የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ዘወረደ
ዘወረደ ማለት "ከላይ የመጣ፣ የወረደ'' ማለት ነው።  ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን "ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ፤ አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይ ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም"  እያለች በሰንበት ዋዜማ ዜማውን መሐትው (መግቢያ) አድርጋ የሳምንቱን ዜማ በማስተጋባት የጌታችንን ከሰማይ መውረድ ታመሠጥርበታለች፤ ታመሰግንበታለች። (ጾመ ድጓ፥ ዘዘወረደ ዋዜማ)
ይህን ሳምንት በልዕልና በዘለዓለማዊ ቅድስና እና በማትመረመር ጥበብ ራሱን ሰውሮ የሚኖር አምላክ በገሃድ  ለሰው ልጅ የተገለጠበትን፣ ዘለዓለማዊ አምላክ ሰውን ከተደበቀበት  ለመፈለግ ብሎ ''ኦ አዳም አይቴ ሀሎከ- አዳም ሆይ ወዴት ነህ" እያለ በማያልቅ የፍቅር ድምፅ ፍለጋ ወደ ዱር (ወደ ዓለም) የገባበትን ሳምንት የምንዘክርበት ነው። አምላካችን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ምን ያህል በበዛ ፍቅሩ እንደሚፈልገው፣ ከፍ ላለ ዓላማውም እንዳጨው ያሳየበት፣ ከሁሉም ደግሞ በሕሊና ሊታሰብ የማይችለውን የሰማይ አኗኗሩን ትቶ በሚታይ የአዳም ሥጋ የተገለጠበት፣ መጋረጃው እሳት፣ ዙፋኑ እሳት፣ ልብሱ እሳት የሆነው አምላክ በሚበሰብስ ሥጋ የተገለጠበት፣ በጨርቅ፣ ያንን የሚያስደነግጥ መለኮታዊ ክብሩን ስለ ሰው ልጅ መዳን ተጨንቆ በሕፃን አምሳል ተገልጦ በበረት የተገኘበትን ሳምንት እናስብበታለን።
🙏3
ነፍሴ ሆይ

ነፍሴ ሆይ /3/ እግዚአብሔርን ባርኪ
አጥንቶቼም ሁሉ /3/ የተቀደሰ ስሙን

በደስታ ዘምሪ በአዲስ ምስጋና
ጸጥታ እና ሰላም አድሎሻልና
መሠንቆውን አንሺ ቅኔ ተቀኚለት
ለውጦሻልና በደስታ ዘይት
አዝ

ሀሴትን አድርጊ ነፍሴ በእግዚአብሔር
ይሰጥሻልና በክብር ላይ ክብር
ደሴቶች ሲያወሩ በደስታ መንፈስ
እየተወያዩ ስለ ሥሉስ ቅዱስ
አዝ

ሰማያት ሲያወሩ ጽድቅን ሲወያዩ
ሲጠራው አድምጪ ቀላዩን ቀላዩ
ደመናው ጭጋጉ በዙሪያው ከበውት
ቅኔ ያቀርባሉ ለፍጥረታት አባት
አዝ

መብረቅም ይሰማል ሰማዩን ሰንጥቆ
ምስጋናውን ሊያቀርብ ጊዜውን ጠብቆ
በፊቱ ይነዳል እሳትም በግርማ
ምድር ተናወጠች ነጎድጓዱን ሰምታ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
የ2017 ዓ.ም የአንጀኛ ዓመት የመንፈቀ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
*******

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media
Adama, Ethiopia

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አንደኛ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና በወረዳው በሚገኙ ካቴድራል አድባራትና ገዳማት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ገለጸ፡፡

በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ከ6960 በላይ ( ከስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ተማሪዎች በሃያ ስድስቱም አብያተ ክርስቲያናት የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ባወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ሲሆን:-

👉 ከ1ኛ-5ኛ ክፍል የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም
- ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
ከ6ኛ-9ኛ ክፍል የካቲት 30 ቀን/ 2017 ዓ.ም
- ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት

በአፋን ኦሮሞ እና በአማረኛ እንደሚሰጥ የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/አንድነት ጽ/ቤት ለሚዲያችን ገልጿል።

#ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን #ሰንበት #ትምህርት #ቤት #አዳማ
👍5
እንኳን ለአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

"በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።
በቀስቴ የምታመን አይደለሁምና፥ ሰይፌም አያድነኝምና፤ አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን፥
የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው።" መዝ 43(44) ፡ 5 - 7

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
በመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረደ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተዘጋጀው የአንደኛ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከ1ኛ _ 5ኛ ክፍል በሁሉም አጥቢያ የተሰጠው በሰላም ተጠናቋል። የረዳን እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን
የና/ደ/ቤቴል ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አንደኛው መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና
👍3