የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.12K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የመንብረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2017 ዓ.ም አንደኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ምዘና አሰጠ፡፡
የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በወረደ ሥር ላሉ 26 አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ለይ በሀገረ አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በወጠ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በ23/06/2017 ከ1ኛ -5ኛ ክፍል   እና በ30/06/2017 ዓ.ም ከ6ኛ - 9ኛ ክፍል ያሉ አዲሱን የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት እየተገበሩ ላሉ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ላይ ምዘና አሰጥቷል፡፡
2👍1
Kutaa Lallaba Shawaa Bahaatti Tokkummaan manneen barnoota dilbataa mana lubbummaa teessoo phaaphasii magaalatti qormaataa/ madaallii simisteraa tokkoffaa kennisiise jira.
Tokkummaan manneen barnoota dilbataa mana lubbummaa teessoo phaaphasii magaalatti manneen barnoota dilbataa aanicha jalatti argaman 26 irratti sagantaa tokkummaan manneen barnoota dilbataa waligalaa biyyaa baasee irratti hundaa’ee guraandhala 23/2017 B.A kutaa 1ffaa- 5ffaa fi guraandhala 30/2017 B.A kutaa 6ffaa-9ffaa kan jiran manneen barnoota dilbataa kariikulamii haaraawa sirna barnoota barattoota dilbataatin barsiisa jiran irratti madaalii qormaata simisteeraa tokkoffaa kennisisee jira.
👍1
የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ከ14 አጥቢያ ሰ/ት/ቤት የሰበሰበውን 105000 ቢር ለመቄዳንያ ድጋፍ አደረገ።
👏10👍7
የና/ደ/መ/መድኃኔዓለም ገዳምና ካቴድራል ፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት ከገዳሙና ከካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ በመተባባር ለገዳሙና ካቴድራሉ ማኅበረ ካህናት የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መርሐግብር አካሔድዋል፡፡ ሥልጠናው የተሰጠው ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድንት አገልጋይ በየሆኑት ቀሲስ አለማየሁ ሲሆን ከሥልጠናው በተጨማሪ ከማኅበራት ካህናት በተሰኑ ጥያቄዎች ላይ በቂ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ጳውሎስ መርሐግብሩን በጸሎት በማስጀመር የሥልጠናውን ዓላማውን በመግለጸ መርሐግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን ማኅበረ ካህናቱም በሥርዓተ ትምህርቱ ተግበራ ላይ ከማስተማረ ጀምሮ በንሰሐ ልጆቻቸው በኩል ሰፊ የቅስቃሳና ሥርዓተ ትምህርቱን የማስተዋወቅ ሥራ እንዲሰሩ  መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም መሰል ሥልጠናዎች ጠቀሜታቸው የጎላ በመሆኑ እንዲሚቀጥሉም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
👍5