Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
አጭር ወግ ለካስ ታምርያለሽ? 😘
ዛሬ ቀኑ ከሌሎች ቀኖች ይልቅ ለእኔ ልዩ ነው…
ሰዓቱ እንኳን በዝምታ እየጓዘ ነው የሚመስለኝ… የልቤ ምት ከወትሮው የተለየ ሆኖብኛል… 💓
ከፍቅር ጋ ሁለተኛ አመታችን ይዘናል 🙏
ያሳለፍነው ፍቅር ሁለት ዓመት ሳይሆን ቀናት ይመስላሉ… ጊዜው ሄዷል…
የኔና የሱ ነገር በቀላሉ የሚነገር ታሪክ አይደለም…
ብቻ ሰዓት እንዳይሄድብኝ በመስታወት ፊት ቆሜ ራሴን ማስዋብ ጀመርኩ…
ቀይ ቀሚሴ አርጌ…
ከንፈሬን ተቀብቼ…
ፀጉሬን ተስተካክዬ…
መስታወት ፊት እራሴን ተመለከትኩ…
ሁሉ ነገሬ በሰውነቴ ላይ ተስማምቶአል… ✨
ከውጭ የማበራ ብቻ አይደለሁም…
ውስጤ በደስታ ተሞልቶአል… 😊
“ዛሬ ይለያል…”
በሩ አጠገብ ቆሜ መጠበቅ ጀመርኩ…
እጄ ስልኬን ይዞ…
ዓይኔ መንገዱን…እያየ
“መጣ? አልመጣ?”...እያልኩ....
ደወልኩለት…
ፍቅር የት ደረስክ?
“እየመጣሁ ነው ፍቅሬ…”
ያ ቃል…ልቤን ሰወረው
“ፍቅሬ…” 💕
ከጥቂት ጊዜ በኋላ…
መኪናው ከፊቴ አቆመና…
ከመኪናው ወረደ…
ወደ እኔ በፍቅር አይኖቹ ተመለከተኝ…
እኔ ግን በዚያ ቅጽበት ራሴን እንኳን ረሳሁ…
“እጅግ ውብ ነሽ…የኔ ፍቅር” አለኝ…
ደስታዬ ልክ አልፎ ፈገግ አልኩለት… 😊
በሩን ከፍቶ ወደ መኪናው አስገባኝ…
መኪናውተነሳ…
ከአንድ ውብ ሆቴል ሲደርስ አቆመው…
ከውጪ ውበቱ ልዩ ነው…
እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ገባን…
የውስጡ ብርሃን እንደ ህልም ነው… ✨
ሙዚቃው እንደ ንፍስ ጆሮን የሚነካ… 🎶
በዝምታ ወደ ውስጤ እየፈሰሰ ነበር…
እጄን ይዞኝ…
ወንበር ስቦ አስቀመጠኝ…
እኔ ደግሞ ዓይኑን እያየሁ ተቀመጥኩ…
በፍቅር ሁለታችንም ቀልጠናል… 💞
ምግብ እየተጎራረስን ከጨረስን በኋላ…
“ትንሽ ቆይቼ እመለሳለሁ…” ብሎ ፍቅር ተነሳ…
እኔ ብቻዬን ቀረሁ…
ነገር ግን ሀሳቦቼ እኔን አልተዉኝም…
ስለ ወደፊታችንን እያሰብኩ…
በዚያን ጊዜ…
ድንገት ወንበሩ ተንቀሳቀሰ…
አንድ ሰው ፍቅር የተነሳበትን ወንበር ስቦ ተቀመጠ…
“አንቺ…” አለኝ…
ከስንት ጊዜ በኋላ የሰማሁት ድምፅ…
ያ ድምፅ…
ያ ያለፈው ታሪኬ…
የበፊት ፍቅረኛዬ…
“ለካስ እንደዚህ ውብ ነሽ ለካ??…”
ሳቅኩ😏😃…
“ምን ፈልገህ መጣህ?”
“እሱ አይመጥንሽም… ይቅርብሽ…”
“ተነሳ!… ይህ ወንበር ሰው አለው…”
“አውቃለሁ… ሲሄድ ጠብቄ ነው የመጣሁት…”
“መልሰሽ አፍቅሪኝ…”
ሀሀሀሀ… 😂
“ምነው ያኔ?”
“አታምሪም ብለህ አልተውከኝም?”
ዝምምም…
“አሁን ውበቴ ታየህ?” 🔥
እየተከራከርን ሳለ—
ፍቅሬ ተመለሰ…
“እንዴ…?” አለ…ደንገጥ ብሎ
እኔ በእርጋታ እያየሀሁት—
“ይሄ ሰው ማለት… ያኔ የተወኝ ነው…”
እሱም ፈገግ አለ…
ድሮም “የጣሉት ነገር… ሲያነሱት ሁሉም ይመኛል…”
እጁን ዘረጋልኝ…
“እኔን ትመርጫለሽ?”ኣ
አዎ… የኔ ውድ ባል… ❤️
እጄን በእጁ ላይ አኖርሁ…
ከዛን ወገቤን አቅፎ…
በሰዎች መሀል አቆመኝ…
ዓይኑ በዓይኔ ላይ ተተከለ…
ከዚያ…
በቀስታ ከንፈሬን በከንፈሮቹ ነካ…
ሳም… 💋
ለአፍታ መሳሳማችን ገተን
ሁለታችንም ወደ ተቀመጠው ሰወዬ እየተመለከትን
“ለሰርጋችን አንዳትቀር እሺ…”
ተሳሳቅን… 😂
ለካስ ታምርያለሽ…😘
=>የኔ ሴት
ወንድ ቢተውሽ… ወንድ ይመጣል…
ማንም ወንድ መጣም ሄደ…
አንቺነትሽ አይቀንስም…
ብቻ ሁሌም ቢሆን
ከሁሉም አስቀድመሽ
እራስሽን ጠብቂ… 😍
@Rufaylen13 💫
✍️ ህላዌ 💕
ዛሬ ቀኑ ከሌሎች ቀኖች ይልቅ ለእኔ ልዩ ነው…
ሰዓቱ እንኳን በዝምታ እየጓዘ ነው የሚመስለኝ… የልቤ ምት ከወትሮው የተለየ ሆኖብኛል… 💓
ከፍቅር ጋ ሁለተኛ አመታችን ይዘናል 🙏
ያሳለፍነው ፍቅር ሁለት ዓመት ሳይሆን ቀናት ይመስላሉ… ጊዜው ሄዷል…
የኔና የሱ ነገር በቀላሉ የሚነገር ታሪክ አይደለም…
ብቻ ሰዓት እንዳይሄድብኝ በመስታወት ፊት ቆሜ ራሴን ማስዋብ ጀመርኩ…
ቀይ ቀሚሴ አርጌ…
ከንፈሬን ተቀብቼ…
ፀጉሬን ተስተካክዬ…
መስታወት ፊት እራሴን ተመለከትኩ…
ሁሉ ነገሬ በሰውነቴ ላይ ተስማምቶአል… ✨
ከውጭ የማበራ ብቻ አይደለሁም…
ውስጤ በደስታ ተሞልቶአል… 😊
“ዛሬ ይለያል…”
በሩ አጠገብ ቆሜ መጠበቅ ጀመርኩ…
እጄ ስልኬን ይዞ…
ዓይኔ መንገዱን…እያየ
“መጣ? አልመጣ?”...እያልኩ....
ደወልኩለት…
ፍቅር የት ደረስክ?
“እየመጣሁ ነው ፍቅሬ…”
ያ ቃል…ልቤን ሰወረው
“ፍቅሬ…” 💕
ከጥቂት ጊዜ በኋላ…
መኪናው ከፊቴ አቆመና…
ከመኪናው ወረደ…
ወደ እኔ በፍቅር አይኖቹ ተመለከተኝ…
እኔ ግን በዚያ ቅጽበት ራሴን እንኳን ረሳሁ…
“እጅግ ውብ ነሽ…የኔ ፍቅር” አለኝ…
ደስታዬ ልክ አልፎ ፈገግ አልኩለት… 😊
በሩን ከፍቶ ወደ መኪናው አስገባኝ…
መኪናውተነሳ…
ከአንድ ውብ ሆቴል ሲደርስ አቆመው…
ከውጪ ውበቱ ልዩ ነው…
እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ገባን…
የውስጡ ብርሃን እንደ ህልም ነው… ✨
ሙዚቃው እንደ ንፍስ ጆሮን የሚነካ… 🎶
በዝምታ ወደ ውስጤ እየፈሰሰ ነበር…
እጄን ይዞኝ…
ወንበር ስቦ አስቀመጠኝ…
እኔ ደግሞ ዓይኑን እያየሁ ተቀመጥኩ…
በፍቅር ሁለታችንም ቀልጠናል… 💞
ምግብ እየተጎራረስን ከጨረስን በኋላ…
“ትንሽ ቆይቼ እመለሳለሁ…” ብሎ ፍቅር ተነሳ…
እኔ ብቻዬን ቀረሁ…
ነገር ግን ሀሳቦቼ እኔን አልተዉኝም…
ስለ ወደፊታችንን እያሰብኩ…
በዚያን ጊዜ…
ድንገት ወንበሩ ተንቀሳቀሰ…
አንድ ሰው ፍቅር የተነሳበትን ወንበር ስቦ ተቀመጠ…
“አንቺ…” አለኝ…
ከስንት ጊዜ በኋላ የሰማሁት ድምፅ…
ያ ድምፅ…
ያ ያለፈው ታሪኬ…
የበፊት ፍቅረኛዬ…
“ለካስ እንደዚህ ውብ ነሽ ለካ??…”
ሳቅኩ😏😃…
“ምን ፈልገህ መጣህ?”
“እሱ አይመጥንሽም… ይቅርብሽ…”
“ተነሳ!… ይህ ወንበር ሰው አለው…”
“አውቃለሁ… ሲሄድ ጠብቄ ነው የመጣሁት…”
“መልሰሽ አፍቅሪኝ…”
ሀሀሀሀ… 😂
“ምነው ያኔ?”
“አታምሪም ብለህ አልተውከኝም?”
ዝምምም…
“አሁን ውበቴ ታየህ?” 🔥
እየተከራከርን ሳለ—
ፍቅሬ ተመለሰ…
“እንዴ…?” አለ…ደንገጥ ብሎ
እኔ በእርጋታ እያየሀሁት—
“ይሄ ሰው ማለት… ያኔ የተወኝ ነው…”
እሱም ፈገግ አለ…
ድሮም “የጣሉት ነገር… ሲያነሱት ሁሉም ይመኛል…”
እጁን ዘረጋልኝ…
“እኔን ትመርጫለሽ?”ኣ
አዎ… የኔ ውድ ባል… ❤️
እጄን በእጁ ላይ አኖርሁ…
ከዛን ወገቤን አቅፎ…
በሰዎች መሀል አቆመኝ…
ዓይኑ በዓይኔ ላይ ተተከለ…
ከዚያ…
በቀስታ ከንፈሬን በከንፈሮቹ ነካ…
ሳም… 💋
ለአፍታ መሳሳማችን ገተን
ሁለታችንም ወደ ተቀመጠው ሰወዬ እየተመለከትን
“ለሰርጋችን አንዳትቀር እሺ…”
ተሳሳቅን… 😂
ለካስ ታምርያለሽ…😘
=>የኔ ሴት
ወንድ ቢተውሽ… ወንድ ይመጣል…
ማንም ወንድ መጣም ሄደ…
አንቺነትሽ አይቀንስም…
ብቻ ሁሌም ቢሆን
ከሁሉም አስቀድመሽ
እራስሽን ጠብቂ… 😍
@Rufaylen13 💫
✍️ ህላዌ 💕
🔥3❤2
Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
🥀ማናት🤔 ማናት🤔 አሏት🥀
.
.
ስሟን በጣታቸው እንዳልታረቁባት
የሕይወትን ምግብ ከጇ እንዳልበሉባት
ለስግደት የሚያደርስ ቢያጥራቸው ትምህርት
ደሞ ማናት እሷ.. አማልጅኝ ምንላት.. ብለው አንቁአሸሹአት
🥹
ማርያምዬ እኮ ናት......
የ እግዚአብሔር ልጅ የእየሱስ እናት....
አጥብታ ያዘለች ምስራቀ ምስራቃት....
ጎንበስ ቀና ብላ የምታማልደን በእግዚአብሔር መንበር ፊት
አረ እሷን አትንኩአት
ማነች እሷ አትበሏት
እመ ብርሃን ነች አምላከ ወላዲት
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ያላት ትልቅ ውበት
እመ ብርሃን ነች...
.. ምዕራገ ፀሎት
በማህፀኗ ያደረ..
... እግዚአብሔር አክብሮአት
ሚካኤል በክንፉ...
....... ደብቆ የከለላት
ሰላም ለኪ ብሎ......
....... ገብርኤል ያከበራት
ፋኑኤል በግርማ...
............ ህብስት የመገባት
ዶኪማስ በምልጃ.......
............. ከጉድ የወጣባት
በላየሰብዕ ሞቶ......
.......... በፅኑ ቃልኪዳን ከሞት የዳነባት
ፈጣሪዋ አክብሮ........
...........ፅዮን ያደረጋት
እሷ አክሊለ ሰማዕታት..
.
.
.
.
ድንግል ማርያም ናት😍🥹🥹🥹
ማናት አትበሏት!!❤🥀
.
.
ስሟን በጣታቸው እንዳልታረቁባት
የሕይወትን ምግብ ከጇ እንዳልበሉባት
ለስግደት የሚያደርስ ቢያጥራቸው ትምህርት
ደሞ ማናት እሷ.. አማልጅኝ ምንላት.. ብለው አንቁአሸሹአት
🥹
ማርያምዬ እኮ ናት......
የ እግዚአብሔር ልጅ የእየሱስ እናት....
አጥብታ ያዘለች ምስራቀ ምስራቃት....
ጎንበስ ቀና ብላ የምታማልደን በእግዚአብሔር መንበር ፊት
አረ እሷን አትንኩአት
ማነች እሷ አትበሏት
እመ ብርሃን ነች አምላከ ወላዲት
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ያላት ትልቅ ውበት
እመ ብርሃን ነች...
.. ምዕራገ ፀሎት
በማህፀኗ ያደረ..
... እግዚአብሔር አክብሮአት
ሚካኤል በክንፉ...
....... ደብቆ የከለላት
ሰላም ለኪ ብሎ......
....... ገብርኤል ያከበራት
ፋኑኤል በግርማ...
............ ህብስት የመገባት
ዶኪማስ በምልጃ.......
............. ከጉድ የወጣባት
በላየሰብዕ ሞቶ......
.......... በፅኑ ቃልኪዳን ከሞት የዳነባት
ፈጣሪዋ አክብሮ........
...........ፅዮን ያደረጋት
እሷ አክሊለ ሰማዕታት..
.
.
.
.
ድንግል ማርያም ናት😍🥹🥹🥹
ማናት አትበሏት!!❤🥀
❤4
Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
#እውነተኛ ገጠመኝ
“አመቱ እንዴት ነበር?”
ይህ ጥያቄ ቀላል ይመስላል… ግን ለአንዳንዶቻችን መልሱ ከልብ የሚወጣ ቁስል ነው።
ከኤልሱ ጋ የቅርብ ጓደኛሞች ነን። በክፍል ውስጥ በፈገግታዋ የምትታወቀው እሷ ነች—ፈገግታዋ እንደ ብርሃን ሁሉን የሚያበራ ነው ሁሌ እንደሳቀች።
👭😅
የሁለታችንም ዕድሜ ተመሳሳይ ስለሆነ መግባባት አልከበደንም።
እኛ ከጓደኛነት በላይ ነን—
እኔም ስለእሷ፣ እሷም ስለኔ የማታውቀው ነገር የለም ።🤗
ከሰሞኑን አንድ ቀን ካፌ ተቀጣጥረን ሻይ እየጠጣን ሳለ፤ ውይይታችን በቀልድና በሳቅ የተሞላ ነበር።😘
በመካከል ግን ድንገት የመጣልኝን ጥያቄ ጠየኳት—
“አመቱ እንዴት ነበር ኤልሱዬ?”
እሷ ፈገግ እያለች።
“አሪፍ ነበር…” አለችኝ።😊
ግን ያ ፈገግታዋ እንደ ንፋስ በአንዴ ደብዘዝ አለ።🥹
“ምነው ኤልሱዬ? አስቀየምኩሽ?” አልኳት ቀስ ብዬ።
“አረ… አንቺ ምን ታስቀይሚኛለሽ…” አለች፤ ድምጿ እየተንቀጠቀጠ፣
“አመቱ ነው እንጂ…”😰
“ምነው አመቱ ምን አረገሽ?” ብዬ ጠየኳት።
ቀስ እያለ እንባ አይኖቿን እየሞሉ—
ቃላቷ እየተቆራረጠ …😪
“አመቱ አመቱማ… የተረገመ ነው…” ።
“እኔንም የረገመ…”
ልቤ ተሰበረ።💔
“ንገሪኝ…” ኤልሱዬ ምን ሆንሽብኝ።
“ተይው…” አትወቂው፣ አለችኝ
(ልቧ እየተጨናነቀ)😫
“አንቺ ምን ታደርጊልኛለሽ…?”
“ንገሪኝ እንጂ…” ምን አጋጥሞሽ፤ ነው? 🤔
ትንሽ ዝም ካለች በኋላ…
ከዚያ በቀስታ ልቧን ከፈተችልኝ—
ይህ አመትማ “ክብሬን… ነጥቆ አርክሶኛል…” ተይው ቁስሌን አታስታውሽኝ😭
“በዚህ አመት…” አይ ይሄ አመትስ፣
“ራሴን ጠብቄ… ስንት አመት ለህልሜ እንዳልኖርኩ…እራሴን ከወንድ ዱካ እንዳልጠበኩ
በአንድ ጨለማ ቀን… ግን ሁሉን ነገሬን ወሰደብኝ…”
በዚህ አመት ተደፍሬያለሁ😭💔
ድምፃዋ ተቋረጠ።
የማውቅሽ ይመስለኝ ነበር ጓደኛሽ የሆንኩ ይመስለኝ ነበር
😭 አንጀቴ አልቻለም ተነስቼ አቀፍኳት።🤗
እሷ በእኔ ላይ ተደፍታ ታለቅሳለች…
እኔም አልቻልኩም—አብሬአት አለቀስኩ።😭
“አመቱ… እየሳቀ፤
እኛን ግን …እያስለቀሰን ነበር''
በፈገግታ ውስጥ የተሸሸገ ህመም ስንት አለ⁈
😭ይህ አመት....ብቻ አለቀ....🙏
@Rufaylen13 💫
✍️ ህላዌ💕
“አመቱ እንዴት ነበር?”
ይህ ጥያቄ ቀላል ይመስላል… ግን ለአንዳንዶቻችን መልሱ ከልብ የሚወጣ ቁስል ነው።
ከኤልሱ ጋ የቅርብ ጓደኛሞች ነን። በክፍል ውስጥ በፈገግታዋ የምትታወቀው እሷ ነች—ፈገግታዋ እንደ ብርሃን ሁሉን የሚያበራ ነው ሁሌ እንደሳቀች።
👭😅
የሁለታችንም ዕድሜ ተመሳሳይ ስለሆነ መግባባት አልከበደንም።
እኛ ከጓደኛነት በላይ ነን—
እኔም ስለእሷ፣ እሷም ስለኔ የማታውቀው ነገር የለም ።🤗
ከሰሞኑን አንድ ቀን ካፌ ተቀጣጥረን ሻይ እየጠጣን ሳለ፤ ውይይታችን በቀልድና በሳቅ የተሞላ ነበር።😘
በመካከል ግን ድንገት የመጣልኝን ጥያቄ ጠየኳት—
“አመቱ እንዴት ነበር ኤልሱዬ?”
እሷ ፈገግ እያለች።
“አሪፍ ነበር…” አለችኝ።😊
ግን ያ ፈገግታዋ እንደ ንፋስ በአንዴ ደብዘዝ አለ።🥹
“ምነው ኤልሱዬ? አስቀየምኩሽ?” አልኳት ቀስ ብዬ።
“አረ… አንቺ ምን ታስቀይሚኛለሽ…” አለች፤ ድምጿ እየተንቀጠቀጠ፣
“አመቱ ነው እንጂ…”😰
“ምነው አመቱ ምን አረገሽ?” ብዬ ጠየኳት።
ቀስ እያለ እንባ አይኖቿን እየሞሉ—
ቃላቷ እየተቆራረጠ …😪
“አመቱ አመቱማ… የተረገመ ነው…” ።
“እኔንም የረገመ…”
ልቤ ተሰበረ።💔
“ንገሪኝ…” ኤልሱዬ ምን ሆንሽብኝ።
“ተይው…” አትወቂው፣ አለችኝ
(ልቧ እየተጨናነቀ)😫
“አንቺ ምን ታደርጊልኛለሽ…?”
“ንገሪኝ እንጂ…” ምን አጋጥሞሽ፤ ነው? 🤔
ትንሽ ዝም ካለች በኋላ…
ከዚያ በቀስታ ልቧን ከፈተችልኝ—
ይህ አመትማ “ክብሬን… ነጥቆ አርክሶኛል…” ተይው ቁስሌን አታስታውሽኝ😭
“በዚህ አመት…” አይ ይሄ አመትስ፣
“ራሴን ጠብቄ… ስንት አመት ለህልሜ እንዳልኖርኩ…እራሴን ከወንድ ዱካ እንዳልጠበኩ
በአንድ ጨለማ ቀን… ግን ሁሉን ነገሬን ወሰደብኝ…”
በዚህ አመት ተደፍሬያለሁ😭💔
ድምፃዋ ተቋረጠ።
የማውቅሽ ይመስለኝ ነበር ጓደኛሽ የሆንኩ ይመስለኝ ነበር
😭 አንጀቴ አልቻለም ተነስቼ አቀፍኳት።🤗
እሷ በእኔ ላይ ተደፍታ ታለቅሳለች…
እኔም አልቻልኩም—አብሬአት አለቀስኩ።😭
“አመቱ… እየሳቀ፤
እኛን ግን …እያስለቀሰን ነበር''
በፈገግታ ውስጥ የተሸሸገ ህመም ስንት አለ⁈
😭ይህ አመት....ብቻ አለቀ....🙏
@Rufaylen13 💫
✍️ ህላዌ💕
ስጋዬን አልመረጥኩ ወይ አልሆንኩ ከነፍሴ
አለምም አልጠላም ወይ አላውቅ ውዳሴ
ደከመኝ ሰለቸኝ ስጋዬም ሳይደላት
መሃል ቤት ሰፍሬ ነፍሴንም ወዮላት::
ነሐሴ 26 2018
✍️𝓣𝓼𝓮𝓰𝓼𝓱
🔥1😢1
Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
አስታራቂ መደብበጣራስር ውለው
ሁለት አባዎራ፣
አንድ ወንበር ቢያገኙ
በእንጨት የተሰራ፣
እኔ ልቅደም እኔ
በማለት ሲጋፉ፣
ቢሰበርባቸው .........
ሁለቱም ተስማምተው
መደብ ላይ አረፉ።🥰1
Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ....
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!
።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።።።።
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም።
ነግሬሽ ነበረ...
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
።።።።
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።
።።።
ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።
።።።
ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!
ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ....
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!
።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።።።።
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም።
ነግሬሽ ነበረ...
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
።።።።
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።
።።።
ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።
።።።
ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!
🔥2
Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
ርእስ?
I can’t find. Drop yours in the comments
...
ዝም ብልስ
ምናለ ባልጠይቅ ምናለ ባልመልስ
አንደበቴን ለጉሜ
በራሴው ምላስ ላይ እኔው ራሴ ቆሜ
ዝም ብል ምናለበት?
ቢለማም ቢከፋም
የሚሰማ እንጂ ‘ሚናገር አልጠፋም...
...እንኳን የሰው ልብ ብሶት ነው መንገዱ
ብሶታል አፈሩ
ብሶታል ሀገሩ
ብሶታል ሴት ወንዱ
አንዲት አቅም አልባ
ሞት ነግሶ በደጇ በሬሳ ተከባ
አለቃቀስ ጠፍቷት ግራ ስትጋባ
መናገርም ያማል
መመልከትም ያማል
አይን እንኳን በአቅሙ ከዘመን ያብራል
መላ ለጠፋበት በእንባ ይለግማል
...
ክፍቱን የተተወ የመቃብር ላንቃ
የጎበዝ እስክሬን ያለ ከፈን ያለ ሳንቃ
ሀዘን ነው ገጠሩ ... ብሶት ነው ከተማው
እግዚኦ ነው ግጥሙ ... እግዚኦ ነው ዜማው
ግዜ ሆድ ብሶታል ... ሁሉም ኮንኖታል
ዝም ብል ምናለ ...
ምን አገኘ ከፋኝ ያለ...
ምላሽ በሌለበት ‘ምጮህ በምን ግዴ
እግዜሩስ ዝም ያለው ከፍቶት ይሆን’ዴ?
።።።።።።።
I can’t find. Drop yours in the comments
...
ዝም ብልስ
ምናለ ባልጠይቅ ምናለ ባልመልስ
አንደበቴን ለጉሜ
በራሴው ምላስ ላይ እኔው ራሴ ቆሜ
ዝም ብል ምናለበት?
ቢለማም ቢከፋም
የሚሰማ እንጂ ‘ሚናገር አልጠፋም...
...እንኳን የሰው ልብ ብሶት ነው መንገዱ
ብሶታል አፈሩ
ብሶታል ሀገሩ
ብሶታል ሴት ወንዱ
አንዲት አቅም አልባ
ሞት ነግሶ በደጇ በሬሳ ተከባ
አለቃቀስ ጠፍቷት ግራ ስትጋባ
መናገርም ያማል
መመልከትም ያማል
አይን እንኳን በአቅሙ ከዘመን ያብራል
መላ ለጠፋበት በእንባ ይለግማል
...
ክፍቱን የተተወ የመቃብር ላንቃ
የጎበዝ እስክሬን ያለ ከፈን ያለ ሳንቃ
ሀዘን ነው ገጠሩ ... ብሶት ነው ከተማው
እግዚኦ ነው ግጥሙ ... እግዚኦ ነው ዜማው
ግዜ ሆድ ብሶታል ... ሁሉም ኮንኖታል
ዝም ብል ምናለ ...
ምን አገኘ ከፋኝ ያለ...
ምላሽ በሌለበት ‘ምጮህ በምን ግዴ
እግዜሩስ ዝም ያለው ከፍቶት ይሆን’ዴ?
።።።።።።።
👏2
Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
የማታ እንጀራ
የማታ እንጀራ ስጠኝ
የጠዋት አታስመርጠኝ
ዘግይተህ በኋላ አስጊጠኝ
ማታ በክብሬ ደብቀኝ
ከሰው በር አንተው አርቀኝ
ጉልበቴ ጽናቱን ይዞ
አቅሜም እንደ አቅሙ ተጉዞ
ያልጠየቁኝን ሳልመልስ
መንገዴን በወግ ልጨርስ
በዓይን እሳት አታስገርፈኝ
ማታ አመሻሹን ደግፈኝ
በጥላ እንዳልበረግግ
በረፋድ እንዳላጣ ጥግ
አልጠብቅ እርጥባን ከሰው
የማታ ምግቤን አርሰው
ሲመሻሽ አታንበርክከኝ
ሲደክመኝ ወንዝ አታሻግረኝ
ሲጨንቀኝ ከእኔ አትራቀኝ
እንደ ንጋቱ ጠብቀኝ
አንገቴ እንዳለ ቀና
የወዳጅ ደጃፍ ሳልጠና
"ዘራፍ!" እንዳልኩኝ ያብቃልኝ
ሲጨልም መንገድ አቅናልኝ
አደራ ! ጌታየ አደራ!
አትንሳኝ የማታ እንጀራ!!!
የማታ እንጀራ ስጠኝ
የጠዋት አታስመርጠኝ
ዘግይተህ በኋላ አስጊጠኝ
ማታ በክብሬ ደብቀኝ
ከሰው በር አንተው አርቀኝ
ጉልበቴ ጽናቱን ይዞ
አቅሜም እንደ አቅሙ ተጉዞ
ያልጠየቁኝን ሳልመልስ
መንገዴን በወግ ልጨርስ
በዓይን እሳት አታስገርፈኝ
ማታ አመሻሹን ደግፈኝ
በጥላ እንዳልበረግግ
በረፋድ እንዳላጣ ጥግ
አልጠብቅ እርጥባን ከሰው
የማታ ምግቤን አርሰው
ሲመሻሽ አታንበርክከኝ
ሲደክመኝ ወንዝ አታሻግረኝ
ሲጨንቀኝ ከእኔ አትራቀኝ
እንደ ንጋቱ ጠብቀኝ
አንገቴ እንዳለ ቀና
የወዳጅ ደጃፍ ሳልጠና
"ዘራፍ!" እንዳልኩኝ ያብቃልኝ
ሲጨልም መንገድ አቅናልኝ
አደራ ! ጌታየ አደራ!
አትንሳኝ የማታ እንጀራ!!!
👏2
Forwarded from 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
እያንዳንዱ ሃብታም ሁሉም ባለፀጋ:
ያለፈ ታሪኩን ሲተርክ ሲያወጋ:
ከትንሿ ነገር ሊስትሮ ከመስራት:
በብዙ ችግሮች ኑሮን እንደመምራት:
በብዙ ሙከራ ለስኬት መድረሱን:
እየደጋገመ ይናገራ እሱን:
ዝቅ ብሎ መስራቱን እኛ መች ጠፋብን፡
ከዛስ የሚለው ነው የተሰወረብን።
ያለፈ ታሪኩን ሲተርክ ሲያወጋ:
ከትንሿ ነገር ሊስትሮ ከመስራት:
በብዙ ችግሮች ኑሮን እንደመምራት:
በብዙ ሙከራ ለስኬት መድረሱን:
እየደጋገመ ይናገራ እሱን:
ዝቅ ብሎ መስራቱን እኛ መች ጠፋብን፡
ከዛስ የሚለው ነው የተሰወረብን።
🔥2