የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ሁሉም የሰ/ት/ቤት አባላት በሥርጭት ላይ የሚገኘውን የሰ/ት/ቤት መማርያ መጻሕፍትን እንዲገዙ የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጥሪ አቀረበ፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………….
መጋቢት 24/2017 ዓ.ም
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………….
በትግበራ ላይ የሚገኘው የሰ/ት/ቤት ሥርዓተ ትምህርት ግቡን እንዲመታ ከሚያስፈልጉት ሥራዎች አንዱ ለተማሪዎች የመማርያ መጻሕፍትን ለመማር አመቺ በሚሆን መልኩ ማዘጋጀት ሲሆን ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰ/ትቤቶች አንድነት ከ1ኛ -- 7ኛ ክፍል በአማርኛ ፤ ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል በአፋን ኦሮሞ በድምሩ 64 የመጻሕፍት ዓይነቶች ተዘጋጅተው በሊቃውንት ጉባኤ ታርመውና ታትመው በቅናሽ ዋጋ እየተሠራጩ ሲሆን ከ8ኛ -12ኛ ክፍል ያሉት የመማርያ መጻሕፍት ደግሞ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ የመንበረ ጵጵስና ሰ/ት/ቤቶች አንድነትም ብዛት ያላቸውን መጻሕፍት በሰ/ት/ቤቶች ጥያቄ መሠረት መጻሕፍቶችን በማስመጣት እያሠራጨ ይገኛል፡፡
ይህ መጻሕፍት ለትውልድ እንዲዳረስ ፤ ትውልዱ መጻሕፍቶቹን ተጠቅሞ ሃይማኖቱን እንዲያውቅ ፤ ሕይወቱን በኦርቶዶክሳው መንገድ እንዲመራ ያግዝ ዘንድ በሁሉም አጥቢያ የሚገኙ የሰ/ት/ቤት አባላት በየሰ/ት/ቤቱ መጻሕፍቱን ለመግዛት በመመዝገብ፤ ወላጆች ለልጆቻቼው መጻሕፍቱን በመግዛት ፤ ማሕበረ -ካህናትና ሰባኪያን በማስተዋወቅ ፤ ሰ/ት/ቤቶች መጻሕፍቱን የሚፈልጉትን ወላጆችና ሰ/ት/ቤት አባላትን በመመዝገብና በማስተባበር እንዲሁም መረጃን ለሁሉም በማዳረስ ሃይማኖታዊ ኃላፊነታችን እንድንወጣ የሀ/ስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከሀገር አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የመጣው መጻሕፍት በመንበረ ጵጵስና ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ቢሮ እየተሠራጨ ይገኛል፡፡
………………………………………………………………………………….
መረጃው የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው፡፡
4
1
አስደሳች ዜና ለመጽሐፍት ፈላጊዎች
📔📘📘🗄📘🗄📗📗🗄📘🗄📘📘🗄📗🗄📙📙📙📙📙📙📙📙
በሙሉ ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ከመጋቢት 26-28ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት በፖስታ ቤት በልዩ ቅናሽ የለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ይዞሎት ቀርባል ታዲያ እርሶ ምን ይጠብቃሉ? እድሉን ፈጥነው ይጠቀሙ።ለወዳጅ ዘመድዎ ይሸምቹ። ለበለጠ መረጃ በ 0974734478 ላይ ይደውሉ
*****📕📗📗📗📘📙📚📔📒📕📕📕📚📙📘🗞📋📁📂📂🗂📰📋📖📖📖📖📖📔📙📓📘📘📒📙📕
**ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ልማት ተቋማት አስተዳደር ክፍል*
👍1