የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ጌታ የሚወደው መባል እንዴት መታደል ነው! ጌታ ፍቅሩን የገለፀበት ከስጦታዎች ሁሉ ስጦታ እመቤታችንን ለእናትነት የሰጠው ፤
በመከራ ጊዜ ያልተለየው ታላቁ ሐዋርያ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው!

መልካም በዓል! መልካም ዕለተ ሰንበት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
🙏5👍1
የክርስቲያን የመጀመሪያ ጠባይ መሆን ያለበት አንዲት በሆነች እምነት ፍጹም አንድ የሆነና ራስ ወዳድ ባልሆነ መንፈስ መዋደድ ነው፡፡

ለቅዱስ ፖሊካርፐስ በላከው መልዕክቱ እንዲህ ይላል፡- ለአንድነት ትኩረት ስጥ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና፤ እግዚአብሔር አንተን እንደ ያዘህ ሁሉንም በደንብ ያዛቸው፤ በሕይወትህ እንደ ፍጹም ሯጭ ሁን፡፡ ሥራው ድካሙ ብዙ ነው፤ ነገር ግን የሚገኘው የበለጠ ነው፡፡

ክርስቶስ በሞትና በሰይጣን ላይ ድል በማድረጉ ምዕመናን ከአምላክ ሕይወትንና ፍቅርን አግኝተዋል፡፡እንዲሁም ከወንድሞቻቸው ጋር በክርስቶስ አንድ ሆነዋል፡፡በክርስቶስ ላለን ሕይወት እምነት የመጀመሪያው ነው፤ ፍቅር ግን የመጨረሻው ነው፡፡ የሁለቱም አንድነት እግዚአብሔር ነው፡፡
🌷🌷🌷🌷ሰ/ት/ቤቶች አንድነት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹
አዳማ
👍2
ጥር 6 ከዘጠኙ የጌታችን ንዑሳት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው በዓለ ግዝረት ነው።

"ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።" ሉቃ 2፡21

መልካም በዓል!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
1👍1🙏1
እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ጥር 7 በዚህች ቀን ቅድስት ሥላሴ  የሰናዖርን ግንብ ያፈረሱበት መታሰቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው።

"ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ቋንቋ እንዳይሰማ ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።" ዘፍ 11፡7

መልካም በዓል!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
🥰51
የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረደ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት የጥምቀት ወረብ ጥናት ከወራት በፊት የጀመረ ስሆን በደ/ፀ/ቅ/ማርያም ካቴድራል ት/ቤት እና የሀገረ ስብከቱ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ከ17 አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች የተወጣጡ ከ250 ዘማሪያን በለይ ተሳትፎ ያደረጉበት የነበረው ጥናት በ04/05/2017 ዓ.ም ተጠናቋል ።