የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ይኽ የጌታችን ትሕትና ብዙዎችን አስደንቋል፤ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንትም በቅዳሴያቸው ላይ “በይእቲ ሌሊት አኀዝዎ ወጸቢሖ ረበናተ አይሁድ ወሊቃነ ካህናት ምስለ ጲላጦስ መስፍን ወነበሩ ዐውደ ለኰ
ንኖቱ…” (በዚያች ሌ
ሊት ያዙት.
በነጋም ጊዜ የአይሁድ መምህሮችና የካህናት አለቆች ከገዢው ከጲላጦስ ጋራ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፤ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ የመላእክት ሰራዊት በመፍራት የሚቆሙለትን በፊታቸው አቆሙት፤ ክፉ ባሪያ ርሱን ያልበደለውን ፊቱን በጥፊ ይመታው ዘንድ እጁን አጸና፤ የመላእክት አለቆች በፍጹም ድንጋፄ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት ይሰግዱ ዘንድ አጐነበሱለት) በማለት ዐርብ ጠዋት አይሁድ ጌታን ወደ ፍርድ ዐደባባይ እንዴት እንዳቀረቡት በስፋት አስተምረዋል፡፡
ጌታ ከመወለዱ አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድሞ ጌታችን በንጉሥ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፰ ላይ “ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጭፍሮች ጌታን ከሰቀሉት በኋላ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ኾኖ በአራት ሲከፋፍሉት ከላይ ዠምሮ ወጥ ኾኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ ያልነበረው እጀ ጠባቡን ደግሞ በመውሰድ ርስ በርሳቸው ለማን እንዲኾን በርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባለዋል፤ ይኽቺውም ቀሚሱ ሰብአ ሰገል ያመጡለት ሲያድግ የምታድግ ዐሥራ ኹለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የነበረችው ሴት የተፈወሰችበት ገባሪተ ተአምራት ነበረች (ማቴ ፪፥፲፩፤ ፱፥፳)፡፡
አይሁድ ይኽነን ማድረጋቸው ለጊዜው “ኹለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል” (ማቴ ፭፥፵) በማለት ኹለት ልብስ አታኑሩ በማለት የሚያስተምረው የርሱ ልብስ ለአራት ቤት ጭፍራ በቃ ለማለት ለመዘበት ሲኾን ፍጻሜው ግን ልብስ የወንጌል ምሳሌ አራት ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ወገን ኹና ለመጻፏ፤ አለመቅደዳቸው በምስጢር አንድ የመኾኗ፤ አንድም አራቱ ኹሉ ባንዲቱ ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ክፍል ስትኾን አንድ ሕግ ለመኾኗ ምሳሌ፤ አንድም “አንቅደድ” ማለታቸው ትስብእቱን ከመለኮቱ ሳንለይ እንመን ሲያሰኛቸው ነው በማለት መተርጒማነ ሐዲስ ያመሰጥራሉ (ማቴ ፳፯፥፴፭፤ ማር ፲፭፥፳፬፤ ሉቃ ፳፫፥፴፬፤ ዮሐ ፲፱፥፳፫)፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነን ሲገልጹ “ወእምዝ አዕተቱ አልባሲሁ ወአልበስዎ ሜላተ ልብስ…” (ከዚያም ልብሶቹን ገፍፈው የመንግሥት ልብስ የሚኾን ነጭ ሐር የካህናት ልብስ የሚኾን ቀይ ሐር ሕብራቸው ቀይና ጥቁር የሚኾን ልብስ አለበሱት፤ የአጣቢ ሳሙና ማንጻት የማይቻለው እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ እንደ በረድ የኾነ ነጭ ልብስ የሚለብስ ሲኾን፤ ለኪሩቤል የመብረቅ ልብስን ለሱራፌል ግርማ ያለው ልብስን የሚያለብሳቸው ርሱን እንደዚኽ በምድር በመዘባበት ቀይ ሐርና ነጭ ልብስ አለበሱት) በማለት አስተምረዋል፡፡
ልዑል አምላክ ዘመኑ ሲፈጸም ስለሚቀበላቸው ሕማማተ መስቀል አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፮ ላይ “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ዳግመኛም ከ፯፻ ዓመት አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስም ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጌታችንን አይሁድ ገርፈውታል፡፡
አንድም ንጹሐ ባሕርይ ጌታችን መገረፉ ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡና እየገረፈ ወደ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ሊክስለት ሲኾን ዳግመኛም በጌታ ላይ አይሁድ የግፍ ድርብ አድርገውበታል በሀገራቸው የሚሰቀል አይገረፍም ነበር በተጨማሪም በኦሪት ልምድ ከአርባ አትርፎ መግረፍ የተከለከለ ሲኾን እነርሱ ግን ፴፱ ጊዜ ከገረፉ በኋላ ቊጥር ተሳሳትን እያሉ ሥጋው ዐልቆ ዐጥንቱ እንደ በረድ ነጭ እስከሚኾን ድረስ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ግርፋትን ገርፈው እንደ ብራና ወደዚያና ወደዚኽ ወጥረው ሲሰቅሉት ዐጥንቱ ታይቶ የሚቈጠር ኹኗል፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነኑ ሲያብራሩ
“ወእምድኅረ አሠርዎ ቀሠፍዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ጲላጦስ ወአርባዕቱ ሐራ በሐብል ወበአስዋጥ መጠነ ፷፻ ወ፮፻፷፮ … ”
(ጌታችን ኢየሱስንም ካሠሩት በኋላ አራት ቤት ጭፍሮችና ጲላጦስ በገመድና ባለንጋ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ጊዜ ገረፉት፤ ዐምስት እልፍ ነው የሚሉም አሉ፤ የግርፋቱን ቊጥር እያሳሳቱ ገርፈውታልና፤ የሚሞት እንዳይገረፍ የማይሞት እንዲገረፍ እያወቁ፤ በግፍ ገርፈው በግፍ ገደሉት የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ፤ ከግርፋቱም ጽናት የተነሣ ሥጋው ኹሉ ዐለቀ፤ ሺሕ ከ፮፻ ከሚኾኑ ቊስሎቹም ወገን ዐጥንቶች ታዩ፤ ጥቁርና ሰማይ የሚመስሉ ቊስሎቹ ግን ሺሕ አንድ መቶ ከዘጠና ናቸው፤ የማይገረፍ አምላክ በዚኽ ሥጋ ተገረፈ፤ ጲላጦስ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችንን የገረፈው በዦሮ ለሚሰማው በዐይን ለሚያየው ሰው ዕጹብ ድንቅ ነው፤ በመገረፉም አይሁድን ደስ አሰኛቸው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን በመገረፉ ሰው ኹሉ ከተገረፈባት ኀጢአት ፍዳ አዳነን፤ ስለ ልጆቹና ስለ አዳም መገረፍን መታሠርን ከፍሏልና) በማለት ለኹላችን ካሳ ስለተገረፈው ግርፋት አስተምረዋል፡፡
በነቢዩ ኢሳይያስ ላይ ጌታ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” ብሎ ያናገረው ሊደርስ ሊፈጸም ክብር ይግባውና በአምላካችን ፊት ላይ አይሁድ ምራቃቸውን ተፍተውበታል፤ ዳግመኛም ዲያብሎስ ምራቀ ምክሩን እየተፋ ወደ ሲኦል ላወረደው ለአዳም ሊክስለት የማኅበረ አይሁድን ምራቅ ክብር ይግባውና አምላካችን በትዕግሥት ተቀብሎታል፡፡

ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል ሲያብራሩ “አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ…” (የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና፤ በቀኝ እጁ ዘንግ አስያዙት፤ ሲያሽሟጥጡ በፊቱ እየወደቁ እጅ ነሡለት፤ የመላእክት ሰራዊት እየደነገፁ የሚሰግዱለትን የአይሁድ ንጉሥ ቸር ውለኻል አሉት፤ ሥልጣናትና ሊቃናት እየፈሩ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት እጅ ነሡት፤
ዐምስት የሚኾኑ መዘባበቻቸውን ከጨረሱ በኋላ በምራቁ ኹለተኛ ዐይኖችን በሚፈጥር በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዳግመኛም ፊቱን በጥፊ መቱት፤ ኪሩቤል ፊቱን ከማየት የተነሣ በእሳት አክናፍ የሚሰወሩት ያልበደላቸውን ርሱን አይሁድ በጥፊ መቱት፤ ፊቱ እንደ መንፈስ ቅዱስና እንደ አባቱ ሲኾን በተዋሐደው ሥጋ ፊቱን ጸፉት ከፊቱ ግርማ የተነሣ ፍጥረቱ ኹሉ የሚርዱለት የሚንቀጠቀጡለት የፈጣሪያቸውን ፊቱን ጸፉት፤ መዠመሪያ በመመታቱና የሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ራሱ የቈሰለ ከመኾኑም በላይ
የያዘውን በትር ከእጁ ተቀብለው ራሱን መቱት፤ ነገር ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ ርግማንን አጠፋልን፤ ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እ ባብ

ሰባቱን ራሶቹን ዐሥሩን

ቀንዶቹን

አጠፋልን) በማለት አስተምረዋል፡፡
ክብር ይግባውና ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ ጌታችንን በመኻከል አድርገው ሰቅለውታል (ማቴ ፳፯፥፴፰፤ ማር ፲፭፥፳፯፤ ሉቃ ፳፪፥፴፫፤ ዮሐ ፲፱፥፲፰)፡፡ ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት ነው በተጨማሪም ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕ ፶፫፥፲፪ ላይ “ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምስጢሩ ግን በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር (ማቴ ፳፭፥፴፫፤ ራእ ፩፥፯)፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ውስጥ የኸኑት ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳና በርዜዳ ስለዚኽ ነገር ሲገልጹ “ወሰቀልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል እንዘ ገጹ መንገለ ምሥራቅ ወእዴሁ ዘየማን መንገለ ደቡብ ወእዴሁ ዘፀጋም መንገለ ሰሜን…” (ጌታችን ኢየሱስንም በዕንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት፤ ፊቱን ወደ ምሥራቅ ቀኝ እጁን ወደ ደቡብ፤ ግራ እጁን ወደ ሰሜን አድርገው ሰቀሉት…ከርሱም ጋር ኹለቱን ወንበዴዎች አንዱን በቀኝ አንዱን በግራው በመኻከላቸው ጌታችን ኢየሱስን አድርገው ሰቀሉ፤ ሕዝቡም ርሱም እንደነርሱ ወንበዴ ነው ይሉት ዘንድ ሰቀሉት፤ ርሱ ግን ወድዶ ከወንበዴዎች ጋር በዕንጨት መስቀል ተሰቀለ፤ ልዑላን መላእክት ፈርተው በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉለት ርሱ በሚሰቅሉት ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ (ፊልጵ ፪፥፲፤ ራእ ፬፥፲-፲፩)፤
በከሃሊነቱ ሰማይና ምድርን ያጸና ከግርማውም የተነሣ ሰማያትና ምድር የሚንቀጠቀጡለትን ርሱን ደካማ ዕንጨት ተሸከመው (ምሳ ፴፥፬፤ ኢሳ ፵፪፥፭)፤ ርሱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ከራሱ ያስታርቀን ዘንድ ከሰማይ ዝቅ ብሎ ከምድር ከፍ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ርሱም ስለእኛ በሥጋው በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ከኀጢአታችን ይለየን ዘንድ በቸርነቱ ያድነን ዘንድ ተሰቀለ (፩ጴጥ ፪፥፳፬)፤ ርሱ ግን ሰማያትን ይቀድስ ዘንድ በአየር ያሉ አጋንንትን ያወርዳቸው ዘንድ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ሙሴ አርዌ ብርትን በገዳም እንደ ሰቀለው ርሱም በዕንጨት ላይ ተሰቀለ ፤ በርሱ ያመነ ኹሉ ይድናል እንጂ እንዳይጐዳ የክብር ባለቤት ርሱ ግን ስለ እኛ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ (ዮሐ ፫፥፲፬-፲፭)፤ አውቀውስ ቢኾን የክብር ባለቤት ጌታን ባልሰቀሉት ነበር (፩ቆሮ ፪፥፰)፤ ሰማይ ዙፋኑ ሲኾን ምድርም በእግሮቹ የተረገጠች ስትኾን ስለኛ በዕንጨት ተሰቀለ (ኢሳ ፷፮፥፩)፤ ርሱ ግን ተጠብቆለት ስላለ ስለ ደስታው የመስቀልን መከራ ንቆ አቃልሎ ተቀበለ ኀፍረትንም ናቃት፤ ለተሰቀለው ለርሱ የማይሰግድ ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይኹን (ፊልጵ ፪፥፰-፲፩)፤ ርሱ ግን ስለ ዓለሙ ደኅንነት በማእዝነ ምድር ወደ ላይ ወደ ታች ወደ ግራ ወደ ቀኝ ኾኖ እንደ መጋረጃ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ፤ እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጠረ) በማለት በስፋት የነገረ ስቅለቱን ምስጢር አስተምረዋል፡፡
በመስቀል ሲሰቀልም በቀኙ የተሰቀለው ጥጦስ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ይባላል፤ በቀኝ የተሰቀለው ጥጦስ ፀሓይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ደም ስትኾን፣ ከዋክብት ከብርሃናቸው ሲራቈቱ፣ ድንጋዮች ሲሠነጠቁ፣ መቃብራት ሲከፈቱ፣ ሙታን ሲነሡ፣ የምኩራቡ መጋረጃ ወደ ኹለት ወደ ሦስት ሲቀደድ ሰባቱ ተአምራት ሲደረጉ አይቶ አምላክነቱን ተረድቶ ወደ ርሱ ሲለምን በግራ የተሰቀለው ወንበዴ ሰምቶ “አንተስ ክርስቶስ አይደለኽምን? ራስኽንም እኛንም አድን” ይል ዠመር (ሉቃ ፳፫፥፴፱)፡፡
ያን ጊዜ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ጌታችን ለቤዛ ዓለም የተሰቀለ እውነተኛ የባሕርይ አምላክነቱን ስለተረዳ በግራ የተሰቀለውን “አንተ እንደዚኽ ባለ ፍርድ ሳለኽ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይኽ ግን ምንም ክፋት አላደረገም” ብሎ ከገሠጸው በኋላ ኀጢአት ሳይኖርበት የተሰቀለውን ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን “ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ” (ጌታ ሆይ በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ) እያለ ሲለምነው ጌታችንም “እውነት እልኻለኊ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኾናለኽ” ብሎት ደመ ማኅተሙን ሰጥቶታልና ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በዚኽ መጽሐፉ ላይ፡- “ምስጋና ለአንተ ይገባል፤ የሞትን ፃዕረኝነት (ችንካር) ትሽር ዘንድ ክፋትን የሠራኽ ሳትኾን (ሳትሠራ) በኹለት ሽፍቶች (ወንበዶች) መኻከል የተቸነከርኽ እውነተኛ ኢየሱስ ምስጋና ለአንተ ይገባል” በማለት ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን አመስግኗል (ሉቃ ፳፫፥፴፱-፵፫)፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ . . . .
ስቅለት!

እንኳን አደረሳችሁ!

“ሕመማችንንም ተሸክሞአል”  ኢሳ 53፡4
4🔥1🙏1
"ዓለም እንደ አጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው።"  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወስምንቱ ዓመተ ምሕረት!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን-

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ከሀገር ዉጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፣

በቤዛዊ መሥዋዕትነቱ ከሞተ ኃጢአት ታድጎ የትንሣኤ ሙታንን በር የከፈተልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
"ወአነ እሜው ነፍስየ ቤዛ አባግዕየ ከመ ካዕበ አንሥእ፤አንሥእ፤
ዳግመኛ አነሣት ዘንድ ነፍሴን የበገቼ ቤዛ አድርጌ እሰጣለሁ ዮሐ 10፥17

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰብአዊ ክዋኔው ሰው ቢሆንም በመለኮታዊ ክዋኔው የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃል ወይም ወልደ እግዚአብሔር ነው፣
በመሆኑም በሰብአዊ ክዋኔው መዋች ሲሆን በመለኮታዊ ክዋኔው ተነሽና አንሺ ነው፤ ከዚህ አንጻር ሥግው ቃል ሁለቱንም ተግባራት በአንድ አካልና ክዋኔ የመፈጸም ሥልጣን አለው፣ ይህም በመሆኑ ራሴን የማኖርና የማንሣት ሥልጣን አለኝ በማለት እውነታውንና ምንነቱን አሳየ፤

ጌታችን ይህንን አስመልክቶ ከመሞቱና ከመነሣቱ በፊት ለቅዱሳን ሐዋርያት በተደጋጋሚ አስረድቶአል፣ ስለሆነም የጌታችን ሞትና ትንሣኤ ድንገተኛና የግድ ሳይሆን ታውቆ ያደረና የውድ እንደሆነ ከዚህ እውነታ እንረዳለን፤

ጌታችን ይህንን ተግባር በውድ ፈቃዱ የፈጸመው በእግዚአብሔር አሰራር ከዚህ ውጭ የዓለም ድኅነት የሚከናወንበት ዕድል ስለሌለ ነው፤ በእግዚአብሔር አሰራር ኃጢአትና በደል የሚሰረዘው በቤዛዊ መሥዋዕት ብቻ እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በነበረው የቤዛዊ መሥዋዕት አቀራረብ የታወቀ ነው፤

በመሆኑም የሰውን ምልአት ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ሰርዞ ሰውን ከሞት ቅጣት ነጻ ለማውጣት ብቃት ያለው ቤዛዊ መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነበረበት፤ ይሁን እንጂ ለዚህ ዓይነቱ ቤዛዊ መሥዋዕት ብቁ የሆነ ከፍጡራን ወገን ስላልተገኘ "ለሊሁ መሥዋዕት፣ ወለሊሁ ሠዋዒ፣ ወለሊሁ ተወካፌ መሥዋዕት ማለትም" ራሱ መሥዋዕት፣ ራሱ መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት፣ ራሱ ተወካፌ መሥዋዕት አምላክ ሆኖ የቤዛነታችንን መሥዋዕት ራሱ በራሱ ለራሱ አቀረበ"፤

በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕትም እኛን ከሞት ቅጣት ነጻ አደረገን፤ትንሣኤያችንንም በትንሣኤው አበሰረ፣ በክርስትና ሃይማኖት የሚገኝ ፍጹም ድኅነትና ነጻነት በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ የተመሠረተ ነው፤

የተወዳደችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን በትንሣኤው ትንሣኤያችንን ሲያበስረን የትንሣኤ ሰዎች ሆነን በመንፈስና በሞራል በማደግ ብርሃናተ ዓለም ልንሆን እንጂ እንደገና የጨለማው ኃይል መሳሪያዎች ልንሆን አይደለም፤ የሞቱና የትንሣኤው ምስጢር በንጹሁ ኅሊናችን ካስተዋልነው ውስጣችን እሱን ለመቀበል የሚያዳግተው አይደለም፤

ከዚህ አንጻር በትንሣኤው አምነን ትንሣኤያችንን እየተጠባበቅን የምንገኝ ሕዝበ ክርስቲያን በቅን አስተሳሰብ፣በርቱዕ አእምሮና በኃይለ ሃይማኖት እየታገዝን ጨለማውን ዓለም ወደ ብርሃን ለመለወጥ መጣርና መትጋት ይጠበቅብናል፤

የጨለማው ዓለም መንፈስ ሊያጠፋን ካልሆነ በቀር እንደማይጠቅመን በተጨባጭ የምናውቀው ነው፤ ወደድንም ጠላንም ያለን ብቸኛ አማራጭ ብርሃንን መከተል ነው፤ እሱም እግዚአብሔር ነው በብርሃን የሚመላለስ እንደማይጐዳ በእግዚአብሔር የሚኖርም ተጐድቶ አያውቅምና ነው፤

ዓለም እንደ አጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው፤ ስለሆነም የኛ ምርጫ ብርሃን የሆነውን እግዚአብሔር እንዲሆን የቤተ ክርስቲያን የዘወትር ጥሪ ነው ፤

በመጨረሻም፡-

የትንሣኤ በዓላችንን ስናከብር ዓለም በክፋቱ ያጨለመባቸውን ወገኖች ጦማችው እንዳይውሉ ካለን ከፍለን የተራቡትን በማብላት፤ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የታረዙትን በማልበስና የዕለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ በማድረግ ቀኑ ለሁላችንም ፍጹም ብርሃን ሆኖ ይውል ዘንድ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን በእግዚአብሑር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም የትንሣኤ በዓል ያድርግልን!!

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ"

“ወስብሐት ለእግዚአብሔር

                   አባ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤

          ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
             አዲስ አበባ' ኢትዮጵያ
ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።
ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል።

( አሻም ሚዲያ ማዕከል  ሚያዚያ ፳፰ ቀን  ፳፻፲፰  ዓ.ም)

በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ ኣምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ተክለሃይማኖት የመግቢያ ንግግር ተጀምሯል።
ጉባኤው በይፋ መጀመሩን ተከትሎ የቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት ለምልዓተ ጉባኤው ቀርቧሎ
በመቀጠልም የሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚወያይባቸውን አጀንዳዳዎች የሚያቀርብ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ተመረጠዋል።

የኮሚቴ አባላቱም
1. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ሊቀ ጳጳስ
4.ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳስ
5. ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ሊቀ ጳጳስ
6. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ
7.ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጳጳስ
መሆናቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የሚዲያ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካል ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት (#EOTCTV) ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በከሰዓት ውሎው ጉባኤውን የሚቀጥል ይሆናል።

መረጃው የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Tv ነው።
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
4
የፈተና ማስታወቂያ

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት ፈተና ቀን አስታወቀ።

በ2018 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና  #ከግንቦት 30_ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን የ4ኛ፣8ኛ እና 10ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና ሰኔ 7/2018 ሙሉ ቀን ይሰጣል።

በተጨማሪ የ2018 ዓ.ም በሀገረ ስብከት ደረጀ ተዘጋጅቶ የሚሰጠው የሚኒስትሪ ፈተና #ሰኔ 28/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስታወቀ።

በዘንድሮው ዓመት በሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ከ1ኛ _9ኛ ክፍል የሚሰጠው የማጠቃለያ ፈተና ኮሮሶች
1. ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
2. የቤተክርስቲያን ታሪክ (7ኛ፣8ኛ፣ እና 9ኛ ክፍል)
3. የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት
4. የግዕዝ ቋንቋ (ከ1ኛ_6ኛ ክፍል) የሚሰጥ ይሆናል።

እንዲሁም ለ4ኛ፣8ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል እና የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጠው ዓመቱን ሙሉ ሲማሩ የነበሩ ስድስቱንም (6) ኮሮሶች  ማለትም #መሠረተ_ሃይማኖት#ልሳነ_ግዕዝ#የቅዱሳት_መጻሕፍት_ጥናት#የቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ#ሥርዓተ_ቤተክርስቲያን እና #ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር  የሚፈተኑ ይሆናሉ።


መረጃው:- የመንበረ ጵጵስና ር/ከ/ወ/ቤ/ክ/ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ነው።
👍71
የሕፃናት የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ሰንበት ትምህርት ቤት ነው።

"የመጀመሪያው ትምህርት ከእግዚአብሔር ቤት ይጀምር"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕፃናት ገና መናገርና መረዳት በሚጀምሩበት ዕድሜያቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣትና መቅደሱን መልመድ እንዳለባቸው አጥብቆ ያሳስባል። "ልጆቻችሁ ዓለማዊ እውቀትን ከመማራቸው በፊት፣ መጀመሪያ የመንፈስ ቅዱስን ጥበብና እግዚአብሔርን መፍራትን ያስተምሯቸው" ይላል። ሕፃንነት ልክ እንደ አዲስ ሰም (Wax) በመሆኑ፣ በዚያ ዕድሜ ላይ የተቀረጸ መልካም ሥዕልና ትምህርት በቀላሉ እንደማይጠፋ ያስረዳል።

በዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን

“ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከሆነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ” ብፁዕ አብነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
🥰1👏1
የቤተክርስቲያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማነው

“ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከሆነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ”

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን አደረሳችሁ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከዋክብት የሆኑት ታላቁ  አባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (የቀድሞው የሸዋ ሊቀ ጳጳስ) ለየሰንበት ትምህርት ቤቶችን ሥርዓትና የወጣቶች አገልግሎት ፋይዳ አጥብቀው በሚያስተምሩት ትምህርቶችና ስብከቶች ውስጥ የሚገኝ እውነተኛ የእረኝነት ለትውልድ ያስተላለፉት ታላቅ አደራ ነው።

ይህ አባባል "ምን ማለት እንደሆነ" እና በውስጡ የያዛቸውን ጥልቅ ምስጢራት በዝርዝር እንደሚከተለው እንመልከት፦

1. "የነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ..." (የወደፊት ዕጣ ፈንታ)

ማንኛውም ሕያው ተቋም የወደፊት ሕልውናውና ጥንካሬው የሚወሰነው ዛሬ በሚያመርተው ተተኪ ትውልድ ላይ ነው። ቤተክርስቲያን ነገ ምን ዓይነት መልክ ይኖራታል? ነገ መድረኩን የሚረከቡት፣ ሥርዓቱንና ሃይማኖቱን ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፉት አገልጋዮች (ሊቃውንት፣ ሰባክያን፣ ካህናትና ምእመናን) እነማን ናቸው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ዛሬ ላይ ነው።

ስለዚህ ለነገዋ ቤተክርስቲያን ክብር፣ አንድነትና ጥንካሬ የምንጨነቅና የምናስብ ከሆነ፣ ትኩረታችን መሆን ያለበት ነገ ላይ ሳይሆን ዛሬ ላይ ነው የሚለውን ዐብይ መልእክት ያስተላልፋል።

2. "...ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ"

ይህ የዓረፍተ ነገሩ ክፍል የችግሩን ሁሉ መፍትሔ በግልጽ ያስቀምጣል። የነገዋን ቤተክርስቲያን ውብና ብሩህ ለማድረግ ዛሬ መሥራት ያለብን በሰንበት ትምህርት ቤት ላይ ነው።

"በልባችሁ አኑሩ" ማለት ምን ማለት ነው?

   1. ትኩረትና ድጋፍ መስጠት፦ ሰንበት ትምህርት ቤትን ከተራ የወጣቶች ስብስብ ወይም መዝሙር መለማመጃ ቦታ በላይ አድርጎ ማየት ሳይሆን በዕውቀት፣ በገንዘብና በሃሳብ መደገፍ ማለት ነው።

   2. በትክክለኛው ሥርዓት መምራት፦ አሁን በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና እንደተዘጋጀው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርትና መዋቅር፣ ልጆችንና ወጣቶችን በዕድሜያቸውና በደረጃቸው (ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4) ከፋፍሎ፣ ጥራቱን የጠበቀ መንፈሳዊ ዕውቀት መመገብ ማለት ነው።

   3. ከባዕድ አምልኮ መጠበቅ፦ ወጣቱ ትውልድ  በሪዕዮተ ዓለም ተውጦ እንዳይቀር እና በበዓላት ሽፋን ከሚደረጉ የባዕድ አምልኮ ልማዶች፣  የጨለማ አሠራሮች ርቆ፣ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ብቻ እንዲያመልክ በልባችን ይዘን ማስተማር ማለት ነው።

ብፁዕ አባታችን በረከታቸው ይደረብንና ይህ ቃል ለሁሉም አባቶች፣ እናቶች፣ ካህናትና መሪዎች የተሰጠ የነቃ የደወል ጥሪ ነው።

"ነገ ቤተክርስቲያን አገልጋይ አጥታ እንድትቸገር፣ ወጣቱ በሱስና በባዕድ አምልኮ ጠፍቶ ቤተክርስቲያን ባዶ እንድትሆን ካልፈለጋችሁ፤ ዛሬ ሕፃናትንና ወጣቶችን በሰንበት ትምህርት ቤት ጥላ ሥር ሰብስባችሁ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩቱ። ዛሬ በሰንበት ትምህርት ቤት የምንዘራው የተቀደሰ ዘር፣ ነገ የምናጭደው የቤተክርስቲያን ትልቅ ክብርና ሕያውነት ነው!"።

በዓለ ጰራቅሊጦስ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ መሳካት ያላቸው ሚና

ትውልዱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት በማዘንበል ሃይማኖቱን ችላ እንዳይል በማሰብ አባቶቻችን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን በማወቅ የሚያድግ፤ መልስ ያለው ትውልድ ለመፍጠር ከ1935-1940 ዓ/ም ባለው ጊዜ ሰንበት ት/ቤትን እንደመሠረቱ የሚታወቅ ሲሆን ቀጥሎም በ 1953 ዓ.ም መመሪያ ወጥቶለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ትእዛዝ በየአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያኑ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን በቃለ ዓዋዲው የሰንበት ት/ቤት አወቃቀር በመመሪያ ተካተተ::

የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዋና ተልእኮ እና ግብ ሰዎች በሃይማኖት፣ (ይህም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን እና ያመኑት ደግሞ ሥራቸው ይከተላቸዋልና) በሥነ ምግባር ጸንተው እንዲኖሩ በማድረግ ለመንግሥቱ ማብቃት ነው። በቃለ ዐዋዲው መሠረትም ይህንን ተልእኮ ለመወጣት በሕፃናትና በወጣቶች በኩል ያለውን ኃላፊነት ለሰንበት ትምህርት ቤት በይፋ ተላልፏል።

ሰንበት ትምህርት ቤቶችም እንደ ተቋም ከሕፃንነት እስከ የነገ ተረካቢ፥ ወጣቶች ድረስ ይህንን ትውልድ የመገንባት ሥራውን በሚገባ ለመወጣት በተናጥልም ሆነ በትብብር በአንድነት አደረጃጀቶችን በመጠቀም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ እየተወጡ ይገኛሉ።


የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን መሪ ቃል:-
"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

👉  Website
1
​ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወጣትነት በፈተናና በምኞት ማዕበል የተሞላ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር።

እንኳን ለ15ኛ ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን አደረሳችሁ ።

ስለዚህ ስለ ወጣቶች እንድህ ይለናል ፦
ወጣትነት እንደ "ዱር ፈረስ" እና "እንደሚናወጥ ባሕር" ነው ወጣትነትን ሲገልጸው፦ "ወጣትነት ልክ እንደ ዱር ፈረስ ነው፤ በቀላሉ አይገራም። ወጣትነት ልክ ማዕበል እንደሚናውጠው ባሕር ነው" ይላል። ስለዚህ ወጣቶች በዚህ ዕድሜያቸው እንዳይጠፉና መርከባቸው እንዳይሰምጥ ጠንካራ የመንፈሳዊ ሕይወት መሪ (ኮርቻ) ያስፈልጋቸዋል። ይህ መሪ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ና የሰንበት ትምህርት ቤት ጥበቃ ነው።

👉👉👉👉👉#ሰኔ_14/2018 በ አዳማ ደ/ና/ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን ይከበራል።

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
1👎1