የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.12K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በመንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ አዘጋጅነት ለሦስት ተከታታይ ቀናት በዘርፈ ብዙ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሲመክር  የቆየው  የሊቃውንት  የምክክር ጉባኤ ባለ 14 አንቀጽ የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት  ተጠናቋል። የመግለጫው ሙሉ ሐሳብ   እንደሚከተለው ይነበባል።

============================
ሚያዚያ 22 ቀን 2017ዓ.ም አዲስአበባ 

እኛ ሊቃውንት እንደምንረዳው ጉባኤ ኒቅያ በምንልበት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አነጋገር  ጉባኤ ተደረገ ሲባል ሰዎች ተሰብስበው ይህን ማመን አለብን ያንን መተው አለብን ብለው በድምጽ ብልጫ ተስማምተው የጋራ መግለጫ አወጡ ማለት ሳይሆን ሰፊ እርሻ /ሁዳድ/ ያለው ገበሬ በአዝመራው መሐል እህሉን መስሎ አዝመራውን የሚጎዳ የሚያበላሽ አረም ሲበቅልበት ከእህሉ መካከል አረሙን በጥንቃቄ ነቅሎ እንደሚጥል ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም ክርስቶስን በዓይኗ ዓይታ ትምህርቱን በጆሮዋ ሰምታ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን በአባቶቻችን በሐዋርያት አማካይነት የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ዓይታ በምታውቀውና በምታምነው እውነተኛ ሃይማኖት መሐል የራሷን እምነት ሳይሆን ተመሳስሎ የሚጎዳትን የመናፍቃን የአስተሳሰብ አረም ነቅላ ለመጣል አረሙን ነቅላ ትምህርት አዝመራዋን ትከላከላለች፡፡በኒቅያ ጉባኤም የተደረገው ይኸው ነው አረም አርዮስ ተነቀሎ የክርስቶስ አምላክነት በምላት በስፋት ተነገረ የሃይማኖት መግለጫ የሆነው ጸሎተ ሃይማኖት ጸደቀ ፡፡ እኛም የሠለስቱ ምዕት የልጅ ልጆች የኢትዮጵያ ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የበቀለውንና እየበቀለ ያለውን አረም በትምህርት የአረም ማጥፊያ መድኀኒትነት ለመንቀል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ምእመናንን ለማጽናት በዚህ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጽረ ግቢ ተሰብስበን መክረን ተወያይተን-

1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጉባኤው መክፈቻ የሰጡትን ቃለ ምእዳን አባታዊ መመሪያና ቡራኬን በመቀበል የሰጡትን አባታዊ መመሪያ በየመጣንበት ጉባኤ ቤት ሥራ ላይ ለማዋል ቃል እንገባለን፡፡

2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጉባኤው መክፈቻና በየመርሐ ግብሩ መካከል ያስተላለፉትን የሥራ መመሪያ ወቅቱ በሚጠይቀው ቤተ ክርስቲያን በምትፈልገው ምእመናን ለሚጠይቁት ጥያቄ ሁሉ ምላሽ ለመስጠት በየጉባኤ ቤታችን ከማስተማር ከማገልገል ባሻገር እንደአባቶቻችን ለሃይማኖታችን አለኝታና ጠበቃ ሆነን ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡

3. ጥንታዊት ሐዋርያዊት የሆነችውን የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረጅም ታሪኳ ውስጥ ባሳለፈቻቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ያካበተችውን የእቅበተ እምነት (ሃይማኖት) ልምድ ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያሉትን የዐቃብያነ ሃይማኖት ተጋድሎዎች በመረዳት ቅብብሎሹን ለማስቀጠል ቃል እንገባለን፡፡

4. አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ከሚከሠቱት አሉታዊ ግድፈቶችና ሥርዋጾች መካከል በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በገድላት፣በድርሳናትና በታአምራት የቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት በመከለስ በመሸቀጥና በመበረዝ መንፈሳዊነታቸውን ለቀው የተዛባ ሐሳብ እንዲኖራቸው ከእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ እንዲወጡ የሚደረገው ሴራ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ስለሆነም ጥንታውያን በቀኖና መጻሕፍት የተሠፈሩና የተመዘኑ መጻሕፍቶቻችን ባሉበት ሁኔታ ተጠብቀው ይቀጥሉ ዘንድ እኛ የጉባኤ መምህራን የመጻሕፍቱ ጠበቃ በመሆን  በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ያላለፉ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት አሳታሚነት ያልታተሙ መጻሕፍት ባለመጠቀም ደቀ መዛሙርትና ምእመናን እንዳይገለገሉባቸው ለማስተማር ቃል እንገባለን፡፡

5. የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥዕላት፣መስቀል፣ሥነ ሕንፃና ኪነ ጥበብ ይዘትና ቅርጽ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተለካ ሃይማኖታዊ ምሳሌነታቸው እንደ መጻሕፍት የሚነበብ እንደሰው የሚናገሩ እንደ መምህራን የሚያስተምሩ ንዋያት ናቸው፤ስለሆነም እነዚህን ንዋያተ ቅድሳት በየዘመኑ የሚነሱ የውስጥና የውጭ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የተለያየ ስሜት እንዲፈጥሩ የሚሰጡት ትርጉም እንዲዛባ ለማድረግ የሚያደርጉት ሙከራ እጅግ ብዙ ነው አባቶቻችን በብዙ ውጣ ውረድ ያቆዩልንን የስገኙልንን  እነዚህን ንዋያተ ሃይማኖት ጠብቀን በማስጠበቅ ጥቅማቸውን በማስተማር ባሉበት ሁኔታ ለትውልድ ለማስተላለፍ ምትክ የሌለውን ድርሻችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡

6. አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱን የውስጥ ሁኔታ በማጤን ራሳቸው በሚሰጡን አጀንዳ በሚፈጠር  የተዛባ የፖለቲካ አመለካከት የመሪዎችን አቋምና ትከሻ በመለካት በሚገኝ አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም ሠርጎ በመግባት ኑፋቄን በመዝራት በቀኖና፣በታሪክና በትውፊት በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ በቅዳሴ በትርጓሜ በበዓላት አከባበር ላይ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ እንግዳ ነገሮችን ሊያሸክሙን እንደሞከሩና አንዳንዶቹም አዳዲስ ትርክት እንደጫኑብን ታሪክ እንደቀየሩብን በማኅበረሰቡ ውስጥ ቅራኔ እንደፈጠሩብን ከቀረቡት ጥንታዊ ጽሑፎች ተረድተናል፡፡ስለሆነም የደረሱብን ችግር የቀኖና የትውፊት የታሪክ ተፋልሶ ስህተቶችን በማኅብረሰቡ ውስጥ ሠርጎ የገባ የትርክት አረሙን ከስንዴው በጥንቃቄ በመለየት ወደ ጥንታዊ ማንነታችን ለመመለስ የሚጠበቅብንን ሁሉ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡

7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተች ጀምሮ መከፋፈል ያልገጠማት    የተማከለ የአስተዳደር መርሕ ስለምትከተልና ወጥ በሆነ የአሰራር መዋቅር ስለምትመራ መሆኑ የታወቀ ነው፤ስለሆነም ከቤተ ክርስቲያናችን ኣንጻር የተማከለ ኣሰራር የተሻለ ውጤት እንዳለው ለቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖትና ሥርዐት መጠበቅ ጠቃሚ መሆኑን ስለተገነዘብን  ማእከላዊ መዋቅራችንን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ተስማምተናል፡፡

8. በአምስት ሊቃውንት ቅዱሳን ስም በቡድን ተከፋፍሎ በየርእሱ የተደረገው ውይይትና  የመፍትሔ ሐሳብ ቀርቧል፡፡ቡድኑ የተወያየበት ሠነድ የዚህ ቃለ ጉባኤ አካል በማድረግ ጥቅል ሠነዱ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀርብ የሚድረግ ሆኖ ለማሳያ ያህል በክብዙ በጥቂቱ በአቋም መግለጫ እንዲወጣበት አድርገናል፡፡በዚህም መሠረት

ሀ. በነገረ ማርያምንና በነገረ ክርስቶስን ዙሪያ በጉባኤው ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዚህ ዙሪያ ውይይት ያደረገው ቡድን ለሚነሱ ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽ የሚሰጡ ከቅዱሳት ማጻሕፍት በማጣቀስ የውይይቱን ውጤት አቅርቧል በዚህም መሠረት፡- እመቤታችን በተመለከተ ጊዜውን ተደራሽ ያደረጉ ጥያቄዎች ጥንተ አብሶን፣ ቤዛዊተ ዓለም፣ አማላጅነት፣የጌታችን ወንድሞችና የእመቤታችን ትንሣኤና ተያያዝ ጥያቄዎች በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ሰፊ ውይይትና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ስለሆነም ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ አባቶቻችን ነቢያት፣ አባቶቻችን ሐዋርያት ቀደምት ሊቃውንት ያቆዩልንን የነገረ ማርያም ትምህርት ዛይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጠንክረን እናስተምራለን፡፡
ለ. በነገረ ክርስቶስ ዙሪያ በውስጥና በውጭ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የክርስቶስ የባህርይ አምላክነት ወልድ ፍጥር በሥጋው ይባላል ወይ? ሊቀ ካህናት ቤዛ አስተራቂነት ነገረ ድኅነት ነገረ ቅብዓት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ሰፊ ውይይትና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ስለሆነም ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ ቀደምት ሊቃውንት ያቆዩልንን የነገረ ክርስቶስ ትምህርት ዛይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጠንክረን  እናስተምራለን፡፡

ሐ. አንድምታ ትርጋሜን በተመለከተ ጉባኤው በስፋትና በምልዓት ውይይት አድርጓል በመሆኑም ትርጋሜው ዘሩን ሳይለቅ መሻሻል እንዳለበት በመጀመሪያ በመምህር ኤስድሮስ ከዚያም በአዓጼ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ማስፋፍያ እንደተደረገበት ታሪክ ያስረዳል። በሀገሪቱ ያሉ የመጻሕፍት ትርጋሜ ሊቃውንት የሚስተካከሉ አካባቢያዊ ቃላትን ለማስተካከልና ለማዘመን  የትርጋሜውን የማሻሻል ሥራ የሚሠሩ ሰዎች በእውቀት ፥ በእምነትና በሥነ ምግባር የጎለበቱ ፥ ከእኔነት ሥሜት ወጥተው የቤተ ክርስቲያን ሐሳብ ብቻ የሚከተሉ ርቱዓን መምህራን መሆን እንዳለባቸው ጉባኤው በአጽንዖት ያሳስባል።

11. በሢመተ ክህነት እና በሥርዐተ ምንኩስና ላይ የሚታዩ ጉልህ ጉድለቶችን በሚመለከት በርካታ ችግር መኖሩ በቡድን ውይይቱ በስፋት ተገልጧል ይህን ችግር ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ለክህነት አገልግሎት የሚያበቃ የትምህረት ዝግጅትና ሥነ ምግባር የእድሜ ወሰን ታይቶ እንደ ቀኖና ቤ/ክ/ መሠረት ከሚኖርበት አጥቢያ ቤ/ክ በቂ ማረጋገጫ ተሰጥቶ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብቻ እንዲሰጥ እንዲደረግ እንጠይቃለን። በተጨማሪም ሥርአተ ምንኩስና ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሥርዐተ አበውን ጠብቆ መሥፈርቱን አሟልቶ በየቦታው የሚሠጠው ምንኩስና ቀርቶ በታወቁና በጥንታውያን የምንኩስና ገዳማት  ብቻ እንዲሆን አበክረን እንጠይቃለን፡፡

በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የሊቃውንት ጉባኤን በየአህጉረ ስብከቱ ማደራጀት እና በማዕከል ካለው የሊቃውንት ጉባኤ ጋር ተናቦ መሥራት እንዲቻል ምን ቢደረግ ይሻላል? ለሚለው የሊቃውንት ጉባኤው በየ አህጉረ ስብከቱና በየወረዳው ቢደራጅ እጅግ መልካም በመሆኑ በቡድን ውይይቱ በስፋት ስለተገለጠ ሁለገብ ሙያ ባላቸው ሊቃውንት ተደራጅቶ የሚመሰገንበትና የሚወቀስበት የተሰፈረ የተቆጠረ የሥራ መዘርዝር ተዘጋጅቶለት እንዲሠራና በዚህ ዘርፍ የሊቃውንት ጉባኤ ሐላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን እንጠይቃለን፡፡

12. ሀ.  አዋልድ ቅዱሳት መጻሕፍትን በተመለከተ አንዳንድ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡ መፍትሔው ምን መሆን አለበት) እንዴት ይታረም) አርትዖትስ እንዴት ይፈጸም) የሚለው የውይይት ሐሳብን በተመለከተ ፡-አዋልድ መጻሕፍት በተለይም ገድላትና ድርሳናት ብዛት ያላቸው የተለያዩ ቅጂዎች ስላሉአቸው ቅጂዎቹ ተሰብስበው በሊቃውት ሊመረመሩና እውነተኛው ሊለይ እንደሚገባ፤በመጻሕፍቱ ውስጥ ከሌሎች ቤተ እምነቶች ጋር ሊያጋጩ የሚችሉ፣ በተለይም ክርስቲያኖች በቁጥር አንሰው በሚታዩባቸው አካባቢዎች አገልጋዮች ካህናትንና ምእመናንን ለጉዳት የሚዳርጉ ሐሳቦችን የያዙ መጻሕፍት መኖራቸው የሚሉ በርካታ ነጥቦችን በማንሳት ቡድኑ በስፋት ተወያይቷል ከዚህ በመነሳት በመፍትሔ ሐሳብ ደረጃ የተቀመጡትንና ጉባኤው የተስማማባቸውን የመፍትሔ ሐሳቦች፣ምእመናን ባለመረዳት እንዳይደነጋገሩ አስፈላጊው ጥናት ተደርጎ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው መጻሕፍትን ለይቶ ለማሳወቅ አስቀድሞ በተጻፉ የብራና ቅጂዎች ውስጥ ሳይኖሩ በኋላ በስርዋጽ የገቡ ጤናማ ያልሆኑ ሐሳቦች ከጥንት ቅጂዎቻቸው ጋር በማመሳከር እና እውነተኛውን በመለየት ለማረም፣ከገድላት ከድርሳናት ከዜማ መጻሕፍትም ሆነ ከሌሎች አዋልድ መጻሕፍት ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ለይቶ ማብራራት፣ ማስማማት፣ ማስታረቅ የሚስፈልጋቸውንም ማስታረቅ፣ በስርዋጽ የገባውን በበቂ ጥናት ተለይተው እንዲታረሙ አስፈላጎውን ጥረት እናደርጋለን፣

ለ. የቤተ ክርስቲያን የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትና ሌላ ማንኛውም ነገር ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ አካላት እንዳያሳትሟቸውና እንዳይጠቀሙባቸው እንዴት እንከላከል) የሚለውን ሐሳብ በተመለከተ የተነሱ ጭብጦች፡- የቤተ ክርስቲያን ንብረቶች የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት ግለሰቦች በስማቸው እያሳተሙ ቤተ ክርስቲያን ባለ ቤትነቷን እያሳጧት መሆኑን፣ የትርጓሜና የዜማ መጻሕፍት የየቤታቸው ባህል ስላላቸው ወጥ ለማድረግ አስቸጋሪ መሆኑ ፣ አሳታሚዎችም ያለቤተ ክርስቲያን ፈቃድ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን እያሳተሙ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ መሆኑ፣በትንሣኤ  የማተሚያ ድርጅት ብቻ ይታተምልን በማለት ቡድኑ በስፋት ተወያይቷል ። ከዚህ በመነሳት የቤተ ክርስቲያን ንብረቶች የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት ግለሰቦች በስማቸው ሊያሳተሙ ስለማይገባ የመጻሕፍቱ ባለቤት ቤተ ክርስቲያን ሆና ለግለሰቦች ሳይሆን ለምስክር ጉባኤ ቤቶቹ፣ ለመንፈሳዊ ኮሌጆቹና ዩንቨርስቲዎች እውቅና እየተሰጠና በሊቃውንት ጉባኤ ሰሰእየታረመ የየቤቱ ባህል ተጠብቆ እንዲታተም የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን፣ አሳታሚ ድርጅቶችም የቤተ ክርስቲያን ሀብቶች የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት  ያለቤተ ክርስቲያን ፈቃድ እያሳተሙ ለግል ጥቅማቸው እንዳያውሉ፣ ቢያትሙም ተጠያቂዎች የሚሆኑበትን አሠራር መፍጠር ፣የቤተ ክርስቲያን ሀብቶች የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያለቤተክርስቲያን ፈቃድ እያሳተሙ ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ ግለሰቦችም እንዲታረሙ ጥብቅ መመሪያ ከማስተላለፍም በተጨማሪ ምእመናን በማዕከል ያልታተሙ መጻሕፍትን እንዳይገዙ መመሪያ ቢተላለፍ፣የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን።

13. ዕቅበተ እምነትን በተመለከተ የሚታዩ ጉድለቶች ምን ምን ናቸው? የመፍትሔ   ሐሳቦችስ?ምንም ሳይማሩ ሥልጣነ ክህነት የሚቀበሉና በአስተዳደር ሥልጣን የሚሾሙ አሉ፤ በቂ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ሳይኖራቸው ክህነት የተቀበሉ በሥልጠና ቢያስታካክሉ፤ ወደፊት የሚቀበሉ ዐውቀው እንዲቀበሉ ቢደረግ የሚሉና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ቡድኑ ተወያይቶባቸዋል። ስለሆነም ይህም ችግር እንዲስተካከል የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን፡፡

14. ሀ. በማኅበራዊ ሚድያ የሚሠራጩ የሃይማኖት ትምህርቶችን እንዴት እንከታተል? የሚፈጠሩ ችግሮችንስ እንዴት እንፍታ? እንዳያሻው የሚስተምርን እንዴት እንከላከል ስለሚለውም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያ በማጠናከር ለሁሉም ተደራሽ መሆን የሚቻልበት አሠራር በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተጠንቶ ተግባራዊ እንዲሆን እየጠየቅን ምእመናንም ከእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ትምህርቶችን እንዲከታተሉ እናስተምራለን፡፡

ለ. የቤተ ክርስቲያን አንድነትንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና መጠበቅ የሚቻለው በምን ዘዴ ነው? ማእከላዊነት መጠበቅ፣ ጠንካራ የሕግ አስተዳደር እንዲኖረን ማድረግ፣ በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገርም ሕግ የሚከበርበትን ሁኔታ ማጠናከር፣ ልጆቻችን በመላው ዓለም ስለሚገኙ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት፣ ሕልውና፣ ልዕልና እንደ ሌሎች አብያት ክርስቲያናት ዓለም አቀፍ ሥራ መሥራት፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡
ሐ. በአብነት ት/ቤቶች፣ መምህራን፣ እና ተማሪዎችን እንዴት እንከባከብ? ተጨማሪ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥልጠናዎች እንዴት ይካተቱ? የአብነት ትምህርትን ቤቶች የሊቃውንት መገኛ፣ የቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት የአገልጋዮቿ ሁሉ ምንጭ በመሆናቸው ለአብነት ትምህርት ቤት ልዩ የሆነ ትኩረት መስጠት ስለሚያስ ፈልግ፤ በየአጥቢያው የሚደራጁበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ ለአብያተ ጉባኤ በየደረጃው ልዩ መተዳደሪያ/ሥርዐት እንዲዘጋጅ፣ እንደሚገኙበት ቦታ በገጠር፣ በከተማ፣ በገዳምና በአድባራት ተሳቢ ያደረገ ድጋፍ፣ ክትትል፣ እንክብካቤ፣ ዋስትና፣ ዘላቂ የሕልውና ድጋፍ እንዲደረግ ጠንካራ መመሪያ እንዲወርድ እየጠየቅን እኛም የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡

በመጨረሻም፡-
ይህ በሀገር ደረጃ እንዲህ ባማረ ሁኔታ ሊቃውንት ተሰባስበን እንድንመካከር እንድንወያይ በታሪካችን የዚህ እድል ተቋዳሽ እንሆን ዘንድ ለፈቀዱልን ጉባኤያችንን ተገኝተው የባረኩልልን የተቀደሰ ቡራኬያቸውን ለሰጡን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከፍ ያለ ምስጋናችንን ከአክብሮት ጋር እናቀርባለን።

በጉባኤው ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ለተከታተሉን ጉባኤያችንን ለመሩልን መመሪያና ትምህርት ለሰጡን ለብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከፍ ያለ ምስጋና ከአክብሮት ጋር ስናቀርብልዎ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ይህ ዝክረ ኒቅያ የተሰኘው ሀገር አቀፍ ጉባኤ እንዲካሔድ ከመጀሪያው ጀምሮ ሐሳብ በመስጠት ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን በቅርበት ላደረገው አስተዋጽኦና ሁለንተናዊ ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ሃይማኖት የጸናበትን ርእሰ መናፍቅ የተባለ አርዮስ የተወገዘበትን በኒቅያ ጉባኤ ስያሜ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ድንቅ ጉባኤ እንዲዘጋጅ እኛ የጉባኤ ቤት መምህራን በማዕከል እንድነገናኝ እንድንመካከር እርስ በእርሳችን እንድንተዋወቅ እድሉን ያመቻቸልንን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ ዋና ኃላፊ ክቡር መጋቤ ብሉይ ዕዝራ ለገሠ እና የሥራ አጋሮቻቸው ከልብ በመነጨ ምስጋናና አድናቆታችንን ስንገልጽ በታላቅ አክብሮትና በፍጹም ትህትና ነው፡፡ ለወደፊቱም እንደ አመቺነቱ ዛሬ በዚህ ዐቢይ ጉባኤ የተረከብነውን የቤት ሥራ ለመገምገም ለተጨማሪ ሥራና ኃላፊነት ለመዘጋጀት ይህ ጉባኤ በየዓመቱ ከግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በፊት እንዲዘጋጅ በአክብሮት እንጠይቃለን ።

ዝክረ ኒቅያ በሚል የተዘጋጀው ይህ ጉባኤ ሊቃውንት የተሳካ ይሆን ዘንድ በገንዘብ በሐሳብ ለተባበሩን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም ምስጋናችንን እያቀርብን ይህ ባለ 14 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ ከዝርዝር የውይይት ሰነዱ ጋር ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን!!!
                                    ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
                                              አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ


(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👍2
ለሁሉም ሼር አርጉት
2
ልደታ ለማርያም

የብህንሳው ሊቀ ጳጳስ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም  ‹‹ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ/ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ›› በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታልb፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም  በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት 1 ቀን ተወልዳለች፡፡
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👍32
የአዋሽ መልካሳ ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት የአንደኛ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና በ03/09/2017 ዓ.ም አሰጠ።
ሰ/ት/ቤቱ ሥርዓት ትምህርቱ በዘንድሮው ዓመት የጀመረው ስሆን የ1ኛ ክፍል 55, ተማሪዎች ፣4ኛ ክፍል 45 ተማሪዎች እና 7ኛ ክፍል 50 ተማሪዎች በአጠቃላይ ከ150 ተማሪዎች በለይ ማጠቃለያ ፈተና እንድወስዱ ተድርጓል።
👍32
እንኳን ለ14ኛው ሀገር አቀፍ ሰነበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላለ ጉባኤ እና በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤት ቀን አደረሳችሁ።
ሰኔ 1 2017 ዓ.ም በዓሉን በልዩ ሁኔታ በመንበረ ጵጵስና ደብረ ናዝሬት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ይከበራል
🏡🌷👆👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏እኔም የሰንበት ትምህርት ቤት ልጅ የቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ ነኝ።👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የመንበረ ጵጵስና ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት👏👏👏👏👏👏👏👏👏😚🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
2
ወቅታዊ መልእክት
ግንቦት ፯ ቀን ፳፻፲ወ፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች  ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት !!
   በቅድሚያ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንኳን ለ፳፻፲ወ፯ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት  ምልዓተ ጉባኤ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ የሆነ ውይይት እንድታከናውኑ የልጅነት ጸሎታችን ነው።
  የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የሚወያይበትን አጀንዳ ተመልክተነዋል። የተያዘውም አጀንዳ  ጠቃሚ እንደሆነ ተረድተናል። ነገር ግን አሁን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ላይ የሚስተዋሉ ቁልፍ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል ብለን አናምንም። ምክንያቱም ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ የሚስተዋሉ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ በቁርጠኝነት ዘላቂ መፍትሔ ሊበጅላቸው የሚገቡ ዘርፈ ብዙ አስተዳደራዊ እና ተያያዥ ጉዳዮች ለውይይት ሳይቀርቡ ታልፈዋል።
በመሆኑም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተለይተው፣ በማስረጃ ዳብረው እና  በመጨረሻም ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲ወ፯ ዓ.ም የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከበርካታ አህጉረ ስብከት ከተውጣጡ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር አባላት እና ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከተውጣጡ የክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራሮች፣ የገዳማት እና አድባራት ሰንበት ት/ቤት ሊቃነ መናብርት ጋር በአካልና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።  በመሆኑም በአካልና በቴክኖሎጂ በአመራሮች ውይይት  የተደረገባቸው፤ የጋራ አቋም የተያዘባቸው እንዲሁም በቀጥታ የኦርቶዶክሳዊያን ምእመናንና ምእመናት ጥያቄም ጭምር የሆኑትን፤ እኛ  የነገይቱ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ ወጣቶች በልጅነት አንደበት እንደሚከተለው ለማቅረብ እንወዳለን ።
እነርሱም፦
1. የቤተ ክርስቲያንን ሲኖዶሳዊ ልዕልና እና አንድነትን ማስጠበቅ ፤
ሀ. ታላቂቱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከትናንቱ ይልቅ ዛሬ ተቋማዊ ህልውናዋ እና ልዕልናዋ አስጊ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገ ቤተ ክርስቲያን እና መዋቅራዊ አሠራርን በመፈተሽ እና በማስጠበቅ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ፈተና በፍጥነት ሊያስቆም ይገባል፡፡
ለ. በነገረ ሃይማኖት ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ሐሰተኛ ትምህርቶች ቤተ ክርስቲያን የጠራ ትምህርቷን በተገቢው ሁኔታ፣ በሚገባው ዐውድ እና በሚመለከተው አካል ምላሽ እንዲሰጥባቸው፤
ሐ. ሐሰተኛ ትምህርት ያስተላለፉ ከመምህራን እስከ ሊቃነ ጳጳሳት ያሉ አካላት ላይ ተገቢው ቀኖናዊ ሥራ እንዲሠራ፤
መ. እየተድበሰበሰ ያለው የነገረ ቅብዓት ጉዳይ የማያዳግም እልባት ሊሰጠው ይገባል።
ሠ. በትግራይ ክልል የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ነፍስ ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል። በክልሉ ከሚገኙ አህጉረ ስብከት  አስተዳደራዊ ግንኙነት መቋረጥ እና እስከ አሁንም ይኽ ችግር ተገቢ የኾነ መፍትሔ ባለማግኘቱ፤ መለያየቱ ሥር ሰዶ፤ የጥፋቱ ጉዳት እየጨመረ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ለማይፈልጉ አካላት ሰርግና ምላሽ ሆኖ ነፍሳት በኑፋቄ እየተነጠቁ ይገኛሉ። ከተፈጠረው የአስተዳድር ልዩነት በኋላ የተስተዋሉ የኑፋቄ እና ስልታዊ ጥፋትን አስመልክቶ ያዘጋጀነውን ዝርዝር የማስረጃ ሰነድ ለቋሚ ሲኖዶስና ለቅዱስ ፓትርያርኩ ብናቀርብም ተጨባጭ ምላሽ አልተሰጠም። በመሆኑም በትግራይ ያለ ኦርቶዶክሳዊ ምእመን በሚያስደነግጥ ፍጥነት በኑፋቄ እየተነጠቀ መሆኑን በመረዳት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው በፈጣሪ ፊት፣ በኅሊና እና በታሪክ ያስጠይቃል። አደገኛ ሰብራትም የሚያስከትል በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሠጥበት፤
ረ. በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት ወቅታዊ ችግር፣ ሌሎች የከረሙ አስተዳደራዊ ችግሮች እና ተያያዥ ምክንያቶች አብያተ ክርስቲያናት እየተዘጉ አገልጋይ ካህናት እና ተከታይ ምእመናን ወደ ሌላ እየፈለሱ እና እየተሰደዱ መሆናቸው የሚታይ የአደባባይ ሐቅ ነው። ይኸንኑ ችግር በጥናት ላይ ተመሥርቶ ከመመለስ ይልቅ ጳጳስ በመሾም ጥያቄዎቹ እንደተመለሱ የመቁጠር ከፍተኛ ዝንባሌ ተስተውሏል። በእርግጥ እርሱም ውጤታማ አይደለም። ችግሩን ከሥሩ ተረድቶ ምላሽ ባለመሰጠቱ የክልሉን ኦርቶዶክሳዊ በሌላ ዐውቅልሀለው ባይ አካል እንዲናወጽ ሆኗል:: በቅዱስ ሲኖዶሱም ለቋንቋዎች አገልግሎት የተመደበው በጀት እዚህ ግባ የሚባል ሥራ ሲሠራበት አልታየም። በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኘውን የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልግሎት በማጠናከር የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የካህናት ማሠልጠኛ ማዕከላትን ማስፋፋት፣ መምህራንና አገልጋዮችን በማፍራት ተደራሽነትን የማስፋት ተጨባጭ ሥራ መሥራት ይገባል።
2. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግሮችን (ለጥፋት የዳረገንን ብልሹ አሠራርን) በተመለከተ፦
የሰበካ መንፈሳዊ ሥራ አስፈጻሚ ፣ ጠቅላላ ጉባኤ እና ከመንፈሳዊ ዘርፍ ውጪ ያሉ አስተዳደራዊ ጉዳዮች በቃለ ዐዋዲው እና  በተገቢው የዘርፉ ባለሙያ እንዲመሩ አለማድረግ ለጥፋት እና ለብልሹ አሠራር ዳርጎናል።
ታላቂቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ከማይመጥን እና ብዙ ዋጋ ካስከፈላት አስተዳደራዊ ድክመት በመላቀቅ እና ዘመኑን በመዋጀት  እናት ቤተ ክርስቲያንን  መታደግ ለነገ የማያድር ሥራ ነው ። በመሆኑም :-
ሀ. የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዳይሆን፣ የምእመናን ነፍስ እንዲነጠቅ፣  የኢኮኖሚ አስተዋጽዖዋ እንዲደበዝዝ ፣ ተሰሚነቷና ተቀባይነቷ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት የሆነው በብቁ የአስተዳደር ባለሙያ የመፈጸም ችግር የገነገነ ነው። መንፈሳዊ ዕውቅት ብቻ ባላቸው ነገር ግን የአስተዳደር ክህሎት በሌላቸው፣ ዘመኑን የመዋጀት ክፍተት ባለባቸው ሊቃነ ጳጳሳት እና በዘመድ አዝማድ ደጅ ጥናት ሙያ ሳይኖራቸው በተመደቡ ሓላፊዎች መመራቱ ዋናው የችግሩ አካል ስለሆነ የጠቅላይ ቤተ ክህነት  ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት፣ የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች  የአስተዳደር ዘርፍ ከሊቃነ ጳጳሳት ውጪ በብቁ ባለሙያዎች እንዲመሩ እና ሊቃነ ጳጳሳት በሕግ አውጪነት እና ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ፤ ቤተ ክርስቲያንን እንዲመሩ፤ሕገ ቤተ ክርስቲያን ላይ ማሻሻያ  ማድረግ ይገባል ::

ለ. በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና በቃለ ዐዋዲ የተደነገገው የሰበካ ጉባኤ የአስፈጻሚነት እና የሰበካ መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤያት ሚና መገሰስ ፦ በቃለ ዐዋዲው የተደነገገው የካህናት፣ የምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የአስፈጻሚነት ተሳትፎ ማለትም በወረዳ ቤተ ክህነት፣ በሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ተግባራዊ እንዳይደረግ ተገፍቷል። በዚህም ምክንያት የክፍል እና የመምሪያ ሓላፊዎች  በቤተ ክርስቲያን ሕግ በግልጽ ከተደነገገው ከሦስቱ አካላት ተዋጽዖ ውጪ በሕግ  የማይታወቅ  የመደበኛ ቅጥር ሠራተኞች ስብስብ " የአስተዳደር ጉባኤ " የሚባል መሥርተው ቤተ ክርስቲያኒቱን እየበደሉ ይገኛሉ።  ካህናት፣ ምእመናን ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የአስፈፃሚነት ሚናቸውን እንዲወጡ በሕገ ወጥ  ስብስብ የተነጠቀው የአስፈጻሚነት ድርሻ በየመዋቅሩ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተመልሶ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ።
ሐ. የሀብት ብክነት፦ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረጉ አባቶቻችን ለስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ብለው የገነቧቸው እና ለአገልግሎት ያበቋቸውን ሕንፃዎች ፣ ድርጅቶች እና ቤቶች ዛሬ በአያያዝና በቁጥጥር ሥርዓት ጉድለት ከፍተኛ ዘርፋና ግፍ የሚፈፀምባቸው ሆነዋል፤ ለብክነትም ተዳርገዋል። ለዚህም ጤናማ  የሥራ አፈፃፀም ታሪክ የሌላቸው አካላት እየተፈራረቁ የመዘበሩት የቤቶች ድርጅት አንዱ ማሳያ ነው። ከአጥቢያ ጀምሮ በዘመናዊ አስተዳደር እጦት ምክንያት ለኪራይ አገልግሎት የዋሉ ሕንፃዎች ፣ ቤቶች እና ይዞታዎች በረቀቀ የሙስና ስልት ከሚጠበቅባቸው ገቢ በታች እየሰበሰቡ አብላጫውን አስተዳዳሪ ተብለው በሚሾሙ አካላት ይዘረፋሉ። በመሆኑም አሁን ላይ የአጥቢያዎች ቁመና የሠራተኞች ደሞዝ መክፈል ላይ ብቻ ተቸክሎ የምእመናን ሕይወት፣  ስብከተ ወንጌል ማስፋፋትና ልማት የማይታሰብ ሆኗል።
በመሆኑም ለወንጌል ልማት መዋል የሚገባው ሀብት  ለምዝበራ ተዳርጓል። ቤተ ክርስቲያን መንፈንሳዊ  ዕውቀትን ከዘመናዊው ዕውቀት ጋር ያጣመሩ ፈሪሐ እግዚአብሔር ያላቸው ልጆች የሌሏት ይመስል፤ የለየላቸው ጨካኝ ወንበዴዎች የሚቀራመቷት ሆናለች። በአያያዝ እና በብቁ አስተዳደር እጦት ሀብቷ  ለብክነት ተዳርጓል ፤ ለጥቅመኞችም ሲሳይ ሆኗል።
ይህን የአደባባይ ምሥጢር መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ አይቶ እንዳላየ፤ ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍ ቤተ ክርስቲያንን ለወንበዴዎች አሳልፎ መስጠት ነውና  በቁርጠኝነት ሥር ነቀል ለውጥ ሊደረግ ይገባል።
መ. ከአጥቢያ ጀምሮ በሁሉም መዋቅር ዘመኑን የዋጀ የአስተዳደር ፣ የፋይናስ የግምገማ ፣ የቁጥጥር እና የምዘና ሥርዓት አለመኖር :- በሁሉም መዋቅር የሥራ ግምገማ ፣ የሥራ አፈጻጸም እና የሀብት አጠቃቀም ቁጥጥር ሥርዓት የለም። አጥፊ አይጠየቅም፤ በአጥፊዎች ላይ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አይተገበርም፤ ሹመት፣ ዕድገት፣ ዝውውር ያለ ምዘና ሥርዓት  በዘፈቀደ ይከናወናል። የሠራተኞች የሥራ መደብ በከፍተኛ የብር መጠን ይቸበቸባል ፤ ሌብነት ፣ ሥርዓት አልበኝነት ነግሠው መንፈሳዊነት  ከቦታው ጭራሹኑ ጠፍቷል። የሥራ ዋስትና የለም፤ ከኢአማኒያን እንኳ በማይጠበቅ መልኩ የካህናት፣ የዲያቆናት እና የስብከተ ወንጌል የሥራ መደብ ላይ የአየር ላይ ሽያጭ ፣ የወንዘኝነት  መጠቃቀም የመሳሰሉት ዘግናኝ የግፍ ግፎች ይፈጸማሉ። ይህ ችግር በብዙ ሀገረ ስብከቶች መጠኑ ይነስም ይብዛ የሚስተዋል ሲሆን በተለይ ዋነኛ መገለጫው የሆነው እንደ አዲስ አበባ ባለ ሀገረ ስብከት ጎልቶ ይታያል። እንደ ማሳያ በተለያየ ጊዜ የተሾሙ ብፁዓን አባቶችም ሆነ በተለያየ እርከን ያሉ ሓላፊዎች የግላቸው የአሠራር ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ  አንዱ የችግሩ ምንጭ እንደ ሲኖዶስ አብረው የሚወስኑ ጥቂት የማይባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ቅጠርልኝ፤ አዛውርልኝ፣ መድብልኝ፣ አታዘዋውርብኝ፣ አትቅጣብኝ የሚሉ ጫናዎች እንደሚያሳድሩባቸው ሁሉም በሚባል ደረጃ የሚገልጹት ለተበላሸ  አሠራር ምክንያት ሆኗል። በመሆኑም ይህ የመልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የቅዱስ ሲኖዶስ ቁርጠኛ አቋም ከሆነ አባቶች ለወዳጅ ዘመድ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ማስቆም ያስፈልጋል ።
ረ.  ውስን ሊቃነ ጳጳሳት በእርግና ምክንያት በግልፅ አስተዳደራዊ ሥራ ማከናወን እንደማይችሉ እየተስተዋለ ስለ ነፍሳቱ እረኛ ማጣት ደንታ ቢስ በመሆን መፍትሔ ሳይሰጥ ቀርቷል፤ እንዲሁም ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም ሊቃነ ጳጳሳት ከምእመናን ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ሀገረ ስብከቱ ታውኮ፤ ምእመናን አዝነው እና ከበረቱ ተገፍተው ወጥተው ሲቀሩ ሲኖዶስ በዝምታ ተመልክቶታል። ሀገረ ስብከታቸውን በሚገባ በማያስተዳድሩ ሊቃነ ጳጳሳት ላይ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተደነገገው መሠረት አስተዳደራዊ እርምጃ አለመወሰዱ እና የበዛ ዳተኝነቱ ቤተ ክርስቲያንን ክፉኛ ጎድቷታል። በመሆኑም በእርግና ላይ ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች ረዳት መሾም ፣ የታወቀ የአስተዳድር ድክመት ያለባቸውን አባቶች ተገቢውን የተጠያቂነት አሠራር በተግባር ላይ ማዋል ይገባል።
ሸ. በመንፈሳዊ አገልገሎት ማለትም  በፍትሐት፣ በሥርዓተ ተክሊልና በሥርዓተ ቀብር  ላይ  ከመንፈሳዊ አሠራር ያፈነገጠ የለየለት ንግድ ምእመናንን አስመርሯል። በቅዳሴ ሰዓትና አገልግሎት፣ ማሕሌት፣  ሰዓታት እና በሌሎች መንፈሳዊ አገልገሎቶች ላይ  እየተሰተዋለ ያለው ከመጻሕፍትም ከአባቶችም ያላገኘነው ዐዲስ ባዕድ ልምምድ ተበራክቷ ። በፍቅር እና በረከትን ሽቶ ማገልገል ሞኝነት መስሎ፤ ከመንፈስ ቅዱስ አሠራር ውጪ እንደ መደበኛ ሥራ የማየትና ከፍቅር ይልቅ በሥራ መንፈስ የማገልገል አዝማሚያ መፍትሔ ሊፈለግለት ይገባል።
ከ. በከተማ ልማት እና መስፋፋት ምክንያት ምእመናን ከአምልኮ ሥፍራ እንዳይለዩ እና አድባራቱና ገዳማቱ ተገልጋይ እንዳያጡ፣ ዘመኑ በመዋጀት ከአምልኮ ሥፍራና መልሶ ማልማት ጋር የተጣጣማሙ ስልታዊ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶችን  በማዘጋጀት በአድባራቱ ቦታ እና ከመንግሥት ቦታን በመጠየቅ  ምእመናን ተኮር የልማት ሥራ  መሥራት ምእመናን ከቀያቸው ሣይርቁ አምልኮተ እግዚአብሔርን መፈጸም ያስችላቸዋል። በመሆኑም ነገን አሻግሮ በመመልከት ዛሬ ላይ ወደ ሥራ መግባት ይገባል።
3. የሥነ ምግባር ግድፈት ክብረ ክህነት፣ ክብረ ምንኩስናን የሚያስነቅፍ የተገለጠ የቀኖና ጥሰት መበራከት:-
የታወቀ፣ የተገለጠ የሥነ ምግባር ግድፈቱ ትውልዱን ከቤተ ክርስቲያን እያራቀው ነው። ትናንት ለቀሳውስት እና ለሊቃነ ጳጳሳት የሚሰጠው ክብር ተሸርሽሮ ጀርባ መሥጠት ተጀምሯል። በከተማ መነኮሳት እና መነኮሳይያት ኢክርስቲያናዊ ምግባር ምእመናንና ወጣቱን የማያንጽ አሰናካይ፤ ከሥርዓተ አበው፣ ከሥርዓት ምንኩስና ያፈነገጠ  አሳፋሪ ልምምድ ተበራክቷል።
መንፈሳዊ ሕይወት ተዘንግቶ ፤ ቦታ ተነፍጐት ዓለማዊነትና ሥጋዊ ፍላጎት ነግሧል። ከታወቀ ደሞዝ በላይ ኑሮ ፤ ምንጩ የማይታወቅ፤ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ  ንብረት ማካበት፣ ከገዳማት እና አድባራት ሠራተኛ እስከ ሊቃነ ጳጳሳት ድረስ ሕጋዊ እስኪመስል በአደባባይ ተገልጧል። ይኸ አደገኛ በሽታ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል፤ ባለቤት የሌለው ይመስል ልቅ የሆነውን ጉዳይ ከሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ  ሁሉም በየተዋረዱ ለሥነ ምግባር ጥሰቱ ተጠያቂነት የሚሰፍንበት ሥርዓት ሊበጅለት ይገባል ።

4. በሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ተሳትፎን በተመለከተ
ሀ.  በሀገር ግንባታ፣ በሰላም እና እርቅ ክዋኔ የካበተ እና ተጠባቂ ልምድ እና አስተዋጽዖ ያላት ቤተ ክርስቲያን ፣ በሊቃውንቷ  አዎንታዊ አስተዋጽዎ ማበርከት ሲገባት በግልጽ፤ ከታወቀው አዎንታዊ ሚናዋ ተናጥባለች። በየዕለቱ የሂስና ግለሂስ አስተምህሮን  የምትተገበር ቤተ ክርስቲያን ፣  በጸሎትና በውይይት  ችግሮች የመሻገር ሰፊ ልምድ ያላት ቤተ ክርስቲያን፤  ከባለ ድርሻ አካላት  ጋር ያላትን ግንኙነት በጥበብ በማስኬድ፣ በውይይት ፣ በምልዐት በመመካከር  ማስኬድ ይገባታል። በሀገራዊ ጉዳይ ተቋማዊ ተሳትፎና ድርሻን መወጣት ዐቢይ ተግባር መጠናከር ይገባል ።
ለ. በመንግሥት በኩል እየተዘጋጁ ባሉ ልዩ ልዩ ረቂቅ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ተገቢነት ያለው ተቋማዊ ተሳትፎን በማጠናከር፤  ልዩ ልዩ ረቂቅ የሕግ ፣ የደንብ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ፣ ክትትል ማድረግ  እነዚህ መመሪያዎች ከመውጣታቸው አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያኒቱና በአማኞቿ ላይ የሚያመጣውን በጎም ይሁን ክፉ ተጽእኖ በባለቤትነት መንፈስ በመመርመር ተገቢነት ያለው ሱታፌ እንዲኖራት የሚያስችል አግባብነት ያለው የውክልና ተሳትፎዎች ማድረግ እንድትችል በባለ ሙያዎች በተደራጀ ቡድን ክትትል
እና ተቋማዊ ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል።
ሐ . በሀገራችን የሚፈጠሩ ችግሮች እንዲፈቱ እና ሀገራዊ ሰላም እንዲረጋገጥ አዎንታዊ የቤተ ክርስቲያን ሚናን በተመለከተ ፦ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሀገራዊ ሰላም ፣ በህዝቦች ስደት፣ ሞት  እና አለመረጋጋት ዙሪያ ፤ አስቀድሞ ለዘመናት መገለጫዋ ከሆነው ልምዷ በመነሣት ችግሩ እንዲቀረፍ ፍሬ ያለው ተግባር አልተከናወነም:: ከመግለጫ በዘለለ የተቀናጀ ፣ ውጤት ሊያመጣ የሚችል አዎንታዊ ሚናዋ ደብዝዟል። በመሆኑም  ችግሩን ከመቅረፍ እና በወንድማማቾች መሀል የተፈጠረን ልዩነት በማጥበብ ሀገራዊ ሰላም እንዲሰፍን ቤተ ክርስቲያን  ተጠባቂ ሚናዋን  ከመወጣት አንፃር  ሰፊ ሥራ ይጠበቃል ፡፡
መ. ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም አቀፍ የሃይማኖት እና ሰብዓዊ ክዋኔዎች ላይ በአግባቡ አለመሳተፍ፤ በአኃት አብያተ ክርስቲያናት መደበኛ እና ልዩ ልዩ ጉባኤያት አለመወከል እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተገቢውን ተሳትፎ እና መብቷን የማስከበር ሥራዎች አለማከናወን ይስተዋላል:: ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርቲያን ከምትወከልበት መድረክ መሄድ ካቋረጡ ሰነበቱ። በመሆኑም ይኸ ታላቋን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን የማይመጥን ድርጊት ተገቢው ማስተካከያ ሊሰጠው ይገባል።
ከላይ በዝርዝር የተገለጠው በዋነኛነት የብልሹ አስተዳደር ውጤት፤ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን እንዳታስፋፋ፣፤የነፍስ ድኅነትን እንዳታውጅ፤ መንግሥተ እግዚአብሔርን እንዳትሰብክ እንቅፋት የሆነ፤ ነፍሳትን ከበረቱ ያስኮበለለ፤ የቀሩትም ለቀቢፀ ተስፋ የዳረገ በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፤ ከአሁኑ የከፋ ጥፋት ሳይከሰት  ሥር ነቀል መፍትሔ በመሥጠት   እና የምእመናንን የአስፈፃሚነት ሱታፌ በማረጋገጥ የምንረከባትን  ቤተ ክርስቲያን እንዲታደግልን እና ሐዋርያዊ አደራውን እንዲወጣ በልጅነት መንፈስ ዝቅ ብለን እንማፀናለን ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok
👍1