የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.12K subscribers
1.76K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ

‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ
ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት››
(ማቴ 5÷51 ፤   ቅዱስ ያሬድ)

ከዚህ በፊት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች የበርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሕይወት በመጥፋቱና ከሞት የተረፉትም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጠው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት፣ በደረሰው ሞትና ስደት ምእመናን እያዘነ ባሉበት፣ እኛም ከኃዘናችን ባልተጽናናንበት ሁኔታ ጥቃቱ በአዲስ መልኩ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት በግፍ ማለፉን፣ በሕይወት የተረፉትም በታጣቂዎቹ መታገታቸውንና የደረሱበት አለመታወቁን፣ h10 የሚበልጡ አባውራዎች ቤትና ንብረት እንደተቃጠለ በመግለጽ ከሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሪፖርት የተመለከትነው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነው፡፡

አገር  ሰላም ብለው በሚኖሩት ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ በሌላቸው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላትም ግድያውን በሃይማኖት ስም ይፈጽሙት እንጂ የሃይማኖት ስዎች ግን አይደሉም፡፡ ዓላማቸውም በሀገራችን ለረዥም ዘመናት ተከባብረው አብረው በኖሩት የሃይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን መፍጠር  ነውና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል፡፡

በመሆኑም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለታዊ ኑሮ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣

ፍርድን በመሻት የሚጮኸው ስለስሙ መከራን የተቀበሉት የንጹሐን ደም ተገቢውን ፍትሕ ይፈልጋልና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ወደፊትም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ የዜጐች ሀብትና ንብረት እንዳይወድም መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን እንዲያከናውን ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንኦት ያስተላልፋል፤

በደረሰው አደጋ ዙሪያ ተነጋግሮ ተገቢውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተሰበሰበው ቋሚ ሲኖዶስም የአካባቢው ችግር አስተማማኝ በሆነ መንገድ ተፈትቶ ዘላቂ ስላም እስኪገኝ ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የተሰየመው የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚመለከታቸውም አካላት በየድርሻቸው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ በክብር ያሳስባል፡፡

የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው መስተዳድርም ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደፊትም ችግሩ እንዳይደገም ከመሠረቱ መፍታት የሚያስችል እርምጃ እንዲወስድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትጠይቃለች፡፡

በመጨረሻም ስለስሙ በሥጋቸው መከራን በመቀበል ሕይወታቸውን በአጡት ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን ልዑል እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስን እንዲሰጥልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲያጽናናልን እንጸልያለን፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቋሚ ሲኖዶስ
የካቲት 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
1
አድዋ

"በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።" መዝ 43፡5

እንኳን ለአድዋ ድል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

👉  Website
1
አድዋ የቤተክርስቲያን ሀገሪነት ማሰያ ነው።

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ጋር በመተባበር የአድዋን በዓል አከበረ።

በመርሐ ግብሩ ጥናታዊ ጹሕፍ የቀረበ ስሆን በጹሕፉ ላይ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተወህዶ ቤተክርስቲያን በሀገረ ሉዓላዊነት መጠበቀ ላያ ያሳየችው ታላቅ ሚና በስፋት ተዳሰዋል። አባቶቻቸውን ጠላት ሀገረን ለመውረር ስመጣ ''ኢትዮጵያ ስጋችን ቤተክርቲያን ነፍሳችን ናት ነፍስ እና ስጋ ደግሞ አንድ ነው። ሀገረ ያለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ያለ ሀገር የለም። ሃይማኖትና ነጻነትን ማጣት ሽንፈት ነው። ስለ ሀገረ ሃይማኖትና ነጻነትን መሞት ክብረ ነው'' ብለው ታቦት ይዘው ጠላት ድል ነስተዋል።
በሽርካ ወረዳ ሁለት ወንድማማች አረጋውያን የሆኑ  ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተሰማ።

በዚህም እስከ አሁን በወረዳው ባለፉት ሦስት !ቀናት ውስጥ ብቻ 31 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገልጿል።

የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የኦርቶዶክሳውያን አሰቃቂ ግድያ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።

ለማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ በደረሰው መረጃ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ሀገረ ስብከቱ በሚገኘው በሽርካ ወረዳ ጢጆ ለቡ ቀበሌ የሚኖሩ ሁለት የ70ና 72 ዓመት ወንድማማች ኦርቶዶክሳውያን አረጋውያን መሳሪያ በታጠቁ ኃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

የግድያው መነሻ ከሰሞኑ በወረዳው 21 የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ጋር የተያያዘ ሲሆን ከበባ ተደርጎባቸው መገደላቸውን መረጃው አስነብቧል።

የተገዱሉት ምእመናን ሀብትና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች ምእመናን ቀዬአቸውን ለቀው በመውጣት እየሸሹ እንደሚገኙም ተነግሯል።

በመረጃው እንደተገለጸው ባለፉት 3 ቀናት ማለትም በየካቲት 19፣20ና 22 በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በተፈጸሙ የግድያ ተግባራት እስከ አሁን ከ30 በላይ  ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል ተብሏል።

በተጨማሪም እስከ አሁን በሀገረ ስብከቱ ሥር ባለው የሽርካ ወረዳ  ብቻ ከ164 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው የመረጃ ምንጫችን ነግረውናል።  ይህ በእንዲህ እንዳለ በተፈጸሙ ጥቃቶች በሕይወት ይኑሩ ወይም ይሙቱ የማይታወቁ በርካታ ምእመና እንዳሉም ተነስቷል።

የሁለቱ ወንድማማቾች ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በጋለማ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን በደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በወረዳው እየተባባሰ የመጣው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ መተላለፉን በመረጃው ላይ ተጠቅሷል።

©ማኅበረ ቅዱሳን
😢1
“በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን ከልብ ቶሎ የማይወጣ፤ ለዘመናትም በህሊና መዝገብ ላይ የሚቆይ ነው፡፡” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለሃይማኖት በመምህር ዘለዓለም ወንድሙ ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።


የቅዱስነታቸው መልእክት ከዚህ እንደሚከተለው ይቀርባል።


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን !!

‹‹ወነአምር ከመ ለእመሂ ተነሥተ ቤተ ማኅደርነ ዘበምድር ዘውእቱ ሥጋ ብነ ሕንጻ በኀበ እግዚአብሔር በሰማያት ዘኢገብሮ እደሰብእ፤ በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን፡፡›› (2ቆሮ. 5፡1)

በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን ከልብ ቶሎ የማይወጣ፤ ለዘመናትም በህሊና መዝገብ ላይ የሚቆይ ነው፡፡

በመሆኑም የሚከተሉት ሃይማኖት ወይም መርጠው ያልተወለዱበት አካባቢ እንደበደል ተቆጥሮባቸው ከየአቅጣጫው በሚሰነዘረው ጥቃት በሚገደሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ምእመናን በአጠቃላይ የሰው ልጆች ኀዘን ልባችን በትካዜ ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት በመንፈሳዊ ሕይወቱ እና በትጋቱ ለቤተ ክርስቲያን ተስፋ የነበረው፤ ለበርካታ ዓመታትም በገጠር፣ በከተማ፣ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥትን ሲያስተምር የቆየው የመንፈስ ቅዱስ ልጃችን መ/ር ዘለዓለም ወንድሙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት በተጓዘባት ሰሜን አሜሪካ ባጋጠመው ሕመም ከዚህ ዓለም ድካም በሥጋ ማረፉን ስንሰማ ታላቅ ድንጋጤ ፈጥሮብናል፡፡

በእርግጥ መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማእት በሥጋ ከእኛ ቢለይም ያለዋጋ የተቀበለውን የእግዚአብሔር ቃል ለምእመናን በማስተማር አደራውን በሚገባ ተወጥቶአልና በሰማይ ወደሚጠብቀው ዘለዓለማዊ ስፍራ በክብር እንደሚገባ እናምናለን፡፡

የመልካም ሰዎች መጉደል ለሀገር በተለይም ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚያስጨንቅ ቢሆንም ሁሉን የሚችል አምላክ ተተኪዎችን እንዲያዘጋጅልን በመጸለይ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ልጃችን ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ምእመናን መጽናናትን እየተመኘን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ የአገልጋዩ ወልደ ሰማዕትን ነፍስ በመንግሥቱ ያሳርፍልን፤

“እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር  ኣሜን!

               + አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
             የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
                አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ