የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
በአዳማ ቦኩ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የፈለገ ምህረት ሰንበት ትምህርት  ቤት  የነዳያን ምገባ መርሃግብር አከናወነ፦   ሰንበት ትምህርት  ቤቱ በየአመቱ የዳግማትንሳኤ ዕለት እንደሚያደርገው ዘንድሮም ከበጎ አድራጊ ክርስቲያኖች  ሰብስቦ  በአጥቢያው ያሉ ነዳያንን፣ በከርቸሌ የሚገኙ እስረኞችን፣ በአርቱ አርሴማ የሚገኙ ፀበልተኞችን እና ሌሎችንም የተቸገሩ የታመሙ ወገኖችን ምግብ በማዘጋጀት መግቧል። ይሄ መልካም ስራ ለሚቀጥሉት አመታትም የሚቀጥል ይሆናል የዓመት ሰው ይበለን። አሜን
በአዳማ ናዝሬት ደብረ ታቦር ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን የፈለገ ብርሃን ሰንበት ትምህርት  ቤት  የነዳያን ምገባ መርሃግብር አከናወነ፦   ሰንበት ትምህርት  ቤቱ በየአመቱ የትንሳኤ ዕለት እንደሚያደርገው ዘንድሮም ከበጎ አድራጊ ክርስቲያኖች  ሰብስቦ  በአጥቢያው ያሉ ነዳያንን፣ እስረኞችን፣ በግቢው የሚገኙ ፀበልተኞችን እና ሌሎችንም የተቸገሩ የታመሙ ወገኖችን የምገባ መርሃግብር አዘጋጅቷል።
በናዝሬት ደብረ መድሃኒት መድሃኒዓለም ገዳም እና ካቴድራል የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት  ቤት  የነዳያን ምገባ መርሃግብር አከናወነ፦   ሰንበት ትምህርት  ቤቱ በየአመቱ የትንሳኤ ዕለት እንደሚያደርገው ዘንድሮም በአጥቢያው ያሉ ነዳያንን እና ሌሎችንም የተቸገሩ የታመሙ ወገኖችን ምግብ በማዘጋጀት የምገባ እና የትምህርት መርሃ ግብር አከናውኗል።