ABELA TECH
8.05K subscribers
1.07K photos
47 videos
170 files
980 links
📌 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 📌

✏️ በOnline ገንዘብ ማግኛ ዘዴዎች
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ የWebsite ጥቆማዎች
✏️ ምርጥ ምርጥ የሚባሉ አፖች
✏️ እና ሌሎችንም ያገኛሉ።

➤ TikTok Account: https://tiktok.com/@abela_tech

For Cross👉 @Abel_user
For Questions👉 @Abela_TechGroup
Download Telegram
✳️ኤርባስ A380 ሱፐርጃምቦ የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ ተጠቅሞ በረራ ያደረገው አውሮፕላን❗️

🔺የዓለማችን ግዙፉ አውሮፕላን “ኤርባስ A380 ሱፐርጁምቦ” በፈረንሳይ ቱሉዝ እና ኒስ ከተሞች መካከል የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ በመጠቀም የተሳካ የሶስት ሰዓት በረራ ማድረጉ ተገለፀ።

🔺ኤርባስ A380 ሱፐርጁምቦ አውሮፕላን መቶ በመቶ የምግብ ማብሰያ ዘይት ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ በረራ ሲያደርግ የመጀመሪያ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች የኤርባስ ስሪት አውሮፕላኖች ግን ባሳለፍነው ዓመት 3 የተሳካ በረራ አድርገዋል።

🔺የካርበን ልቀትን በ80 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የምግብ ዘይት ነዳጅ፤ ጥቅም ላይ ከዋለ የምግብ ዘይት፣ ከስብ እንዲሁም ለምግብነት ከማይውሉ ሰብሎች የሚሰራ ነው ተብሏል።

🔺ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ የተባለው ዘይት የካርበን ልቀትን በመቀነስ ረገድ 65 በመቶ ሚና ይኖረዋል ብሏል። በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በ2050 የካርበን ልቀትን ወደ ዜሮ ለማምጣት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እንደሚረዳም ማህበሩ አስታውቋል።

🔺እንደ ኤርባስ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ሁሉም አውሮፕላኖቹ እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ ማለትም መደበኛውን ነዳጅ ከኬሮሲን ጋር ቀላቅለው ለመብረር የሚያስችላቸው የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።
#Tech_News #Airplane