🙏🙏🙏🙏እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏🙏
❖ ❖ ❖ የዐቢይ ፆም ስምንተኛ ሳምንት። 💦💦💦💦💦"ሆሣዕና" ❖ ❖ ❖
ሆሣዕና ማለት በዕብራይስጡ ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ መድኃኒት ማለትም ነው፡፡ ከጌታችን ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡
ሆሣዕና፡-- የተባለበት ምክንያት ጌታ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት የሚታሰብበትና የሚዘመርበት በመሆኑ ነው፡፡ የሆሣዕና ሥርዓት ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዕለቱ ፍጻሜ ድረስ የተለየ አገልግሎት አለው፡፡
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።
ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ“ አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡
አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸው፡፡ የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች- ዘሁል22+28 ፤ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል ፣ የሆሣዕና እህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል፡፡
ለምን የተዋረዱትን አህያዎች መረጠ ?
1. ትሕትናን ለማስተማር
የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ ደመና አዞ ነፋስ ጠቅሶ በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ነው ነገር ግን የመጣው ለሰው ልጅ ትህትናን ሊያስተምር ነውና በአህያ ተቀመጠ
2. ትንቢቱን ለመፈጸም
ትንቢት- ‹‹ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ በእህያም በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል›› ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው ዘካ 9+1
3. ምሳሌውን ለመግለጽ
ምሳሌ- ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል፡፡
4. ምሥጢሩን ለመግለጽ
ምሥጢር- በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል
√ አህያ የእስራኤል ምሳሌ ፤ ውርንጫላይቱ የአሕዛብ ምሳሌ
አህያይቱ ቀንበር መሸከም የለመደች ናት እስራኤልም ሕግ መጠበቅ ለምደዋልና ፤ ውርንጫላይቱ መሸከም አለመደችም አሕዛብም ሕግ መጠበቅ አለመዱምና
√ አህያ የኦሪት ምሳሌ ፤ ውርንጫይቱ የወንጌል ምሳሌ
አህያ ቀንበር መሸከም እንደለመደች ኦሪትም የተለመደች ሕግናትና ውርንጫላይቱ ቀንበር መሸከም አለመደችም ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ሕግ ናትና
√ በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው
√ በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል:: ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ
√ በአህያዋ ላይ ኳርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ሕግ ሠራህልን ሲሉ ነው።
√ ስለምን ልብሳቸውን አነጠፉለት ቢባል ? በእዩ ልማድ ነው፡፡ እዩ የተባለው ሰው በእስራኤል ላይ ሲነግሥ እስራኤል ልብሳቸውን አንጥፈውለት ነበረና በዚያ ልማድ አንጥፈውለታል
√ እኩሌቶቱ ደግሞ ዘንባባ አንጥፈውለታል ።
* ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፦
ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤ አንድም ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡
* የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦
ቴምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ ቴምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የቴምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አንተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡
* የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦
ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡
* ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፦
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡ ኢየሱስ ኢየሩሳሌምን ሲያያት አለቀሰላት፡፡ “አንቺ ኢየሩሳሌም ለሰላምሽ የሚያስፈልገውን ነገር ምነው አውቀሽ ቢሆን ኖሮ አሁን ግን ይህ ነገር ከዓይንሽ ተሰውሮብሻል ጠላቶችሽ በዙሪያሽ እንደ አጥር ከብበው በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል… ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያድንሽና ሊጐበኝሽ

የመጣበትን ጊዜ
ባለማወቅሽ ነው እያለ እረገማት
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ሰለ ደኅንተቷ ሊያሳስባት ፈልጐ ነው፡፡ በማያወላዳ መንገድ ንጉሧና መድኃኒቷ እንደሆነ ገለጸላት፡፡ ወደ ራሷ ተመልሳ ጸጋዋን እንድትቀበል የልቧን ድንዳኔ ትታ እርሱን እንድትሰማ አስጠነጠቃት፡፡ ግን አልተጠነቀቀችም፡፡ ለጊዜው በክብር ተቀበለችው፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ግን ተወችው፤ በመስቀል ላይ ሰቀለችው፡፡ የደኅንነቷን ቀን ማወቅ ተሳናት፡፡ በዚህም ደግሞ ከብዙ ዓመታት በኋላ መዓት ወረደባት፡፡ ይህ የሚያሳዝን የኢየሩሳሌም ሥራ የእኛም ሥራ ነው፡፡ ኢየሱስን መድኃኒታችንን መቀበል አንፈልግም ወይም ተቀብለን በኃጢአታችን ከእኛ እንዲርቅ እናደርገዋለን፡፡ በቅዱስ ቁርባን ወደ እኛ ሲመጣ በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ ትንሽ ቆየት ብለን ደግሞ እናዋርደዋለን፡፡ ከእርሱ ጋር እንጣላለን፡፡ ከኃጢአት ጋር ጓደኝነት እንይዛለን፡፡ በኃጢአት ስንወድቅ እርሱን እንደገና እንሰቅለዋለን፡፡ ኢየሱስ እኛን “አቤት በዚህ ቀን ለደኅንነትህ የሚደረገውን ብታውቅ ኖሮ …፣ ይህ ሁሉ ከዓይንህ ተሰውሮብሃል ማወቅን አልፈለግህም፡፡ ይህን እወቅ ግን አንድ ቀን …” እያለ አዝኖ ይፈርድብናል፡፡ ይህንን በማሰብ ሲመጣና ሲናገረን እምቢ አንበለው አናባርረው፡፡ በኋላ እርሱ ቂም ይዞ እምቢ እንዳይለና እንዳያባርረን ደኅንነታችንን ራሳችን አናጥፋት፡፡
በዚህ ዕለት ፀበርት /ዘንባባ/ እየተባረከ ለሕዝብ ይታደላል ይኽንን በመያዝ ዕለቱ የፀበርት እሑድ ይባላል፡፡ታሪኩ በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ይገኛል፡፡
√ማቴ.21፡4
√ ማር.11፡1-10
√ሉቃ.19፡28-40
√ዮሐ.12፤15
• የሆሣዕና መዝሙር፡-
- ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ
• የሆሳዕና የቅዳሴ ምንባባት
( ዕብ.8÷1-ፍጻ. )
ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡
(1ኛ ጴጥ.1÷13 )
ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡
( ሐዋ.8÷26-ፍጻ. )
የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡
• የሆሣዕና ምስባክ የቅዳሴ ( መዝ.80÷3 )
ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡
በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡
እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ“
ትርጉም፦
በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡
(ወይም መዝ.80÷2 )
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡
በእንተ ጸላዒ፡፡
ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡“
ትርጉም፦
ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡
• የሆሣዕና ወንጌል የቅዳሴ ( ዮሐ.12÷1-11 )
ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ......
• የሆሣዕና ቅዳሴ
- ቅዳሴ ዘጐርጐርዮስ

ሰሙነ ሕማማት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሰኞ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ተራበ፤ ፍሬ ባገኝባት ብሎ ከመንደር ዳር የነበረችውን በለስ ተመለከተ፤ ፍሬ ስላጣባት ‹‹ለዘለዓለሙ ፍሬ አይገኝብሽ›› ብሎ ረገማት፡፡ ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! የዚህም ትርጉም ወይም ምሥጢሩ ከበለስ ፍሬ መሻቱ ከሰው ፍቅር ተርቦ ለማጣቱ ለመግለጽ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከእኛ የመልካም ምግባር ፍሬ ለማግኘት ይመጣልና መልካም ፍሬን ልናፈራ ይገባል።(ማቴ.፳፩፥፲፱፣ማር.፲፩፥፲፪-፲፬)
ምንጭ:- ማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ

👍2
የቅድስት ቤተ ክርስቲያ የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት እና ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት አእምሯዊ ንብረት ሆነው መመዝገባቸው ተገለጸ ፡፡
ሚያዚያ 07 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት የሆኑት ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና እንዲሁም ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡
ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዜማ ንዋያተ ቅዱሳቱ እና ቅዱሳት መጻሕፍቱ ተመዝግበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆናቸው ከባለሥጣኑ በወጣው ደብዳቤ ተረጋግጧል።
የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ ንብረቶች ተመዝግበው ዕውቅና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

👍1
ሰላም እንደምን አላችሁ እንኳን ለሰሞነ ህማማት በሰላም አደረሳችሁ ። ይህንን የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ ዘንድ እንጠይቃለን ።
"""""""""""" ረቡዕ """""""""""
፩፦ "ምክረ አይሁድ ይባላል"
"የአይሁድ ሊቀ ካህናትና ፀሀፍት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ዕለት ነው " ሉቃ _ ፳፪ ፦ ፩-፮
፪፦ "የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል"
"ጌታችን በዚህ ዕለት በስምዖን ዘለምፅ ቤት ተቀምጦ ሳለ ማርያም እንተ ዕፍረት (ባለሽቶዋ ማርያም) በአልባስጥሮስ ሽቶ የተሞላ ብልቃጥ ይዛ በመሄድ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራስ (ፀጉር) ላይ ቀባችው" ማቴ _ ፳፩ ፦ ፮-፯
፫ ፦ "የዕንባ ቀንም ይባላል"
"ማርያም እንተ ዕፍረት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር ስር ተደፍታ መላ ሀጢያቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ አጥባዋለችና በዕንባዋ ያጠበችውንም እግር በፀጉሯ አብሳዋለችና" ማር _ ፲፬ ፦ ፱
"ሠናይ ቀን ይሁንላችሁ