የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
🎤🎤🎤መልካም ዜና ❤️❤️❤️❤️
የሥርዓተ ትምህርት መመሪያ መጽሐፍት 🔔🔹 ከ 1ኛ_4ኛ ክፍል በኦሮምኛ ቋንቋ
🔷🔷ከ5ኛ _7ኛ ክፍል በአማርኛ ቋንቋ ሕትመቱ ተጠናቋል ።
👍3
🎤🙏❤️ Oduu Gammachisaa🌷❤️🙏
Kitaabni Sirna Barnoota Barattoota Dilbataa kan kutaa
1ffaa_4ffaa Afaan Oromoon
Kutaa 5ffaa_7ffaa Afaan Amaariffaan qophaa'ee maxxansi isaa dhumee jira.
የግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት  የአገልጋይ እጦት እንደገጠመው ተገለጸ።

የመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የሚገኙ አባላት የልማት ተነሺዎች መሆናቸው አገልግሎቱን እንዳሰተጓጎለውም ተጠቁሟል። 

አቶ ዘውዱ ከተማ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሰብሳቢ ከማኀበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ በአካባቢው የሚኖር ሰውና ምእመን በመቀነሱ ሳምንታዊ ፕሮግራሞችን ወደ ወርሀዊ የመቀየር፣ሕጻናት ባሉበት ሆነው እንዲማሩ ዕድሉን እንዲያገኙ የማመቻቸት እና የኦላይን ትምህርቶችን ለመስጠት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ 

የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላቱ በኢኮኖሚያዊ፣በማኅበራዊ ጉዳዮች በተለይም በሃይማኖታዊ አንጻር ቃለ እግዚአብሔር እንዳይሰሙ ጫና እንደደረሰባቸው የሰንበት ትምህርት ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዘነበ ክፍሉ ተናግረዋል።

በአገልጋይ እጦት ምክንያት አንዳንድ ክፍሎች መታጣፋቸውን የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባል የሆኑት መቅደላዊት ተሾመ የተናገሩ ሲሆን ያሉትም ጥቂት አባላቶች ክፍሎችን ደርበው እንዲያገለግሉ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ችግሩን ለማቃለል በገዳሙ ውስጥ የሚገኙ አባቶችን በመጠቀም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላቱ እንዲመጡ ቅስቀሳ የማካሄድ እና በወር አንድ ጊዜ ጉባኤ በማዘጋጀት እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን አባሏ አንስተዋል፡፡

ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው።
😢4👍2
"ጾምን የምንጾመው  ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ  ነው::" ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የዐቢይ ጾምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ !

የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ /አዲስ አበባ)

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው መነሻ <<ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ወደ በረኻ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡>> በማለት የጌታችንና አምላካችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጾሙን ጥንተ ነገር አውስተዋል።

ቅዱስነታቸው በአርባ ቀናት ውስጥ የጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዲያቢሎስ መፈተንና ድል መንሳትም አብራርተው  ሲያወሱ <<በዚህ ጊዜ የጌታችን መልስ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” የሚል ነበረ፤
ጌታችን በዚህ አባባሉ የዲያብሎስን ክፉ ሐሳብ የሚንድ እንጂ የእሱ ታዛዥ አለመሆኑን ኣሳየ፤ ዲያብሎስ በዚህ ሳያበቃ በትዕቢት በፍቅረ ንዋይና በባዕድ አምልኮ ሊጥለው ደጋግሞ ሙከራ አደረገ፤ ግን አልተሳካለትም፤>> ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የመጾማችንን ምክንያት ሲያጠይቁ <<...የዲያብሎስን ፈተናዎች እንዴት በድል ማለፍ እንደምንችል ጌታችን በተግባር ኣሳይቶናል፤ ጌታችን ዲያብሎስን ያሸነበፈበት ስልት በመንፈስ ልዕልና እንጂ በዱላም፣ በካባድ መሳሪያም ኣይደለም፤ አለመሆኑንም የድርጊቱ ሂደት በግልጽ ያመለክታል፤ እንግዲያውስ እኛም ዲያብሎስን የምናሸንፈው በዚህ የመንፈስ  ልዕልና ነው ማለት ነው::... ስለሆነም ጾምን የምንጾመው በዚህ ስልት ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ  ነው::
ከዚህ አኳያ ዲያብሎስን ለማሸነፍ መጾም ግድ ስለሆነ ጌታችን በከፈተልንና ባሳየን መንገድ እንጾማለን>> ብለዋል።

ስንጾምም <<የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት፣ ከዚያም ከቃሉ በተነገረን መሠረት የተራቡትን ልንመግብ፣ የተራቈቱትን ልናለብስ፣ የተጣሉትን ልናስታርቅ፣ ፍትሕ ያጡትን ፍትሕ እንዲያገኙ ልናደርግ፣ ለንኡሳን የሕብረተ ሰብ ክፍሎች የተለየ ትኵረት ልንሰጥ፤ እኩልና ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል በሰው ልጆች መካከል ልናረጋግጥ፣ ሰብኣዊ ክብር እንዳይነካ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ አደገኛ የቃላት ውርወራና መነቃቀፍ እንዲቀር ልናደርግ ነው፤>> በማለት አጽንዖት ሰጥተው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጾም የሥጋ ምኞትን የምታጠፋ የነፍስን ቁስል የምታደርቅ  ለጎልማሶችም ጸጥታንና እርጋታን የምታስተምር ደገኛ ሥርዓት ነች፡፡
👍2
ዘወረደ
ዘወረደ ማለት "ከላይ የመጣ፣ የወረደ'' ማለት ነው።  ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን "ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ፤ አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይ ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም"  እያለች በሰንበት ዋዜማ ዜማውን መሐትው (መግቢያ) አድርጋ የሳምንቱን ዜማ በማስተጋባት የጌታችንን ከሰማይ መውረድ ታመሠጥርበታለች፤ ታመሰግንበታለች። (ጾመ ድጓ፥ ዘዘወረደ ዋዜማ)
ይህን ሳምንት በልዕልና በዘለዓለማዊ ቅድስና እና በማትመረመር ጥበብ ራሱን ሰውሮ የሚኖር አምላክ በገሃድ  ለሰው ልጅ የተገለጠበትን፣ ዘለዓለማዊ አምላክ ሰውን ከተደበቀበት  ለመፈለግ ብሎ ''ኦ አዳም አይቴ ሀሎከ- አዳም ሆይ ወዴት ነህ" እያለ በማያልቅ የፍቅር ድምፅ ፍለጋ ወደ ዱር (ወደ ዓለም) የገባበትን ሳምንት የምንዘክርበት ነው። አምላካችን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ምን ያህል በበዛ ፍቅሩ እንደሚፈልገው፣ ከፍ ላለ ዓላማውም እንዳጨው ያሳየበት፣ ከሁሉም ደግሞ በሕሊና ሊታሰብ የማይችለውን የሰማይ አኗኗሩን ትቶ በሚታይ የአዳም ሥጋ የተገለጠበት፣ መጋረጃው እሳት፣ ዙፋኑ እሳት፣ ልብሱ እሳት የሆነው አምላክ በሚበሰብስ ሥጋ የተገለጠበት፣ በጨርቅ፣ ያንን የሚያስደነግጥ መለኮታዊ ክብሩን ስለ ሰው ልጅ መዳን ተጨንቆ በሕፃን አምሳል ተገልጦ በበረት የተገኘበትን ሳምንት እናስብበታለን።
🙏3