የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.12K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
Kutaa Lallaba Shawaa Bahaatti Tokkummaan manneen barnoota dilbataa mana lubbummaa teessoo phaaphasii magaalatti qormaataa/ madaallii simisteraa tokkoffaa kennisiise jira.
Tokkummaan manneen barnoota dilbataa mana lubbummaa teessoo phaaphasii magaalatti manneen barnoota dilbataa aanicha jalatti argaman 26 irratti sagantaa tokkummaan manneen barnoota dilbataa waligalaa biyyaa baasee irratti hundaa’ee guraandhala 23/2017 B.A kutaa 1ffaa- 5ffaa fi guraandhala 30/2017 B.A kutaa 6ffaa-9ffaa kan jiran manneen barnoota dilbataa kariikulamii haaraawa sirna barnoota barattoota dilbataatin barsiisa jiran irratti madaalii qormaata simisteeraa tokkoffaa kennisisee jira.
👍1
የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ከ14 አጥቢያ ሰ/ት/ቤት የሰበሰበውን 105000 ቢር ለመቄዳንያ ድጋፍ አደረገ።
👏10👍7
የና/ደ/መ/መድኃኔዓለም ገዳምና ካቴድራል ፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት ከገዳሙና ከካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ በመተባባር ለገዳሙና ካቴድራሉ ማኅበረ ካህናት የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መርሐግብር አካሔድዋል፡፡ ሥልጠናው የተሰጠው ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድንት አገልጋይ በየሆኑት ቀሲስ አለማየሁ ሲሆን ከሥልጠናው በተጨማሪ ከማኅበራት ካህናት በተሰኑ ጥያቄዎች ላይ በቂ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ጳውሎስ መርሐግብሩን በጸሎት በማስጀመር የሥልጠናውን ዓላማውን በመግለጸ መርሐግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን ማኅበረ ካህናቱም በሥርዓተ ትምህርቱ ተግበራ ላይ ከማስተማረ ጀምሮ በንሰሐ ልጆቻቸው በኩል ሰፊ የቅስቃሳና ሥርዓተ ትምህርቱን የማስተዋወቅ ሥራ እንዲሰሩ  መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም መሰል ሥልጠናዎች ጠቀሜታቸው የጎላ በመሆኑ እንዲሚቀጥሉም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
👍5
የአንተ ሥራ

የአንተ ሥራ የአንተ ሥራ
የአንተ ሥራ ለዓለም ይወራ /2/
አዝ

በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት
መጻጉዕ ተብሎ ተኝቶ ባዐራት
ዘመን ያስቆጠረ ሠላሳ ስምንት
ተነሳ ተባለ አገኘ ምህረት
አዝ

ሰውነቱ ደቆ እጅግ የታመመ /2/
በሱ ድንቅ ስራ አልጋ ተሸከመ /2/
አዝ

ወገን ያልነበረው ወድቆ የተረሳ /2/
ምሕረት አገኘና በድንገት ተነሳ /2/
አዝ

ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ሲናገር
ያልተፈቀደውን ይሄው ሰንበት ሲሽር
አየነው ሰማነው አያሻም ምስክር
ብለው ተነሱበት በጠማማ ምክር

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት  ከማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል እና ማኅበራት ጥምርት ጋር በመተባባር  ተግዳሮትን መቋቋምና  ዕድሎችን መጠቀም በምል ርዕስ ሥልጠና  ለአጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ሥራ አመራር እና ሥራ አስፈጻሚ እንድሁም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ፤ግቢ ጉባኤያት  እና የማኅበራት ተወካዮች በማሳተፍ ሥልጠና አሰጠ፡፡
ደብረ ዘይት (እኩለ ጾም)

"ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳት በፊት ይነዳል።" መዝ 49(50)፡2-3

መልካም ዕለተ ሰንበት!
የበረከት ጾም ያድርግልን።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
የናዝሬት ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ገዳምና ካቴድራል ፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት የሥራ አመራር ልዑካን ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ከሚገኙ ከሦስት ሰ/ት/ቤቶችን ጋር የልምድ ልውውጥ መርሐግብር አካሔደ፡፡ የልምድ ልውውጥ መርሐግብሩ ዋና ዓላማው የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው አቻ ሰ/ት/ቤቶች ጋር የአፈጻጸም ተሞክሮ መውሰድና ልምድ በመቅሰም የሰ/ት/ቤቱን አገልግሎቱን ማጠናከር ነው፡፡ የሰ/ት/ቤቱ የሥራ አመራር ልዑካንም ከመናገሻ ገነት ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት፣ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ  ኆኅተ መንግሥተ ሰማይ ሰ/ት/ቤት እና የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ  ውልደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጋር በሰ/ት/ቤቶቹ የማኅበራዊ አገልግሎት በተለይም በነድያን አገልግሎት፣ በሥርዓተ ትምህርት አተገባበርና በመዋቅራዊ አደረጃጀት ዙሪያ ልምድ የተወሰደ ሲሆን በተጨማሪነትም ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይም ልምድ ለመውሰድ ተችሏል።

👉👉 መረጃው ከሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት👈👈