የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
የሰንበት ትምህርት ቤቶች የመማርያ መጻሕፍት ሥርጭት                                                                                            *****

በኢት
ዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ዕድሜን መሠረት ያደረገ ወጥ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት አዘጋጅቶ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በትግበራ ላይ ይገኛል።

ለሥርዓተ ትምህርት ትግበራውም ለረጅም ጊዜያት በቤተክርስቲያን ሊቃውንትና መምህራን እንዲሁ በሥርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች ሲደከምበት የኖረውን የሥርዓተ ትምህርት መማርያ መጻሕፍት በባለፈው ዓመት ከ1ኛ-4ኛ ክፍል 23 የመማሪያ መጻሕፍት በማሳተም በሥርጭት ላይ ማዋሉ ይታወቃል።

በዘንድሮውም ዓመት ደግሞ በአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ

👉 ከ1-4ኛ ክፍል 23 የኦሮምኛ ትርጉም የመማርያ መጻሕፍት በአራት ጥራዝ

👉 ከ5ኛ እስከ 7ኛ ክፍል በ3 ጥራዝ የተዘጋጁ 18 መጻሕፍት በአጠቃላይ 41 መጻሕፍት  ተዘጋጅተው ለኅትመትና ለሥርጭት በቅተዋል።  

ለሕዝበ ክርስቲያንም በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡


(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
🙏2
በምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት በመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ  (አዳማ ) ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርቱን እያስተማሩ ከሚገኙ መምህራን ጋር  በትምህርት አተገባበሩ ዙርያ  በቀን 20/07/2017 ዓ.ም ውይይት እና ስልጠና ተከናወነ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የመንበረ ጵጵስና ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በ2014 ዓ.ም በ2 ሰ/ት/ቤቶች ብቻ የተጀመረውን የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ በማጠናከር  በአሁኑ ሰዓት በከተማው በሚገኙ 26 ሰ/ት/ቤቶች እየተገበረ የሚገኝ ሲሆን ፤ ባለፉት 3 ዓመታት ለሥርዓት ት/ቱ ባለ ድርሻ አካላት ብዙ ስልጠናዎች  ሰጥቷል።የዛሬው ሰልጠና በዋናነት “የማስተማር  ሥነ -ዘዴ” ላይ ያተኮረ ሲሆን ፤ ስልጠናው  ከመንበረ ፓትርያርክ  የጠቅላይ ቤተ ክህነት  ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በመጡት መ/ር ያረጋል ተሰጥቷል። በስልጠናው የሰ/ት/ቤት አባላት ፣ሰባኪያነ ወንጌል እና  የአብነት መምህራን የተሳተፋ ሲሆን ከስልጠናው በተጨማሪ መምህራን በማስተማር ሒደቱ ያጋጠሟቸውን ችግሮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደረጓል።   
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።             የመንበረ ጵጵስናው ሰ/ት/ቤቶች አንድነት
👍3🙏2
ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሰንበት ት/ቤቶች መማሪያ መጸሐፍት የአርትዖ ሥራ መርሐ ግብር ተካሔደ።
የመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሚዘጋጀው የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መማሪያ መጻሕፍት ከ1-7ኛ ክፍል በአማርኛ እንዲሁም 1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ደግሞ በኦሮምኛ ቋንቋ አዘጋጅቶ ለኅትመት እና ሥርጭት ማብቃቱ ይታወቃል።  አሁን ደግሞ ከ8-12ኛ ክፍል ያሉትን የመማሪያ መጸሐፍት አዘጋጅቶ ለማጠናቀቅ ባሳለፍነው ሳምንት ከመጋቢት 19 እስከ 21 ለ3 ተከታታይ ቀናት በጌቴሰማኔ ቤተ ደናግል ጠባባት የሴቶች ገዳም  የ8ኛ እና የ9ኛ ክፍል መጸሐፍትን የአርትኦት ሥራ ማካሔዱን በመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወ/ትንሣኤ ገልጸዋል። በዚህ የአርትኦት ሥራ የሊቃውንት ጉባኤ ምክትል ሐላፊ መጋቤ ምሥጢር ፍሬ ስብሐት ዱባለን ጨምሮ መምሪያው ሊቃውን ፣ የነገረ መለኮት ምሁራን ፣  የሰንበት ት/ቤቶች መምህራን እና የሥርዓተ ትምህርት ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
የመምሪያው ሐላፊ  እንደገለጹት የአርትኦት ሥራውን አርታኢያኑ በ3 ምድብ ተከፋፍለው የሠሩት ሲሆን  በእያንዳንዱ ምድብ ከ3-4 መጸሐፍት አርትኦት እንደተደረጉ እንዲሁም በአርትዖ ሥራው ላይ በየቡድኑ ቀርበው የነበሩ አሻሚ ጉዳዮች ላይ ሁሉም የአርትዖ ኮሚቴ ዓባላት ባሉበት በአንድነት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው መፍትሔ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
በአርትኦት ሥራው ተሳታፊ የነበሩት ዓባላትም ቆይታቸው የተሳካ የአርትዖ ሥራውም ውጤታማ እንደነበር ገልጸዋል። በመጨረሻም በዚህ የአርትኦት ሥራ ላይ ጊዜያቸውን ሰጥተው ለተሳተፉ የአርትኦት ኮሚቴ አባላት በሙሉ የመምሪያ ሓላፊ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወ/ትንሣኤ ምስጋናን አቅርበዋል።
👍1
ሁሉም የሰ/ት/ቤት አባላት በሥርጭት ላይ የሚገኘውን የሰ/ት/ቤት መማርያ መጻሕፍትን እንዲገዙ የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጥሪ አቀረበ፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………….
መጋቢት 24/2017 ዓ.ም
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………….
በትግበራ ላይ የሚገኘው የሰ/ት/ቤት ሥርዓተ ትምህርት ግቡን እንዲመታ ከሚያስፈልጉት ሥራዎች አንዱ ለተማሪዎች የመማርያ መጻሕፍትን ለመማር አመቺ በሚሆን መልኩ ማዘጋጀት ሲሆን ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰ/ትቤቶች አንድነት ከ1ኛ -- 7ኛ ክፍል በአማርኛ ፤ ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል በአፋን ኦሮሞ በድምሩ 64 የመጻሕፍት ዓይነቶች ተዘጋጅተው በሊቃውንት ጉባኤ ታርመውና ታትመው በቅናሽ ዋጋ እየተሠራጩ ሲሆን ከ8ኛ -12ኛ ክፍል ያሉት የመማርያ መጻሕፍት ደግሞ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ የመንበረ ጵጵስና ሰ/ት/ቤቶች አንድነትም ብዛት ያላቸውን መጻሕፍት በሰ/ት/ቤቶች ጥያቄ መሠረት መጻሕፍቶችን በማስመጣት እያሠራጨ ይገኛል፡፡
ይህ መጻሕፍት ለትውልድ እንዲዳረስ ፤ ትውልዱ መጻሕፍቶቹን ተጠቅሞ ሃይማኖቱን እንዲያውቅ ፤ ሕይወቱን በኦርቶዶክሳው መንገድ እንዲመራ ያግዝ ዘንድ በሁሉም አጥቢያ የሚገኙ የሰ/ት/ቤት አባላት በየሰ/ት/ቤቱ መጻሕፍቱን ለመግዛት በመመዝገብ፤ ወላጆች ለልጆቻቼው መጻሕፍቱን በመግዛት ፤ ማሕበረ -ካህናትና ሰባኪያን በማስተዋወቅ ፤ ሰ/ት/ቤቶች መጻሕፍቱን የሚፈልጉትን ወላጆችና ሰ/ት/ቤት አባላትን በመመዝገብና በማስተባበር እንዲሁም መረጃን ለሁሉም በማዳረስ ሃይማኖታዊ ኃላፊነታችን እንድንወጣ የሀ/ስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከሀገር አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የመጣው መጻሕፍት በመንበረ ጵጵስና ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ቢሮ እየተሠራጨ ይገኛል፡፡
………………………………………………………………………………….
መረጃው የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው፡፡
4