የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.12K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ዛሬ ግን ስለ ሰው ፍቅር ከሰማይ የወረደውን፣ በጎል (በበረት) የተጣለውን፣ በጨርቅ የተጠቀለለውን አምላክ ከሰው ልጅ ጋር በአንድነት ለማመስገን መጡ፡፡ ‹‹ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ ንጉሥ፤ ሰውና መላእክት፣ ንጉሥ ክርስቶስን ያመሰግኑ ዘንድ ተባበሩ›› እንዲል፡፡መላእክት በተፈጥሯቸው የማይሞቱ (ሕያዋን) ሲሆኑ ሰው ደግሞ ሟች ነው፤ ሞት ይስማማዋል፡፡ በጌታችን ልደት ግን መላእክትና የሰው ልጆች በአንድ ማኅበር፣ በአንድ ቃል ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር›› እያሉ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡
ይህም የሆነው በጌታችን መወለድ ምክንያት ነው፡፡ በጌታችን ልደት ምክንያት እኛም ዳግመኛ ተወለድን፡፡ የጌታችን ልደት የእኛም የክርስቲያኖች ሁሉ ልደት ነው፡፡ ከሦስቱ የቀጰዶቅያ አባቶች አንዱ፣ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ይህን ምሥጢር ሲገልጥ ‹‹የክርስቶስ ልደት የመላው ሰው የልደት ቀን ነው›› ሲል መስክሯል፡፡
እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አደረሳችሁ

🌷🌷🌷🌷🌷ሰ/ት/ቤቶች አንድነት
👍1
Har’a garuu jaalala ilma namaaf Waaqayyoo isa samii irraa bu’ee, mooraa keessatti gatamee, Waaqa isaa huccuudhan maramee sana ilma namaa waliin ta’uun faarsuuf dhufan."ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ ንጉሥ፤ ሰውና መላእክት፣ ንጉሥ ክርስቶስን ያመሰግኑ ዘንድ ተባበሩ›› እንዲል፡፡  Kunoo, ergamoonni Kiristoos Mootichaaf sitti haa lallaban; Namni fi ergamoonni walitti makamuun Kiristoos Mooticha galateeffatan Ergamoonni uumama isaaniitiin kan hin duune (jiraataa) fi namni du’aa dha. Duuti isaaf mijata. Garuu gaafa Gooftaan keenya dhalate ergamoonni fi ilmi namaa jecha tokkoon "ስብሐት ለእግዚአብሔር" jechaa garee tokko ta'anii Waaqayyoon galateeffachaa turan.
Kunis kan ta'e dhalachuu Gooftaa keenyaati. Sababa dhalachuu Gooftaa keenyaatiin lammata dhalanne. Guyyaan dhaloota Gooftaa keenyaa Iyyasuus Kiristoos guyyaa dhaloota kiristaana hundaati. Abbootii Qaphadooqiyaa sadan keessaa tokko, abbaan mana kiristaanaa guddichi Qulqulluu Baasiliyoos kan Qeesariyaa, iccitii kana yommuu mul'isu "guyyaan dhaloota Kiristoos guyyaa dhaloota nama hundumaati" jechuun ragaa ba'eera.
Baga dhalachuu Gooftaa Keenya Iyyasuus Kiristoosin isin gahe.

🌷🌷🌷🌷Tokkuummaa Manneen Barnoota Dilbataa
👍2
የልደቱን በዓል በልደቱ ቦታ በዋዜማ እንዲህ እንድናከብር የረዳን እግዚአብሔር ይመስገን።
ሁላችንንም እንኳን ለልደት በዓሉ በሰላም አደረሰን።
🥰9
ጌታ የሚወደው መባል እንዴት መታደል ነው! ጌታ ፍቅሩን የገለፀበት ከስጦታዎች ሁሉ ስጦታ እመቤታችንን ለእናትነት የሰጠው ፤
በመከራ ጊዜ ያልተለየው ታላቁ ሐዋርያ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው!

መልካም በዓል! መልካም ዕለተ ሰንበት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
🙏5👍1
የክርስቲያን የመጀመሪያ ጠባይ መሆን ያለበት አንዲት በሆነች እምነት ፍጹም አንድ የሆነና ራስ ወዳድ ባልሆነ መንፈስ መዋደድ ነው፡፡

ለቅዱስ ፖሊካርፐስ በላከው መልዕክቱ እንዲህ ይላል፡- ለአንድነት ትኩረት ስጥ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና፤ እግዚአብሔር አንተን እንደ ያዘህ ሁሉንም በደንብ ያዛቸው፤ በሕይወትህ እንደ ፍጹም ሯጭ ሁን፡፡ ሥራው ድካሙ ብዙ ነው፤ ነገር ግን የሚገኘው የበለጠ ነው፡፡

ክርስቶስ በሞትና በሰይጣን ላይ ድል በማድረጉ ምዕመናን ከአምላክ ሕይወትንና ፍቅርን አግኝተዋል፡፡እንዲሁም ከወንድሞቻቸው ጋር በክርስቶስ አንድ ሆነዋል፡፡በክርስቶስ ላለን ሕይወት እምነት የመጀመሪያው ነው፤ ፍቅር ግን የመጨረሻው ነው፡፡ የሁለቱም አንድነት እግዚአብሔር ነው፡፡
🌷🌷🌷🌷ሰ/ት/ቤቶች አንድነት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹
አዳማ
👍2