የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረደ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተዘጋጀው የአንደኛ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከ1ኛ _ 5ኛ ክፍል በሁሉም አጥቢያ የተሰጠው በሰላም ተጠናቋል። የረዳን እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን
የና/ደ/ቤቴል ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አንደኛው መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና
👍3
ሰንበት ቅድስት

ሰንበት ቅድስት ዕለተ ዕረፍት
የደስታ ቀን ናት ዕለተ ትፍሥሕት
የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን አይተው
ያመሰገኑባት ሥሉስ ቅዱስ ብለው
አዝ
በዕለተ ሰንበት ከሰማይ ወረደ
በድንግል ማኅፀን ሥጋን ተዋሐደ
ሰንበትን ቀደሳት ከዕለታት ለይቶ
ሞትን አሸንፎ ከመቃብር ወጥቶ
ኑ እናክብራት ኑ እንቀድሳት
የበዓላት በኩር ሰንበት ቅድስት ናት/2/
አዝ
ጌታ በሰንበት ነው ሥልጣኑን ያሳየ
ሰይጣንን ከሰው ልብ በቃሉ የለየ
ጎባጣ ያቀና ድውይ የፈወሰ
የስውራንን ዐይን ብርሃን የመለሰ
ኑ እናክብራት ኑ እንቀድሳት
የበዓላት በኩር ሰንበት ቅድስት ናት/2/
አዝ
ኑ በቅዳሴ በማኅሌት እናክብር
ጌታችን ሲመጣ እንዳይዘጋብን በር
የሰንበት ጌታዋ በሰንበት ይመጣል
ቅድስቷን ከተማ ለጻድቃን ያወርሳል
ኑ እናክብራት ኑ እንቀድሳት
የበዓላት በኩር ሰንበት ቅድስት ናት/2/
አዝ
ዛሬ ለምስጋና ለቁርባን መጥተናል
ለሚመጣው ሕይወት እርሱ ያዘጋጀናል
ዛሬ የሰማነው የወንጌሉ ቃል ነው
ለዘላለም ሕይወት ለክብር የሚያበቃው
ኑ እናክብራት ኑ እንቀድሳት
የበዓላት በኩር ሰንበት ቅድስት ናት/2/

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
መዝ 68፡9 እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡

የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡
3👍2
😭10
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የመንብረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2017 ዓ.ም አንደኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ምዘና አሰጠ፡፡
የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በወረደ ሥር ላሉ 26 አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ለይ በሀገረ አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በወጠ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በ23/06/2017 ከ1ኛ -5ኛ ክፍል   እና በ30/06/2017 ዓ.ም ከ6ኛ - 9ኛ ክፍል ያሉ አዲሱን የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት እየተገበሩ ላሉ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ላይ ምዘና አሰጥቷል፡፡
2👍1