የአዳማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
1.11K subscribers
1.77K photos
24 videos
22 files
227 links
ይሄ የቴሌግራም ገፅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተክህነተ በሰ/ት/ቤቶች አንድነት የተከፈተ ሲሆን በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዜና ቤተክርስቲያንና ወቅታዊ ጉዳይ የምንዘግብበት ነው። እርሶም ለኦርትዶክሳውያን ሁሉ ቻናሉን በማጋራት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ድምጽ ይሁኑ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Download Telegram
አስደሳች ዜና ለመጽሐፍት ፈላጊዎች
📔📘📘🗄📘🗄📗📗🗄📘🗄📘📘🗄📗🗄📙📙📙📙📙📙📙📙
በሙሉ ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ከመጋቢት 26-28ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት በፖስታ ቤት በልዩ ቅናሽ የለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ይዞሎት ቀርባል ታዲያ እርሶ ምን ይጠብቃሉ? እድሉን ፈጥነው ይጠቀሙ።ለወዳጅ ዘመድዎ ይሸምቹ። ለበለጠ መረጃ በ 0974734478 ላይ ይደውሉ
*****📕📗📗📗📘📙📚📔📒📕📕📕📚📙📘🗞📋📁📂📂🗂📰📋📖📖📖📖📖📔📙📓📘📘📒📙📕
**ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ልማት ተቋማት አስተዳደር ክፍል*
👍1
ጥንተ ስቅለት

"ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።" ዮሐ 3፡14

መጋቢት 27 የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትና ዓለምን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ያዳነበት የጥንተ ስቅለት መታሰቢያ ነው።

መልካም በዓል!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👍3🥰2
Ergaa Tokkummichaa
Tajaajila bara bite
Akka ta’uu qabutti bara ce’uun kan danda’amu,  barumsa mana kiristaanaa waqtii isaa eeggate akkuma haala jireenyaa barichaatti dhiyeessii fi qaqqabinsa isaa bal’isuudhaan yoo ta’u, adeemsi kunis adeemsa keessatti  carraa fi rakkoo wal-cinatti keessummeessan ta’uusaatiin, bu’uura barsiisa mana kiristaanaatiin barumsa Q. Phaawuloos kiristaanota barsiise, “Abboota keessan dubbii Waaqayyo isinitti himan yaadadhaa; firii jireenya isaanii akkaa ilaaltan amantii keessaniin isaan fakkaadhaa” Ibr. 13:7,  jedhu eeguun fi haala amma tajaajilli irra jiru hubachuun galma gahumsa tajaajila M/B/Dilbataaf qorumsa  yeroo amma argaa jirru kana keessa darbuuf, tooftaadhaan tajaajiluu fi rakkoowwan garaagaraa akkuma dhufaatii isaaniitti keessa darbuuf mala ciminaan hojjechuu diriirsuu irratti ni xiyyeeffata. “Guyyoonni hamoo waan ta’aniif baricha bitaa” Efes. 5:16
የአንድነቱ መልእክት
ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16
👍2
👍2
በምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት በመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ (አዳማ) ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ስር ከሚገኙ የሰ/ት/ቤት  ሥራ አመራር ፣ ሥራ አስፈጻሚዎች ፣ የክፍልና ን/ክፍል ተጠሪዎች ጋር እየተተገበረ በሚገኘው ስልታዊ እቅድ እና በተሻሻለው የሰ/ት/ቤቶቸ መዋቅር ዙሪያ  በቀን 04/07/2017 ዓ∙ም ስልጠና እና ውይይት ተከናወነ፡፡
*******************
በአዳማ ከተማ ለሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች  ከአሁን በፊት  የሰ/ት/ቤቶችን ስልታዊ እቅድና በተሻሻለው የሰ/ት/ቤቶቸ መዋቅር ዙሪያ  ስልጠናዎች ተስጥተው ከሀምሌ 2016 ጀምሮ ስልታዊ እቅዱና የተሻሻለው የሰ/ት/ቤቶቸ መዋቅር እየተተገበረ ሲሆን ፤ ሰ/ት/ቤቶች በትግበራ ሂደት ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች፣ የግንዛቤ ክፍተቶችና መሻሻል የሚገባችው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ  ስልጠናና እና ውይይት ፤ የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ክፍል ሃላፊ ፣ የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አመራር ተወካዮች እና የመንበረ ጵጵስና ርዕስ ከተማ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር  በተገኙበት  ተከናውኗል፡፡
መርሐ ግብሩ የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ክፍል ሃላፊ መጋቢ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኃ/ገብርኤል ተስፋ ባስተላልፉት  መልእት  ተጀምሯል፡፡ የስልታዊ እቅድና የሰ/ት/ቤት መዋቅር አስፈላጊነት የሚመለት ስልጠና በመ/ር ዮሐንስ አለማየሁ በመንበረ ፓትርያርክ የሀገር አቀፍ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት እቅድ ጥናትና ምርምር ዋና ማስተባበሪያ ሃላፊ የ የተሰጠ ሲሆን፤የሰ/ት/ቤት ተወካዮች  በትግበራ ሂደት ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች፣የግንዛቤ ክፍተቶችና መሻሻል የሚገባችው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጥያቄና አስተያይት ሰጥተዋል፡፡
በተነሱ ጥያቂዎች ላይ መ/ር አለምአንተ አበጀ የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ እና በመ/ር መ/ር ዮሐንስ አለማየሁ በመንበረ ፓትርያርክ የሀገር አቀፍ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት እቅድና ጥናትና ምርምር ዋና ማስተባበሪያ ሃላፊ  ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም የሀ/ስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ክፍል ሃላፊ መጋቢ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኃ/ገብርኤል ተስፋ ሰ/ት/ቤቶች ትውልድን ለማዳንና ፤ ዘመኑን ለመሻገር የተሻሻለውን  የሰ/ት/ቤቶቸ መዋቅር እና ስልታዊ እቅድ  ከአጥቢያ ሰበካ ጐባኤ ፤ማህበረ ካህናት እና ስብከተ ወንጌላ ጋር በመቀራርብ እና በመተባበር  ሰ/ት/ቤቶች እንዲተገብሩ  ጥብቅ መልእክት አስተላልፈው መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል፡፡