የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በመሆኑም በሰብአዊ ክዋኔው መዋች ሲሆን በመለኮታዊ ክዋኔው ተነሽና አንሺ ነው፤ ከዚህ አንጻር ሥግው ቃል ሁለቱንም ተግባራት በአንድ አካልና ክዋኔ የመፈጸም ሥልጣን አለው፣ ይህም በመሆኑ ራሴን የማኖርና የማንሣት ሥልጣን አለኝ በማለት እውነታውንና ምንነቱን አሳየ፤

ጌታችን ይህንን አስመልክቶ ከመሞቱና ከመነሣቱ በፊት ለቅዱሳን ሐዋርያት በተደጋጋሚ አስረድቶአል፣ ስለሆነም የጌታችን ሞትና ትንሣኤ ድንገተኛና የግድ ሳይሆን ታውቆ ያደረና የውድ እንደሆነ ከዚህ እውነታ እንረዳለን፤

ጌታችን ይህንን ተግባር በውድ ፈቃዱ የፈጸመው በእግዚአብሔር አሰራር ከዚህ ውጭ የዓለም ድኅነት የሚከናወንበት ዕድል ስለሌለ ነው፤ በእግዚአብሔር አሰራር ኃጢአትና በደል የሚሰረዘው በቤዛዊ መሥዋዕት ብቻ እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በነበረው የቤዛዊ መሥዋዕት አቀራረብ የታወቀ ነው፤

በመሆኑም የሰውን ምልአት ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ሰርዞ ሰውን ከሞት ቅጣት ነጻ ለማውጣት ብቃት ያለው ቤዛዊ መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነበረበት፤ ይሁን እንጂ ለዚህ ዓይነቱ ቤዛዊ መሥዋዕት ብቁ የሆነ ከፍጡራን ወገን ስላልተገኘ "ለሊሁ መሥዋዕት፣ ወለሊሁ ሠዋዒ፣ ወለሊሁ ተወካፌ መሥዋዕት ማለትም" ራሱ መሥዋዕት፣ ራሱ መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት፣ ራሱ ተወካፌ መሥዋዕት አምላክ ሆኖ የቤዛነታችንን መሥዋዕት ራሱ በራሱ ለራሱ አቀረበ"፤

በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕትም እኛን ከሞት ቅጣት ነጻ አደረገን፤ትንሣኤያችንንም በትንሣኤው አበሰረ፣ በክርስትና ሃይማኖት የሚገኝ ፍጹም ድኅነትና ነጻነት በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ የተመሠረተ ነው፤

የተወዳደችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን በትንሣኤው ትንሣኤያችንን ሲያበስረን የትንሣኤ ሰዎች ሆነን በመንፈስና በሞራል በማደግ ብርሃናተ ዓለም ልንሆን እንጂ እንደገና የጨለማው ኃይል መሳሪያዎች ልንሆን አይደለም፤ የሞቱና የትንሣኤው ምስጢር በንጹሁ ኅሊናችን ካስተዋልነው ውስጣችን እሱን ለመቀበል የሚያዳግተው አይደለም፤

ከዚህ አንጻር በትንሣኤው አምነን ትንሣኤያችንን እየተጠባበቅን የምንገኝ ሕዝበ ክርስቲያን በቅን አስተሳሰብ፣በርቱዕ አእምሮና በኃይለ ሃይማኖት እየታገዝን ጨለማውን ዓለም ወደ ብርሃን ለመለወጥ መጣርና መትጋት ይጠበቅብናል፤

የጨለማው ዓለም መንፈስ ሊያጠፋን ካልሆነ በቀር እንደማይጠቅመን በተጨባጭ የምናውቀው ነው፤ ወደድንም ጠላንም ያለን ብቸኛ አማራጭ ብርሃንን መከተል ነው፤ እሱም እግዚአብሔር ነው በብርሃን የሚመላለስ እንደማይጐዳ በእግዚአብሔር የሚኖርም ተጐድቶ አያውቅምና ነው፤

ዓለም እንደ አጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው፤ ስለሆነም የኛ ምርጫ ብርሃን የሆነውን እግዚአብሔር እንዲሆን የቤተ ክርስቲያን የዘወትር ጥሪ ነው ፤

በመጨረሻም፡-

የትንሣኤ በዓላችንን ስናከብር ዓለም በክፋቱ ያጨለመባቸውን ወገኖች ጦማችው እንዳይውሉ ካለን ከፍለን የተራቡትን በማብላት፤ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የታረዙትን በማልበስና የዕለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ በማድረግ ቀኑ ለሁላችንም ፍጹም ብርሃን ሆኖ ይውል ዘንድ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን በእግዚአብሑር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም የትንሣኤ በዓል ያድርግልን!!

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ"

“ወስብሐት ለእግዚአብሔር

                   አባ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤

          ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
             አዲስ አበባ' ኢትዮጵያ
ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።
ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል።

( አሻም ሚዲያ ማዕከል  ሚያዚያ ፳፰ ቀን  ፳፻፲፰  ዓ.ም)

በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ ኣምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ተክለሃይማኖት የመግቢያ ንግግር ተጀምሯል።
ጉባኤው በይፋ መጀመሩን ተከትሎ የቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት ለምልዓተ ጉባኤው ቀርቧሎ
በመቀጠልም የሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚወያይባቸውን አጀንዳዳዎች የሚያቀርብ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ተመረጠዋል።

የኮሚቴ አባላቱም
1. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ሊቀ ጳጳስ
4.ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳስ
5. ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ሊቀ ጳጳስ
6. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ
7.ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጳጳስ
መሆናቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የሚዲያ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካል ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት (#EOTCTV) ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በከሰዓት ውሎው ጉባኤውን የሚቀጥል ይሆናል።

መረጃው የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Tv ነው።
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
4
የፈተና ማስታወቂያ

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት ፈተና ቀን አስታወቀ።

በ2018 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና  #ከግንቦት 30_ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን የ4ኛ፣8ኛ እና 10ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና ሰኔ 7/2018 ሙሉ ቀን ይሰጣል።

በተጨማሪ የ2018 ዓ.ም በሀገረ ስብከት ደረጀ ተዘጋጅቶ የሚሰጠው የሚኒስትሪ ፈተና #ሰኔ 28/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስታወቀ።

በዘንድሮው ዓመት በሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ከ1ኛ _9ኛ ክፍል የሚሰጠው የማጠቃለያ ፈተና ኮሮሶች
1. ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
2. የቤተክርስቲያን ታሪክ (7ኛ፣8ኛ፣ እና 9ኛ ክፍል)
3. የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት
4. የግዕዝ ቋንቋ (ከ1ኛ_6ኛ ክፍል) የሚሰጥ ይሆናል።

እንዲሁም ለ4ኛ፣8ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል እና የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጠው ዓመቱን ሙሉ ሲማሩ የነበሩ ስድስቱንም (6) ኮሮሶች  ማለትም #መሠረተ_ሃይማኖት#ልሳነ_ግዕዝ#የቅዱሳት_መጻሕፍት_ጥናት#የቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ#ሥርዓተ_ቤተክርስቲያን እና #ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር  የሚፈተኑ ይሆናሉ።


መረጃው:- የመንበረ ጵጵስና ር/ከ/ወ/ቤ/ክ/ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ነው።
👍71
የሕፃናት የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ሰንበት ትምህርት ቤት ነው።

"የመጀመሪያው ትምህርት ከእግዚአብሔር ቤት ይጀምር"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕፃናት ገና መናገርና መረዳት በሚጀምሩበት ዕድሜያቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣትና መቅደሱን መልመድ እንዳለባቸው አጥብቆ ያሳስባል። "ልጆቻችሁ ዓለማዊ እውቀትን ከመማራቸው በፊት፣ መጀመሪያ የመንፈስ ቅዱስን ጥበብና እግዚአብሔርን መፍራትን ያስተምሯቸው" ይላል። ሕፃንነት ልክ እንደ አዲስ ሰም (Wax) በመሆኑ፣ በዚያ ዕድሜ ላይ የተቀረጸ መልካም ሥዕልና ትምህርት በቀላሉ እንደማይጠፋ ያስረዳል።

በዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን

“ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከሆነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ” ብፁዕ አብነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
🥰1👏1
የቤተክርስቲያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማነው

“ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከሆነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ”

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን አደረሳችሁ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከዋክብት የሆኑት ታላቁ  አባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (የቀድሞው የሸዋ ሊቀ ጳጳስ) ለየሰንበት ትምህርት ቤቶችን ሥርዓትና የወጣቶች አገልግሎት ፋይዳ አጥብቀው በሚያስተምሩት ትምህርቶችና ስብከቶች ውስጥ የሚገኝ እውነተኛ የእረኝነት ለትውልድ ያስተላለፉት ታላቅ አደራ ነው።

ይህ አባባል "ምን ማለት እንደሆነ" እና በውስጡ የያዛቸውን ጥልቅ ምስጢራት በዝርዝር እንደሚከተለው እንመልከት፦

1. "የነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ..." (የወደፊት ዕጣ ፈንታ)

ማንኛውም ሕያው ተቋም የወደፊት ሕልውናውና ጥንካሬው የሚወሰነው ዛሬ በሚያመርተው ተተኪ ትውልድ ላይ ነው። ቤተክርስቲያን ነገ ምን ዓይነት መልክ ይኖራታል? ነገ መድረኩን የሚረከቡት፣ ሥርዓቱንና ሃይማኖቱን ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፉት አገልጋዮች (ሊቃውንት፣ ሰባክያን፣ ካህናትና ምእመናን) እነማን ናቸው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ዛሬ ላይ ነው።

ስለዚህ ለነገዋ ቤተክርስቲያን ክብር፣ አንድነትና ጥንካሬ የምንጨነቅና የምናስብ ከሆነ፣ ትኩረታችን መሆን ያለበት ነገ ላይ ሳይሆን ዛሬ ላይ ነው የሚለውን ዐብይ መልእክት ያስተላልፋል።

2. "...ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ"

ይህ የዓረፍተ ነገሩ ክፍል የችግሩን ሁሉ መፍትሔ በግልጽ ያስቀምጣል። የነገዋን ቤተክርስቲያን ውብና ብሩህ ለማድረግ ዛሬ መሥራት ያለብን በሰንበት ትምህርት ቤት ላይ ነው።

"በልባችሁ አኑሩ" ማለት ምን ማለት ነው?

   1. ትኩረትና ድጋፍ መስጠት፦ ሰንበት ትምህርት ቤትን ከተራ የወጣቶች ስብስብ ወይም መዝሙር መለማመጃ ቦታ በላይ አድርጎ ማየት ሳይሆን በዕውቀት፣ በገንዘብና በሃሳብ መደገፍ ማለት ነው።

   2. በትክክለኛው ሥርዓት መምራት፦ አሁን በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና እንደተዘጋጀው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርትና መዋቅር፣ ልጆችንና ወጣቶችን በዕድሜያቸውና በደረጃቸው (ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4) ከፋፍሎ፣ ጥራቱን የጠበቀ መንፈሳዊ ዕውቀት መመገብ ማለት ነው።

   3. ከባዕድ አምልኮ መጠበቅ፦ ወጣቱ ትውልድ  በሪዕዮተ ዓለም ተውጦ እንዳይቀር እና በበዓላት ሽፋን ከሚደረጉ የባዕድ አምልኮ ልማዶች፣  የጨለማ አሠራሮች ርቆ፣ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ብቻ እንዲያመልክ በልባችን ይዘን ማስተማር ማለት ነው።

ብፁዕ አባታችን በረከታቸው ይደረብንና ይህ ቃል ለሁሉም አባቶች፣ እናቶች፣ ካህናትና መሪዎች የተሰጠ የነቃ የደወል ጥሪ ነው።

"ነገ ቤተክርስቲያን አገልጋይ አጥታ እንድትቸገር፣ ወጣቱ በሱስና በባዕድ አምልኮ ጠፍቶ ቤተክርስቲያን ባዶ እንድትሆን ካልፈለጋችሁ፤ ዛሬ ሕፃናትንና ወጣቶችን በሰንበት ትምህርት ቤት ጥላ ሥር ሰብስባችሁ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩቱ። ዛሬ በሰንበት ትምህርት ቤት የምንዘራው የተቀደሰ ዘር፣ ነገ የምናጭደው የቤተክርስቲያን ትልቅ ክብርና ሕያውነት ነው!"።

በዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ መሳካት ያላቸው ሚና

ትውልዱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት በማዘንበል ሃይማኖቱን ችላ እንዳይል በማሰብ አባቶቻችን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን በማወቅ የሚያድግ፤ መልስ ያለው ትውልድ ለመፍጠር ከ1935-1940 ዓ/ም ባለው ጊዜ ሰንበት ት/ቤትን እንደመሠረቱ የሚታወቅ ሲሆን ቀጥሎም በ 1953 ዓ.ም መመሪያ ወጥቶለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ትእዛዝ በየአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያኑ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን በቃለ ዓዋዲው የሰንበት ት/ቤት አወቃቀር በመመሪያ ተካተተ::

የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዋና ተልእኮ እና ግብ ሰዎች በሃይማኖት፣ (ይህም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን እና ያመኑት ደግሞ ሥራቸው ይከተላቸዋልና) በሥነ ምግባር ጸንተው እንዲኖሩ በማድረግ ለመንግሥቱ ማብቃት ነው። በቃለ ዐዋዲው መሠረትም ይህንን ተልእኮ ለመወጣት በሕፃናትና በወጣቶች በኩል ያለውን ኃላፊነት ለሰንበት ትምህርት ቤት በይፋ ተላልፏል።

ሰንበት ትምህርት ቤቶችም እንደ ተቋም ከሕፃንነት እስከ የነገ ተረካቢ፥ ወጣቶች ድረስ ይህንን ትውልድ የመገንባት ሥራውን በሚገባ ለመወጣት በተናጥልም ሆነ በትብብር በአንድነት አደረጃጀቶችን በመጠቀም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ እየተወጡ ይገኛሉ።


የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን መሪ ቃል:-
"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

👉  Website
1
​ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወጣትነት በፈተናና በምኞት ማዕበል የተሞላ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር።

እንኳን ለ15ኛ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን አደረሳችሁ ።

ስለዚህ ስለ ወጣቶች እንድህ ይለናል ፦
ወጣትነት እንደ "ዱር ፈረስ" እና "እንደሚናወጥ ባሕር" ነው ወጣትነትን ሲገልጸው፦ "ወጣትነት ልክ እንደ ዱር ፈረስ ነው፤ በቀላሉ አይገራም። ወጣትነት ልክ ማዕበል እንደሚናውጠው ባሕር ነው" ይላል። ስለዚህ ወጣቶች በዚህ ዕድሜያቸው እንዳይጠፉና መርከባቸው እንዳይሰምጥ ጠንካራ የመንፈሳዊ ሕይወት መሪ (ኮርቻ) ያስፈልጋቸዋል። ይህ መሪ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ና የሰንበት ትምህርት ቤት ጥበቃ ነው።

👉👉👉👉👉#ሰኔ_14/2018 በ አዳማ ደ/ና/ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን ይከበራል።

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
1👎1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከግንቦት 30_ሰኔ 7/2018 ዓ.ም ድረስ የሞደል እና ማጠቃለያ ፈተና ከ1_10ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች ይሰጣል👆👆👆👆👆👆👆

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇#ሰኔ_14/2018 በአዳማ ደ/ና/ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን ይከበራል።

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
2
🎤🎤🎤መልእክት
"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ"

መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት  የሰንበት ት/ቤቶች ማጀራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዘንድሮ የሰንበት ት/ቤቶች ቀን የሁሉም ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት በየአለበት ቦታ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪቃል   እንዲከበር መልእክት አስተላለፈ።

እንደሚታወቀው ላለፋት አስርት አመታት በቅዱስ ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ደንብ ከጸደቀበት እና በረከታቸው ይደርብን እና በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትሪያሪክ የባዕለ ጰራቅሊጦስ ቀን የሰንበት ት/ቤቶች ቀን እንዲሆን በሰጡት አባታዊ መመርያ መሠረት በየዓመቱ በአለ ጰራቂሊጦስን ቀን መሠረት አድርጎ የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሁሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት የሁለት ቀን  ጠቅላላ ጉባኤውን እና የጉባኤው ማጠቃለያ ቀን በባዕለ ጰራቅሊጦስ እለት ከአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት  በደማቅ ሁኔታ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን በጋራ  ሲያከብር መቆየቱ ይታወሳለ።

ይሁን እና በዚህ አመት በአሉ የዋለበት ቀን ከ7ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዋዜማ ላይ በመሆኑ  የየአህጉረ ስብከት ተወካዮች ለመገኘት ባለመቻላቸው ጠቅላላ ጉባኤው የተዘዋወረ በመሆኑ ሁለም ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ቀንን   "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪ ቃል እንዲከበር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት  የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት  መልእክት አስተላልፏል።

የመንበረ ጵጵስና ር/ከ/ወረዳ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት  የዘንድሮ የሰንበት ት/ቤቶች ቀን ሁሉም አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች አባላት እና የክብር አባላት እንድሁም ታጋባዝ እንግዶች በተገኙበት በዓሉን ሰኔ14/2018 ዓ.ም በአዳማ ደብረ ናዝሬት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ለማክበር ዝግጅት ላይ ይገኛል።

ነገር ግን ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በዕለቱ  ሁላችንም በየአጥቢያችን በሚኖር የሰንበት ት/ቤት ጉባኤ እና የተለያዩ መርሐ ግብራት ላይ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን መሪ ቃሉን መሠረት በማድረግ ከአባላቶቻችን ጋር እንድናከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በመርሐ ግብሮቹም መሪቃሉን መሠረት ያደረገ ቃለ እግዚአብሔር እና በዝማሬ እንድናከብር እያልን  በድጋሚ   የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት  ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለሁሉም የሰንበት ትቤት አባላት  እና አመራሮች  እንኳን ለሰንበት ት/ቤቶች ቀን እና ለባዕለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ እያለ   ሰንበት ት/ቤትች በእለቱ በዐሉን አክብረው እንዲውሉ  እና    የሰንበት ት/ቤት አመራሮች  እንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታችሁን ለመላው አባላቶቻችሁ እንድታስተላልፋ ከወዲሁ  ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 14/2018 ዓ.ም በአዳማ ደብረ ናዝሬት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት
15ኛ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን ይከበራል።


የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት።

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
በመዋቅራዊ አንድነት እጅና ጓንት ሆነን ሰንበት ት/ቤቶቻችን ብናግዛቸው ምድርን ሁሉ ክርስቲያን የማድረግ እምቅ አቅም አላቸው።

«የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ» (ኤፌ. ፬፥፫)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ በመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የምትገኙ ውድ የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ መደበኛ አባላት፣ ልዩ መደበኛ አባላትና የክብር አባላት፤
በመጀመሪያ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የልደት ቀን፣ የሐዋርያት የዕውቀት ማኅደርና የስብከተ ወንጌል መጀመሪያ በዓል በሆነው በበዓለ ጰራቅሊጦስ  እንዲሁም በመላው ዓለም በታላቅ ድምቀት በሚከበረው #ለ፲፭ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በሰላምና በጤና ለደረሰን ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው።

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስና ለ፲፭ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

ግንቦት ፳፫ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም የምናከብረው ይህ ታላቅ ዕለት፣ ሐዋርያት በማርቆስ እናት በማርያም ቤት በአንድ ልብ ሆነው በጸሎትና በሱባኤ ሲተጉ፣ መንፈስ ቅዱስ በእሳት ላንቃ አምሳል ወርዶ የዓለምን ድንበር ጥሰው ወንጌልን እንዲሰብኩ ኃይልና ጥበብ የለበሱበት ዕለት ነው። "ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረዳ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፣ በኢየሩሳሌም በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከዓለም ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆኑኛላችሁ" የሐ. ሥራ 1:8 

የመንበረ ጵጵስና ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ዘንድሮ ይህንን በዓል ሰኔ 14/2018 ዓ.ም በአዳማ ደብረ ናዚሬት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የተለያዩ መርሐ ግብር አዘጋጅቶ ከእናንተ ጋር ለማክበር ዚግጅት ላይ ይገኛል። አንድነቱ ይህንን በዓል ሲያከብር፣ ብርሃነ ዓለም ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ለእፌሶን ክርስቲያኖች ያስተላለፈውን ኀይለ ቃል መሪ ቃል አድርጎ ነው፦ ''የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" (ኤፌ. ፬፥፫)። ይህንን ታላቅ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ የወረዳችን ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ለአገልግሎታችን ምሰሶ ለሆናችሁ አካላት ሁሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት እና ጥሪ ያስተላልፋል፦

፩. ለአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች
የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የቤተ ክርስቲያን የእውቀት ምንጭ የሆኑትን የነገዋን የቤተክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ ሥርዓተ ትምህርትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮች አቅም በማሳደግ ፣ ዘመኑን በዋጀ አሰራር ፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተክርስቲያን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉ አባቶች ሊቃውንት ፣ካህናት፣ ዲያቆናት፣ሰባኪያን፣እና ልዩ ልዩ የሙያ ባለቤቶች የሆኑ ወንድሞች እና እህቶች እንዲሁም በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የጸኑ እናቶች እና አባቶችን አገልጋይ ማፍሪያ መነሻዎች ናቸው። ታላቁ የአገልግሎታችን አባት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እንዳሉት፤ “የሰንበት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያን ችግኞችና የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ኃይሎች” ናቸው።

እኛ በእቅድ እና በተደረጃ መዋቅራዊ አሰራር  ዛሬ የምንሠራው ሥራ የወደፊቷን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ የሚወስን በመሆኑ፣ አጥቢያዎቻችን ዘመኑን የዋጀ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈና ትውልዱን ከሉላዊነት (Globalization) ተጽዕኖና ከሥነ-ልቦና ቀውስ ሊጠብቅ የሚችል ስልታዊ ዕቅድ መሠረት አድርጎ መሥራት ይኖርባቸዋል።

በጥቂት በጎ አድራጊዎች እጅ ላይ የተንጠለጠለ አገልግሎት ብዙዎችን መድረስ አይችልም። በመሆኑም አጥቢያዎች የተለያዩ የልማት ተቋማትን በማቋቋም፣ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በመተግበር ራሳቸውን በፋይናንስ ሊያጠናክሩና የቤተ ክርስቲያንን አደራ ሊወጡ ይገባል።

፪. ለመደበኛ አባላት
ውድ መደበኛ አባላት፤ እናንተ በመዋቅሩ ውስጥ በየክፍሉ (በትምህርት ፣ በበጀትእና ንብረት አስተዳደር ፣ በመዝሙር እና ኪነ-ጥበብ፣ በሰው ሀብት ና በሕዝብ ግንኙነት እና ወ.ዘ.ተ) ተመድባችሁ በአውደ ምህረት በሰርክ ጸሎት፣ በሰንበት፣ በአደባባይ በዓላት አገልግሎት፣ በማኅበራዊ አገልግሎት ሌሊትና ቀን የምትደክሙ የዕለት ተዕለት አገልግሎቱ የጀርባ አጥንቶች ናችሁ።

👉#በተሰባሰባችሁበት የአገልግሎት መድረክ ሁሉ የመንፈስ አንድነት በመጠበቅ ልዩነትን በማጥበብና በማስወገድ ፣ በመካከላችሁ ፍቅርንና ሰላምን ልታጸኑ ይገባል። አንድነታችን ጠላትን የሚያሸንፍበት ትልቁ መሣሪያችን ነው።
👉#ሃይማኖቱን ጠንቅቆ ያወቀና ለሚጠይቀው ሁሉ መልስ ያለው ትውልድ ለመሆን በቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና በሊቃውንት ጉባኤ ተገምግሞ እየተሰጠ በላው ወጥ በሆነ ሥርዓተ ትምህርታችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃት በመከታተልና በሥነ-ምግባራችሁ የጸናችሁ አርአያ ልትሆኑ ይገባል።

፫. ለልዩ መደበኛ እና ለክብር አባላት
በሥራ፣ በትምህርት ወይንም በተለያዩ ማኅበራዊ ኃላፊነቶች ምክንያት በቋሚነት በመዋቅሩ ውስጥ ተገኝታችሁ ማገልገል ባትችሉም፤ በእውቀታችሁ፣ በገንዘባችሁ፣ በምክራችሁና በልምዳችሁ ከሰንበት ትምህርት ቤታችሁ ጎን ቆማችሁ አገልግሎቱን ለምትደግፉ ልዩ መደበኛና የክብር አባሎቻችን በሙሉ በቤተ ክርስቲያን ስም የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

👉#በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውስጥ ያላችሁ ልዩ ልዩ የሙያ ባለቤቶች (መሐንዲሶች፣ ሐኪሞች፣ መምህራንና የሕግ ባለሙያዎች ወ.ዘ.ተ) ያላችሁን እምቅ አቅም ለአጥቢያችሁ ዕድገትና ልማት ይበልጥ እንድታፈሱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
👉#"ሰንበት ትምህርት ቤቶች የእኛ ናቸው" በሚለው መንፈስ፣ በተለይም አሁን ባለንበት የወቅቱ ግዴታ ጠንካራ የገንዘብ አቅም ለመፍጠር በምናደርገው ጥረት ውስጥ ድርሻችሁን ከፍ በማድረግ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሥራዎችን አብረን እንድንሠራ ጥሪያችን የጸና ነው።

በአጠቃላይ ሳንረዳቸውና ሳናግዛቸው እንኳን እስካሁን ይህንን ያህል የወንጌል ፍሬ ማፍራት የቻሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን፤ በተጠናና በመዋቅራዊ አንድነት ሁላችንም መደበኛ፣ ልዩ መደበኛና የክብር አባላት በአንድነት እጅና ጓንት ሆነን ብናግዛቸው ምድርን ሁሉ ክርስቲያን የማድረግ እምቅ አቅም አላቸው።

በዚህ በዓለ ጰራቅሊጦስ እና በ፲፭ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን፣ በመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የምንገኝ አገልጋዮች ሁሉ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅና በተግባር የተገለጠ አሻራ ለማሳረፍ ቃል እንግባ!

በማርቆስ እናት በማርያም ቤት የወረደው መንፈስ ቅዱስ እሳታዊ ቃሉን፣ ሰማያዊ ኃይሉንና አንድነቱን በአገልግሎታችንና በሀገራችን ላይ ያፍስስልን።

መልካም የበዓለ ጰራቅሊጦስና የ፲፭ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን!
👇👇👇👇👇👇👇👇
ሰኔ 14/2018 በአዳማ ደብረ ናዝሬት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት እንገናኝ 👆👆👆👆👆👆

ይትባረክ አምላከ አበዊነ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት።

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም  አዳማ ,ኢትዮጵያ
"Gurmaa'ina caasaatiin tokko taanee yoo manneen barumsaa Dilbataa keenya gargaarre, addunyaa hundumaa kiristaana gochuuf dandeettii dacha dachaa ta'e qabu."

«Tokkummaa Afuuraa Eeguuf Jabaadhaa» (Efe. 4:3)

Maqaa Abbaa fi Ilmaa fi Afuura Qulqulluu Waaqa Tokkoon, Ameen.

Biyya Lallaba Shawaa Bahaa, Mana Lubbummaa Aanaa Teessoo Phaphasummaa jala kan jirtan manneen barumsaa Dilbataa aanaalee kabajamoo, miseensonni idilee, miseensonni idilee addaa fi miseensonni kabajaa;
Duraan dursee guyyaa dhaloota Mana Kiristaana keenya qulqulleettii, kuusaa beekumsa duukaa bu'oota fi jalqaba lallaba wangeelaa kan ta'e Ayyaana Pharaaqliixoos akkasumas guutuu addunyaatti haala ho'aadhaan kan kabajamu #Ayyaana_Guyyaa_Manneen_Barumsaa_Dilbataa_Idil-addunyaa_15ffaatiin nagaa fi fayyaadhaan kan nu ga'e Waaqayyoof ulfinni fi galanni haa ta'u.

Baga Ayyaana Pharaaqliixoos fi Ayyaana Guyyaa Manneen Barumsaa Dilbataa Idil-addunyaa 15ffaan nagaadhaan isin ga'e!

Caamsaa 23 Bara 2018 A.L.I. kan kabajnu guyyaan guddaan kun, Duuka bu'oonni mana Maariyaam haadha Maarqoos keessatti laphee tokkoon kadhannaa fi subaa'eedhaan yommuu jabaatan, Afuurri Qulqulluun bifa arraba ibidaatiin bu'ee daangaa addunyaa cabsuun wangeela akka lallabaniif humnaafi ogummaa guyyaa itti uffatanidha. "Haa ta'u malee, yommuu Afuurri Qulqulluun isin irratti bu'u humna ni argattu, Iyyerusaalemitti, Yihuudaa hundumaatti, Samaariyaatti fi hamma daangaa addunyaatti dhugaa baatota koo ni taatu" Hojii Duuka Bu'oota 1:8

Tokkummaan Manneen Barumsaa Dilbataa Mana lubummaa  teessoo Phaphasummaa barana ayyaana kana Waxabajjii 14/2018 A.L.I. Mana Kiristaana Adaamaa Dabra Naazireet Iyyasuus keessatti qophiiwwan adda addaa qopheessuudhaan isinii wajjin kabajuuf qophii irra jira.

Tokkummaan Manneen barnoota dilbataa ayyaana kana yommuu kabaju,  ergaa Qulqulluun Phaawuloos kiristaanota Efesooniif dabarse  bu'uuraa godhachuudhani: ''Tokkummaa afuuraa eeguuf jabaadhaa" (Efe. 4:3). Ayyaana guddichaa kana sababeeffachuudhaan, Tokkummaan Manneen Barumsaa Dilbataa Aanaa keenyaa utubaa tajaajila keenyaa kan taatan qaamolee hundaaf ergaa baga ittiin isin ga'ee fi waamicha dabarsa:

1. Manneen Barumsaa Dilbataaf

Manneen barumsaa Dilbataa madda beekumsa Mana Kiristaanaa kan ta'an, dhaloota bakka bu'oo borii miseensota mana barumsaa Dilbataa keenyaa gurmaa'iinsa caasaa ijaarameen, sirna barnootaa walfakkaataa fi meeshaleen barsiisuun, dandeettii tajaajiltotaa guddisuun, hojimaata barichaa bite fi jireenya qulqulluudhaan Mana Kiristaanaa fi biyya kallattii hundumaan tajaajilan abbootii beektota, luboota, diiyaqonoota, lallabdoota fi ogeessota hojii adda addaa kan ta'an obboolotaa akkasumas amantaa fi naamusaan kan jabaatan haadhotafi abbootii madda tajaajiltota itti horatanidha. Abbaa tajaajila keenya Eebbifamoo Abuna Gorgooriyoos (Lammaffaan) akka dubbatanitti; “Barattoonni Dilbataa biqiltuu Mana Kiristaanaa fi humna bakka bu'oo boriti.”

Nuti karooras ta'ee hojimaata caasaa ijaarameen har'a hojiin hojjennu jabinna Mana Kiristaana Ortodoksii kan borii kan murteessu waan ta'eef, manneen barnoota dilbataa keenya kan barichaa bite, teknoolojiidhaan kan deeggaramee fi dhaloota dhiibbaa gilobalization fi burjaaja'iinsa sammuu irraa eeguu danda'u karoora tarsiimoo bu'uura godhatee hojjechuu qaba.

Tajaajjilli gargaarsa tola ooltota muraasa qofa irratti rarra'ee namoota hedduu bira ga'uu hin danda'u. Kanaafuu manneen barnoota dilbataa dhaabbata misoomaa adda addaa hundeessuudhaan, hojiiwwan madda galii hojiirra oolchuun ofiin of dandeessuu fi amaanaa Mana Kiristaanaa ba'uu qabu.

2. Miseensota Idileef
Kabajamoo Miseensonni idilee keenyaa isin caasaa keessatti kutaalee adda addaan (barnootaan, bulchiinsa baajataafi qabeenyaa, faarfannaafi kine-xibaabiin, qabeenya humna namaafi qunnamtii uummataa fi kkf) ramadamtanii dirree dhiifamaa, kadhannaa yeroo hundaa, sanbata, ayyaanota adabaabaayii fi tajaajila hawaasummaa keessatti halkanii fi guyyaa kan dhamaatan lafee dugdaa tajaajila guyyaa guyyaati.
👉 #Bakka tajaajilaa itti walitti qabamtan hundatti tokkummaa afuuraa eeguudhaan, garaagarummaa dhiphisuu fi balleessuun, gidduu keessanitti jaalalaa fi nagaa mirkaneessuu qabdu. Tokkummaan keenya meeshaa keenya guddicha diina ittiin mo'anudha.

👉 #Amantaa isaa gadi fageenyaan kan beekee fi kan gaafatamu hundaaf deebii kan qabu dhaloota ta'uuf, beekamtii Qulqulluu Sinoodositiin, yaa'ii beektotatin madaalamee kennamaa kan jiru sirna barnootaa walfakkaataa keessan yeroo kamiyyuu caalaa dammaqinaan hordofuufi naamusa keessaniin fakkeenya jabaa ta'uu qabdu.

3. Miseensota Idilee Addaa fi Kabajaaf
Hojii, barnoota yookiin sababa itti gaafatamummaa hawaasummaa adda addaatiin dhaabbataan caasaa keessatti argamtanii tajaajiluu baattanis; beekumsa, maallaqa, gorsaafi muuxannoo keessaniin mana barumsaa dilbataa keessan cinaa dhaabbatanii tajaajila kan deeggartan miseensota idilee addaa fi kabajaa hundaaf maqaa Mana Kiristaanaatiin galata ol'aanaa dhiheessina.

👉 #Mana barumsaa dilbataa keenya keessa kan jirtan ogeessonni hojii adda addaa (Enginaroonni, ogeessota fayyaa, barsiistotaafi ogeessota seeraa fi kkf) dandeettii keessan dacha dachaa ta'e guddinnaafi misooma manneen barnoota dilbataa keessaniif caalaatti akka gumaachitan waamicha keenya dabarsina.

👉 #"Manneen barumsaa dilbataa kan keenya" yaadaa jedhuun, keessattuu yeroo ammaa kanatti dirqama yeroo keenyaa kan ta'e humna maallaqa jabaa uumuuf carraaqqii gonu keessatti qooda keessan ol'aana gochuun hojiiwwan dhiibbaa uumuu danda'an waliin akka hojjennu waamichi keenya jabaadha.

Walumaagalatti utuu hin gargaarinii fi hin deeggariin iyyuu hamma ammaatti firii wangeelaa hangana buusuu kan danda'an manneen barumsaa dilbataa keenya; qo'annoo fi tokkummaa caasaatiin hundumti keenya idilee, idilee addaa fi miseensonni kabajaa tokkummaadhaan tokko taanee yoo gargaarre addunyaa hundumaa kiristaana gochuuf dandeettii dacha dachaa ta'e qabu.

Ayyaana Pharaaqliixoos fi Ayyaana Guyyaa Manneen Barumsaa Dilbataa Idil-addunyaa 15ffaa kanarratti, Tajaajiltonni Mana lubbummaa Teessoo Phaphasummaa jala jirru hundinuu tokkummaa afuuraa eeguufi hojiidhaan ashaaraa kaa'uudhaf waadaa haa gallu!

Mana Maariyaam haadha Maarqoos keessatti kan bu'e Afuurri Qulqulluun sagalee isaa ibiddichaa, humna isaa samii fi tokkummaa isaan tajaajila keenyaa fi biyya keenya irratti haa dhangalaasu.

Ayyaana Pharaaqliixoos fi Ayyaana Guyyaa Manneen Barumsaa Dilbataa Idil-addunyaa 15ffaa Ayyaanaa Gaarii!
👇👇👇👇👇👇👇👇
Waxabajjii 14/2018 Mana kiristaanaa Adaamaa Dabra Naazireet Iyyasuusitti wal haa arginu 👆👆👆👆👆👆

Yitbaaraki Amlaaka Abawinaa!

Galanii Waaqayyof, Galannii Deessuu Waaqatiif, Galannii Fannoo Gooftaf yaa ta'u Ameen.

Biyya Lallaba Shawaa Ba'aa Wajjira Tokkummaa Mannee Barnoota Dilbataa Mana Lubummaa Aanaa Teessoo Phaaphasii Adaamaa.

Caamsaa 22/2018 A.L.I. Adaamaa, Itoophiyaa