የምዘና ቀን ተወሰነ
የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ከጥር 24_የካቲት 1/2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ይሰጣል።
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2018 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ከጥር 24_የካቲት 1/2018 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስና ስር ላሉ በ32 አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች እንደሚሰጥ ገለጸ።
ማጠቃለያ ፈተናው የሚሰጠው በሁለት ሳምንት ሲሆን ከ1ኛ ክፍል እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ጥር 24/2018 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00_6:00 የሚሰጥ ይሆናል።
በአንደኛ ወሰነ ትምህርት የሚፈትኑት ትምህርት
1. መሠረተ ሃይማኖት
2. ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
3. የቤተ ክርስቲያን ታርክ(1ኛ ክፍል የለም)
4. ልሳነ ግዕዝ
ከ7ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የካቲት 1/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00_11:00 በሁሉም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ይሆናል።
በአንደኛ ወሰነ ትምህርት የሚፈትኑት ትምህርት
1. መሠረተ ሃይማኖት
2. ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
3. የቤተ ክርስቲያን ታርክ (ለ7ኛ ክፍል ብቻ)
4. ልሳነ ግዕዝ
5. የቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት (8ኛ እና 9ኛ ክፍል ብቻ)
የሚሰጥ ስለሆነ ተማሪዎች እና አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ከአሁኑ ዝግጅት እንዳታደርጉ የመንበረ ጵጵስና ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መልዕክት ያስተላልፋል
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Telegram
https://t.me/adamaunity
👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@adama_unityss
👉 Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185

❤5
#ቤተክርስቲያኒቷ የጥምቀትና የመስቀል ማክበሪያ የይዞታ ካርታ ተረከበች።
የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት
#ሐመረ_ተዋሕዶ_ሚዲያ
#አዳማ ጥር 5 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ በአዳማ ከተማ አድባራትና ገዳማት በዓለ ጥምቀትንና የመስቀል በዓልን የሚያከብሩበትን ቅዱስ ሥፍራ ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ከከተማ መስተዳደሩ ሀገረ ስብከቱ መረከቡን፤
ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ በይፋ አብሥረዋል።
ይህ ታሪካዊ የምሥራች የተሰማው፣ የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክቶ በሀገረ ስብከቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
ብፁዕነታቸው ቀደም ሲል የነበረውን የመስቀል አደባባይ ታሪክ በማስታወስ፣ በሀገራዊ የልማት እንቅስቃሴ ምክንያት ለተፈጠረው የይዞታ ለውጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥያቄ በአግባቡ ተረድተው የይዞታ ካርታው እንዲሰጥ ላደረጉት ለአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴና ካቤናቸው በሀገረ ስብከቱ፣ በራሳቸውና በመላው ኦርቶዶክሳውያን ስም አመሥግነዋል።
ብፁዕነታቸው አያይዘውም በዓሉን በተመለከተ ባስተላለፉት አባታዊ መመሪያ፤ በአዲሱ የጥምቀተ ባሕር በዓሉን በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት፣ በፍቅርና በአንድነት ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም በዓሉ በሰላም እሴቶች፣ በመተሳሰብና ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በታላቅ ዲሲፕሊን እንዲከናወን አደራ ብለዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያልተፈቀዱ አላስፈላጊ ነገሮች ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
"አዳማ ከተማችን ለሀገራችንም ሆነ ለዓለማችን ተምሳሌት የሆነች ውብ ከተማ ነች" ያሉት ብፁዕነታቸው፣ ሁሉም ምዕመን በዓሉን በባለቤትነትና በተቆርቋሪነት ስሜት እንዲያከብር አባታዊ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሳሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ በበኩላቸው፣ ለአዲሱ ሥፍራ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን አረጋግጠዋል።
ባሕረ ጥምቀቱ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ምዕመናንና አገልጋዮች የመንገድና የአቅጣጫ ለውጦችን እንዲያስተውሉና በተለይም ራቅ ያሉ አድባራት ሰዓታቸውን በአግባቡ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።
የአድባራትና ገዳማት አስተዳሪዎችም ከሀገረ ስብከቱ የወጣውን መመሪያ የማስፈጸም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአድባራትና የገዳማት አስተዳሪዎች በታሪካዊው የምሥራች የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ ገልጸዋል።
ለዚህ ስኬት መገኘት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለብፁዕነታቸው፣ ለሀገረ ስብከቱ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥያቄ በአዎንታ በመቀበል ለተባበረው ለከተማው መስተዳድር ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል።
ተሳታፊዎቹም ከሀገረ ስብከቱ የተሰጠውን መመሪያ ሙሉ በሙሉ ለመፈጸምና ለመተግበር ዝግጁና ቁርጠኛ መሆናቸውን በማረጋገጥ ስብሰባው በጸሎት ተጠናቋል።
በወይይቱም መድረክ ላይ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ጌቱ ሞቲ የሀገረ ስብከቱ ም/ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያው ክፍል ኃላፊዎች፣ የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች : ሰባክያን : የሰንበት ት/ቤትና የማሕበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢና ፎቶ
ዲ/ን አየለ
#ሐመረ_ተዋሕዶ_ሚዲያ #የምሥራቅ_ሸዋ_ሀገረ_ስብከት
#አዳማ #ብፁዕ_አቡነ_ጎርጎርዮስ
#ጥምቀት #መስቀል #የይዞታ_ካርታ
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን