የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.12K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በሽርካ ወረዳ ሁለት ወንድማማች አረጋውያን የሆኑ  ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተሰማ።

በዚህም እስከ አሁን በወረዳው ባለፉት ሦስት !ቀናት ውስጥ ብቻ 31 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገልጿል።

የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የኦርቶዶክሳውያን አሰቃቂ ግድያ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።

ለማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ በደረሰው መረጃ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ሀገረ ስብከቱ በሚገኘው በሽርካ ወረዳ ጢጆ ለቡ ቀበሌ የሚኖሩ ሁለት የ70ና 72 ዓመት ወንድማማች ኦርቶዶክሳውያን አረጋውያን መሳሪያ በታጠቁ ኃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

የግድያው መነሻ ከሰሞኑ በወረዳው 21 የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ጋር የተያያዘ ሲሆን ከበባ ተደርጎባቸው መገደላቸውን መረጃው አስነብቧል።

የተገዱሉት ምእመናን ሀብትና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች ምእመናን ቀዬአቸውን ለቀው በመውጣት እየሸሹ እንደሚገኙም ተነግሯል።

በመረጃው እንደተገለጸው ባለፉት 3 ቀናት ማለትም በየካቲት 19፣20ና 22 በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በተፈጸሙ የግድያ ተግባራት እስከ አሁን ከ30 በላይ  ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል ተብሏል።

በተጨማሪም እስከ አሁን በሀገረ ስብከቱ ሥር ባለው የሽርካ ወረዳ  ብቻ ከ164 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው የመረጃ ምንጫችን ነግረውናል።  ይህ በእንዲህ እንዳለ በተፈጸሙ ጥቃቶች በሕይወት ይኑሩ ወይም ይሙቱ የማይታወቁ በርካታ ምእመና እንዳሉም ተነስቷል።

የሁለቱ ወንድማማቾች ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በጋለማ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን በደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በወረዳው እየተባባሰ የመጣው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ መተላለፉን በመረጃው ላይ ተጠቅሷል።

©ማኅበረ ቅዱሳን
😢1
“በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን ከልብ ቶሎ የማይወጣ፤ ለዘመናትም በህሊና መዝገብ ላይ የሚቆይ ነው፡፡” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለሃይማኖት በመምህር ዘለዓለም ወንድሙ ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።


የቅዱስነታቸው መልእክት ከዚህ እንደሚከተለው ይቀርባል።


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን !!

‹‹ወነአምር ከመ ለእመሂ ተነሥተ ቤተ ማኅደርነ ዘበምድር ዘውእቱ ሥጋ ብነ ሕንጻ በኀበ እግዚአብሔር በሰማያት ዘኢገብሮ እደሰብእ፤ በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን፡፡›› (2ቆሮ. 5፡1)

በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን ከልብ ቶሎ የማይወጣ፤ ለዘመናትም በህሊና መዝገብ ላይ የሚቆይ ነው፡፡

በመሆኑም የሚከተሉት ሃይማኖት ወይም መርጠው ያልተወለዱበት አካባቢ እንደበደል ተቆጥሮባቸው ከየአቅጣጫው በሚሰነዘረው ጥቃት በሚገደሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ምእመናን በአጠቃላይ የሰው ልጆች ኀዘን ልባችን በትካዜ ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት በመንፈሳዊ ሕይወቱ እና በትጋቱ ለቤተ ክርስቲያን ተስፋ የነበረው፤ ለበርካታ ዓመታትም በገጠር፣ በከተማ፣ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥትን ሲያስተምር የቆየው የመንፈስ ቅዱስ ልጃችን መ/ር ዘለዓለም ወንድሙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት በተጓዘባት ሰሜን አሜሪካ ባጋጠመው ሕመም ከዚህ ዓለም ድካም በሥጋ ማረፉን ስንሰማ ታላቅ ድንጋጤ ፈጥሮብናል፡፡

በእርግጥ መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማእት በሥጋ ከእኛ ቢለይም ያለዋጋ የተቀበለውን የእግዚአብሔር ቃል ለምእመናን በማስተማር አደራውን በሚገባ ተወጥቶአልና በሰማይ ወደሚጠብቀው ዘለዓለማዊ ስፍራ በክብር እንደሚገባ እናምናለን፡፡

የመልካም ሰዎች መጉደል ለሀገር በተለይም ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚያስጨንቅ ቢሆንም ሁሉን የሚችል አምላክ ተተኪዎችን እንዲያዘጋጅልን በመጸለይ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ልጃችን ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ምእመናን መጽናናትን እየተመኘን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ የአገልጋዩ ወልደ ሰማዕትን ነፍስ በመንግሥቱ ያሳርፍልን፤

“እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር  ኣሜን!

               + አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
             የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
                አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የጉዞ ትኬቱን ከሚቀርባችሁ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት ያገኛሉ።
👏81
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ.ም አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አደረገ።

የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በጠቅላላ ጉባኤ #የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀርቧል።  በመቀጠልም  በሰንበት ትምህርት ቤቶች የልማት አሰራር ዙሪያ በመ/ር አታለይ መብራቱ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን;  የተጠናከረች ቤተ ክርስቲያን እንድትኖረን ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤቶቻችንን የገንዘብ አቅም ማሳደግና ማጠናከር እንደሚጠበቅ ተገልጧል፡፡

በመቀጠል በመንበረ ጵጵስና አንድነት ልማት ክፍል በኩል በአንድነቱ ሥር በሉህ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በጋራ ከአንድነቱ ጋር በመሆን ሊሰሩ የሚገባ ፕሮጀክት በመቅረጽ ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ውይይት ተደርጎበት ፕርጀከቱ በጠቅላላ ጉባኤ ጸድቋል።

የቀረበው ፕሮጀከት ለሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እና ለአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የልማት ሥራዎችን የሚያነቃቃ እና በሁሉም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እየተተገበረ ያለሁን #ሥርዓተ_ትምህርት በፋይናንስ የሚደግፍ መሆኑን ተጠቁሟል ።

ስለዚህ ይህን ፕሮጀክት ወደ መሬት አውርዶ እንድተገበረ የሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተሳትፎ እና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ተገልጿል።

መረጃው:-  በም/ሸ/ሀ/ስብከት የመንበረ ጵጵስና ር/ከ/ወ/ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ነው።
3
❖ ሆሣዕና በአርያም ❖

ሆሣዕና የዐቢይ ጾም ስምንተኛውና የመጨረሻው እሑድ ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትሕትና በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ ቅድስት ኢየሩሳሌም መግባቱ የሚታሰብበት ታላቅ በዓል ነው።

“ሆሣዕና” የሚለው ስያሜ “ሆሼዕናህ” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም “እባክህ አሁን አድን” ማለት ነው።

ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ ነቢያት እግዚአብሔርን ለማመስገንና ምሕረቱን ለመለመን ይጠቀሙበት የነበረ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሕፃናትና አእሩግ ጌታን የተቀበሉበት የምስጋና መዝሙር ሆኗል።

ይህ ዕለት “የጸበርት እሑድ” በመባልም ይታወቃል፤ የዘንባባ ዝንጣፊ መያዝ ጥንታዊ የታሪክና የምሥጢር መሠረት ያለው ሲሆን ሣራ ይስሐቅን በወለደች ጊዜና እስራኤል ባሕረ ኤርትራን ሲሻገሩ ደስታቸውን በዘንባባ ገልጠዋል።

ዘንባባ እሳት የማይበላውና ደርቆ እንደገና የሚያለመልም በመሆኑ ጌታ የማይመረመር ባሕርይ ያለውና የደረቀ ሕይወትን የሚያለመልም አምላክ መሆኑን ያመለክታል።

በዕለቱ ዘንባባውን እንደ ቀለበት ማሠራችን ጌታ ለአዳም፣ ለእመቤታችንና ለእስራኤል የገባውን የምሕረት ቃል ኪዳን ለማስታወስ እንዲሁም እኛም ለንስሐ ቃል የምንገባበት ምልክት ነው።

ጌታችን በፈረስ ፋንታ በአህያ ላይ ተቀምጦ መግባቱ ትልቅ ትምህርት አለው፤ ፈረስ የጦርነት ምልክት ሲሆን አህያ ግን የትሕትናና የሰላም ተምሳሌት በመሆኗ ጌታ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያሳያል።

በአህያ የተቀመጠ ሰው በቀላሉ እንደሚገኝ ሁሉ ጌታም በእምነት ለሚፈልጉት ሁሉ የቅርብ አምላክ መሆኑን ያስተምራል።

ትልቋ አህያ የሸክም ወይም የሕገ ኦሪት ምሳሌ ስትሆን ውርንጫዋ ደግሞ ማንም ያልተጫነባት የሕገ ወንጌልና የአሕዛብ ምሳሌ ናት። ነቢዩ ዘካርያስ “ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ብሎ የተነገረው ትንቢት በዚህ ዕለት ተፈጽሟል።

ሕዝቡ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ ማንጠፋቸው ለክብሩ መግለጫ ሲሆን ሕፃናት “ሆሣዕና በአርያም” እያሉ መዘመራቸው ደግሞ መድኃኒትነት ለእርሱ ብቻ እንደሚገባ ምስክርነት ሰጥተዋል።

በዓለ ሆሣዕና የሕማማት ሳምንት መግቢያ ዋዜማ በመሆኑ በዚህ ዕለት በቤተ ክርስቲያን የዘንባባ ዝንጣፊ ተባርኮ ለምእመናን ይታደላል፤ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ስለማይደረግም ቀድሞ አጠቃላይ ጸሎተ ፍትሐት ይከናወናል።

እኛም እንደ አህያይቱ ጌታን በሕይወታችን ልንሸከመው ልባችንንም ከኃጢአት አንጽተን ፍቅርንና ትሕትናን ገንዘብ ልናደርግ ይገባል።

ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር የተወደደች ሀገራችንን ኢትዮጵያን መሐሏን ገነት አድርጎ ዳር ድንበሯን በመለኮታዊ እሳት ይጠብቅልን፤ በመካከላችን የማይነካ ሰላምንና የማይፈርስ አንድነትን ያጽናልን፤ ለሁላችንም ከክፋት የምንርቅበትና ወደ እርሱ የምንቀርብበትን የዕድሜ ባለጸግነትና የንስሐ ዘመንን ይስጠን፤ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም የመንግሥቱ ወራሾች የዘለዓለማዊ ክብሩም ቀዳሾች ያድርገን። አሜን።

በዲ/ን አየለ

#ሆሣዕና #ዐቢይ_ጾም #የሰላም_ንጉሥ #ኢየሩሳሌም #ተዋሕዶ #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #ዘንባባ #Hoseanna #Orthodox #Ethiopia
የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና (Mid Exam) ማሳሰቢያ
​ለመንበረ ጳጳስ ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሙሉ፤
​የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና (mid exam) ከሚያዝያ 17 እስከ ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም የሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
​ተማሪዎች ለፈተናው አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን፤ ዝርዝር መርሃ ግብሩን ከየሰንበት ትምህርት ቤቶቻችሁ መከታተል ትችላላችሁ።
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የትምህርት አፈጻጸም ክፍል

Beeksisa Qormaata Walakkaa Semisiteera Lammaffaa (Mid Exam)
​Mannen Barumsa Sanbataa magaalaa adaamaa hundaaf;
​Qormaatni walakkaa semisiteera lammaffaa (mid exam) bara 2018, Ebla 17 hanga Ebla 25/2018tti manneen barumsa sanbataa hunda keessatti kan kennamu ta'uu isiniin beeksifna.
​Barattoonni qormaata kanaaf qophii barbaachisaa akka taasistan jabeessinee dhaamna. Sagantaa bal’aa manneen barumsa sanbataa keessan irraa hordofuu ni dandeessu.
Kutaa Raawwii Barnootaa Tokkummaa Manneen Barumsa Sanbataa Magaalaa Adaamaa
👍5