አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
7.82K subscribers
894 photos
402 videos
169 files
2.11K links
قال الإمام مالك ((لايصلح آخر هذه الأمة إلا بماصلح به أولها))
Download Telegram
አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
Photo
በ 3 ጁዝ

አንደኛ የወጣው አቡበክር አህመድ
አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
Photo
በ 5 ጁዝ

አንደኛ የወጣው ሚፍታህ መሀመድ
Forwarded from ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ!
ምርጥ ስጦታ 💎

ምርጥ እና ፅድት ያሉ የሱና ኡስታዞች ቻናል ለማግኘት Add የሚለውን በመጫን ያግኙ 🚀
Forwarded from ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ!
ጥያቄ ተሳተፉ ! 📮

ትክክለኛው መልስ የመለሰ ጠቃሚ ቻናሎችን ያገኛል add  የሚለውን ተጫኑ !


🚀 በቁርኣን ውስጥ ስማቸው በግልጽ የተጠቀሰ ብቸኛዋ ሴት ማን ናቸው?
ቢያንስ ከራሳችን እንማር
~
ሰሞኑን በሱዳንና በየመን ውጥንቅጥ እዚያና እዚህ ቆመው የሚጠዛጠዙ አካላትን እያየሁ ነው። መቼም እንደ ሰለፊያ ደዕዋ የጎንዮሽ ፍትጊያ እና የርስ በርስ መናቆር የበዛበት የለም። ይሄ አሳዛኝ እውነታ በየ ሃገሩ በሰፊው የሚታይ ነው። ጉዳዩ መተራረም ላይ ቢቆም ጥሩ ነበር። መናቆሩ ግን ከዚያ በብዙ ርቀት ያልፋል።

* አንዱ በሌላው ጉዳት፣ በሌላው ህመም፣ በሌላው ሞት እስከሚደሰት ይደርሳል።
* ከሱና ማስወጣት፣ ተብዲዕ መደራረግማ በሰፊው የተንሰራፋ ነው። ከእስልምና ለማስወጣት ዳር ዳር የሚልም አይጠፋም።
* ጉዳዩ በደንብ ስሜት እንደገባበት ከሚያጋልጡ ነጥቦች ውስጥ አንዱ መኮራረፉ ሶላት እስካለመከተል መድረሱ ነው። የባሱ ሰዎችን እየተከተሉ ትናንት አብረዋቸው የነበሩትን ግን በተለያዩ ማግስት ለሶላት እስከመሸሽ የሚደርሱ አሉ። በሱና ስም ስሜት መጋለብ!
* በሰላም ጊዜ ያልተወራ ነውር በተጋጩ ማግስት ይዘከዘካል። (ያው ውንጀላው ውሸትም ሊሆን ይችላል።)

* በሰላም ጊዜ ሲወዳደሱ እንዳልነበር ከግጭት በኋላ "እከሌ ጃሂል ነው" ማለት የተለመደ ነው።
* ንግግርን እየቆለመሙ መወንጀል፣ ያልተባለ መለጠፍ፣ ሰቅጣጭ ስድቦችን መሰዳደብ የተለመደ ነውር ነው።
* በአንድምታ (በላዚም) መክሰስ በስፋት አለ። "ላዚሙል መዝሀብ ለይሰ ቢመዝሀብ" የሚለው ነባር ቃዒዳ ተዘንግቷል።
* ረድ አድርጎ ማለፍ የሚባል አይታወቅም። ነጋ ጠባ መጨቃጨቅ፣ ሰዎችን በዚህ መጥመድ በስፋት የሚታይ ነው። አንዳንዶች የሚጠሉት አካል ጥፋት ላይ ሲወድቅ ለቀደመ የውሃ ቀጠነ ክሳቸው ማሳመኛ አገኘን ብለው ሰርግና ምላሻቸው ይሆናል። በማዘን ፋንታ ይቦርቃሉ። "ተመልሻለሁ" ቢባሉ እንኳ የማይዋጣቸው፣ ደጋግመው በዚያው ክሳቸው የሚቀጥሉ በተጨባጭ አሉ።

* ያለ ገደብ "እነ እከሌ ከኢኽዋን የከፉ ናቸው" እያሉ መወረፍ ጎልቶ ይታያል።
* የራስን ጅህልና ሸፍኖ ወይም የራስን ጃሂል አቅፎ ሌሎችን በጅህልና ማጣጣል ይጎላል።
* ውሸት በጣም በዝቷል። ያውም በሰው ክብር ላይ ለመረማመድ!! በውሸት እከሌ በጥቅም ተገዝቷል፣ እከሌ አክስዮን ገብቷል፣ እከሌ እንዲህ ሆኖ ነው፣ ... ማለት በብዛት አለ።

* የርስ በርስ ጥላቻው እስከ መደባደብ፣ አንዱ ሌላውን ለማጥፋት እስከ መሞከር ይደርሳል። እዚሁ በሃገራችን ውስጥ በስለት የተወጋጉ፣ በዱላ የተደባደቡ፣ በዚህ የተነሳ ወህኒ የገቡ፣ የውሸት ክስ እየለጠፉ ለፖሊስ አሳልፈው የሚሰጡ፣ ፈቃድ ከመንጠቅም በላይ ለባሰ አካል አሳልፈው የሰጡ፣ ... ብዙ አሳፋሪ ተግባሮች አሉ። ትዳር የፈረሰበት፣ ቤተሰብ የተለያየበት ብዙ አሳዛኝ ነገሮች አሉ።

የሚታዩትና የሚደርሱት ብዙ ናቸው። እነዚህን ነገሮች ባላነሳቸው እመርጥ ነበር። የሌሎች መሳቂያ፣ መሳለቂያ መሆን በጣም ያማል። ነገር ግን የአደባባይ ሐቅ ከሆነ በኋላ መመካከሩ እንጂ መሸፋፈኑ ፋይዳ አይኖረውም።

አይናቸው ላይ ባጠለቁት የልዩነት መነፅር በመመልከት የምፅፈውን ሃሳብ በቅንነት የማያዩት፣ አልፎም በሚፈልጉት መልኩ የሚመነዝሩት እንደሚኖሩ ይገባኛል። የችግሩ አንዱ መገለጫም ይሄው ነው። ቢሆንም ዝምታ መፍትሄ አይሆንም። ቢሆንም "ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና" የሌሎችን ውንጀላ በመስጋት ከመመካከር መራቅ አይገባም። "ብልጥ ከሌሎች ይማራል፤ ሞኝ ከራሱ ይማራል" ይባላል። የመጀመሪያውን ብስለት ባለማስተዋል፣ ራስን ባለመቆጣጠር አልፈነዋል። ቢያንስ ከራሳችን ድክመት ብንማር ጥሩ ነው። ከደረሱትና ከሚደርሱት እንማር። በምን መልኩ?

1. ወደራሳችን በጥልቀት እንመልከት። #ራስን_ጥሎ ሁሌ ሌሎችን ማሳደድ ኣኺራን ይጎዳል፣ ቡድንተኝነትን ያወርሳል። የልብ ድርቀትን ያስከትላል።
2. የዑለማኦችን አካሄድ የምንፈልገውን እየመረጥን ሳይሆን ወይም በሌሎች የተመረጠልንን ሳይሆን ከነፍሲያ ወጥተን ከሁሉም አቅጣጫ እንመልከት። ነጠላ ንግግሮቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ አፈፃፀማቸውንም እናጥና። የእውነት እኛ በምናደርገው መጠን ሰው ላይ በማክ * ፈርም ይሁን ተብዲዕ በማድረግ ላይ የተናጠል ፍርድ ለመስጠት ይቸኩላሉ ወይ? በጭራሽ!

3. በምናራምዳቸው እርምጃዎች ላይ የደዕዋችንን መስለሐ በሚገባ እናጢን። ደዕዋችንን የሚያሳጣን፣ መስጂዶቻችንን የሚያስነጥቀን ከሆነ ጩኸታችን ምን ፋይዳ አለው? አካሄዳችን የሰለፊያን ደዕዋ የሚያጠለሽ ከሆነ ወደድንም ጠላንም የጠላትን አጀንዳ እየፈፀምን ነው።
4. ከሱና ዑለማኦች ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ላይ አንገደብ። ይሄ አካሄድ አንዳንዶችን ተ0ሱብና ጉሉው ላይ ሲጥላቸው እያየን ነው። እውነታውን የማያምኑት ችግሩ ስለሸፈናቸው ነው።

5. ተዝኪየተ ነፍስ ላይ እናተኩር። ለችግሩ መስፋት አንዱ ትልቅ ሰበብ የተቅዋ፣ የወረዕ መሳሳት ነው። ሌሎች ላይ ዋሽቶ መክሰስ፣ ሳያረጋግጡ በግምት መወንጀል፣ በጥላቻ ድንበር ማለፍ፣ የራስን ነውር እየደበቁ ሌሎችን መናከስ፣ ... አላህን መፍራት እንደሌለ ወይም እንደሳሳ የሚያጋልጥ ነው። እና እራሳችንን አንርሳ።
6. አቅማችንን እንወቅ። ከቁመታችን በላይ የሆኑ ርእሶችን አናቡካ።

7. ወደ ኢስላም ጠቅልለን እንግባ። አኽላቅም፣ ዙህድም፣ ወረዕም፣ ሲራም፣ ተርጊብና ተርሂብም የኢስላም አካል መሆናቸውን ከምላስ ባለፈ በተግባር እናረጋግጥ። ሰለፎች ከነዚህ ነጥቦች አንፃር የነበሩበትን የላቀ ደረጃ እናጥና።
8. ሰው ተከትለን ገደል እንዳንገባ እንጠንቀቅ። በየመንደሩ የወደድኩትን ውደዱ፣ የጠላሁትን ጥሉ የሚሉ የሹም ዶሮዎች ይኖራሉ። እናስተውል! እነዚህ አካላት አብረውን ቀብር አይገቡም። እጃችንን ይዘው ሲራጥ አያሻግሩንም። እርቃናችንን ብቻችንን ለሒሳብ እንደምንቆም እናስብ። ነገ ከመመርመራችን በፊት ዛሬ ራሳችንን፣ አካሄዳችንን እንመርምር። እናስተውል! ከአንዳንዶች መናከሶች ጀርባ በሱና ስም የሚቀርብ የተዳፈነ የግል ቅሬታ አለ። የአንዳንዶቹ ጉልበት ጭፍን ጭፍራቸው ስለሆነ ገለል በማለት ራሳችንንም እናድን፣ እነሱንም እናስተንፍስ። ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም።

9. የታየ ሁሉ ባደባባይ አይወራም። ጥፋት የመሰለን ነገር ጊዜ ስንወስድ እንዳሰብነው ላይሆን ይችላል። ክፍተትም ቢሆን መናገሩ ችግር የሚያባብስ ከሆነ አያያዛችንን ማጤን ያስፈልጋል።
10. ለሰፊው ህዝብ እንዘን። በመጯጯህ ከሱና፣ ከዒልም፣ ከመስጂድ የምናርቃቸው እንዳይኖሩ ጥንቃቄ እናድርግ።
11. የመንሀጅ ጥንካሬ ብዙ በመጮህ፣ ብዙ በመዝለፍ፣ ሳያጣሩ በግምት በመወንጀል፣ ንግግር እየቆለመሙ በመፈረጅ አይደለም የሚለካው። ስንወድም፣ ስንጠላም፣ ስናወድስም ስንተችም በልክ በሚዛን ሊሆን ይገባል። ይሄ ቁርኣናዊ መርህ ነው።

ማሳሰቢያ፦
የፅሁፌ አላማ ራሴን ከችግሩ ነፃ አድርጌ ሌሎችን መንካት አይደለም። ይልቁንም ሰከን ብሎ በማጤን ለራሳችንም፣ ለወገናችንም፣ ለደዕዋችንም እንዘን፣ ሁላችንም እናስተውል የሚል ነው። አላህ ያለለት ሰው፣ ጎድቶም ተጎድቶም የኋላ ኋላ ሊነቃ ይችላል። በጊዜ ብንነቃ ግን ጉዳት እንቀንሳለን። ደግሞም ሳይመለሱ መሄድም አለ። በሰው ሐቅ ላይ ድንበር መተላለፍ ደግሞ ለመመለስም እንቅፋት ሊሆን ይችላል። አላህ ማስተዋሉን ያድለን።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረጀብ 18/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
قد طال الشوقُ عليّ،
وأثقلَ الغيابُ قلبي…
متى نذهبُ إلى العمرة؟
أطرقُ بابَك بالدعاء،
ولا يفتحُ الطريق.
أبكي شوقًا لبيتِك يا الله،
فالروحُ متعبةٌ من الانتظار،
ولا عزاءَ لها
إلا وعدُك
أنك لا تردُّ قلبًا
تعلّق بك.

ያአላህ

ቤትህን .....አቅርብልን


أخوكم محبكم :أبو أيوب محمد سعيد محمد

https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Forwarded from ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ!
ጥያቄ ተሳተፉ !  📮

ትክክለኛው መልስ የመለሰ ጠቃሚ ቻናሎችን ያገኛል add  የሚለውን ተጫኑ !


🚀
ጥያቄ፦ ታላቁ ነቢይ ኑህ ዐለይሂ ሰላም መርከባቸውን እንዲሰሩ አላህ ባዘዛቸው ጊዜ፣ መርከቧን የሰሩት በምን ቦታ ላይ ነበር ?