"ዓለም እንደ አጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወስምንቱ ዓመተ ምሕረት!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን-
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ከሀገር ዉጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፣
በቤዛዊ መሥዋዕትነቱ ከሞተ ኃጢአት ታድጎ የትንሣኤ ሙታንን በር የከፈተልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
"ወአነ እሜው ነፍስየ ቤዛ አባግዕየ ከመ ካዕበ አንሥእ፤አንሥእ፤
ዳግመኛ አነሣት ዘንድ ነፍሴን የበገቼ ቤዛ አድርጌ እሰጣለሁ ዮሐ 10፥17
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰብአዊ ክዋኔው ሰው ቢሆንም በመለኮታዊ ክዋኔው የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃል ወይም ወልደ እግዚአብሔር ነው፣

በመሆኑም በሰብአዊ ክዋኔው መዋች ሲሆን በመለኮታዊ ክዋኔው ተነሽና አንሺ ነው፤ ከዚህ አንጻር ሥግው ቃል ሁለቱንም ተግባራት በአንድ አካልና ክዋኔ የመፈጸም ሥልጣን አለው፣ ይህም በመሆኑ ራሴን የማኖርና የማንሣት ሥልጣን አለኝ በማለት እውነታውንና ምንነቱን አሳየ፤
ጌታችን ይህንን አስመልክቶ ከመሞቱና ከመነሣቱ በፊት ለቅዱሳን ሐዋርያት በተደጋጋሚ አስረድቶአል፣ ስለሆነም የጌታችን ሞትና ትንሣኤ ድንገተኛና የግድ ሳይሆን ታውቆ ያደረና የውድ እንደሆነ ከዚህ እውነታ እንረዳለን፤
ጌታችን ይህንን ተግባር በውድ ፈቃዱ የፈጸመው በእግዚአብሔር አሰራር ከዚህ ውጭ የዓለም ድኅነት የሚከናወንበት ዕድል ስለሌለ ነው፤ በእግዚአብሔር አሰራር ኃጢአትና በደል የሚሰረዘው በቤዛዊ መሥዋዕት ብቻ እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በነበረው የቤዛዊ መሥዋዕት አቀራረብ የታወቀ ነው፤
በመሆኑም የሰውን ምልአት ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ሰርዞ ሰውን ከሞት ቅጣት ነጻ ለማውጣት ብቃት ያለው ቤዛዊ መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነበረበት፤ ይሁን እንጂ ለዚህ ዓይነቱ ቤዛዊ መሥዋዕት ብቁ የሆነ ከፍጡራን ወገን ስላልተገኘ "ለሊሁ መሥዋዕት፣ ወለሊሁ ሠዋዒ፣ ወለሊሁ ተወካፌ መሥዋዕት ማለትም" ራሱ መሥዋዕት፣ ራሱ መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት፣ ራሱ ተወካፌ መሥዋዕት አምላክ ሆኖ የቤዛነታችንን መሥዋዕት ራሱ በራሱ ለራሱ አቀረበ"፤
በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕትም እኛን ከሞት ቅጣት ነጻ አደረገን፤ትንሣኤያችንንም በትንሣኤው አበሰረ፣ በክርስትና ሃይማኖት የሚገኝ ፍጹም ድኅነትና ነጻነት በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ የተመሠረተ ነው፤
የተወዳደችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
ጌታችን በትንሣኤው ትንሣኤያችንን ሲያበስረን የትንሣኤ ሰዎች ሆነን በመንፈስና በሞራል በማደግ ብርሃናተ ዓለም ልንሆን እንጂ እንደገና የጨለማው ኃይል መሳሪያዎች ልንሆን አይደለም፤ የሞቱና የትንሣኤው ምስጢር በንጹሁ ኅሊናችን ካስተዋልነው ውስጣችን እሱን ለመቀበል የሚያዳግተው አይደለም፤
ከዚህ አንጻር በትንሣኤው አምነን ትንሣኤያችንን እየተጠባበቅን የምንገኝ ሕዝበ ክርስቲያን በቅን አስተሳሰብ፣በርቱዕ አእምሮና በኃይለ ሃይማኖት እየታገዝን ጨለማውን ዓለም ወደ ብርሃን ለመለወጥ መጣርና መትጋት ይጠበቅብናል፤
የጨለማው ዓለም መንፈስ ሊያጠፋን ካልሆነ በቀር እንደማይጠቅመን በተጨባጭ የምናውቀው ነው፤ ወደድንም ጠላንም ያለን ብቸኛ አማራጭ ብርሃንን መከተል ነው፤ እሱም እግዚአብሔር ነው በብርሃን የሚመላለስ እንደማይጐዳ በእግዚአብሔር የሚኖርም ተጐድቶ አያውቅምና ነው፤
ዓለም እንደ አጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው፤ ስለሆነም የኛ ምርጫ ብርሃን የሆነውን እግዚአብሔር እንዲሆን የቤተ ክርስቲያን የዘወትር ጥሪ ነው ፤
በመጨረሻም፡-
የትንሣኤ በዓላችንን ስናከብር ዓለም በክፋቱ ያጨለመባቸውን ወገኖች ጦማችው እንዳይውሉ ካለን ከፍለን የተራቡትን በማብላት፤ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የታረዙትን በማልበስና የዕለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ በማድረግ ቀኑ ለሁላችንም ፍጹም ብርሃን ሆኖ ይውል ዘንድ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን በእግዚአብሑር ስም እናስተላልፋለን፤
መልካም የትንሣኤ በዓል ያድርግልን!!
“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ"
“ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አባ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤
ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ' ኢትዮጵያ

ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።
ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል።
( አሻም ሚዲያ ማዕከል ሚያዚያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም)
በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ ኣምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ተክለሃይማኖት የመግቢያ ንግግር ተጀምሯል።
ጉባኤው በይፋ መጀመሩን ተከትሎ የቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት ለምልዓተ ጉባኤው ቀርቧሎ
በመቀጠልም የሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚወያይባቸውን አጀንዳዳዎች የሚያቀርብ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ተመረጠዋል።
የኮሚቴ አባላቱም
1. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ሊቀ ጳጳስ
4.ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳስ
5. ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ሊቀ ጳጳስ
6. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ
7.ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጳጳስ
መሆናቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የሚዲያ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካል ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት (#EOTCTV) ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በከሰዓት ውሎው ጉባኤውን የሚቀጥል ይሆናል።
መረጃው የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Tv ነው።

የፈተና ማስታወቂያ
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት ፈተና ቀን አስታወቀ።
በ2018 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና #ከግንቦት 30_ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን የ4ኛ፣8ኛ እና 10ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና ሰኔ 7/2018 ሙሉ ቀን ይሰጣል።
በተጨማሪ የ2018 ዓ.ም በሀገረ ስብከት ደረጀ ተዘጋጅቶ የሚሰጠው የሚኒስትሪ ፈተና #ሰኔ 28/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስታወቀ።
በዘንድሮው ዓመት በሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ከ1ኛ _9ኛ ክፍል የሚሰጠው የማጠቃለያ ፈተና ኮሮሶች
1. ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
2. የቤተክርስቲያን ታሪክ (7ኛ፣8ኛ፣ እና 9ኛ ክፍል)
3. የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት
4. የግዕዝ ቋንቋ (ከ1ኛ_6ኛ ክፍል) የሚሰጥ ይሆናል።
እንዲሁም ለ4ኛ፣8ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል እና የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጠው ዓመቱን ሙሉ ሲማሩ የነበሩ ስድስቱንም (6) ኮሮሶች ማለትም #መሠረተ_ሃይማኖት፣ #ልሳነ_ግዕዝ፣ #የቅዱሳት_መጻሕፍት_ጥናት፣ #የቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ፣ #ሥርዓተ_ቤተክርስቲያን እና #ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር የሚፈተኑ ይሆናሉ።
መረጃው:- የመንበረ ጵጵስና ር/ከ/ወ/ቤ/ክ/ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ነው።

👍7❤1
የሕፃናት የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ሰንበት ትምህርት ቤት ነው።
"የመጀመሪያው ትምህርት ከእግዚአብሔር ቤት ይጀምር"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕፃናት ገና መናገርና መረዳት በሚጀምሩበት ዕድሜያቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣትና መቅደሱን መልመድ እንዳለባቸው አጥብቆ ያሳስባል። "ልጆቻችሁ ዓለማዊ እውቀትን ከመማራቸው በፊት፣ መጀመሪያ የመንፈስ ቅዱስን ጥበብና እግዚአብሔርን መፍራትን ያስተምሯቸው" ይላል። ሕፃንነት ልክ እንደ አዲስ ሰም (Wax) በመሆኑ፣ በዚያ ዕድሜ ላይ የተቀረጸ መልካም ሥዕልና ትምህርት በቀላሉ እንደማይጠፋ ያስረዳል።
በዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን
“ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከሆነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ” ብፁዕ አብነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Telegram
https://t.me/adamaunity
👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185

🥰1👏1
የቤተክርስቲያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማነው
“ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከሆነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ”
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን አደረሳችሁ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከዋክብት የሆኑት ታላቁ አባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (የቀድሞው የሸዋ ሊቀ ጳጳስ) ለየሰንበት ትምህርት ቤቶችን ሥርዓትና የወጣቶች አገልግሎት ፋይዳ አጥብቀው በሚያስተምሩት ትምህርቶችና ስብከቶች ውስጥ የሚገኝ እውነተኛ የእረኝነት ለትውልድ ያስተላለፉት ታላቅ አደራ ነው።
ይህ አባባል "ምን ማለት እንደሆነ" እና በውስጡ የያዛቸውን ጥልቅ ምስጢራት በዝርዝር እንደሚከተለው እንመልከት፦
1. "የነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ..." (የወደፊት ዕጣ ፈንታ)
ማንኛውም ሕያው ተቋም የወደፊት ሕልውናውና ጥንካሬው የሚወሰነው ዛሬ በሚያመርተው ተተኪ ትውልድ ላይ ነው። ቤተክርስቲያን ነገ ምን ዓይነት መልክ ይኖራታል? ነገ መድረኩን የሚረከቡት፣ ሥርዓቱንና ሃይማኖቱን ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፉት አገልጋዮች (ሊቃውንት፣ ሰባክያን፣ ካህናትና ምእመናን) እነማን ናቸው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ዛሬ ላይ ነው።
ስለዚህ ለነገዋ ቤተክርስቲያን ክብር፣ አንድነትና ጥንካሬ የምንጨነቅና የምናስብ ከሆነ፣ ትኩረታችን መሆን ያለበት ነገ ላይ ሳይሆን ዛሬ ላይ ነው የሚለውን ዐብይ መልእክት ያስተላልፋል።
2. "...ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ"
ይህ የዓረፍተ ነገሩ ክፍል የችግሩን ሁሉ መፍትሔ በግልጽ ያስቀምጣል። የነገዋን ቤተክርስቲያን ውብና ብሩህ ለማድረግ ዛሬ መሥራት ያለብን በሰንበት ትምህርት ቤት ላይ ነው።
"በልባችሁ አኑሩ" ማለት ምን ማለት ነው?
1. ትኩረትና ድጋፍ መስጠት፦ ሰንበት ትምህርት ቤትን ከተራ የወጣቶች ስብስብ ወይም መዝሙር መለማመጃ ቦታ በላይ አድርጎ ማየት ሳይሆን በዕውቀት፣ በገንዘብና በሃሳብ መደገፍ ማለት ነው።
2. በትክክለኛው ሥርዓት መምራት፦ አሁን በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና እንደተዘጋጀው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርትና መዋቅር፣ ልጆችንና ወጣቶችን በዕድሜያቸውና በደረጃቸው (ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4) ከፋፍሎ፣ ጥራቱን የጠበቀ መንፈሳዊ ዕውቀት መመገብ ማለት ነው።
3. ከባዕድ አምልኮ መጠበቅ፦ ወጣቱ ትውልድ በሪዕዮተ ዓለም ተውጦ እንዳይቀር እና በበዓላት ሽፋን ከሚደረጉ የባዕድ አምልኮ ልማዶች፣ የጨለማ አሠራሮች ርቆ፣ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ብቻ እንዲያመልክ በልባችን ይዘን ማስተማር ማለት ነው።
ብፁዕ አባታችን በረከታቸው ይደረብንና ይህ ቃል ለሁሉም አባቶች፣ እናቶች፣ ካህናትና መሪዎች የተሰጠ የነቃ የደወል ጥሪ ነው።
"ነገ ቤተክርስቲያን አገልጋይ አጥታ እንድትቸገር፣ ወጣቱ በሱስና በባዕድ አምልኮ ጠፍቶ ቤተክርስቲያን ባዶ እንድትሆን ካልፈለጋችሁ፤ ዛሬ ሕፃናትንና ወጣቶችን በሰንበት ትምህርት ቤት ጥላ ሥር ሰብስባችሁ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩቱ። ዛሬ በሰንበት ትምህርት ቤት የምንዘራው የተቀደሰ ዘር፣ ነገ የምናጭደው የቤተክርስቲያን ትልቅ ክብርና ሕያውነት ነው!"።

Telegram
የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ መሳካት ያላቸው ሚና
ትውልዱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት በማዘንበል ሃይማኖቱን ችላ እንዳይል በማሰብ አባቶቻችን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን በማወቅ የሚያድግ፤ መልስ ያለው ትውልድ ለመፍጠር ከ1935-1940 ዓ/ም ባለው ጊዜ ሰንበት ት/ቤትን እንደመሠረቱ የሚታወቅ ሲሆን ቀጥሎም በ 1953 ዓ.ም መመሪያ ወጥቶለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ትእዛዝ በየአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያኑ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን በቃለ ዓዋዲው የሰንበት ት/ቤት አወቃቀር በመመሪያ ተካተተ::
የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዋና ተልእኮ እና ግብ ሰዎች በሃይማኖት፣ (ይህም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን እና ያመኑት ደግሞ ሥራቸው ይከተላቸዋልና) በሥነ ምግባር ጸንተው እንዲኖሩ በማድረግ ለመንግሥቱ ማብቃት ነው። በቃለ ዐዋዲው መሠረትም ይህንን ተልእኮ ለመወጣት በሕፃናትና በወጣቶች በኩል ያለውን ኃላፊነት ለሰንበት ትምህርት ቤት በይፋ ተላልፏል።
ሰንበት ትምህርት ቤቶችም እንደ ተቋም ከሕፃንነት እስከ የነገ ተረካቢ፥ ወጣቶች ድረስ ይህንን ትውልድ የመገንባት ሥራውን በሚገባ ለመወጣት በተናጥልም ሆነ በትብብር በአንድነት አደረጃጀቶችን በመጠቀም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ እየተወጡ ይገኛሉ።
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Telegram
https://t.me/adamaunity
👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ መሳካት ያላቸው ሚና
ትውልዱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት በማዘንበል ሃይማኖቱን ችላ እንዳይል በማሰብ አባቶቻችን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን በማወቅ የሚያድግ፤ መልስ ያለው ትውልድ ለመፍጠር ከ1935-1940 ዓ/ም ባለው ጊዜ ሰንበት ት/ቤትን እንደመሠረቱ የሚታወቅ ሲሆን ቀጥሎም በ 1953 ዓ.ም መመሪያ ወጥቶለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ትእዛዝ በየአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያኑ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን በቃለ ዓዋዲው የሰንበት ት/ቤት አወቃቀር በመመሪያ ተካተተ::
የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዋና ተልእኮ እና ግብ ሰዎች በሃይማኖት፣ (ይህም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን እና ያመኑት ደግሞ ሥራቸው ይከተላቸዋልና) በሥነ ምግባር ጸንተው እንዲኖሩ በማድረግ ለመንግሥቱ ማብቃት ነው። በቃለ ዐዋዲው መሠረትም ይህንን ተልእኮ ለመወጣት በሕፃናትና በወጣቶች በኩል ያለውን ኃላፊነት ለሰንበት ትምህርት ቤት በይፋ ተላልፏል።
ሰንበት ትምህርት ቤቶችም እንደ ተቋም ከሕፃንነት እስከ የነገ ተረካቢ፥ ወጣቶች ድረስ ይህንን ትውልድ የመገንባት ሥራውን በሚገባ ለመወጣት በተናጥልም ሆነ በትብብር በአንድነት አደረጃጀቶችን በመጠቀም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ እየተወጡ ይገኛሉ።
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Telegram
https://t.me/adamaunity
👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወጣትነት በፈተናና በምኞት ማዕበል የተሞላ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር።
እንኳን ለ15ኛ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን አደረሳችሁ ።
ስለዚህ ስለ ወጣቶች እንድህ ይለናል ፦
ወጣትነት እንደ "ዱር ፈረስ" እና "እንደሚናወጥ ባሕር" ነው ወጣትነትን ሲገልጸው፦ "ወጣትነት ልክ እንደ ዱር ፈረስ ነው፤ በቀላሉ አይገራም። ወጣትነት ልክ ማዕበል እንደሚናውጠው ባሕር ነው" ይላል። ስለዚህ ወጣቶች በዚህ ዕድሜያቸው እንዳይጠፉና መርከባቸው እንዳይሰምጥ ጠንካራ የመንፈሳዊ ሕይወት መሪ (ኮርቻ) ያስፈልጋቸዋል። ይህ መሪ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ና የሰንበት ትምህርት ቤት ጥበቃ ነው።
👉👉👉👉👉#ሰኔ_14/2018 በ አዳማ ደ/ና/ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን ይከበራል።

❤1👎1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከግንቦት 30_ሰኔ 7/2018 ዓ.ም ድረስ የሞደል እና ማጠቃለያ ፈተና ከ1_10ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች ይሰጣል👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇#ሰኔ_14/2018 በአዳማ ደ/ና/ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን ይከበራል።
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Telegram
https://t.me/adamaunity
👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇#ሰኔ_14/2018 በአዳማ ደ/ና/ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን ይከበራል።
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Telegram
https://t.me/adamaunity
👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
❤2
🎤🎤🎤መልእክት
"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ"
የ
እንደሚታወቀው ላለፋት አስርት አመታት በቅዱስ ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ደንብ ከጸደቀበት እና በረከታቸው ይደርብን እና በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትሪያሪክ የባዕለ ጰራቅሊጦስ ቀን የሰንበት ት/ቤቶች ቀን እንዲሆን በሰጡት አባታዊ መመርያ መሠረት በየዓመቱ በአለ ጰራቂሊጦስን ቀን መሠረት አድርጎ የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሁሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት የሁለት ቀን ጠቅላላ ጉባኤውን እና የጉባኤው ማጠቃለያ ቀን በባዕለ ጰራቅሊጦስ እለት ከአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን በጋራ ሲያከብር መቆየቱ ይታወሳለ።
ይሁን እና በዚህ አመት በአሉ የዋለበት ቀን ከ7ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዋዜማ ላይ በመሆኑ የየአህጉረ ስብከት ተወካዮች ለመገኘት ባለመቻላቸው ጠቅላላ ጉባኤው የተዘዋወረ በመሆኑ ሁለም ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ቀንን "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪ ቃል እንዲከበር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መልእክት አስተላልፏል።
የመንበረ ጵጵስና ር/ከ/ወረዳ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዘንድሮ የሰንበት ት/ቤቶች ቀን ሁሉም አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች አባላት እና የክብር አባላት እንድሁም ታጋባዝ እንግዶች በተገኙበት በዓሉን ሰኔ14/2018 ዓ.ም በአዳማ ደብረ ናዝሬት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ለማክበር ዝግጅት ላይ ይገኛል።
ነገር ግን ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በዕለቱ ሁላችንም በየአጥቢያችን በሚኖር የሰንበት ት/ቤት ጉባኤ እና የተለያዩ መርሐ ግብራት ላይ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን መሪ ቃሉን መሠረት በማድረግ ከአባላቶቻችን ጋር እንድናከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በመርሐ ግብሮቹም መሪቃሉን መሠረት ያደረገ ቃለ እግዚአብሔር እና በዝማሬ እንድናከብር እያልን በድጋሚ የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለሁሉም የሰንበት ትቤት አባላት እና አመራሮች እንኳን ለሰንበት ት/ቤቶች ቀን እና ለባዕለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ እያለ ሰንበት ት/ቤትች በእለቱ በዐሉን አክብረው እንዲውሉ እና የሰንበት ት/ቤት አመራሮች እንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታችሁን ለመላው አባላቶቻችሁ እንድታስተላልፋ ከወዲሁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ"
የ
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማጀራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዘንድሮ የሰንበት ት/ቤቶች ቀን የሁሉም ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት በየአለበት ቦታ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪቃል እንዲከበር መልእክት አስተላለፈ።እንደሚታወቀው ላለፋት አስርት አመታት በቅዱስ ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ደንብ ከጸደቀበት እና በረከታቸው ይደርብን እና በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትሪያሪክ የባዕለ ጰራቅሊጦስ ቀን የሰንበት ት/ቤቶች ቀን እንዲሆን በሰጡት አባታዊ መመርያ መሠረት በየዓመቱ በአለ ጰራቂሊጦስን ቀን መሠረት አድርጎ የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሁሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት የሁለት ቀን ጠቅላላ ጉባኤውን እና የጉባኤው ማጠቃለያ ቀን በባዕለ ጰራቅሊጦስ እለት ከአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን በጋራ ሲያከብር መቆየቱ ይታወሳለ።