Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
Photo
ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምትቀይራቸው የብር ኖቶች 3ነጥብ6 ቢሊዮን ወጪ አወጣች
ኢትዮጵያ ለ23 ዓመታት ያህል ስትጠቀምባቸው የነረበሩትን የብር ኖቶችን መቀየሯ ይፋ ተደረገ።
በዚህም 262 ቢሊየን መጠን ያላቸው የብር ኖቶች የታተሙ ሲሆን ለህትመቱም 3ነጥብ6 ቢሊዮን ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ለኢትይዮጵያን ቢዝነስ ሪቪው መጽሔት (EBR) ገልጸዋል።
ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ያስታወቁ ሲሆን የአምስት ብር ኖትም በጊዜ ሂደት በሳንቲም እየተተካ እንደሚሄድ አስታውቀዋል፡፡
ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ እንደሚጨምር የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ ተብሏል።

የዱለቻ - አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታ ተቋረጠ
የአዋሽ ወንዝ ሙላት ያደረሰው የጎርፍ ማጥለቅለቅ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተቋራጭነት በግንባታ ላይ የሚገኘውን የዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ መቆሙን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በአፋር ክልል የክረምት ዝናብ በመብዛቱ ከፍተኛ የሚባል የጎፍ መጥለቅለቅ አጋጥሞ እስካሁንም ድረስ ብዙ ዜጎች ተጎጅ ሆነዋል።
በዚሁ የጎርፍ መጥለቅለቅ በአፋር ክልል በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ እየተገነባ ያለው የዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከነሀሴ 26/2012 ጀምሮ የግንባታ ስራው እንደተቋረጠ የኢትዮጵያ ኮንስትራክ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የህዝብ ግነኙነት ኃላፊ ጥንፉ ሙጬ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
https://addismaleda.com/archives/13595

የኢትዮጲያ ህዝባዊ አብታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) የምርጫ ቦርድ ህጉን ተከትሎ እየሰራ አይደለም ሲል ወቀሰ፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች እኩል መሟላት ያለብንን አሟልተን ብንገኝም ምርጫ ቦርድ እራሱ ያወጣውን ህግ እየተገበረ አይደለም ሲሉ የኢህፓ ምክትል ሊቀ መንበር ሰለሞን ተሰማ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
እርሳቸው እንደሚሉት የመጀመርያው የኢህአፓ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ታህሳስ 4 እና 5 2012 ጉባኤ ያካሔደ ሲሆን በአዲሱ ምርጫ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ህግ 1162/2011 መሰረት 10 ሺህ የሚሆን ፊርማ እና የአምስት መቶ አንድ የጉባኤ ተሳታፊዎች አሟልተን ነበር ነገር ግን ይሄን ባደረግን በ45 ቀን ውስጥ የሙሉ እውቅና ፈቃድ ሊሰጠን ሲገባ ከልክሎናል ብለዋል
https://addismaleda.com/archives/13592

ዜና ከምንጩ
የኢትዮጲያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድን ወቀሰ
በአምስት ክልሎች ላይ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 217 ሺህ ሠዎች ተፈናቀሉ
በኢትዮጵያ ባለፉት የክረምት ወራት በአምስት ክልሎች፣በ 40 ወረዳዎች እና በ25 ዞኖች ላይ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 580 ሺህ ሠዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 217ሺህ የሚሆኑት ደግሞ መፈናቀላቸውን የሠላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ።
https://addismaleda.com/archives/13654

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) አዲስ ባንክ እያቋቋሙ ነው
በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ቦርድ ሰብሳቢነት የሚቋቋመው ሆሳዕና ባንክ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣውን ደንብ እና መርሆዎች በመከተል በኹለት ቢሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል በምስረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። በዋነኝነት በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የደቡብ ክልል ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን አነሳሽነት በምስረታ ላይ የሚገኘው ይህ ባንክ በአገራችን ያለውን ውስን የፋይናንስ ዘርፍ በማጠንከር ስራ ላይ የራሱን የሆነ አስተዋፅዎ እንደሚያበርክት ተገልጿል።
በተጨማሪም በተለያዩ የደቡብ ከተሞች፣ በአዲስ አበባ፣ በናዝሬት፣ በድሬዳዋ እንዲሁም በሌሎች ትልልቅ ከተሞች ያለውን የፋይናንስ አቅም እና የማህበረሰቡን የመቆጠብ ባህል ታሳቢ በማድረግ የባንክ አገልግሎትን በሁሉም ቦታ በይበልጥ ተደራሽ የማድረግ እቅድን ይዞ በመመስረት ላይ እንደሚገኝ የባንኩ የፕሮጀክት ማናጀር የሆኑት ኤርሲዶ ሌንዴቦ (ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
https://addismaleda.com/archives/13612

ዘመናዊው የቄራ ግንባታ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ምክንያት ተስተጓጎለ
በ2012 ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ነበረበት
የአዲስ አበባ የቄራዎች ድርጅት በሃና ማርያም አካባቢ ሊያከናውነው የነበረውን ዘመናዊ የቄራ ግንባታ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ምክንያት ግንባታውን ለመጀመር መቸገሩን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። ባጠናቀቅነው የ2012 በጀት ዓመት ግንባታው ለማጠናቀቅ የታቀደ ቢሆንም በሕገ- ወጥ መሬት ወረራ ምክንያት ግንባታው እስከአሁን አለመጀመሩን ድርጅቱ ለአዲስ ማለዳ አስታወቋል።
https://addismaleda.com/archives/13610

ዲጅታል ዲፕሎማሲ እና ትራንፎርሜሽን
ዲጅታል ዲፕሎማሲ እና ትራንስፎርሜሽን መሰረት ያደረገ ስብሰባ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር በጋራ በሐያት ሪጀንሲ እየተካሄደ ይገኛል።
በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያን በተለያዩ የዓለም አገራት የሚወክሉ አምባሳደሮች እና ቆንስላዎች ተገኝተዋል።

3 ሺህ የከተማ አውቶብሶች ግዢ ሊፈጸም ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2013 በጀት አመት አገልግሎት የሚሰጡ ከ 3ሺኅ በላይ የከተማ አውቶብሶችን 9 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ በመመደብ ግዢ እያካሔደ እንደሆነ አንበሳ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
https://addismaleda.com/archives/13598

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዳዲስ ሹመቶች ሰጡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዳዲስ ሹመቶች እና የስራ ምደባ ሰጡ።
የተጀመረውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና በተለያዩ ግዜያት የሚነሱ የህዝብ ቅሬታዎችን ለመመለስ የአመራር ሽግሽግና አዳዲስ የስራ ስምሪት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ዛሬ ለ8 አመራሮች ምደባ መሰጡትን የከንቲባ ጸኀፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት
1. ሙሉጌታ ተፈራ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
2. ተፈራ ሞላ - የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
3. ጀማል ረዲ - የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. መኮንን አምባዬ - የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
5 ሺሰማ ገ/ስላሴ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ
6. ተተካ በቀለ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ አደረጃጀት አማካሪ
7. ጥላሁን ፍቃዱ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ
8. የትናየት ሙሉጌታ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጸህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

በእስር ላይ የነበሩ 274 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
ወደ ሳኡዲ አረቢያ ያለ ህጋዊ ሰነድ የገቡ እና በጂዳ ከተማ በእስር ላይ የነበሩ 274 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዛሬ መስከረም 6 /2013 ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ።
ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል መስፍን ገብረ ማርያምን ጨምሮ ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች ተገኝተው አቀባበል ተደርጎላቸዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአፍሪካ 50 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በከፋ የድህነት ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላል ተባለ
አፍሪካ በአሁን ወቅት የዓለም ስጋት በሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በዘንደውሮው በፈረንጆቹ በ2020 መጨረሻ ላይ 13 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ ከድህነት ወለል በታች ይወድቃሉ ተብሎ ሲጠበቅ ወደ 50 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ በከፋ የድህነት ደረጃ ላይ ሊደርሱባት ይችላል ተብሎ እንደሚገመት የቢል እና ሚኒንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አስታወቀ ፡፡
በዚህ ዓመት በወባ በሽታ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ በእጥፍ እንደሚጨምር የተተነበየ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ 80 ሚሊዮን ሕፃናትም በቀላሉ መከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ፋውንዴሽኑ ለአዲስ ማለዳ በላከው ሪፖርቱ ላይ አመላክቷል።
https://addismaleda.com/archives/13659

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራል
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ተከብሮ እንደሚውል አባገዳዎች ዛሬ መስከረም06/2013 በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 በአዲስ አበባ ፣ የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 24/2013 በቢሾፍቱ እንደሚከበር አባገዳዎች ገልጸዋል፡፡
አባ ገዳዎቹ የኢሬቻ በዓል በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በሚታደሙበት ሲከበር የነበረ ሲሆን የዘንድሮው በዓል ግን የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከበር ገልጸዋል።
በኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥር በሽታውን ለመከላከል እና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር መሰረት የሚወሰን ሲሆን የገዳ ስርዓት ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብም ይህንን ከግምት በማስገባት በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ ማቅረባቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

ልደቱ አያሌው ክስ ቀረበባቸው
ልደቱ አያሌው የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ 1177/2012 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ ሦስትን በመተላለፍ ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ ቀረበባቸው፡፡
ክሱ በምስራቅ ሸዋ ዞን ጠቅላይ አቃቤ ህግ የቀረበባቸው ሲሆን በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ክስ ተመስርቶባቸዋል ፡፡
ልደቱ ከዚህ በፊት በሰኔ 23 እና 24 በቢሾፍቱ ከተማ አመጽና ሁከት እንዲቀሰቀስ በገንዘብ ሲደግፉና ሲያስተባብሩ ነበር ተብለው ምርምራ ሲከናወንባቸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
በመሆኑም አቃቤ ህግ በዚህ ምርመራ ላይ ፍቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያ አግኝቼባቸዋለሁ በማለት ነው ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ ያቀረበባቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በፍርድ ቤቱ ጉዳያቸው እየታየ ይገኛል ሲል ፋና ዘግቧል፡፡

‹‹የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ማክበር እና ማስከበር ያልቻለ መንግሥት ስለ ልማት እና ብልፅግና የማውራት የሞራል ልዕልና ሊኖረው አይችልም›› ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን
በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደረሰው ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ እና በመንግሥት በኩል የሚሰጡ ችግር ፈቺ ያልሆኑ ምላሾች የችግሩ ምንጭ አካባቢውን ከሚያስተዳድረው የመንግሥት መዋቅር እና ችግሩን በቸልታ እያየ ያለው የፌደራል መንግሥት ነው ብለን እንድናምን አስገድዶናል ብሏል።
ከዚህ በፊት የተፈፀሙ ጥቃቶች አጥፊዎች እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮች ላይ ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ባለመወሰዱ ችግሩ አሁንም ቀጥሏል ሲል ኢዜማ አስታውቋል።
ኢዜማ ክልሉን በሚመሩት ኃላፊዎች ላይ ማጣራት ተደርጎ እርምጃ ካልተወሰደ ግድያና ማፈናቀሉ ይቆማል ብሎ እንደማያምንም ጠቅሷል።
የፌደራል መንግሥት እንደዚህ ዓይነቱ ጥቃቶች ከመድረሳቸው በፊት የመከላከል እና በቶሎ የማስቆም ሥራ ከምንም ጉዳይ በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባም አሳስቧል።
የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን በሕይወት መኖር ማክበር እና ማስከበር ነው። ይሄን ማድረግ ያልቻለ መንግሥት ስለ ልማት እና ብልፅግና የማውራት የሞራል ልዕልና ሊኖረው አይችልም ብሏል ኢዜማ።

በእነ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብት ጥያቄ እና የዐቃቤ ሕግ ተቃውሞ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
https://addismaleda.com/archives/13665
https://addismaleda.com/archives/13665