የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
#ጾመ_ነነዌ፦ የንስሐና የምሕረት አዋጅ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ቀኖና መሠረት፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ጾመ ነነዌ ነው።
ይህ ጾም የትንሣኤ ጾም (ዐቢይ ጾም) አዋጅ ነጋሪ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን፣ በየዓመቱ በባሕረ ሐሳብ ቀመር  ስሌት የሚወጣ ነው።

በዚህም መሠረት የ 2018 ዓ.ም. ጾመ ነነዌ ጥር 25 ቀን (ሰኞ) ይገባል  የበረከት ፆም ያድርግልን።
🙏63
#መንፈሳዊ_ኢቨንት ቀጣዩ #የሰንበት_ትምህርት_ቤት_ፈተና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ረጅም የታሪክ ጉዞ ውስጥ የሰንበት ትምህርት ቤቶች የወጣቱ ትውልድ መንፈሳዊ ማደጊያ፣ የቤተክርስቲያን ተተኪ ኃይል መፈልፈያና የሃይማኖታዊ እሴቶች መጠበቂያ ምሽጎች በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቤተክርስቲያኒቱ ጥላ ሥር በተለይም በሰ/ት/ቤት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ በነበሩ ወጣቶች ከአገልግሎት (Ministry) ወደ ዝግጅት (Events) እያዘነበለ መምጣቱ በደንብ መታዘብ ችያለሁ። በተለይም በከተማችን ውስጥ ባሉ ሰ/ት/ቤቶች ውስጥ ባሉ "ባለ መክሊት" አገልጋዮች ውስን ማፈንገጦች ነገ ሰ/ት/ቤቶቻችንን በእጅጉ ዋጋ እንደሚያስከፍሉ ተሰምቶኛል።

በዚህ ጽሑፍ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ላይ እያጠሉ ያሉትን "መንፈሳዊ ኢቨንቶች" ተብለው የሚጠሩ አዳዲስ ስብስቦች፣ በውስጣዊ መዋቅር፣ በአባላት ሥነ-ምግባርና በቤተክርስቲያኒቱ ዓለም አቀፋዊ ተልእኮ ላይ እያመጡ ያሉትንና ሊያመጡ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ። ይህ ርዕስ እንደሚያስከፋችሁ ባውቅም (የማውቃችሁ ፣ የምቀርባችሁ) ልተባበራችሁ አልችልም።

የሰንበት ትምህርት ቤቶች መደበኛ መዋቅር የተመሰረተው በፈቃደኝነትና በነጻ አገልግሎት ላይ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ መዋቅር እየተሸረሸረ መምጣቱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚገኙ ታዋቂ አድባራትና ገዳማት አባላት እንዲሁም ከመንፈሳዊ ኮሌጆች የተመረቁ ወጣቶች ትኩረታቸውን ከመደበኛው የሰንበት ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርትና አገልግሎት ወደ ግል ድርጅታዊ አደረጃጀቶች እያዞሩ ይገኛሉ ። ለዚህም አብነት እንዲሆነን በከተማችን ድሬዳዋ ካሉት አድባራት መካከል ከግማሽ በላይ በሚኾኑት ሰ/ት/ቤቶች ውስጥ ይህ ስብስብ እየተፈለፈለ ይገኛል። ለማሳያ ያህል በደ/ም/ቅ/ሚካኤል/ካቴ -> ቶጳዝዮን ኢቨንት ፣ በደ/ሰ/መድኃኔዓለም/ካቴ -> አጋፋሪ ኢቨንት ፣ በኆ/ሰ/ቅ/ማርያም/ካቴ -> የዲያቆናት ኢቨንት ፣ በሳ/ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል/ካቴ-> ዕንቁ ኢቨንት ፣ በመ/ብ/ቅ/ሥላሴ/ቤ/ክ -> ቃና ኢቨንት ወዘተ...

ይህ ሽግግር በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ "ተቋማዊ ንጥቂያ" (Institutional Poaching) እየተባለ የሚጠራውን ክስተት በጥቂቱ እያስከተለ እንዳለ ማስተዋል ችያለሁ ይህም በጊዜ መፍትሔ ካልተበጀለት እያደር እያደገ የሚሔድና ከቤተክርቲያናዊ ማዕከልነት አውጥቶ ግለሰባዊ ማድረጉ አይቀሬ ነው። የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የነበሩ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ስም በተደራጁ ነገር ግን የግል ጥቅም በሚመራባቸው ስብስቦች ውስጥ መሳተፋቸው የነገ የቤተክርስቲያን ትልቁ ፈተና ነው። ለዚህም እንደ አብነት #ሎዛ ኢቨንትን ማንሳት ይቻላል።

ታዲያ እነዚህ ስብስቦች ከመደበኛ የቤተክርስቲያን መዋቅር የወጡ ቢሆንም ፣ በተግባር ግን ከዋናው ተቋም (ሰንበት ትምህርት ቤት) ጋር በሰው ኃይልና በጊዜ አጠቃቀም ረገድ ግጭት ውስጥ የሚከትና የሚያውክ ነው ። አብዛኞቹ አዘጋጆችና አባላት ከሰ/ት/ቤቶችና ከመንፈሳዊ ኮሌጆች የተወጣጡ መሆናቸው፣ በቤተክርስቲያን የነገረ-መለኮት ዕውቀት የታነጸውንና ጸጋ ያላቸውን ልጆች ኃይል  ወደ ንግድ ሥራ እንዲያዘነብል አድርጎታል ።

በዚህ ስብስብ ውስጥ ያሉ አባላት በሰንበት ትምህርት ቤት  የአባላት በመደበኛ የትምህርትና የጸሎት ጊዜያት ላይ እንዲሁ መደበኛ መርሐግብሮች አለመገኘታቸው ነው ምክንያቱም የሚጠሩባቸው ዝግጅቶች ከመደበኛ መርሐግብር ሰዓት ጋር ተመሳሳይነት አላቸውና። ቀደም ሲል የሰንበት ትምህርት ቤት አባል መሆን ማለት በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሙሉ ጊዜንና ጉልበትን ለቤተክርስቲያን መስጠት ቢሆንም አሁን ላይ ግን አባላት ለግል ኢቨንቶቻቸው ቅድሚያ ሲሰጡ ይታያሉ። ምክንያት ሲጠየቁም "ሥራ ነው" የሚል ምላሽ መስጠታቸው መንፈሳዊ አገልግሎትን ወደ ተራ ዓለማዊ የሥራ ውል ዝቅ ማድረጉን ያሳያል ።

ይህ "ሥራ ነው" የሚለው አመለካከት የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች አባላቱ በቤተክርስቲያኒቱ መርሃግብር ላይ እንዲገኙ ቢጠይቁም፣ አባላቱ ግን ከኢቨንት አዘጋጆቹ ጋር የገቡትን የገንዘብ ውል በማስቀደም መደበኛ ፕሮግራሞችን ያቋርጣሉ። ይህ ሁኔታ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአመራር ክፍተት እንዲፈጠርና የአገልግሎት ጥራት እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል ።

ሌላው ላነሳው የምፈልገው ነገር የሰርግ እጀባ መርሐግብሮች በተለይ በአዲስ አበባ ከሰ/ተማሪዎች እጅ እያመለጡ በኢቨንት አዘጋጆች ስር እየወደቁ እንዳሉ መታዘብ ችያለሁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሥርዓተ ተክሊል (ጋብቻ) አንዱ የቤተክርስቲያን ምስጢር ነው። ይህ ምስጢር የሚፈጸመው በካህናትና በዲያቆናት አማካኝነት ሲሆን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችም በዝማሬና በሥርዓት አጀባ ለበረከት ያገለግሉ ነበር ። ይሁን እንጂ አሁን ላይ ይህ የሰርግ ማጀብ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ወደ "ኢቨንት" አደረጃጀቶች በመዛወሩ፣ አገልግሎቱ ከበረከት ወደ ንግድ ተቀይሯል።

ታዲያ ይህ ነገር ያሉት ችግሮች ምን ምን ናቸው ስንል

1) የሥርዓት መዛባት፡ በኢቨንቶች የሚመሩ የሰርግ ማጀቢያዎች ከቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ሥርዓት ይልቅ ለውጫዊ ድምቀትና Show የሚመቹ ዝግጅቶችን ያስቀድማሉ። ይህ ደግሞ የምስጢረ ጋብቻውን ረቂቅ መንፈሳዊ ትርጉም ያደበዝዘዋል ።

2) የአባላት የሥነ-ምግባር ብክለት፡ ወጣቶች ዝማሬንና መንፈሳዊ አገልግሎትን እንደ ገቢ ምንጭ ማየታቸው፣ ወደፊት ለቤተክርስቲያን ያላቸውን ቅንነትና ታማኝነት ይቀንሰዋል ።

3) የዋጋ ተመንና የአድልዎ አገልግሎት፡ ኢቨንቶቹ ለሚያቀርቡት አገልግሎት አስቀድመው የዋጋ ተመን ያወጣሉ። ያንን ዋጋ የመክፈል አቅም የሌላቸው አማኞችን አያገለግሉም። ይህ ደግሞ "በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ" (ማቴ 10፡8) የሚለውን የወንጌል ትእዛዝ በግልጽ መጣስ ነው አገልግሎት አይሸቀጥበትም። እዚህ ጋር "ሰባኪዎችና ዘማሪዎችስ ይከፈላቸው የለ" የሚል መሞገቻ ይቀርባል። ብዙ የሚያስብል ቢኾንም በአጭሩ እነርሱም ቢሆኑ "ይሄን ያህል ካልተከፈለኝ አልሰብክም ፣ አልዘምርም" ያሉ እንደኾነ ፍጹም ስሑታን ናቸው የነሱ ልክ አለመሆን እናንተን ልክ አያደርግም!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ አስተምህሮ አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ጸጋና መንፈሳዊ ስጦታ ለምእመናን ያለ ዋጋ እንዲያካፍሉ ያዝዛል። ማቴዎስ 10፡8 ላይ የሚገኘው "በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ" የሚለው ቃል፣ ካህናትና ዲያቆናት ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልጋይ ሊመራበት የሚገባ መመሪያ ነው። ሆኖም ግን የመንፈሳዊ ኢቨንት አዘጋጆች ይህንን ቃል በተለያየ ሰበብ ወደ ጎን ሲገፉ ይታያሉ ።

አዘጋጆቹ ለሚጠይቁት ክፍያ "የሥራ ማስኬጃ"፣ "የትራንስፖርት" ወይም "የአባላት አበል" የሚሉ ስሞችን ቢሰጡም፣ በተግባር ግን ትርፍን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ይህ ድርጊት በቤተክርስቲያን ቀኖና ዘንድ "ሲሞናዊነት" ተብሎ ከሚጠራው መንፈሳዊ አገልግሎትን በገንዘብ ከመለወጥ ኃጢአት ጋር ይያያዛል። በቤተክርስቲያኒቱ መጻሕፍት ውስጥ፣ በተለይም በፍትሐ ነገሥትና በቃለ ዓዋዲ ውስጥ፣ ማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎት በገንዘብ ሊደለል ወይም ሊሸጥ እንደማይገባ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተቀምጧል ።
1
የኢቨንቶች መስፋፋት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ላይ እያመጣ ያለው ትልቁ ተግዳሮት የአባላት መመናመንና የታማኝነት መጥፋት ነው። ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ከሚያከናውኑት ነጻ አገልግሎት ይልቅ በኢቨንቶች ውስጥ የሚያገኙት ክፍያና ዝና ይበልጥ ይስባቸዋል ። ይህም የሚከተሉትን አሉታዊ ውጤቶች ያስከትላል፡-

1) የትምህርት ጥራት መውረድ፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጆችና በሰ/ት/ቤቶች ውስጥ የተከታታይ ዓመት ኮርስ የተመረቁ ወጣቶች ትኩረታቸው ወደ ኢቨንት ሥራዎች በመሆኑ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰጠው የሃይማኖት ትምህርት ጥራት ያለው መምህር ያሳጣዋል ።

2) የሥርዓት መላላት፡ በኢቨንቶች ውስጥ የሚታዩት ዘመናዊና ለዓይን የሚማርኩ ነገር ግን መንፈሳዊ ይዘት የሌላቸው ዝግጅቶች፣ ወደ መደበኛው የሰንበት ትምህርት ቤት ሥርዓት ውስጥ እየሰገገ መግባታቸው የሥርዓት መላላትን ይፈጥራል ።

3) ተቋማዊ አለመረጋጋት፡ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች አባላቶቻቸውን መቆጣጠር የማይችሉበት ደረጃ ላይ ያደርሳል። አባላቱ ከኢቨንት አዘጋጆቹ ጋር ያላቸው ግንኙነት ከቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር በላይ ጠንካራ እየሆነ መጥቷልና ።

ዛሬን ሳይሆን ነገን እያሰብን የኢቨንቶች መስፋፋት በቤተክርስቲያን የረጅም ጊዜ ዕቅድ ላይ ያለው ተጽዕኖ መመልከት እንችላለን።

ቤተክርስቲያኒቱ ወጣቱን ትውልድ ለመተካካት የምታደርገው ጥረት እነዚህ የግል ኢቨንቶች ምክንያት እንቅፋት ናቸው። ወጣቶች ለቤተክርስቲያን ያላቸውን አገልግሎት እንደ ሥራ (Career) ማየታቸው፣ ወደፊት ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆር ሳይሆን ለግል ጥቅሙ የሚሰላ አገልጋይ እንዲበቅል ያደርጋል ። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የሚደቀን ትውልዳዊ ስጋት ነው ።

ዘመናዊው ቴክኖሎጂና ማኅበራዊ ሚዲያ ለመንፈሳዊ ኢቨንቶች መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የኢቨንት አዘጋጆቹ በማኅበራዊ ሚዲያ ባላቸው ጠንካራ ተከታይ ሳቢያ ብዙ ደንበኞችንና ተከታዮችን ማፍራት ችለዋል ። ይህ ሁኔታ ደግሞ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ያለውን የአገልግሎት ዘይቤ ለወጣቶች "ያረጀና አሰልቺ" እንዲመስል አድርጎታል ።

ኢቨንቶቹ የሚዲያ አጠቃቀማቸውን ለገበያ ማስተዋወቂያነት ስለሚጠቀሙበት ማንኛውም አገልግሎት ለካሜራና ለቪዲዮ እንዲመች ተደርጎ መዘጋጀቱ፣ ትኩረቱ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው እንዲሆን አድርጎታል ።

ወጣቶች በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያዩዋቸው ደመቅ ያሉ መንፈሳዊ ዝግጅቶችና የሰርግ ቪዲዮዎች፣ መንፈሳዊነትን ከዝናና ከገንዘብ ጋር አቆራኝተው ያቀርቧቸዋል። ይህም በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ያለውን የትሕትናና የነጻ አገልግሎት እንዲናቅ አድርጓል። በተጨማሪም፣ በእነዚህ ኢቨንቶች የሚዘጋጁ መዝሙሮችና ትርኢቶች ከቤተክርስቲያኒቱ ዜማና ሥርዓት ይልቅ ወደ ዓለማዊ የሙዚቃ ስልቶች ያደሉ በመሆናቸው፣ የምእመናንን መንፈሳዊ ስሜት ወደ ሥጋዊ ስሜት ይለውጣሉ ።

ታዲያ ይህንን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ላይ እያጠላ ያለውን ጥላ ለማስወገድና መንፈሳዊ ኢቨንቶችን ወደ ሥርዓት ለማስገባት ቤተክርስቲያኒቱ የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርባታል ብዬ አምናለሁ ። ምናልባት ይህ የመፍትሔ ሐሳብ አዘጋጆቹንም ሆነ አባላቱን እንደማያስማማ ባውቅም ሐሳቤን ግን አቀርባለሁ።

1) ቢቻል ሙሉ ለሙሉ ማስቆም! ይህ ካልተቻለ ግን

2) የቃለ ዓዋዲና የሰንበት ትምህርት ቤት መመሪያዎችን ማሻሻል፡ የኢቨንቶች አደረጃጀትና ከአባላት ጋር ያላቸው ግንኙነት በግልጽ ሊደነገግ ይገባል። አባላት በግል ስብስቦች ውስጥ ሲሳተፉ ከደብራቸው ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸውና አገልግሎቱ ከንግድ ነጻ መሆን እንዳለበት ጥብቅ መመሪያ ማውጣት ያስፈልጋል ።

3) አገልግሎትን ማዕከላዊ ማድረግ፡ የሰርግ ማጀብና መሰል ማኅበራዊ አገልግሎቶች በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥር ባሉ "የማኅበራዊ አገልግሎት ክፍሎች" በኩል እንዲከናወኑ ማድረግ። የሚገኘውም ገቢ ለግል ሳይሆን ለቤተክርስቲያኒቱ ልማት እንዲውል በማድረግ የንግድ ገጽታውን መቀነስ ይቻላል ።

4) የሥነ-ምግባር ትምህርትን ማጠናከር፡ ለአባላቱ ስለ በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ ስለ ትሕትናና ስለ መንፈሳዊ በረከት ጥልቅ ትምህርት መስጠት። በተለይም ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ለሚመረቁ ወጣቶች የታማኝነትና የአገልግሎት ሥነ-ምግባር ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል ።

5) የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት፡ በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ያሉ አገልጋዮች በግል ኢቨንቶች ውስጥ ሲሳተፉና መደበኛ አገልግሎታቸውን ሲያስተጓጉሉ ተጠያቂ የሚሆኑበት አሠራር መዘርጋት ።

ማጠቃለያ
ወጣቱ ትውልድ አገልግሎትን እንደ ገቢ ምንጭ ሳይሆን እንደ ዘላለም ሕይወት መውረሻ እንዲያየው የማስተማር ኃላፊነት የአባቶችና የአመራሮች ነው። "በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ" የሚለው መለኮታዊ ቃል በሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ዳግም ካልነገሠ፣ የቤተክርስቲያኒቱ ተተኪ ኃይል መንፈሳዊ ይዘቱን አጥቶ ወደ ተራ የንግድ ስብስብነት ሊቀየር ይችላል። ስለዚህ፣ አሁኑኑ ተገቢውን ቁጥጥርና መመሪያ በማውጣት የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ክብርና አገልግሎት መመለስ የቤተክርስቲያኒቱ ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት ።

                       ይቆየን ሚኪያስ ግዛቸው
9👍4👌1😭1
የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።

 
   በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተ ክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ/ም #የአንደኛ_መንፈቅ_ዓመት_ማጠቃለይ_ፈተና በሁለት ዙር የተሰጠ ስሆን #የመጀመሪያ ዙር ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ጥር 24/2018 ዓ.ም እና #ሁለተኛ ዙር ከ7ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል ደግሞ የካቲት 1/2018 ዓ.ም አሰጠ፦

    በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተ ክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ/ም  የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለይ ፈተና በሃያ ዘጠኝ (29) አጥቢያ ሰ/ት/ቤት አምስት ሺ አንድ መቶ ሰላሰ ስምንት (5138) በላይ  ከ1ኛ ክፍል እስከ 6ኛ ክፍል እንዲህም ከ7ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ስምንት (2608) ተማሪዎች በድምሩ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ስድስት (7746) ተማሪዎች የአንደኛ መንፈቀ ዓመት መጠቃለያ ፈተና መውሰዱን አስተወቀ፡፡

ፈተና የሚሰጠው በሀገር አቀፍ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ሲሆን ቀድሞ ከአጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች የትምህርት አፈጻጸም እና ስልጠና ክፍሎች ጋር የፈተና ዝግጅትና እና አሰጣት ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡

በዚህም መሠረት #የመጀመሪያ ዙር ፈተናው በሁሉም አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች  ጥሪ 24/2018 ዓ.ም የተፈተኑ ሲሆን  ከ1ኛ ክፍል እስከ 6ተኛ ክፍል ተማሪዎች  ጠዋት 3:00_6:00  እንድፈተኑ ተድርጓል።

#የሁለተኛ ዙር 1ኛ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና  ከ7ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የካቲት 1/2018 ዓ.ም ከሰዓት ከ8:00_11:00 ሰዓት በሁሉም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በዛሬ እለት ተሰጥቶት በሰላም ተጠናቋል።

በዚህ ፈተና ዝግጅት እና ሥርዓተ ትምህርቱን በማስተማር ከፍተኛ ሚና የተወጣችው የአጥቢያ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ;ሰባኪያነ ወንጌል መምህራኖች እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን ሁሉ የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

በመሆኑም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ካህናት አባቶች፣ሰባኪያን ወንጌል መምህራኖች እና የተማሪ ወላጅ ቤተሰቦች ይህንን የፈተናው መርሐ ግብር በተሳካ ሁኔታ እንዲሰጥ ከሰ/ት/ቤቱ ጎን በመሆን እያገዘችሁ ላላችሁ የመንበረ ጵጵስና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ላቅ ያለ ምስጋነ እያቀረበ እገዘችሁ እንድቀጥል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የአዳማ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185
ፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት
ሁለተኛ ዙር ማጠቃለያ ፈተና።
1
አዋሽ ፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት
ማጠቃለያ ፈተና።
ፈለገ ሰላም ዘመላእክት ሰንበት ትምህርት ቤት ሁለተኛ ዙር ማጠቃለያ ፈተና።
1
ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ፈለገ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤተ ሁለተኛ ዙር ማጠቃለያ ፈተና።
1