ) ሳይሰጣቸው ከግቢው እንዲወጡ መደረጉን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎቹ "የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 13/2015 ተማሪዎቹን አስመርቆ የመመረቂያ ወረቀት በመስጠት የሸኘ ቢሆንም፤ ከአክሱምና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለመጣን ተማሪዎች ግን "እንድናስተምር እንጂ ቴምፖ እንድንሰጥ የሚያስገድደን አካል የለም።" የሚል ምላሽ መስጠቱ ትልቅ ቅሬታ አሳድሮብናል።" ሲሉ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ ንባብ -> http://addismaleda.com/archives/34583
__
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
በሸዋሮቢት ከተማ የጸጥታ ኃይሎች የቤት ለቤት ፍተሻ እና ወከባ እየፈጸሙ ነው ተባለ
👉የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ኹለት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል
እሁድ ሐምሌ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል በሸዋሮቢት ከተማ እና አካባቢው የመከላከያ ሠራዊት አባላት የቤት ለቤት ፍተሻ እንደሚያደርጉ እና በነዋሪዎች ላይ ወከባ እየፈጸሙ ነው ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ አክለውም፤ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በከተማው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ጨምሮ በነዋሪዎች ቤት በመግባት "ፋኖ ናችሁ፣ የፋኖ ፎቶ በቤታቸሁ ለጥፋችሗል" በሚል ድብደባ እና ወከባ እያካሄዱ ነው ብለዋል፡፡
ድርጊቱ የተጀመረው ከሐሙስ ሐምሌ 20/2015 መሆኑን በመጠቆም፤ "ጸጉር አሳድገሃል" እንዲሁም "በእጅ ስልክ ቀረርቶና የፋኖ ምስል ጭነሃል" በሚል ሰላማዊ ሰዎችን ላይ ድብደባ እንደሚፈጽሙ ተመላክቷል።
ለተጨማሪ ንባብ -> addismaleda.com/archives/34587

በሸኔ ታግተው የነበሩ ኹለት ንፁሃን እና አራት የታጣቂ ቡድኑ አባላት በወንዝ መወሰዳቸው ተሰማ
እሁድ ሐምሌ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል አቦቴ ደገም ወረዳ በአነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ታግተው የተወሰዱ ኹለት ንፁሃን ሰዎች እንዲሁም አራት የታጣቂ ቡድኑ አባላት በወንዝ ተወስደው ሕይወታቸው ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለደ ገልጸዋል፡፡
ንፁሃኑ በታጣቂ ቡድኑ የተወሰዱት ባለፈው ሐሙስ ሐምሌ 20/2015 ሌሊት ጨፌ በተባለች አነስተኛ የገጠር መንደር መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፤ የታጣቂ ቡድኑ አባላት ካገቷቸው ሰዎች ጋር በሽሽት ላይ በነበሩበት ወቅት በአካባቢው ያለን ወንዝ ለመሻገር ሲሞክሩ ኹለት ንፁሃን እና አራት የታጣቂ ቡድኑ አባላት ሞልቶ በነበረው ወንዝ መወሰዳቸው ተገልጿል።
ለተጨማሪ ንባብ -> addismaleda.com/archives/34590

በወልቂጤ ጅማ መንገድ የታጠቁ ኃይሎች በአሽከርካሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ዝርፊያ እየፈጸሙ ነው ተባለ
እሁድ ሐምሌ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከወልቂጤ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ጊቤ ሸለቆ ውስጥ የታጠቁ ኃይሎች በተሽከርካሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ዝርፊያ እየፈጸሙ መሆኑን አሽከርካሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
በዚህም በጊቤ ወንዝ አካባቢ የፖሊስ ልብስ ለብሰው የሚንቀሰቀሱ ኃይሎች፤ በተለይ በምሽት የሚያሽከረክሩ ሹፌሮችን በማሰቆም ገንዘብ አምጡ እንደሚሉና ገንዘብ አንሰጥም የሚሉ ሹፌሮችን የመኪናቸውን መስታወት እንደሚሰብሩ ነው የተናገሩት።
ለተጨማሪ ንባብ -> addismaleda.com/archives/34595
__
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
እሁድ ሐምሌ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከወልቂጤ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ጊቤ ሸለቆ ውስጥ የታጠቁ ኃይሎች በተሽከርካሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ዝርፊያ እየፈጸሙ መሆኑን አሽከርካሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
በዚህም በጊቤ ወንዝ አካባቢ የፖሊስ ልብስ ለብሰው የሚንቀሰቀሱ ኃይሎች፤ በተለይ በምሽት የሚያሽከረክሩ ሹፌሮችን በማሰቆም ገንዘብ አምጡ እንደሚሉና ገንዘብ አንሰጥም የሚሉ ሹፌሮችን የመኪናቸውን መስታወት እንደሚሰብሩ ነው የተናገሩት።
ለተጨማሪ ንባብ -> addismaleda.com/archives/34595
__
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ማጣራት ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ማግኘቱን አስታወቀ
ሰኞ ሐምሌ 24 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የቀረቡለትን የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጥያቄዎችን ተከትሎ ባደረገው የማጣራት ሥራ ሕጋዊነት የሌላቸው ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ዩንቨርስቲው የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ተቋማት በሚቀጠሩበት ወይም ተቀጥረው እየሠሩ ባሉበት ጊዜ የሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ይጣራልን ጥያቄዎችን እየተቀበለ የትምህርት ማስረጃ አጣርቶ በማረጋገጥ በተከታታይ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት የማጣራት ሂደት ከአንዳንድ ተቋማት የቀረቡ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን የትምህርት ማስረጃዎች፤ በዩኒቨርሲቲው በተሰጣቸው የተማሪ ውጤት ኮፒ ላይ የአጠቃላይ ነጥብ ለውጥ የተደረገባቸው እንዲሁም ፈጽሞ በዩኒቨርሲቲው ያልተማሩባቸው ሐሰተኛ ዲግሪ ማስረጃዎች መሆናቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
በመሆኑም መሰል ኃላፊነት የጎደላቸው ተግባራት እንዳይበረታቱ ብሎም ሕዝብና መንግሥት ሙያዊ ብቃት በሌላቸውና ኃላፊነት በጎደላቸው ዜጎች ለጉዳት እንዳይጋለጥ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ማስረጃ ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማስመሰልና በመቀየር እንዲሁም፤ በዩኒቨርሲቲው ሥምና ሎጎ ያልተማሩበትን ዲግሪ ይዘው የማጭበርበር ተግባር ላይ የተሠማሩና ወደ ፊትም የሚሠማሩ ቢኖሩ ለሕዝብ የማጋለጥ ሥራ በተከታታይነት እንዲሠራ ዩኒቨርሲቲው መወሰኑን ገልጿል፡፡
ስለሆነም ከላይ በተያያዘው የሐሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ሪፖርት ላይ ሥማቸው የተጠቀሱ ግለሰቦች፤ በእነዚህ የትምህርት ማስረጃዎች በየትኛውም ተቋም ቢቀጠሩ ማስረጃዎቻቸው ሕጋዊነት የሌላቸው መሆኑን ማረጋገጡን ዩንቨርስቲው አስታውቋል፡፡

የአፈር ማዳበሪያ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሸከርካሪ ተገልብጦ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
ሰኞ ሐምሌ 24 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) 225 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያና ከ16 ሰው በላይ ጭኖ ጉዞውን ከደባርቅ ጃናሞራ ሲጓዝ የነበረ ኮድ A06872 et ካሶኒ መኪና መካነ-ብርሃን ከተማ ከመድረሱ በፊት መንገዱን ስቶ በመገልበጡ፤ የ9 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ4 በላይ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።
አደጋው የተከሰተው ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ሲሆን፤ ሰዎቹ አብዛኛውን የተሳፈሩት ቧሂት መገንጠያ ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ተሳፋሪዎቹም የሴፍትኔት የእርዳታ ብር ለማውጣት የመጡ እንደነበር በስፍራው አስከሬን ያነሱ ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ከባድ ቁስለኞቹ በጃናሞራ እና ወደ ደባርቅ ሆስፒታል ለሕክምና መላካቸውን የጃናሞራ ኮሚኒኬሽን አስታውቋል፡፡

ሎሬት መላኩ ወረደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ሰኞ ሐምሌ 24 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ ዘረመል ሀብት ላይ ሰፊ ጥናት እና ምርምር በማድረግ የሚታወቁት ሎሬት መላኩ ወረደ (ዶ/ር) ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ቀደምት ኃላፊዎች መካከል አንዱ የሆኑት የዓለም ሎሬት መላኩ ወረደ፤ በኢትዮጵያ የጄኔቲክ ሐብት ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የ‘ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ’ን መሸለማቸው ይታወቃል፡፡
ሎሬት መላኩ የኢትዮጵያ የዘረመል (ጂን) ባንክን አቋቁመው ለ16 ዓመታት ያህል የመሩ ሲሆን፤ በመምህርነት እንዲሁም የጅማንና የአዋሳን እርሻ ኮሌጆች በመምራት ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል፡፡
ሎሬት መላኩ ወረደ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት በመጠበቅና ለምርምር እንዲውል በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን፤ ሳይንሱንና የኢትዮጵያን አርሶ አደሮች አገር በቀል እውቀት በማስማማት እንዲሁም ለአርሶ አደሮች መብት ተሟጋች በመሆን ይታወቁ ነበር፡፡

በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል
ሰኞ ሐምሌ 24 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ጀነራል ካውንስል በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ነጥብ ላይ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን በሙሉ ድምጽ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
ውጤቱንም በማስመልከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለሚዲያ አካላት ነገ 4 ሰዓት ላይ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 28-30/10/2015 ድረስ በ182 የፈተና ጣቢያዎች ለ75 ሺሕ 090 ተማሪዎች፣ 1 ሺሕ 900 ፈታኞችን፣ 700 ሱፐር ቫይዘሮችንና 182 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን በማሳተፍ መሰጠቱ ይታወሳል።