Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
29.8K subscribers
15.6K photos
55 videos
15 files
8.11K links
ዜና ከምንጩ
Download Telegram
‹‹አሁንም ድረስ በመሰረተ ልማት እጦት እየተሰቃየን ነው›› የኮሪደር ልማት ተነሺዎች

👉 ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተፈቷል ለማለት አንደፍርም- የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ በፒያሳ እና አራት ኪሎ አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች በኮሊደር ልማቱ ምክንያት ከቀድሞ የመኖሪያ መንደራቸው መነሳታቸው ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ተለዋጭ ቤቶች እና ቦታዎችን በእጣ በማቅረብ በወጣላቸው እጣ መሰረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ለልማት ተነሽዎቹ መኖሪያ ቦታን አስረክቧል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39389
በጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ ተለያዩ ክልሎች ደም ማድረስ አልቻልኩም ሲል የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎትአስታወቀ

አሁንም ብዙ ደም ፈላጊዎች እኛን እየተማጸኑ ነው-የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በተለያዩ ክልሎች እያጋጠመ ላለው የደም እጥረት የጸጥታ ጉዳይ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ሀላፊ ሲስተር ሀና ለገሰ አስታውቀዋል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39393
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች አማራጭ ድረ-ገጾችን ተጠቅመው ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39397
ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በውጭ ሀገራት ለመገናኘት ሀሳብ ማቅረቡን አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ

አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንዳሉት የታጠቁ ኃይሎች እና ራሳቸውን ከምክክሩ ያገለሉ ፓርቲዎችን እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

"የታጠቁ ሀይሎችን እስካሁን ገጽ ለገጽ ወይም በቀጥታ አግኝተን አነጋግረናቸው አናውቅም ያሉት ኮሚሽነሩ የፖለቲካ ጥያቄ አቅርበው በምክክሩ እንዲሳተፉ በተለያየ መንገድ ጥሪ አድርገናል፤ ለድህንታቸው ሙሉ ዋስትና እንደምንሰጥ ከዛም አልፎ በውጭ ሀገራት ተገናኝተን ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆናችንን ገልጸናል ሲሉ ከዚህ በፊት የተደረገውን ጥረት አንስተዋል።

ከግጭት እና ጦርነት ያተረፍነው እንግልትና ስቃይ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን እኛ የማደራደር ሀላፊነት ባይኖረንም ግጭቶች የሚፈቱበትን መንገድ የመቀየስ ስራ ግን እንሰራለን ብለዋል፡፡
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
Photo
አቶ ታዲዮስ ታንቱ የ6 ዓመት ከ3ወር ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተጣለባቸው

አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 ክሶች ነው የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው።

አቶ ታዲዮስ ታንቱ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አንደኛው ክስ ላይ እንዳመላክተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/(1)ሀ እና አንቀጽ 257/ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ግንቦት 11 ቀን እና በመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እና በተለያዩ የዩቲዩብ ቻናሎች ህዝባዊ አመጽ መቀስቀስ ወንጀል የሚል ነው።

በ2ኛ ክስ በተመለከተ ደግሞ የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7/4 በመተላለፍ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

በ3ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ ከንቀጽ 32 /1ሀ ና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እቅስቃሴን ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሀሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ4ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ህዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም የ6 ልጆች አባት መሆናቸውንና የ70 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሁለት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 24 መሰረት በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ከ2ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የአልኮል መጠን ቅጣት መተላለፉ ተገለጸ

ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ጠጥቶ ማሽከርከርን ለመቆጣጠር የሚያስችለው የአልኮል ትንፋሽ መመርመሪያ በተለያዩ ጊዜያት ተግባራዊ የተደረገ ቢሆንም መቀዛቀዞች እና ተግባራዊነቱ እየቀነሰ ነው የሚል ሀሳብ ሲዘዋወር ቆይቷል፡፡

የአልኮል ትንፋሽ መመርመሪያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል በመቆሙ ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር እንዳልተቻለ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመት ማሳወቁ ይታወሳል ቢሆንም ከበሽታው መረጋጋት ጋር ተያይዞ የተቋረጠው ምርመራ መቀጠሉ ተገልጻል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39405
ባለሃብቱ አቶ መቅደስ አክሊሉ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ላለፉት ሶስት ቀናት በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው የነበሩበት ያልታወቀው ባለሀብቱ አቶ መቅደስ አክሊሉ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጧል፡፡

አቶ መቅደስ የአቢሲኒያ ባንክ ዋና ባለ ድርሻ ሲሆኑ ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የታወቀ ነገር አለመኖሩ የተነገረ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የ13 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸውም ታውቋል::
"የድጎማ ፖለቲካ ፖርቲዎችን መፍጠር ማቆም አለብን" ሲል ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በመንግሥት ድጎማ ላይ ተንጠልጥሎ ፖርቲ መመስረት መቆም አለበት ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ ይህን ያለው በቅርቡ ያደረገዉን አገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡

"በኢትዮጵያ የመድብለ ፖርቲ ምስረታ ከተጀመረበት 1984 ዓ.ም በመንግሥት ድጋፍ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል" ያለው ቦርዱ በዚህም ፖርቲዎች በመንግሥት ድጎማ ላይ ተንጠልጥለዉ የቆዩ መሆናቸውን እና "የመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ዓላማዉ ተጨማሪ ድጋፍ ሰጥቶ ፖርቲዎች ከፍ የሚሉበት እንጂ፤ የሥራ መፍጠሪያ አይደለም" ብሏል፡፡

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ውብሸት አየለ "የድጎማ ፖለቲከኛ አንድ ቦታ ላይ መቆም ይኖርበታል" ሲሉ አዲስ ለሚመጡ ፓርቲዎች አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ አዲስ የሚመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት የሙሉ ዕዉቅና ለማግኘት ሲከፍሉ የነበረዉን 2 መቶ ብር ወደ 30 ሺሕ ከፍ ማድረጉን ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
Photo
‹‹የኮሪደር ልማት ግንባታና የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ለእንግልት እየዳረገን ነው›› ነዋሪዎች

‹‹የኮሪደር ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ብቻ ነው ችግሩ መፈታት የሚችለው›› መምሪያው


ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የኮሪደር ልማት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል በመሆኑም በመንገድ ዳርቻዎች ላይ የሚካሄደው ግንባታ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቁን መጨመሩ ተገልጻል፡፡

በአንደኛ እና ሁለተኛ ዙር የግንባታ ሂደት የቀጠለው የኮሪደር ልማት አስቀድሞ ከነበረው የመንገድ መጨናነቅ እና የትራፊክ ፍሰት እጅግ እንደጨመረ እና ተሸከርካሪዎችም ሆኑ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ካሰቡበት ቦታ ለመድረስ አማራጭ መንገዶችን ቢጠቀሙም ችግሩ እየባሰ እንጂ እየተፈታ እንዳልሄደ ይናገራሉ፡፡

በሰዓት ወደ ስራ ገበታ መግባትም ሆነ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ በመንገድ ላይ የሚያጋጥመው የትራፊክ መጨናነቅ ቀደም ብሎም ቢሆን ዋነኛ ችግር የነበረውን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል ይላሉ፡፡

አማራጭ መንገዶች ለተሸከርካሪዎች ክፍት ቢደረጉም የመንገዱ እና የተሽከርካሪው ብዛት አለመመጣጠኑ መጨናነቁን ሊያስተካክል አለመቻሉም በምሬት የሚገልጹት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች እኔ ነኝ የሚል ተጠሪ አካል ለጉዳዩ ትክክለኛና አፋጣን ምላሽ እየሰጠ አይደለም ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በዛየሚሉ አሽከርካሪዎች “አቋራጭ መንገድ ነው የምንጠቀመው በታሪፍ ዋጋ አያዋጣንም” በማለት የዋጋ ጭማሪ እያደርጉ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡
አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያ እና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን ለገሰ በአሁን ሰዓት በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘው የከተማ ልማት ከተለመደው ውጪ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅን አስከትሏል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ መጨናነቁን እና አደጋውን ለመቀነስ እየተሰራ እንደሆነ እና አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ክፍት በማድረግ እንዲሁም ግንባታ በሚካሄድባቸው ቦታዎች በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የገለጹት ኢንስፔክተር ሰለሞን የኮሪደር ልማቱን በፍጥነት በመጨረስ ወደ መደበኛው የትራፊክ እንቅስቃሴ መግባት ዋነኛ መፍትሄ እንደሆነም ነው ያነሱት፡፡
‹‹በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙት 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ናቸው የተከፈቱት›› የዞኑ ትምህርት መምሪያ

ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ ከሚገኙ 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ትምህርት እየተሰተባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በዘንድሮ ትምህርት ዘመን 710 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ መመዝገብ የቻሉት 70 ሺህ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተከፍተው ሥራ የጀመሩት ትምህርት ቤቶችም ከችግሮች የጸዱ አይደሉም ያሉት አቶ ጌታሁን ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሕጻናት በየመንገዱ “መጽሐፍና ደብተራቸው እየተቀደደባቸው እና እየተደበደቡ አልቅሰው ይመለሳሉ” ብለዋል።

ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንደላኩ የተሰማባቸው ወላጆችም እስከ “15 ሺህ ብር ቅጣት፣ ድብደባን ጨምሮ እስከ ግድያ የደረሰ ግፍም እንደተፈጸመባቸው” የትምህርት መምሪያ ኃላፊው ለአሚኮ ተናግረዋል።

አቶ ጌታሁን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቤት ሲውሉ በተለይም ሴት ልጆች “ያለዕድሜ ጋብቻ እየተፈጸመባቸው ነው” ሲሉ ገልጸው ወንዶቹም ቢኾኑ ዘመን በወለደው አጓጉል ቦታ እየዋሉ ለወላጆቻቸው የጭንቀት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
‹‹በዘፈቀደ የሚሰጡ ሹመቶች ከባድ ቅጣትን ያስከትላሉ›› የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር

ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍቃድና እውቅና ውጪ የሚደረጉ ሹምሽሮች እስከ በጀት መገደብ የሚደርስ ቅጣት ሊጣል ይችላል ሲል በጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አስጠንቅቋል፡፡

ጊዚያዊ አስተዳደሩ በአቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ተፈርሞ ባሰራጨው መመሪያ ፤ " የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች ማደናቀፍ እና በዘፈቀደ ህጋዊ ያልሆነ ሹመት መስጠትና መንሳት የበጀት ቅጣትና የህግ ተጠያቂነት ያስከትላል " ሲል ነው ማስጠንቀቂያ የሰጠው።

መንግስታዊ ስልጣን እና ሃላፊነት የሌለው ' ቡድን ' በማለት የተጠቀሰው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የሚሰጠው ሹመት የመሻርና ሹመት የመስጠት ተግባር ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

በመሆኑም ቡድኑ የሚያካሄዳቸውን ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዲቆም ይህንን የጊዚያዊ መንግስቱ መመሪያ በመቀበል ፍርድ ቤት ጨምሮ የዞን እና የወረዳ የመንግስት መዋቅሮች ህጋዊ አሰራር እንዲከተሉና ህግ በሚጥስ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንዲሁም በክልሉ በየመዋቅሩ ያሉ ምክር ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ መሆኑን በመቀበል ሹመት ከመስጠትና ከመሻር እንዲቆጠቡ ሲል ነው ያሳሰበው፡፡

ላለፉት ወራት የዘለቀው የህወሃት አመራሮች ፍትጊያ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን እኔ ብቻ ነኝ እውቅና ያለኝ የሚለው የሁለቱ ቡድኖች መካረርም ምንም አይነት መፍትሄ አላገኘም፡፡
“በኢትዮጵያ ታሪክ ከኦሮሞ ማህበረሰብ አንድ መሪ ወጥቶ ወደ ቤተመንግስት እና ወደ ፊት ሲመጣ ግርግር መፍጠር አዲስ አይደለም፡፡ ዘመነ መሳፍንትን የፈጠረው የኦሮሞ ቤተ መንግስት መግባት ነው፡፡ ኦሮሞን ተረኛ የሚሉት በጥላቻ ነው“
አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን የመጨረሻ ክፍል ቃለ-ምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ።

https://youtu.be/LQUJn733Jto?si=L7DmDjdZEA5rzf8W