BBC Afan Oromo news
4.9K subscribers
92 photos
349 links
BBC afaan oromoo oduu haaraa
Download Telegram
Forwarded from MEREJA TV
#የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ እንዲራዘም ያቀረበችውን ጥያቄ እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡

የተ.መ.ድ የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሀገራትን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የአሜሪካ የማዕቀብ ይራዘምልኝ ጥያቄ ህጋዊነት የሌለው ነው በሚል አለመቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፖምፔዮ በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዳይራዘም የሚያደርጉ ሀገራት ዋጋ ሊከፍሉ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ፖምፔዮ የተመድ አባል ሀገራት ማእቀቡን እንዲራዘም ድጋፍ የሚሰጡ ከሆነ አሜሪካ በኢራን ላይ እጅግ ጥብቅ የሚባል ማእቀብ ትጥላለች ብለዋ#አዲስነገር #Whatsnew\ebs

@ebstvworIdwide
@ebstvworIdwide
#ኢቢኤስ
#EBS
Forwarded from MEREJA TV
#በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ7 ወራት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለመጀምር ትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

መንግስት በትምህርት ቤቶች

👉🏾 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣
👉🏾 የውሃ እና የእጅ ማፅጃ አቅርቦቶችን በማሟላት
👉🏾 ትምህርት ቤቶችን የማፅዳት ስራዎችን በማከናወን መደበኛ ትምህርት እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ተማሪዎች እንደየ ደረጃው ወደ ክፍል ገብተው ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ የገለፁ ሲሆን ትምህርት ሲጀመርም በአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚጀመር መሆኑን እና በቀጣይም ሌሎች የትምህርት ክፍሎች ወደ መደበኛ ትምህርቱ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs

@ebstvworIdwide
@ebstvworIdwide
#ኢቢኤስ
#EBS