የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
የጉዞ ትኬቱን ከሚቀርባችሁ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት ያገኛሉ።
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት መርቲ አቦምሳ ወረዳ ፈረቀሳ ቀበሌ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ተገደሉ !!!

የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት መርቲ አቦምሳ ወረዳ ፈረቀሳ ቀበሌ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን እና 1 ሙስሊም በታጣቂዎች ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

እያሰለሰ በቀጠለው የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ችግር ዛሬም በሦስት ኦርቶዶክሳውያን እና በ1 ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ሕልፈተ ሕይወት ማድረሱን የአሥር ኦርቶዶክሳውያን ከብቶች፣ ጎተራዎች እና ቤት ንብረቶች በእሳት በመቃጠሉ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን  ብፁዕ  አቡነ ኤልሣዕ የሶማሌ እና የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት  ጳጳስ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው መንግሥት ሕገ ወጥ ታጣቂዎችን በማጥፋት የኦርቶዶክሳውያንን ደህንነት የመጠበቅ እና ሰላምን የማስፈን ተግባሩን እንዲያከናውንም ጠይቀዋል።

©EOTC TV
😢12
በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ 21 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አስታወቁ።

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
የካቲት ፳/፳፻፲፰ ዓ/ም

በምሥራቅ አርሲ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ቀጥሎ ትላንት የካቲት 19 ቀን 2018ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በጀመረ ጥቃት 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌና ምሥራቅ አርሲ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።

ከሞቱት 21 ምእመናን መካከል አንደኛው ካህን ሲሆኑ
የሁሉም ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት የካቲት 20/2018 ዓ/ም መፈጸሙንም ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተናግረዋል።

እንደብፁዕነታቸው ተጨማሪ መረጃ ሁለት ምእመናን መታፈናቸውንና ስምንቱ ደግሞ የት እደደረሱ አይታወቅም።

በተጨማሪም የበርካቶች ንብረት መዘረፉንና በዚህ ሰዓት ላይ ከፍተኛ ውጠረት በመንገሱ በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደማይቻል ብፁዕነታቸው አሳውቀዋል። የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ባስተላለፉት መልእክት የልጆቻችን ሞት የእኛም ሞት ነው ያሉ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኘተዋል።

አያይዘውም ገዳዮቻችን “በከንቱ ስለምን ይገድሉናል? የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ተጨማሪ የሰው ነፍስ እንዳይጠፋ የመከላከሉ ሥራ ሊሠራ ይገባል” በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
😭3👍1