የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ዜና ሰንበት ት/ቤት

በመንበረ ጵጵስና ስር ያሉህ 33 ሰንበት ትምህርት ቤቶች የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር አደረጉ።

የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በስሩ ያሉትን 33 አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ሥራ አመራር ያሰተፈ የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር አደረገ።

የካቲት 7/2018 ዓ.ም በአዳር መርሐ ግብሩ ከ165 የሰንበት ሥራ አመራር የተሳተፉበት እና በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች የና/ደ/መ/መድኃኔዓለም ካቴድራል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት፣ የና/ቦ/ደ/ምህረት ፈለገ ምህረት ሰንበት ት/ቤት እና የወንጂ ኩ/ም/ቅ/አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ ፈለገ ህይወት ዘእምጻድቃን ሰንበት ት/ቤት በሥርዓተ ትምህርት አፈጻጸም ፣እቅድ አተገባበር እና ልምት አገለግሎት ዙሪያ ልምዳቸውን አካፍሏል።

በተጨማሪ የና/ደ/ፀ/ቅድስት ማርያም ካቴድራል ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት፣ የና/ደ/ሰ/ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል እና የና/ም/ደ/ታቦር ቅ/እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ፈለገ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በአባላት መረጃ አያያዝ ፣ መዝሙር ዜማ መሳሪያ እና ስነ ጥበባት አገልግሎት አንዲሁም የባለድርሻ አካላት ግንኙነት ዙሪያ ልምዳቸውን አካፍሏል።

ሰንበት ት/ቤቶች በቀረበው የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር የተሻለ ግንዛቤ ያገኙ ስሆን በቀጣይ በተሻለ አገልግሎት ሁሉም ልምዱን እርስበርስ እንድንለዋወጥ እና ባገኙት ተሞክሮ አገልግሎቱን እንድፈጽሙ ያስችላቸዋል።

መረጃ:- የአዳማ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


“ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከሆነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ” ብፁዕ አብነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185