የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
❤️ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ ተነሥቷል እንጂ በዚህ የለም ሉቃ 24:5

👏እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በፍቅር
አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
🌿🌿🌿🎤🎤

የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ : የዘለዓለም አምላክ ወልድ
ዋሕድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዕለት መግነዝፍቱልኝ  መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ሥልጣኑ ተነስቷልና እንኳን ደስ አለን:: 
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፣
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን፣
አሠሮ ለሰይጣን፣
አግዐዞ ለአዳም፣ 
ሰላም፣
እምይእዜሰ፣
ኮነ፣ 
ፍሥሐ ወሰላም!
1
ቤዛ

ቤዛ ማለት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም አዳነ ተቤዠ ብሎ ይፈታል። ስለዚህም በየመጻሕፍቶቻችን ማዳን፣መቤዠት ለሚሉ ትርጉሞች ቤዛ...ቤዛ ሲል ይገኛል ለምሳሌ ፦

....በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ
                                     *ዘጸ 30:12

° እዚህ ጋር ቤዛ ገንዘብ ተብሎ ተፈቷል ሙሴ ሕዝቡን በሚቆጥርበት ጊዜ በሕዝቡ መቅሰፍት እንዳይታዘዝ ለነፍሱ ቤዛ እንዲሰጥ ታዟል።

° ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው
                                            ምሳ 13:8

እዚህ ጋር ቤዛ ሀብት ተብሎ ተተርጉሟል እርግጥ ነው አቅንቶ ተርጉሞ ለሌላ ማድረግ ይቻላል ነገር ግን ቀጥታ ንባቡ ቤዛን ሀብት አድርጎታል።

እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።
                                   
                                           ኢሳ 41:3

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?

                                        ማቴ 16:26

° እዚህ ጋር ቤዛ ፈንታ ተብሎ ተተርጉሟል


  ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
                                       የሐዋ 7:35

° እዚህ ጋር ቤዛ፣ሹም፣ዳኛፈራጅ ተብሎ ይፈታል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ደሙ በማፍሰስ ሥጋውን በመልዕልተ ቀራንዮ በመቁረስ ተከናውኗል።

ስለ አዳም እና ልጆቹ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ሆኗል !

የእመቤታችን ቤዛነት

እነ ቅዱስ ያሬድ እነ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጻሕፍታቸው ተባብረውበታል በጠቅላላ በሁሉም ዘመናት የተነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተባብረውበታል።

ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ቤዛ

ቤዛ ማለት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም አዳነ ተቤዠ ብሎ ይፈታል። ስለዚህም በየመጻሕፍቶቻችን ማዳን፣መቤዠት ለሚሉ ትርጉሞች ቤዛ...ቤዛ ሲል ይገኛል ለምሳሌ ፦

....በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ
                                     *ዘጸ 30:12

° እዚህ ጋር ቤዛ ገንዘብ ተብሎ ተፈቷል ሙሴ ሕዝቡን በሚቆጥርበት ጊዜ በሕዝቡ መቅሰፍት እንዳይታዘዝ ለነፍሱ ቤዛ እንዲሰጥ ታዟል።

° ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው
                                            ምሳ 13:8

እዚህ ጋር ቤዛ ሀብት ተብሎ ተተርጉሟል እርግጥ ነው አቅንቶ ተርጉሞ ለሌላ ማድረግ ይቻላል ነገር ግን ቀጥታ ንባቡ ቤዛን ሀብት አድርጎታል።

እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።
                                   
                                           ኢሳ 41:3

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?

                                        ማቴ 16:26

° እዚህ ጋር ቤዛ ፈንታ ተብሎ ተተርጉሟል


  ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
                                       የሐዋ 7:35

° እዚህ ጋር ቤዛ፣ሹም፣ዳኛፈራጅ ተብሎ ይፈታል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ደሙ በማፍሰስ ሥጋውን በመልዕልተ ቀራንዮ በመቁረስ ተከናውኗል።

ስለ አዳም እና ልጆቹ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ሆኗል !

የእመቤታችን ቤዛነት

እነ ቅዱስ ያሬድ እነ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጻሕፍታቸው ተባብረውበታል በጠቅላላ በሁሉም ዘመናት የተነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተባብረውበታል።

ሌላው ቢቀር ዕለት ዕለት ማኅሌት የሚቆም ሰው ይህንን ያውቃል !

ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።


የእመቤታችን ቤዛነት ክርስቶስን በመውለድ ፣ በኃጢአት ዓይኑ ለታወረበት ዓይን በመሆን ተገልጾል።

ሲጠቃለል

ክርስቶስ ቤዛ ሆኖ አዳነን፥ እመቤታችን ቤዛዊተ ኩሉ መባሏ

1. ለዓለም ድኅነት ምክንያት ናትና
"አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እም ገነት" አባ ሕርያቆስ
ክርስቶስ የባሕርይ ቤዛ ነው፥ እመቤታችን የጸጋ ናት (ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ጸጋ እንዲል)

2. ምክንያተ ድምሳሴ ጥንተ አብሶ ናትና

= ጥንተ አብሶ
   - ሰዋሰዋዊ ትርጉሙ የመጀመሪያ በደል፥
   - መጽሐፋዊ ምሥጢራዊ ትርጉሙ መርገመ ሥጋ ወነፍስ - ከአዳም ጀምሮ የሚተላለፍ ኃጢአት አንድም እግዚአብሔርን ማጣት አንድም ከጸጋ እግዚአብሔር መራቆት (መሞት) ማለት ነው

ሉቃ 1:28 "ቡርክት አንቲ እምአንስት"፣
መሓ 4:7 "ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ #ነውርም_የለብሽ"

3. በንጽሕና የተዋበች፣ ከምድር እስከ ሰማይ የደረሰች መሰላል ናትና
- (ምድር ያለው ውድቀቱን ያይደለ ሰማይ ያለ መነሣቱን ያየንብሽ)

4. መንበረ መለኮት ናትና
ዳን 7:9-13 "..."
አንድም "አንቲ ተዓብዪ እምኪሩቤል ወትፈደፍዲ እምሱራፌል" እንዲል

5. በጸጋ መድኃኒተ ዓለም ናትና
- የመዳን ምክንያት መሆን መቻል ነው፥
  - "ዘርን ባያስቀርልን" ኢሳ 9:1
  - "ምልክትን ይሰጣችኋል" ኢሳ 7:14

6. ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ናትና
   #ይህን መቧሏ ስለምንድን ነው ቢሉ
      - ጥንተ አብሶ የለባትምና
      - ድንግል ወእም ከእርሷ ውጪ የለምና
      - የመለኮት ማደርያ ናትና
      - አልቦ ኃጢአት ናትና
      - ከእርሷ በቀር ወላዲተ አምላክ የሚባልም ሆነ ሊባል የሚችል

ምክር ቢጤ ፦ ይህን ሳያውቁ ስለ ቤዛ ድምዳሜ መስጠት ነውር ነው ከትልቅ ሰው አይጠበቅም።

                        
👍2🥰1
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶት የነበረው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው መታገዱ ተገለጸ።

ሚያዝያ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።
              
ምንጭ:-   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
1
3
በአዳማ ቦኩ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የፈለገ ምህረት ሰንበት ትምህርት  ቤት  የነዳያን ምገባ መርሃግብር አከናወነ፦   ሰንበት ትምህርት  ቤቱ በየአመቱ የዳግማትንሳኤ ዕለት እንደሚያደርገው ዘንድሮም ከበጎ አድራጊ ክርስቲያኖች  ሰብስቦ  በአጥቢያው ያሉ ነዳያንን፣ በከርቸሌ የሚገኙ እስረኞችን፣ በአርቱ አርሴማ የሚገኙ ፀበልተኞችን እና ሌሎችንም የተቸገሩ የታመሙ ወገኖችን ምግብ በማዘጋጀት መግቧል። ይሄ መልካም ስራ ለሚቀጥሉት አመታትም የሚቀጥል ይሆናል የዓመት ሰው ይበለን። አሜን
በአዳማ ናዝሬት ደብረ ታቦር ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን የፈለገ ብርሃን ሰንበት ትምህርት  ቤት  የነዳያን ምገባ መርሃግብር አከናወነ፦   ሰንበት ትምህርት  ቤቱ በየአመቱ የትንሳኤ ዕለት እንደሚያደርገው ዘንድሮም ከበጎ አድራጊ ክርስቲያኖች  ሰብስቦ  በአጥቢያው ያሉ ነዳያንን፣ እስረኞችን፣ በግቢው የሚገኙ ፀበልተኞችን እና ሌሎችንም የተቸገሩ የታመሙ ወገኖችን የምገባ መርሃግብር አዘጋጅቷል።