የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
ዜና ሰንበት ት/ቤት

የመጀመሪያ ዙር የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ተሰጠ።

 
   በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተ ክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ዙር የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለይ ፈተና ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ማስፈተኑን አስታወቀ፦

    በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተ ክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ/ም  የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለይ ፈተና በሃያ ዘጠኝ (29) አጥቢያ ሰ/ት/ቤት አምስት ሺ አንድ መቶ ሰላሰ ስምንት (5138) በላይ  ከ1ኛ ክፍል እስከ 6ኛ ክፍል ሥርዓተ ትምህርቱን ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችን በዛሬ እለት ማለትም (24/05/2018ዓ.ም) መሰጠቱን አስተወቀ፡፡

ፈተና የሚሰጠው በሀገር አቀፍ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ሲሆን ቀድሞ ከአጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች የትምህርት አፈጻጸም እና ስልጠና ክፍሎች ጋር የፈተና ዝግጅትና እና አሰጣት ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት ፈተናው የሚሰጠው  በሁሉም አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች  ጥሪ 24/2018 ዓ.ም ሲሆን  1ኛ ,2ተኛ,3ተኛ,4ኛ, 5ኛ እና 6ተኛ ክፍል ተማሪዎች  ጠዋት 3:00_6:00  እንድፈተኑ ተድርጓል።

ፈተናው በሁለቱም ቋንቋ  ማለትም በአማርኛ ቋንቋ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

#የሁለተኛ ዙር 1ኛ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና  ከ7ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የካቲት 1/2018 ዓ.ም ከሰዓት ከ8:00_11:00 ሰዓት በሁሉም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ይሰጣል።

በመሆኑም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ካህናት አባቶች፣ሰባኪያን ወንጌል መምህራኖች እና የተማሪ ወላጅ ቤተሰቦች ይህንን የፈተናው መርሐ ግብር በተሳካ ሁኔታ እንዲሰጥ ከሰ/ት/ቤቱ ጎን በመሆን እያገዘችሁ ላላችሁ የመንበረ ጵጵስና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ላቅ ያለ ምስጋነ እያቀረበ እገዘችሁ እንድቀጥል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የአዳማ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Telegram
https://t.me/adamaunity

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185