የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ 21 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አስታወቁ።

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
የካቲት ፳/፳፻፲፰ ዓ/ም

በምሥራቅ አርሲ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ቀጥሎ ትላንት የካቲት 19 ቀን 2018ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በጀመረ ጥቃት 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌና ምሥራቅ አርሲ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።

ከሞቱት 21 ምእመናን መካከል አንደኛው ካህን ሲሆኑ
የሁሉም ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት የካቲት 20/2018 ዓ/ም መፈጸሙንም ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተናግረዋል።

እንደብፁዕነታቸው ተጨማሪ መረጃ ሁለት ምእመናን መታፈናቸውንና ስምንቱ ደግሞ የት እደደረሱ አይታወቅም።

በተጨማሪም የበርካቶች ንብረት መዘረፉንና በዚህ ሰዓት ላይ ከፍተኛ ውጠረት በመንገሱ በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደማይቻል ብፁዕነታቸው አሳውቀዋል። የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ባስተላለፉት መልእክት የልጆቻችን ሞት የእኛም ሞት ነው ያሉ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኘተዋል።

አያይዘውም ገዳዮቻችን “በከንቱ ስለምን ይገድሉናል? የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ተጨማሪ የሰው ነፍስ እንዳይጠፋ የመከላከሉ ሥራ ሊሠራ ይገባል” በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
😭3👍1
ዋ!.......ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምስሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፀዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና
/ያለም ሎሬት ጸገየ ገ/መድኅን/
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ

‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ
ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት››
(ማቴ 5÷51 ፤   ቅዱስ ያሬድ)

ከዚህ በፊት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች የበርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሕይወት በመጥፋቱና ከሞት የተረፉትም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጠው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት፣ በደረሰው ሞትና ስደት ምእመናን እያዘነ ባሉበት፣ እኛም ከኃዘናችን ባልተጽናናንበት ሁኔታ ጥቃቱ በአዲስ መልኩ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት በግፍ ማለፉን፣ በሕይወት የተረፉትም በታጣቂዎቹ መታገታቸውንና የደረሱበት አለመታወቁን፣ h10 የሚበልጡ አባውራዎች ቤትና ንብረት እንደተቃጠለ በመግለጽ ከሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሪፖርት የተመለከትነው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነው፡፡

አገር  ሰላም ብለው በሚኖሩት ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ በሌላቸው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላትም ግድያውን በሃይማኖት ስም ይፈጽሙት እንጂ የሃይማኖት ስዎች ግን አይደሉም፡፡ ዓላማቸውም በሀገራችን ለረዥም ዘመናት ተከባብረው አብረው በኖሩት የሃይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን መፍጠር  ነውና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል፡፡

በመሆኑም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለታዊ ኑሮ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣

ፍርድን በመሻት የሚጮኸው ስለስሙ መከራን የተቀበሉት የንጹሐን ደም ተገቢውን ፍትሕ ይፈልጋልና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ወደፊትም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ የዜጐች ሀብትና ንብረት እንዳይወድም መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን እንዲያከናውን ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንኦት ያስተላልፋል፤

በደረሰው አደጋ ዙሪያ ተነጋግሮ ተገቢውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተሰበሰበው ቋሚ ሲኖዶስም የአካባቢው ችግር አስተማማኝ በሆነ መንገድ ተፈትቶ ዘላቂ ስላም እስኪገኝ ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የተሰየመው የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚመለከታቸውም አካላት በየድርሻቸው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ በክብር ያሳስባል፡፡

የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው መስተዳድርም ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደፊትም ችግሩ እንዳይደገም ከመሠረቱ መፍታት የሚያስችል እርምጃ እንዲወስድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትጠይቃለች፡፡

በመጨረሻም ስለስሙ በሥጋቸው መከራን በመቀበል ሕይወታቸውን በአጡት ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን ልዑል እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስን እንዲሰጥልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲያጽናናልን እንጸልያለን፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቋሚ ሲኖዶስ
የካቲት 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
1
አድዋ

"በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።" መዝ 43፡5

እንኳን ለአድዋ ድል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

👉  Website
1
አድዋ የቤተክርስቲያን ሀገሪነት ማሰያ ነው።

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ጋር በመተባበር የአድዋን በዓል አከበረ።

በመርሐ ግብሩ ጥናታዊ ጹሕፍ የቀረበ ስሆን በጹሕፉ ላይ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተወህዶ ቤተክርስቲያን በሀገረ ሉዓላዊነት መጠበቀ ላያ ያሳየችው ታላቅ ሚና በስፋት ተዳሰዋል። አባቶቻቸውን ጠላት ሀገረን ለመውረር ስመጣ ''ኢትዮጵያ ስጋችን ቤተክርቲያን ነፍሳችን ናት ነፍስ እና ስጋ ደግሞ አንድ ነው። ሀገረ ያለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ያለ ሀገር የለም። ሃይማኖትና ነጻነትን ማጣት ሽንፈት ነው። ስለ ሀገረ ሃይማኖትና ነጻነትን መሞት ክብረ ነው'' ብለው ታቦት ይዘው ጠላት ድል ነስተዋል።