አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ
9.96K subscribers
1.93K photos
123 videos
15 files
945 links
ለአስተያየት ለጥያቄ በግል ለማውራት @abigezenige ይህን ይጠቀሙ።

ሐምሌ 27/11 ዓ᎐ም
Download Telegram
እንደማታሳፍሩኝ ተስፋ አደርጋለሁ
@abizeeotc ስም አንድ ታሪክ እንሰራለን። አሻራችንን እናሳርፋለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000 145 090 176
ስልክ +251933143133
አስራት በኩራት፥ ስጦታ፥ አጥር ማሰሪያ አሁን እያገለገልኩበት በሚገኘው በደብረ ጸሐይ መድኃኔዓለም ወቅድስት አርሴማና ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በዚህ ገፅ በኩል መስጠት ትችላላችሁ።
ነገ በፌስቡክ live ገብቼ ስለ ቤ/ክኑ እናወራለን፥ ቃል ምትገቡና የምትለግሱ ሰዎችን በቀጥታ እንወያያለን። አጥሩንማ እንሰራዋለን።
https://youtu.be/2SFPn6x6mqw
ኃጢአት መሥራት በራሱ አስቀያሚ ነው፤ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዚያ ኃጢአት መታበይ ግን እጅግ ጽኑ ደዌ ነው፡፡ ጽድቅን ሠርተው በዚያ በሠሩት ጽድቅ ከተኩራሩበት ጽድቁን ያጡታል፡፡ ይህ በኃጢአት ሲኾን ደግሞ የባሰ ነው፤ ወደ ከፋ ጥፋት ይወስደናልና፡፡ ከሠራነው ኃጢአት ይልቅ በሠራነው ኃጢአት መታበይ የሚያመጣው ፍዳ ኵነኔ እጅግ ጽኑ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
1, ቅዱስ ቁርባንን በምንቀበልበት ጊዜ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
2, ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኋላ ምን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል?
3, ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ እና ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት ምንድነው?
share comment like copy

ቅዱስ ቁርባንን በምንቀበልበት ጊዜ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
ጌታችን በቃሉ እንዳስተማረን ቅዱስ ቁርባን ደካማ ስጋችን በእግዚአብሔር ፀጋ ከብሮ የሚኖርበት ድንቅ ምሥጢር ነው፡፡ በኃጢአት የደከመ ሰውነታችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሆን፣ የክርስቶስን ሥጋና ደም ለመቀበል በንስሐ መታጠብ አለበት፡፡ ንስሐውም እንደ ሮማዊው መቶ አለቃ ፍፁም ራስን ዝቅ በማድረግ፣ በትህትና የሚፈጸም መሆን አለበት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቅፍርናፎም በገባ ጊዜ አንድ መቶ አለቃ ቀርቦ ልጁን እንዲያድንለት ለመነው፤ ጌታችን ወደ መቶ አለቃው ቤት ሄዶ ልጁን እንደሚፈውስለት በነገረው ሰዓት ትሁት፣ ተነሣሂ ልቦና ነበረው መቶ አለቃ “አቤቱ! አንተ ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፡፡” (ማቴ. 8፡8) በማለቱ ጌታችን አመስግኖታል፡፡ እኛም የከበረ የክርስቶስ አካል ቤት በተባለ ሰውነታችን በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት እንደሚገባ ሲነገረን እንደ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በትዕቢት ሳይሆን እንደ መቶ አለቃው በትህትና፣ ኃጢአታችንን በመናዘዝ “አቤቱ! አንተ በእኔ በኃጢአት በከረሰ ሰውነት ልታድር አይገባህም፣ እንደ ቸርነትን አንጻኝ፣ ቀድሰኝ” ልንል ይገባል፡፡ ለዚህም እንዲረዳን በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶቻችን ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ የሚጸለዩ ልቦናን ከምድራዊ ሀሳብ ከፍ የሚያደርጉ፣ ትምህርተ ሃይማኖትን የጠነቀቁ ጸሎቶችን አዘጋጅተውልናል፡፡
ስለሆነም የሚቆርቡ ምዕመናን ከመቁረባቸው በፊት የሚጸለየውን ጸሎት ይጸልዩ ዘንድ ይገባል፡፡ ቅዱስ ቁርባንን ካህናት፣ ሕጻናት፣ ደናግል፣ ሕዝባዊያንና ምዕመናን ቤተክርስቲያን የሠራችላቸውን ቅደም ተከተል ጠብቀው ይቆርባሉ፡፡ ሥጋውን ካህኑ በእጁ ሲያቀብል ደሙን ንፍቅ ካህኑ በዕርፈ መስቀል ለካህናት እንዲሁም ዲያቆኑ ለምዕመናን በዕርፈ መስቀል ያቀብላል፡፡ ንፍቅ ካህን ሥጋውን አያቀብልም፡፡ ንፍቅ ዲያቆንም ደሙን ለማቀበል አይችልም፡፡ የአቆራረብ ቅደም ተከተላቸውም ቅድሚያ በመቅደስ ውስጥ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት፣ ቆሞሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት ሲቆርቡ በቅድስት ደግሞ የሚጠቡ ሕጻናት፣ ወንድ ልጆች፣ ሴቶች ልጆች፣ አዋቂ ወንዶችና አዋቂ ሴቶች ይቆርባሉ፡፡ በመጨረሻም ማየ መቁርር (የቅዳሴ ጠበል) ቅዱስ ቁርባንን ለተቀበሉ ወዲያውኑ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም ከቁርባን በኋላ የሚጸለየውን ጸሎት ይጸልያሉ፡፡

ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኋላ ምን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል?
ቅድስት ቤተክርስቲያን የሰርግ ቤት ትባላለች፡፡ በሰርግ ቤት የሙሽራና የሙሽሪት ተዋሕዶ (አንድነት) እንደሚፈጸም በቅድስት ቤተክርስቲያንም የሙሽራው የክርስቶስና የሙሽራይቱ የቤተክርስቲያን ተዋሕዶ (አንድነት) ይነገርባታል፣ ይፈጸምባታል፡፡ (ኤፌ. 5፡21-33) የሰው ልጅ በልማዱ ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ ራሱን ባማረ ልብስ ያስውባል (ታስውባለች)፡፡ በተለይም ደግሞ ወደ ሰርግ ቤት የተጠራ እንደሆነ ልዩና ያማረ ሰርግ ልብስ መልበስ ይገባል፡፡ በወንጌል ትርጓሜ የሰርግ ቤት የተባለች ቅድስት ቤተክርስቲያን ነች፡፡ የሰርጉ ማዕድም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ፣ ክቡር ደም ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል እንዳስተማረ ሙሽራው ባለበት የሰርግ ቤት የሰርግ ልብስ ሳይለብሱ በአልባሌ አለባበስ መገኘት ያስወቅሳል፣ ያስቀጣል፡፡ (ማቴ. 22፡11-13)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲህ የክርስቶስን አካል ወስዳችሁ የአመንዝራ አካል ታደርጉታላችሁን? አይገባም፡፡” (1ኛ ቆሮ. 6፡15) እንዳለ የክርስቲያን ሰውነት በክርስቶስ ሥጋና ደም የከበረ ነውና ሁልጊዜም በንጽሕና፣ ከኃጢአት በመራቅ መጠበቅ አለበት፡፡ በተለይም በቅዱስ ቁርባን ከክርስቶስ ጋር በምንዋሐድባቸው ዕለታት ከሌሎች ጊዜያት በበለጠ ጥንቃቄ ራሳችንን ከኃጢአት ልንጠብቅ ይገባል፡፡ ይህም ባሏን የምትጠብቅ ንጽሕት ሙሽራን ይመስላል፡፡ አንዲት ሴት ምንጊዜም ራሷን በንጽሕና መጠበቅ እንዳለባት ቢታወቅም ባሏን ለተዋሕዶ በምትጠብቅበት ዕለት ግን በተለየ ሁኔታ ራሷን ትጠብቃለች፡፡ እኛም ራሳችንን የክርስቶስ ሙሽራ አድርገን በንስሐ ተጸጽተን ሥጋውን ከበላን ደሙን ከጠጣን በኋላ ልናደርጋቸው የሚገቡንን ጥንቃቄዎች የክርስቶስ አካል ቅድስት ቤተክርስቲያን ደንግጋልናለች፡፡
በፍርድ በሙግት ጠብና ክርክር አይታጣምና ከዚያ ለመራቅ ከቆረቡ በኋላ በዚያው ዕለት ወደ ፍርድ ቤት መሄድና መሟገት ክልክል ነው፡፡ ከመንፈሳዊ ሀሳብ ይልቅ ለስጋዊ ደስታ የተመቸ ነውና በዚሁ ዕለት ለባለትዳሮች ሩካቤ፣ አብዝቶ መብላትና መጠጣት አየይገበባመም፡፡ ጥፍር መቁረጥ፣ ጸጉር መላጨት፣ በውኃ መታጠብና ከልብስ መራቆት ክልክል ነው፡፡ ግብፃውያን ክርስቲያኖች በቆረቡበት ዕለት በባዶ እግር አይሄዱም፡፡ እንቅፋት እንዳያገኛቸውና እግራቸው እንዳይደማ ነው፡፡ እንዲሁም ከቁርባን በኋላ የጸሎት መጻሕፍትን ያነባሉ፡፡ ተረፈ ዕለቱንም ከሰዎች ጋር ባለመገናኘት፣ በሰላምና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያሳልፋሉ፡፡
ከቆረቡ በኋላ በተለይም ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ እንቅፋት (መሰናክል) እክል ቢያጋጥመን ለምሳሌ. ነስር፣ እንቅፋት፣ ትውከት፣ ወደ አፍ የሚገባ ትንኝ፣ ዝንብ… ቢያጋጥመን፤ ንስሃ ልንገባና ያጋጠሙንን እክሎች በሙሉ ለካህን (ለንስሃ አባታችን) ልንናገር ይገባል፡፡የተሰጠንን ንስሃም ሳንፈጽም ዳግም መቁረብ አይፈቀድም (አይገባም)፡፡ ሩቅ መንገድ መሔድ፣ መስገድ፣ አይገባም፡፡ ይህም ምስጢሩ በሥጋ ወደሙ ድካም የለበትምና፡፡ አንድም በመንግስተ ሰማይ ከገቡ በኋላ ድካም የለምና አንድም ድኀነት በሥጋና በደሙ ሳይሆን በትሩፋት ነው እንዳያሰኝ ነው፡፡

ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ እና ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት

ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ ከቅዱስ ምሥጢር የሚቀበሉ ሁሉ እንዲህ ይበሉ፤

አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ርኵስት ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም።
እኔ አሳዝኜሃለሁና በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና ሥራም ምንም ምን የለኝምና። ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፣ ስለ ክቡር መስቀልህም፣ ማሕየዊት ስለ ምትሆን ስለ ሞትህ፣ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ፣ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁም።
የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልኩ ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ።
የዓለም ሕይወት ሆይ! በእርሱ የኃጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ። በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም፣ በመጥምቁ በዮሐንስም አማላጅነት፣ ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም፣ በሰማዕታትና፣ ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።
1👍1
ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ በአፍ ሳለ ሁሉም እያንዳንዱ እንዲህ ይበል፤
“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሥሉስ ዘኢይትነገር ሀበኒ ከመ እንሣእ ለሕይወት ዘንተ ሥጋ ወደመ ዘእንበለ ኲነኔ ሀበኒ እግበር ፍሬ ዘያሠምረከ ከመ አስተርኢ በስብሐቲከ ወእሕየው ለከ እንዘ እገብር ዘዚአከ ፈቃደ በተአምኖ እጼውዐከ አበ ወእጼውዕ መንግሥተከ ይትቀደስ እግዚኦ ስምከ በላዕሌነ፣ እስመ ኃያል አንተ እኵት ወስቡሕ ወለከ ስብሃት ለዓለመ ዓለም”
ትርጉሙ፦ የማይነገር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሦስት የምትሆን ይህን ሥጋና ደም ሕይወት ሊሆነኝ ሳይፈረድብኝ እቀበል ዘንድ ስጠኝ። በጌትነትህ እንድገለጽ ደስ የሚያሰኝህን ፍሬ እሰራ ዘንድ ስጠኝ የአንተንም ፈቃድ እየሰራሁ እኖርልህ ዘንድ ስጠኝ። በማመን አባት ብዬ እጠራሃለሁ መንግሥትህንም እጠራለሁ። አቤቱ ስምህ በእኛ ላይ ይመስገን ምስጉን ክቡር የምትሆን ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘላለሙ!
የቤተክርስቲያን አጥር እንስራ
አካውንት ቁጥር 1000 145 090 176
ስልክ +251933143133
😁1
እንኳን አደረሳችሁ ኑ ወደ YouTube
https://youtu.be/MCYLuhGghqU
ያለማጋነን በቀን ቢያንስ 10 ሰው ስለ መምህር ግርማ ይጠይቁኛል።
እኔ ያለኝ መረጃ
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ከጌታችን ጾም በኋላ ሁለተኛው የኮሮና መግባት ምክንያት በማድረግ ሰዎች እንዳይሰበሰቡ ስለተወሰነ ከዚያን ጊዜ በኋላ አገልግሎት መስጠት አቁመዋል። ስለዚህ አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ ቅድሚያ ከዚህ ገፅ ታገኛላችሁ።
በአስማት በቤተሰብ ጣጣ በዝሙት በመተት በጥንቆላ በአጋንንት አሰራር እየተሰቃያችሁ ያላችሁ ልዑል እግዚአብሔር ይፈውሳችሁ፥ አባታችንም ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን። አሜን።
የጌታችንና የእመቤታችን ምሥጢረ ትንሣኤ
በቅዱስ መጽሐፍ ሲነጻጸር
ከአባ ሳሙኤል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ
አዲስ አበባ
እግዚአብሔር ሰውን አክብሮና አልቆ በመልኩ በምሳሌው ፈጠረው፡፡ ሰው ግን እግዚአብሔር ባስቀመጠው የክብር ሥፍራ አልተገኘምና ተዋረደ፡፡ ከኃጢአቱም የተነሣ ደሃ ሆኗልና ሰው ሆኖ መፈጠር /መወለድ/ የምሬት ርእስ ሆነ፡፡
ሁሉን አይቶ ሁሉን ማጣት የሰው ልጅ የማይለምደው የኑሮ ጥቁር መልኩ ነው፡፡ ሁሉን ያጣ ሁሉን ሲያገኝ የዕድገት ሕግ ያለው፣ የሚናፈቅ ደስታና ሊተርኩት የሚያስቸኩል የኑሮ ገድል ነው፡፡ ሁሉን አይቶ ሁሉን ማጣት ግን የሚያንደረድር የቁልቁለት ጉዞ፣ ጉልበትን እያዛለ ከዕይታ የሚሠውር፣ ልታይ ልታይ ያለውን ሰብእና ደብቁኝ የሚያሰኝ፣ የማይለምዱትና የማይደፍሩት ሥፍራ ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ ሀብት ጨብጣችሁ አግኝቶ እንደማያውቅ ብትቸገሩ ሌሊቱን ያመጣ ቀኑን ያመጣልና በርቱ፡፡ ሀብት በማጣታችሁ ስትበሳጩ ሀብት የማያመጣውን ጤና እንደምታጡ አስቡ፡፡ ወልዳችሁ ሞት ልጆቻችሁን ነጥቋችሁ ከሆነ ማዳን ብቻ ሳይሆን መግደልም የእግዚአብሔር ሥልጣን እንደሆነ በመረዳት ከከንቱ አእምሮ ራቁ፡፡ ሊነጋ የጨለመ እንጂ ጨልሞ ሊቀር የመሸ ሌሊት ስለሌለ በእምነታችሁ ጽኑ! ጌታችን ድል ለነሡ ሽልማት የሚሰጥ ንጉሥ ብቻ ሳይሆን ለወደቁትም ትንሣኤ የሚሆን አምላክ ነውና፡፡
በሥነ ፍጥረት ተመራማሪነቱ የሚደነቅ አንድ የሥነ ሕይወት ሊቅ በባሕር ዳርቻ ዳክዬዎችን እያየ ይመሰጥ ነበር፡፡ ሁል ጊዜ የሚያያቸው እነዚህ ዳክዬዎች በሽታ ገባባቸውና ማለቅ ጀመሩ፡፡ እርሱም መድኃኒት ነበረውና ለማዳን ሲቀርባቸው ይሸሹታል፡፡ ከዚህም የተነሣ ዓይኑ እያየ፣ መድኃኒቱንም በእጁ እንደጨበጠ ዳክዬዎቹ በሙሉ አለቁ፡፡ በዚህን ጊዜ ታዲያ ‹‹ዳክዬ ብሆን ዳክዬዎቹን አድናቸው ነበር›› ብሎ ቁጭቱን ተናገረ ይባላል፡፡
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰው ባልሆንኩ ለሚሉት የሰውነትን ዋጋ ሊገልጥ፣ ሰው የለኝም ለሚሉት ጥሩ ሰዋቸው ሊሆን፣ ሰው በሆንኩ ለሚሉትም ሰው ሊያደርጋቸው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ፣ ሰውነታችንን ተዋሕዶ ሰው ሆነ፡፡ ‹‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡ . . . ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ›› እንዲል ዮሐ.1÷1፡፡
ይኸውም እኛን ከሞት አድኖ የሕይወትን ትንሣኤ ሊሰጠን ነው፡፡ ከጌታችን ሰው መሆን በፊት የነበሩ ጻድቃን ሰዎች ቢኖሩም ከጠባያቸው ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮአቸውም በውርስ ኃጢአት ስለተያዙ /ከእመቤታችን ከቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም ከተወለደው መድኅን ክርስቶስ በቀር/ እኛን ሊያድኑን አልቻሉም ነበርና፡፡ ሊቁ አቡሊደስ ‹‹ከሰው ወገን ማንም ሞትን ያጠፋ ዘንድ፣ ትንሣኤንም ይገልጣት ዘንድ አይችልም፤ ዳዊት በሕያውነት የሚኖር፣ ሞትንም የማያያት ሰው ማነው? ነፍሱን ከሲዖል ሥጋውን ከመቃብር የሚያድን ማን ነው? ብሎ እንደተናገረ መዝ.8÷8፡፡
ራሱን ማዳን ያልቻለው ሌላውን ማዳን እንደምን ይችላል? አንድ ራሱን ሊያድን ያልቻለስ ዓለምን ሁሉ ሊያድን እንደምን ይችላል? ኃጢአት በሰው አድሮ ይኖር ነበርና፤ ሞትም ይከተለው ነበርና/መዝ.8÷9/ ብሏል /ሃይ.አበው ገጽ 145/፡፡
የሠለጠነው ዓለም እንኳ ሰውን በቤተ ሙከራ ለመፍጠር ሲያስብ የሞት ማስወገጃን ለመሥራት ግን ዕቅድ እንኳን የለውም፡፡ ለምን? ቢባል የንጉሡም የምሁሩም አእምሮ ሞትን የሚገዛ ሳይሆን ለሞት የተገዛ ነውና፡፡ ሞት ሁለት ዓይነት መልክ አለው፡፡ ይኸውም የነፍስ ከሥጋ መለየትና የነፍስ ከእግዚአብሔር አንድነት መለየት የሚሉት ናቸው፡፡ የሰው ትልቁ ሞት ሕይወት ከሆነው ከእግዚአብሔር አንድነት መለየቱ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወተ ሥጋ ያሉትን ኃጢአተኞች ‹‹ሙታን›› በማለት የሚጠራቸው ለዚህ ነው /ኤፌ.2÷1/፡፡ መንፈሱ የሞተ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን አንድነት ያፈረሰ በመሆኑ የባከነ ሕይወት ይኖራል፡፡ ነፍሱ ከሥጋው ስትለይም ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ፊት በእሳት ባሕር ይጣላል፡፡ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ አምነው በሕግ በአምልኮ እርሱን የተከተለ፣ በክርስቲያናዊ ምግባር እርሱን የመሰለ ግን ይህ የሞት ኃይል በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ተጽፎ እንደምናገኘው ሞት ለብዙ ዘመናት ኤልያስን አሳዶት ነበርና ሞትን ከለመኑት መካከል አንዱ ነው፡፡ 2ኛ ነገ.4÷35፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ኤልያስ ሞትን አቅም አሳጥቶታል 1ኛ ነገ.17÷22፡፡
በሐዲስ ኪዳንም እግዚአብሔር መንግሥቱን በማስፋፋት ውስጥ ትልቅ ድርሻ (ሓላፊነትን) የተጣለባቸው እነ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስም በተሰጣቸው የጸጋ ሥልጣን በሞት ላይ መራመድና ሙታንን ማስነሣት ችለዋል ሐዋ.5÷1-11፣9÷40፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር አምላክ በጸጋ ያደረባቸው ቅዱሳን ተአምር እና ይህን ያህል ድንቅ ነገር ካደረጉ በማይወሰነው ፍጹም አካሉ እርሱ ባወቀው ድንቅ ጥበቡ ያደረባት እመቤታችንማ ተአምሯ እንዴት ከዚህ አይልቅ?
የእርሷ ሞትና ትንሣኤ ከልጅዋ ሞትና ትንሣኤ ጋር ይነጻጸራል ቢባልስ ምን ይደንቃል? ዳሩ ግን በዕውቀት /በመረጃ/ ያልታገዘ እምነት ጠቀሜታው አመርቂ አይደለምና የጌታችንና የእመቤታችን ምሥጢረ ትንሣኤ ሲነጻጸር /የሚመሳሰልበትንና የማይመሳሰልበትን ምክንያት/ በጥቂቱ እንዳስሳለን፡፡ እመብርሃን ምሥጢሩን ትግለጥልን፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሥድሳ አራት ዓመቷ በእግዚአብሔር ፈቃድ ጥር ሃያ አንድ ቀን ዐርፋለች፡፡ ሐዋርያትም ሥጋዋን ገንዘው ተሸክመው ሊቀብሩ ሲወስዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ልጇን ከመቃብር ሰርቀው ወስደው ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ ያውኩናል፤ ዛሬ ደግሞ እናቱን ተነሣች፣ ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን? ብለው ሥጋዋን ለማቃጠል ወሰኑ፡፡ ከዚያም ታውፋንያ የሚባለውን ሰው ከመካከላቸው መርጠው ‹‹አንተ ሂድና ሥጋዋን ከመሬት ላይ ጣለው፣ እኛም ወስደን እናቃጥለዋለን›› ብለው ላኩት፡፡ እርሱም ተደፋፍሮ ሥጋዋን ከመሬት ላይ ለመጣል አጎበሩን ሲጨብጥ የእግዚአብሔር መልአክ ተቆጥቶ ሁለት እጁን ቆርጦታል፡፡ ወዲያው የእመቤታችንን ሥጋ ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ቅዱሳን መላእክት እየዘመሩ ወደገነት አሳርገውታል፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያትም ዮሐንስ ያየውን ምሥጢር ለእነርሱም እንዲያሳያቸው ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምረው ጾም፣ ጸሎት ለማድረግ ሱባኤ ያዙ፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከሐዋርያት በወረሰችው ትውፊት መሠረት ለጾመ ፍልሰታ ሥርዓት ሠርታ፣ ከሰባቱ አጽዋማት ተርታ አስገብታ ይህን ታላቅ የበረከትና የምሥጢር መገለጫ ጾም ትጾማለች፡፡ ልክ እንደ ሐዋርያቱ የእመቤታችንን ምሥጢረ ትንሣኤና ዕርገት ይገለጥላቸው ዘንድ በመሻት ሕፃናት፣ ጎልማሶችና አረጋውያን በመንፈሳዊ መነቃቃት ሱባኤ ይገባሉ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ጾማቸውን በጀመሩ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ ከገነት አምጥቶ ሰጥቷቸዋል፡፡