የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.12K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በሽርካ ወረዳ ሁለት ወንድማማች አረጋውያን የሆኑ  ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተሰማ።

በዚህም እስከ አሁን በወረዳው ባለፉት ሦስት !ቀናት ውስጥ ብቻ 31 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገልጿል።

የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የኦርቶዶክሳውያን አሰቃቂ ግድያ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።

ለማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ በደረሰው መረጃ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ሀገረ ስብከቱ በሚገኘው በሽርካ ወረዳ ጢጆ ለቡ ቀበሌ የሚኖሩ ሁለት የ70ና 72 ዓመት ወንድማማች ኦርቶዶክሳውያን አረጋውያን መሳሪያ በታጠቁ ኃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

የግድያው መነሻ ከሰሞኑ በወረዳው 21 የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ጋር የተያያዘ ሲሆን ከበባ ተደርጎባቸው መገደላቸውን መረጃው አስነብቧል።

የተገዱሉት ምእመናን ሀብትና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች ምእመናን ቀዬአቸውን ለቀው በመውጣት እየሸሹ እንደሚገኙም ተነግሯል።

በመረጃው እንደተገለጸው ባለፉት 3 ቀናት ማለትም በየካቲት 19፣20ና 22 በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በተፈጸሙ የግድያ ተግባራት እስከ አሁን ከ30 በላይ  ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል ተብሏል።

በተጨማሪም እስከ አሁን በሀገረ ስብከቱ ሥር ባለው የሽርካ ወረዳ  ብቻ ከ164 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው የመረጃ ምንጫችን ነግረውናል።  ይህ በእንዲህ እንዳለ በተፈጸሙ ጥቃቶች በሕይወት ይኑሩ ወይም ይሙቱ የማይታወቁ በርካታ ምእመና እንዳሉም ተነስቷል።

የሁለቱ ወንድማማቾች ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በጋለማ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን በደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በወረዳው እየተባባሰ የመጣው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ መተላለፉን በመረጃው ላይ ተጠቅሷል።

©ማኅበረ ቅዱሳን
😢1
“በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን ከልብ ቶሎ የማይወጣ፤ ለዘመናትም በህሊና መዝገብ ላይ የሚቆይ ነው፡፡” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለሃይማኖት በመምህር ዘለዓለም ወንድሙ ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።


የቅዱስነታቸው መልእክት ከዚህ እንደሚከተለው ይቀርባል።


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን !!

‹‹ወነአምር ከመ ለእመሂ ተነሥተ ቤተ ማኅደርነ ዘበምድር ዘውእቱ ሥጋ ብነ ሕንጻ በኀበ እግዚአብሔር በሰማያት ዘኢገብሮ እደሰብእ፤ በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን፡፡›› (2ቆሮ. 5፡1)

በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን ከልብ ቶሎ የማይወጣ፤ ለዘመናትም በህሊና መዝገብ ላይ የሚቆይ ነው፡፡

በመሆኑም የሚከተሉት ሃይማኖት ወይም መርጠው ያልተወለዱበት አካባቢ እንደበደል ተቆጥሮባቸው ከየአቅጣጫው በሚሰነዘረው ጥቃት በሚገደሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ምእመናን በአጠቃላይ የሰው ልጆች ኀዘን ልባችን በትካዜ ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት በመንፈሳዊ ሕይወቱ እና በትጋቱ ለቤተ ክርስቲያን ተስፋ የነበረው፤ ለበርካታ ዓመታትም በገጠር፣ በከተማ፣ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥትን ሲያስተምር የቆየው የመንፈስ ቅዱስ ልጃችን መ/ር ዘለዓለም ወንድሙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት በተጓዘባት ሰሜን አሜሪካ ባጋጠመው ሕመም ከዚህ ዓለም ድካም በሥጋ ማረፉን ስንሰማ ታላቅ ድንጋጤ ፈጥሮብናል፡፡

በእርግጥ መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማእት በሥጋ ከእኛ ቢለይም ያለዋጋ የተቀበለውን የእግዚአብሔር ቃል ለምእመናን በማስተማር አደራውን በሚገባ ተወጥቶአልና በሰማይ ወደሚጠብቀው ዘለዓለማዊ ስፍራ በክብር እንደሚገባ እናምናለን፡፡

የመልካም ሰዎች መጉደል ለሀገር በተለይም ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚያስጨንቅ ቢሆንም ሁሉን የሚችል አምላክ ተተኪዎችን እንዲያዘጋጅልን በመጸለይ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ልጃችን ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ምእመናን መጽናናትን እየተመኘን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ የአገልጋዩ ወልደ ሰማዕትን ነፍስ በመንግሥቱ ያሳርፍልን፤

“እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር  ኣሜን!

               + አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
             የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
                አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የጉዞ ትኬቱን ከሚቀርባችሁ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት ያገኛሉ።
👏81
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ.ም አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አደረገ።

የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በጠቅላላ ጉባኤ #የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀርቧል።  በመቀጠልም  በሰንበት ትምህርት ቤቶች የልማት አሰራር ዙሪያ በመ/ር አታለይ መብራቱ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን;  የተጠናከረች ቤተ ክርስቲያን እንድትኖረን ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤቶቻችንን የገንዘብ አቅም ማሳደግና ማጠናከር እንደሚጠበቅ ተገልጧል፡፡

በመቀጠል በመንበረ ጵጵስና አንድነት ልማት ክፍል በኩል በአንድነቱ ሥር በሉህ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በጋራ ከአንድነቱ ጋር በመሆን ሊሰሩ የሚገባ ፕሮጀክት በመቅረጽ ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ውይይት ተደርጎበት ፕርጀከቱ በጠቅላላ ጉባኤ ጸድቋል።

የቀረበው ፕሮጀከት ለሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እና ለአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የልማት ሥራዎችን የሚያነቃቃ እና በሁሉም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እየተተገበረ ያለሁን #ሥርዓተ_ትምህርት በፋይናንስ የሚደግፍ መሆኑን ተጠቁሟል ።

ስለዚህ ይህን ፕሮጀክት ወደ መሬት አውርዶ እንድተገበረ የሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተሳትፎ እና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ተገልጿል።

መረጃው:-  በም/ሸ/ሀ/ስብከት የመንበረ ጵጵስና ር/ከ/ወ/ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ነው።
3
❖ ሆሣዕና በአርያም ❖

ሆሣዕና የዐቢይ ጾም ስምንተኛውና የመጨረሻው እሑድ ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትሕትና በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ ቅድስት ኢየሩሳሌም መግባቱ የሚታሰብበት ታላቅ በዓል ነው።

“ሆሣዕና” የሚለው ስያሜ “ሆሼዕናህ” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም “እባክህ አሁን አድን” ማለት ነው።

ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ ነቢያት እግዚአብሔርን ለማመስገንና ምሕረቱን ለመለመን ይጠቀሙበት የነበረ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሕፃናትና አእሩግ ጌታን የተቀበሉበት የምስጋና መዝሙር ሆኗል።

ይህ ዕለት “የጸበርት እሑድ” በመባልም ይታወቃል፤ የዘንባባ ዝንጣፊ መያዝ ጥንታዊ የታሪክና የምሥጢር መሠረት ያለው ሲሆን ሣራ ይስሐቅን በወለደች ጊዜና እስራኤል ባሕረ ኤርትራን ሲሻገሩ ደስታቸውን በዘንባባ ገልጠዋል።

ዘንባባ እሳት የማይበላውና ደርቆ እንደገና የሚያለመልም በመሆኑ ጌታ የማይመረመር ባሕርይ ያለውና የደረቀ ሕይወትን የሚያለመልም አምላክ መሆኑን ያመለክታል።

በዕለቱ ዘንባባውን እንደ ቀለበት ማሠራችን ጌታ ለአዳም፣ ለእመቤታችንና ለእስራኤል የገባውን የምሕረት ቃል ኪዳን ለማስታወስ እንዲሁም እኛም ለንስሐ ቃል የምንገባበት ምልክት ነው።

ጌታችን በፈረስ ፋንታ በአህያ ላይ ተቀምጦ መግባቱ ትልቅ ትምህርት አለው፤ ፈረስ የጦርነት ምልክት ሲሆን አህያ ግን የትሕትናና የሰላም ተምሳሌት በመሆኗ ጌታ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያሳያል።

በአህያ የተቀመጠ ሰው በቀላሉ እንደሚገኝ ሁሉ ጌታም በእምነት ለሚፈልጉት ሁሉ የቅርብ አምላክ መሆኑን ያስተምራል።

ትልቋ አህያ የሸክም ወይም የሕገ ኦሪት ምሳሌ ስትሆን ውርንጫዋ ደግሞ ማንም ያልተጫነባት የሕገ ወንጌልና የአሕዛብ ምሳሌ ናት። ነቢዩ ዘካርያስ “ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ብሎ የተነገረው ትንቢት በዚህ ዕለት ተፈጽሟል።

ሕዝቡ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ ማንጠፋቸው ለክብሩ መግለጫ ሲሆን ሕፃናት “ሆሣዕና በአርያም” እያሉ መዘመራቸው ደግሞ መድኃኒትነት ለእርሱ ብቻ እንደሚገባ ምስክርነት ሰጥተዋል።

በዓለ ሆሣዕና የሕማማት ሳምንት መግቢያ ዋዜማ በመሆኑ በዚህ ዕለት በቤተ ክርስቲያን የዘንባባ ዝንጣፊ ተባርኮ ለምእመናን ይታደላል፤ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ስለማይደረግም ቀድሞ አጠቃላይ ጸሎተ ፍትሐት ይከናወናል።

እኛም እንደ አህያይቱ ጌታን በሕይወታችን ልንሸከመው ልባችንንም ከኃጢአት አንጽተን ፍቅርንና ትሕትናን ገንዘብ ልናደርግ ይገባል።

ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር የተወደደች ሀገራችንን ኢትዮጵያን መሐሏን ገነት አድርጎ ዳር ድንበሯን በመለኮታዊ እሳት ይጠብቅልን፤ በመካከላችን የማይነካ ሰላምንና የማይፈርስ አንድነትን ያጽናልን፤ ለሁላችንም ከክፋት የምንርቅበትና ወደ እርሱ የምንቀርብበትን የዕድሜ ባለጸግነትና የንስሐ ዘመንን ይስጠን፤ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም የመንግሥቱ ወራሾች የዘለዓለማዊ ክብሩም ቀዳሾች ያድርገን። አሜን።

በዲ/ን አየለ

#ሆሣዕና #ዐቢይ_ጾም #የሰላም_ንጉሥ #ኢየሩሳሌም #ተዋሕዶ #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #ዘንባባ #Hoseanna #Orthodox #Ethiopia
የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና (Mid Exam) ማሳሰቢያ
​ለመንበረ ጳጳስ ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሙሉ፤
​የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና (mid exam) ከሚያዝያ 17 እስከ ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም የሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
​ተማሪዎች ለፈተናው አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን፤ ዝርዝር መርሃ ግብሩን ከየሰንበት ትምህርት ቤቶቻችሁ መከታተል ትችላላችሁ።
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የትምህርት አፈጻጸም ክፍል

Beeksisa Qormaata Walakkaa Semisiteera Lammaffaa (Mid Exam)
​Mannen Barumsa Sanbataa magaalaa adaamaa hundaaf;
​Qormaatni walakkaa semisiteera lammaffaa (mid exam) bara 2018, Ebla 17 hanga Ebla 25/2018tti manneen barumsa sanbataa hunda keessatti kan kennamu ta'uu isiniin beeksifna.
​Barattoonni qormaata kanaaf qophii barbaachisaa akka taasistan jabeessinee dhaamna. Sagantaa bal’aa manneen barumsa sanbataa keessan irraa hordofuu ni dandeessu.
Kutaa Raawwii Barnootaa Tokkummaa Manneen Barumsa Sanbataa Magaalaa Adaamaa
👍5
እንኳን አደረሰን

💦💦የሚገርም ፍቅር💦💦💦

የጌታችን ሕማማት በሊቃውንት
:
☞በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት በማዳኑ፣ ዕዉራነ ሥጋን በተአምራት ዕዉራነ ነፍስን በትምህርት በማብራቱ፣ ልሙጻነ ሥጋን በተአምራት ልሙጻነ ነፍስን በትምህርት በማንጻቱ፣ አጋንንትን በማውጣቱ፣ ሙታንን በማንሣቱና ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ ልጅ መኾኑን በማስተማሩ አይሁድ ከፍተኛ ቅንአት ዐድሮባቸው ጌታን ይዘው የካህናት አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ይዘውት በመኼድ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ኹሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሐሰት ምስክር ቢፈልጉም ምንም ዐይነት በደል ሊያገኙበት አልቻሉም ነበር፤ በኋላም ሊቀ ካህናቱ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የኾንኽ እንደ ኾነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልኻለኊ” ብሎ ሲጠይቀው፤ ጌታም “አንተ አልኽ፤ ነገር ግን እላችኋለኊ፤ ከእንግዲኽ ወዲኽ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችኊ” በማለት ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው በአብ ቀኝ ያለው የአብ የባሕርይ ልጅ የኾነው ርሱን በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ማለት፡- ዓለምን በማሳለፍ ኀይል ባለው ዕሪና በባሕርይ ክብሩ መጥቶ ታዩታላችኊ በማለት ተናገረው (ማቴ 26፡63-64)፡፡
ያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ በንዴት ልብሱን ቀደደ፤ በዘሌ 21፡10 ላይ “በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ከወንድሞቹ የበለጠው ካህን ራሱን አይግለጥ ልብሱንም አይቅደድ” በማለት እንዳዘዘው በኦሪት ሥርዐት ካህን በሐዘን ምክንያት ልብሱን ከቀደደና ፊቱን ከነጨ ከሹመቱ የሚሻር ነውና በዚኽም የሊቀ ካህናቱ ኦሪታዊ ክህነት ማለፉን አጠይቋል፡፡
ከዚያ በኋላ ጌታን “ሞት ይገባዋል” በማለት በደረቅ ግንባር ላይ ዐይንን በፈጠረ በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፡- ጌታ በኢሳይያስ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ወኢይትሀከዩ ወሪቀ ውስተ ገጽየ ወኢሜጥኩ ገጽየ እምኀፍረተ ምራቅ” (ዠርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠኊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም) ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ምራቃቸውን ተፍተውበታል፡፡ አንድም አዳምን ዲያብሎስ በገጸ ልቡናው ምራቀ ምክሩን እየተፋ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ካሳ ሊኾን ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፍቶበታል፡፡
ከዚያም ራሱን በዘንግ መቱት “ወኲሉ ርእስ ለሕማም” (ራስ ኹሉ ለሕመም ኾኗል) ብሎ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት ይደርስ ይፈጸም ዘንድ የሕይወት ራስ ርሱን በዘንግ መቱት (ኢሳ ፩፥፭)፤ አንድም ዲያብሎስ የአዳምን ርእሰ ልቡናውን በበትረ ምክሩ እየመታ ሲኦል አውርዶት ነበርና ካሳ ሊኾን ነበር፤ ከዚያም ፊቱን በሻሽ ሸፍነው “መኑ ውእቱ ክርስቶስ ዘጸፍዐከ” (ክርስቶስ በጥፊ የመታኽ ማነው? ንገረን እስቲ ዕወቀን) እያሉ ዘብተውበታል፤ ይኸውም መተርጒማን እንዳመሰጠሩት አዳምና ሔዋን የአምላክነትን ዕውቀት ዕንወቅ ብለው ሲኦል ወርደው ነበርና ልቡና ያሰበውን ኩላሊት ያመላለሰውን ኹሉን የሚያውቅ ርሱ ላይ በዚኽ ቃል መዘበታቸው ለአዳምና ለሔዋን ሊክስላቸው ነው፡፡
ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት የሚያድሩ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የኾኑት ኤልሳቤጥ፣ ቤርዜሊ፣ መልቴዳ በዕለተ ዐርብ በዐይናቸው ያዩትን የጌታን ሕማማት በተናገሩበት ድርሳን ላይ ይኽነን ሲገልጹ፡- “ወሶበ ዘበጥዎ አፉሁ ለእግዚእ ኢየሱስ ሐሙ ከናፍሪሁ ወአስናኒሁ፤ ወውሒዘ ደም ብዙኅ እምአፉሁ…” (ጌታችን ኢየሱስን አፉን በመቱት ጊዜ ከንፈሮቹ ጥርሶቹም ታመሙ፤ ከጌታችንም ከኢየሱስ አፍ ብዙ ደም ፈሰሰ፤ አሕዛብን በሚያጠፋበት ስለቱ (ሥልጣኑ) በኹለት ፊት የኾነ የተሳለ ሰይፍ ከአንደበቱ የሚወጣ ሲኾን (ወደ እኔ ኑ፣ ከእኔ ኺዱ የሚልበት ሥልጣን ገንዘቡ ሲኾን) (ማቴ ፳፭፥፴፩-፵፮)፤ ዳግመኛ አይሁድ ጌታችን ኢየሱስን ፊቱን ፳ ጊዜ በጡጫ መቱት ይኸውም እግዚአብሔር አብን መንፈስ ቅዱስንም በመልክ የሚመስል በባሕርይ የሚተካከል ነው (ዮሐ 10፡30)፤ በጌትነት ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸ ጊዜ ተለውጦ እንደ ፀሓይ ያበራ መልኩ ፊቱ ነው (ማቴ ፲፯፥፪)፤ ርሱ የማይጠልቅ ፀሓይ የማይጠፋ ፋና ነውና፤ በወዳጆቹም ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሓይ ነውና (ራእ ፳፪፥፭)፤ ሰነፎች አይሁድም ከምድር ነገሥታት ይልቅ የሚያስፈራ ፊቱን ሲመቱት የጌታችን የኢየሱስ የፊቱ ግርማ ሦስት ጊዜ ወደ ምድር የኋሊት የጣላቸው መኾኑን አላሰቡትም) በማለት በቅንአት የሰከሩ የዝንጉኣን የአይሁድን ነገር አስምረዋል፡፡
ዓለምን ለማዳን ሲል አካላዊ ቃል ክርስቶስ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም በቅዳሴው ላይ ሲተነትናቸው፡- “በይእቲ ሌሊት እንተ ባቲ ረፈቀ ምስለ አርዳኢሁ መጠወ ነፍሶ ለሞት በፈቃደ አቡሁ ወበሥምረተ ርእሱ…”
(ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በተመጠባት በዚያች ሌሊት በአባቱ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ ሰውነቱን ለሞት ሰጠ፤ ኹሉን የያዘውን ያዙት ኹሉን የሚገዛውን አሰሩት የሕያው የአምላክን ልጅ አሰሩት፤ በቊጣ ጐተቱት በፍቅር ተከተላቸው፤ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተላቸው ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በዐደባባይ አቆሙት ኀጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን ርሱን (ኢሳ ፮፥፪፤ ራእ ፭፥፭-፲፬)፤ ክፉ ባሪያ እጁን አጽንቶ ፊቱን ጸፋው (ዮሐ ፲፰፥፳፪)
የመላእክት ሰራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ (ፊልጵ ፪፥፲) ይኽን ያኽል ትሕትና እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው?፤ ይኽን ያኽል ዝምታ እንደ ምን ያለ ዝምታ ነው?፤ ይኽን ያኽል ቸርነት እንደ ምን ያለ ቸርነት ነው?፤ ይኽን ያኽል ሰውን ማፍቀር እንደ ምን ያለ ፍቅር ነው?፤ ኀያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው፤ በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት፤ ሕይወት የሠራውን ከበደለኞች ጋራ ቈጠሩት፤ አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በአዳም ላይ የሕይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሐሞት ጋራ የተቀላቀለ የኾመጠጠ መጻጻን ጠጣ ወዮ፤ የወልድ መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ኅሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል፤ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ) በማለት ሕማማቱን በስፋት አስተምሮታል፡፡
ወንጌላውያንም እንደጻፉት ጌታችንን አይሁድ ኀሙስ ማታ ከያዙት በኋላ “ወወሰድዎ ለእግዚእ ኢየሱስ እምኀበ ቀያፋ ኀበ ዐውድ ወጎሕ ውእቱ” ይላል በማለዳ ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወደ ፍርድ ዐደባባይ አስረው በማለዳ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ወስደውታል (ማቴ ፳፯፥፲፩፤ ማር ፲፭፥፩፤ ሉቃ ፳፫፥፩፤ዮሐ ፲፰፥፳፰) ይኸውም አዳምን ከመልአከ ገሀነም ፊት አስረው ወስደው አቁመውት ነበርና ለካሣ ሊኾን ነበር፡፡ .
ይኽ የጌታችን ትሕትና ብዙዎችን አስደንቋል፤ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንትም በቅዳሴያቸው ላይ “በይእቲ ሌሊት አኀዝዎ ወጸቢሖ ረበናተ አይሁድ ወሊቃነ ካህናት ምስለ ጲላጦስ መስፍን ወነበሩ ዐውደ ለኰ
ንኖቱ…” (በዚያች ሌ
ሊት ያዙት.
በነጋም ጊዜ የአይሁድ መምህሮችና የካህናት አለቆች ከገዢው ከጲላጦስ ጋራ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፤ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ የመላእክት ሰራዊት በመፍራት የሚቆሙለትን በፊታቸው አቆሙት፤ ክፉ ባሪያ ርሱን ያልበደለውን ፊቱን በጥፊ ይመታው ዘንድ እጁን አጸና፤ የመላእክት አለቆች በፍጹም ድንጋፄ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት ይሰግዱ ዘንድ አጐነበሱለት) በማለት ዐርብ ጠዋት አይሁድ ጌታን ወደ ፍርድ ዐደባባይ እንዴት እንዳቀረቡት በስፋት አስተምረዋል፡፡
ጌታ ከመወለዱ አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድሞ ጌታችን በንጉሥ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፰ ላይ “ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጭፍሮች ጌታን ከሰቀሉት በኋላ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ኾኖ በአራት ሲከፋፍሉት ከላይ ዠምሮ ወጥ ኾኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ ያልነበረው እጀ ጠባቡን ደግሞ በመውሰድ ርስ በርሳቸው ለማን እንዲኾን በርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባለዋል፤ ይኽቺውም ቀሚሱ ሰብአ ሰገል ያመጡለት ሲያድግ የምታድግ ዐሥራ ኹለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የነበረችው ሴት የተፈወሰችበት ገባሪተ ተአምራት ነበረች (ማቴ ፪፥፲፩፤ ፱፥፳)፡፡
አይሁድ ይኽነን ማድረጋቸው ለጊዜው “ኹለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል” (ማቴ ፭፥፵) በማለት ኹለት ልብስ አታኑሩ በማለት የሚያስተምረው የርሱ ልብስ ለአራት ቤት ጭፍራ በቃ ለማለት ለመዘበት ሲኾን ፍጻሜው ግን ልብስ የወንጌል ምሳሌ አራት ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ወገን ኹና ለመጻፏ፤ አለመቅደዳቸው በምስጢር አንድ የመኾኗ፤ አንድም አራቱ ኹሉ ባንዲቱ ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ክፍል ስትኾን አንድ ሕግ ለመኾኗ ምሳሌ፤ አንድም “አንቅደድ” ማለታቸው ትስብእቱን ከመለኮቱ ሳንለይ እንመን ሲያሰኛቸው ነው በማለት መተርጒማነ ሐዲስ ያመሰጥራሉ (ማቴ ፳፯፥፴፭፤ ማር ፲፭፥፳፬፤ ሉቃ ፳፫፥፴፬፤ ዮሐ ፲፱፥፳፫)፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነን ሲገልጹ “ወእምዝ አዕተቱ አልባሲሁ ወአልበስዎ ሜላተ ልብስ…” (ከዚያም ልብሶቹን ገፍፈው የመንግሥት ልብስ የሚኾን ነጭ ሐር የካህናት ልብስ የሚኾን ቀይ ሐር ሕብራቸው ቀይና ጥቁር የሚኾን ልብስ አለበሱት፤ የአጣቢ ሳሙና ማንጻት የማይቻለው እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ እንደ በረድ የኾነ ነጭ ልብስ የሚለብስ ሲኾን፤ ለኪሩቤል የመብረቅ ልብስን ለሱራፌል ግርማ ያለው ልብስን የሚያለብሳቸው ርሱን እንደዚኽ በምድር በመዘባበት ቀይ ሐርና ነጭ ልብስ አለበሱት) በማለት አስተምረዋል፡፡
ልዑል አምላክ ዘመኑ ሲፈጸም ስለሚቀበላቸው ሕማማተ መስቀል አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፮ ላይ “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ዳግመኛም ከ፯፻ ዓመት አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስም ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጌታችንን አይሁድ ገርፈውታል፡፡
አንድም ንጹሐ ባሕርይ ጌታችን መገረፉ ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡና እየገረፈ ወደ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ሊክስለት ሲኾን ዳግመኛም በጌታ ላይ አይሁድ የግፍ ድርብ አድርገውበታል በሀገራቸው የሚሰቀል አይገረፍም ነበር በተጨማሪም በኦሪት ልምድ ከአርባ አትርፎ መግረፍ የተከለከለ ሲኾን እነርሱ ግን ፴፱ ጊዜ ከገረፉ በኋላ ቊጥር ተሳሳትን እያሉ ሥጋው ዐልቆ ዐጥንቱ እንደ በረድ ነጭ እስከሚኾን ድረስ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ግርፋትን ገርፈው እንደ ብራና ወደዚያና ወደዚኽ ወጥረው ሲሰቅሉት ዐጥንቱ ታይቶ የሚቈጠር ኹኗል፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነኑ ሲያብራሩ
“ወእምድኅረ አሠርዎ ቀሠፍዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ጲላጦስ ወአርባዕቱ ሐራ በሐብል ወበአስዋጥ መጠነ ፷፻ ወ፮፻፷፮ … ”
(ጌታችን ኢየሱስንም ካሠሩት በኋላ አራት ቤት ጭፍሮችና ጲላጦስ በገመድና ባለንጋ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ጊዜ ገረፉት፤ ዐምስት እልፍ ነው የሚሉም አሉ፤ የግርፋቱን ቊጥር እያሳሳቱ ገርፈውታልና፤ የሚሞት እንዳይገረፍ የማይሞት እንዲገረፍ እያወቁ፤ በግፍ ገርፈው በግፍ ገደሉት የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ፤ ከግርፋቱም ጽናት የተነሣ ሥጋው ኹሉ ዐለቀ፤ ሺሕ ከ፮፻ ከሚኾኑ ቊስሎቹም ወገን ዐጥንቶች ታዩ፤ ጥቁርና ሰማይ የሚመስሉ ቊስሎቹ ግን ሺሕ አንድ መቶ ከዘጠና ናቸው፤ የማይገረፍ አምላክ በዚኽ ሥጋ ተገረፈ፤ ጲላጦስ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችንን የገረፈው በዦሮ ለሚሰማው በዐይን ለሚያየው ሰው ዕጹብ ድንቅ ነው፤ በመገረፉም አይሁድን ደስ አሰኛቸው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን በመገረፉ ሰው ኹሉ ከተገረፈባት ኀጢአት ፍዳ አዳነን፤ ስለ ልጆቹና ስለ አዳም መገረፍን መታሠርን ከፍሏልና) በማለት ለኹላችን ካሳ ስለተገረፈው ግርፋት አስተምረዋል፡፡
በነቢዩ ኢሳይያስ ላይ ጌታ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” ብሎ ያናገረው ሊደርስ ሊፈጸም ክብር ይግባውና በአምላካችን ፊት ላይ አይሁድ ምራቃቸውን ተፍተውበታል፤ ዳግመኛም ዲያብሎስ ምራቀ ምክሩን እየተፋ ወደ ሲኦል ላወረደው ለአዳም ሊክስለት የማኅበረ አይሁድን ምራቅ ክብር ይግባውና አምላካችን በትዕግሥት ተቀብሎታል፡፡

ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል ሲያብራሩ “አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ…” (የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና፤ በቀኝ እጁ ዘንግ አስያዙት፤ ሲያሽሟጥጡ በፊቱ እየወደቁ እጅ ነሡለት፤ የመላእክት ሰራዊት እየደነገፁ የሚሰግዱለትን የአይሁድ ንጉሥ ቸር ውለኻል አሉት፤ ሥልጣናትና ሊቃናት እየፈሩ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት እጅ ነሡት፤
ዐምስት የሚኾኑ መዘባበቻቸውን ከጨረሱ በኋላ በምራቁ ኹለተኛ ዐይኖችን በሚፈጥር በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዳግመኛም ፊቱን በጥፊ መቱት፤ ኪሩቤል ፊቱን ከማየት የተነሣ በእሳት አክናፍ የሚሰወሩት ያልበደላቸውን ርሱን አይሁድ በጥፊ መቱት፤ ፊቱ እንደ መንፈስ ቅዱስና እንደ አባቱ ሲኾን በተዋሐደው ሥጋ ፊቱን ጸፉት ከፊቱ ግርማ የተነሣ ፍጥረቱ ኹሉ የሚርዱለት የሚንቀጠቀጡለት የፈጣሪያቸውን ፊቱን ጸፉት፤ መዠመሪያ በመመታቱና የሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ራሱ የቈሰለ ከመኾኑም በላይ