ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከአሁን 233 ቢልዮን ብር ወጪ ተደርጓል
+++++++++++++++++
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 233 ቢልዮን ብር ወጪ መደረጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት የኮሙኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደተናገሩት፤ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ በአጠቃለይ 233 ቢልዮን ብር ወጪ ተደርጓል።
ከዚህ ውስጥ 223 ቢልዮን ወይም 91 በመቶ የሚሆነው ወጪ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።
ከመላው ኢትዮጵያዊያን በቦንድ ግዢ 18 ነጥብ 9 ቢልዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፤ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን 1 ነጥብ 6 ቢልዮን ብር መሰብሰቡን አብራርተዋል። በተጨማሪም 3 ነጥብ 2 ቢልዮን ብር በስጦታ የተገኘ መሆኑን አንስተዋል።
የግድቡ ግንባታ እውን መሆን በዓባይ ላይ የነበረውን የቅኝ ግዛት ውል ከማፍረሱም በላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፍላጎት የጥቅም ማረጋገጫ አብነት ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል።
በግንባታው ወቅት የነበሩ የፋይናንስና የዲፕሎማሲ ጫናዎችን ተቋቁሞ በራስ አቅም የመልማት ዕድልን መወሰን የተቻለበት እንደሆነ ጠቁመዋል።
ለግድቡ ግንባታ እውን መሆን መላው ኢትዮጵያውያን በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው ብሎም ባላቸው ነገር ሁሉ ተረባርበው የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል::
https://t.me/abbaytv2015

❤12
አስቸኳይ መመሪያ:
በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ::
የጤና ሚኒስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ጥብቅ ደንቦችን አውጥተዋል! ማወቅ ያለብዎትን ቁልፍ መረጃዎች ይመልከቱ።
አዲስ አበባ - (ህዳር 12/2018 ዓ.ም.) በቅርቡ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ የተዘገበውን የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር የጤና ሚኒስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) አዲስ መመሪያዎችን አስተላልፈዋል።
በሽታው በንክኪ በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ፣ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ከዚህ በታች በተጠቀሰው መሰረት በጥብቅ ይያዛል ተብሏል:
1. ለቤተሰብ አይሰጥም:
የቫይረሱ ሰለባ የሆኑ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም።
2. አይታጠብም:
አስከሬኑ መታጠብ (ማላሸት) አይፈቀድም።
3. ደህንነቱ የተጠበቀ ቀብር:
አስከሬኑ በጤና ባለሙያዎች ክትትል በተጠበቀ መንገድ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ይፈጸማል።
4. የቀብር ቦታ ጥበቃ:
ቀብር የተፈጸመባቸው ቦታዎች ተጨማሪ ስርጭት እንዳይኖር በጥንቃቄ መመራት እና መጠበቅ አለባቸው።
5. የማህበረሰብ ትብብር:
ማህበረሰቡ የበሽታውን አሳሳቢነት ተረድቶ ይህንን አስቸጋሪ ውሳኔ መቀበል እና መተባበር እንዳለበት ጥሪ ቀርቧል።
ስለ ማርበርግ ቫይረስ ቁልፍ መረጃዎች:-
1. የመተላለፊያ መንገድ በንክኪ (ከሕመምተኛ ሰውነት ፈሳሾች ጋር ንክኪ ሲፈጠር)
2. የተሳሳተ ግንዛቤ
እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር አይተላለፍም!
3. የሞት ምጣኔ
ከ24% እስከ 88% ድረስ ይደርሳል (ከኮቪድ እጅግ የከፋ ነው)
4. ከህመም በኋላ :
ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ እስከ አንድ ዓመት ሊቆይ ይችላል።
5. ለዳኑ ሰዎች ማስጠንቀቂያ
ከህመሙ ያገገሙ ወንዶች ለአንድ አመት ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከመፈጸም መቆጠብ አለባቸው።
6. ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው ከቫይረሱ የፀዳ ከሆነ በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም።
የወቅቱ ስታቲስቲክስ
* የተመረመሩ ሰዎች: 33
* በሽታው የተገኘባቸው (Confirmed Cases): 6 ሰዎች
* በሽታው ህይወታቸውን የቀጠፋቸው: 3 ሰዎች
* በህክምና ላይ ያሉ (በህይወት ያሉት): 3 ሰዎች
ይህ መረጃ ይፋ የሆነው የጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለሚዲያ ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ነው።
ለጤንነትዎ ሲባል ይህንን ጠቃሚ መረጃ ያጋሩ!
Via Ethio Fm
🌴🌴🌴

Telegram
Abbay TV ዓባይ ቲቪ
የኢትዮጵያ ምርጥ
❤1
ዶክተር አንዷለም ዳኜ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ::
ተከሳሽ እሱባለው (ሳሙኤል) ነበረ የተባለው ግለሰብ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡00 – 2፡00 በሆነ ሰዓት ባሕርዳር ከተማ ሰባታሚት ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ የጦር መሳሪያ ይዞ ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በሰዓቱ ከባሕርዳር ከተማ ወደ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሄድ የነበረውን ዶክተር አንዷለም ዳኜን የያዘውን ንብረት ለመውሰድ እንዲመቻቸው በማሰብ ያሽከረክር የነበረውን መኪና እንዲያቆም ሲጠይቁት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሁለት ጥይት በመተኮስ ዶ/ር አንዷለም ዳኜን ደረቱን እና ክንዱን በመምታት ገድለውታል።
ስለሆነም ተከሳሹ እሱባለው (ሳሙኤል) ነበረ በፈጸመው የከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ ወይም በአማራጭ የመግደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል የመጀመሪያ ክስ ተከሷል።
በተመሳሳይ ጊዜ እና ቦታ ላይ ወደ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሄድ የነበረው ዶ/ር በረከት አማረ ላይ ሁለት ጥይት በመተኮስ የመኪናውን ቦዲ በመምታት ተበዳዩን የሳተው በመሆኑ በፈጸመው ከባድ የሆነ ሰው መግደል ሙከራ ወንጀል የሚል ሁለተኛ ክስ ተከሷል።
እንዲሁም በሶስተኛ ክስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23(3) ላይ የተመለከተውን ተላልፎ ሀሰተኛ የቀበሌ መታወቂያ ሰነዶችን መገልገል ወንጀል ፈጽሟል በሚል በሰሜን ጎጃም ዞን ፍትሕ መምሪያ ክሶች ቀርበውበታል፡፡
ተከሳሹም የቀረቡበትን ክሶች ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የባሕርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን ማስረጃዎች በመስማት ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ሰጥቶ የመከላከያ ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ ተከሳሹ የቀረቡበትን ክሶች መካለከል አልቻለም::

በመሆኑም በ1ኛው ክስ ስር በወ/ህግ አንቀጽ 671(2) ስ፣ በ2ኛው ክስ በወ/ህግ አንቀጽ 27(1) እና 671(1)(ሐ) ስር፣ እንዲሁም በሶስተኛው ክስ በወ/ህጉ አንቀጽ 378 ስር ድንጋጌዎችን በመቀየር የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶ፣ የቅጣት አስተያየቶችን በመመርመር ተከሳሹ በአጠቃላይ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ መስጠቱን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።
https://t.me/abbaytv2015
https://t.me/abbaytv2015
❤2
በቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ለመሸለም ወደ መድረክ የወጣችው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አርቲስት ማስተዋል ወንድወሰን "በህይወታችሁ ለውጥ ማምጣት ከፈለጋችሁ ጌታን ተቀበሉ" ብላለች። (Fast Mereja እንደዘገበው) የሁሉ በሆነ መድረክ ስብከት ለምን ብለዋል ብዙዎች #ሼር
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈረመ
***
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡
ስምምነቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።
ውይይቱ እና ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ሲካሄድ ነው የቆየው።
ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋ ከበደ በአስተላለፉት መልዕክት፣ ዛሬ ለክልላችን ሕዝብ የመጀመሪያው ትልቅ የሰላም ኩነት የተካሄደበት ቀን ነው ብለዋል።
ከግጭት አሸናፊም ተሸናፊም የለም፣ ከሰላም ሁሉም ያተርፋል፣ ስምምነቱ ለሰላም ወዳድ ሕዝባችን ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ነው ያሉት፡፡
የሕዝብና የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለመጡ ወንድሞቻችን እንደ መንግስት አድናቆትና ክብር አለኝ ብለዋል፡፡
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በበኩላቸው፣ ማንኛውም ግጭት በመጨረሻ የሚፈታው በውይይትና በድርድር ነው ብለዋል።
ችግሮችና የሀሳብ ልዩነትን በንግግር መፍታት ፖለቲካዊ ሽንፈት ሳይሆን ጥበብና ብልጠት መሆኑን ገልጸው፣ ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ አዳዲ በበኩላቸው፣ ስምምነቱ የሀገሪቱን ቀጣይ መዳረሻ የሚያቃና ነው ብለዋል።

የ22 የስፖርት ውድድር ውርርድ ደርጅቶች (ቤቲንግ ድርጅቶች) ፈቃድ ተገደ።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ22 የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የስፖርት ውርርድ ፈቃድ (ቤቲንግ ድርጅቶች) ከህዳር 25 ቀን 2018 ጀምሮ የታገደ መሆኑን አስታውቋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በኅብረተሰቡ ትብብር አማካኝነት ለመንግሥት ገቢ መሆን የነበረበትን ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ የስፖርት አወራራጅ ድርጅት ባለቤቶችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው በይፋ መገለጹ ይታወቃል።
ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በተላከው መረጃ መሰረት ከዚህ በታች ስማቸው በዝርዝር የተጠቀሰው የስፖርት ውድድርና ውርርድ ድርጅቶች የወንጀል ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስ የስፖርት ውድድር ውርርድ የስራ ፈቃዳቸው ከዛሬ ጀምሮ የስራ ፈቃዳቸው ታግዷል፡፡
ፈቃዳቸው የታገደ የስፖርት ውድድርና ውርርድ ቤቶች ፦
- ዳሽ ቤት ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ዋልያ ስፖርት ኃ/የ/የግ/ማህበር
- ኤክስኔት ሶሎሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር/ቱ ኤክስ ቤት/
- ኤች ዲ ኤም /አፍሮ/ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ብላክ ፐርል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- አይከኒክ ስፖርት ኢንተርቴይመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ጃምቦ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ዳአባአክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ኢቲኤል (ኪዉክ) ኃ/የ/የግ/ማህበር
- ቤትአራዳስፖርትእናኢንተርቴመንትኃ/የተ/የግ/ማህበር/ሱፐር/
- ቫሞስ ኢንተርቴይመንት ኃ/የ/የግ/ማህበር - ፍላሽ ስፖርት ውርርድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ሁለገብ ኦንላይን ሶሎሽን ኃ/የ/የግ/ማህበር
- ዘመን ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ሁሉ ጌሚንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- አዲስ ቴልኮ ሰርቢስ አክሲዮን ማህበር/ቤቲካ ስፖርት ውርረድ/
- ዩኒክ /መላ/ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ቶቶ ስፖርት ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ኩኩሉ ስፖርት ስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- መርኬ ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር/ሻምፒዮን/
- ቤት ዘጠኝ ዘጠና አራት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
- ሀሪፍ የስፖርት አገ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር
@tikvah

የውድቀት አዋጅ!
እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያውያን ለደህንነታቸው የቆመ፣ ሀላፊነት የሚሰማው አስተዳዳሪ የሚያገኙት መቼ ነው?! (በድሉ ዋቅጅራ)
በመጀመሪያ
ከአርባ በላይ በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረውም/ሳይማሩም ተመርቀው፣ወይም ትምህርታቸውን 12ኛ ላይ አቁመው፣ እዚህ ግባ የሚባል የስራ እድል በሌለባት ሀገር የሚበተኑ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያን እንደስራ ፈጠራ/እድል በመጠቀም እራሳቸውን በገቢ ለመደጎም የሚያደርጉትን ጥረት በጅምላ አልቃወምም፡፡
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆኑኝ በቁጥር ጥቂት የማይባሉት፣ ለይዘት ፈጠራ ያጠራቸውን እውቀትና የህይወት ልምድ ድንቁር፣ የአእምሮና የስነልቦና ችግር በወለደው ድፍረትና ንቀት ተክተው ‹‹የደደቡትና የሰገጡት›› ናቸው፡፡ እንደሰመረ ባሪያው አሌክስ አብረሀም ወዘተ. ያሉ ሰዎች በቲክቶ በሚሰሩት ጠቃሚ ይዘት ስማቸው እንኳን ሳይጠራ፣ አለመለወጥን፣ አእምሮን ያለመጠቀምን አርማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን መኪና የሚሸልሙ፣ በሚሊየን የሚቆጠር ተከታዮች እንዲያገኙ የሚያግዙ ተቋማትን መመልከት እጅግ በጣም ይሸማቅቃል፤ በሀገርና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ይሁን እንጂ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ‹‹በሀገር እና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ መቁረጥ፣ ሀገርን ለደንቆሮዎች፣ ለደፋሮችና ለአንባገነኖች አሳልፎ መስጠት ነው፡፡›› ይሉ እንደነበረው፣ ይህን ‹‹እንዳሻው›› ብሎ ማለፍ ያዳግታል፡፡
ምን አይነት ተቋማት ናቸው ይህን የሽልማት ፕሮግራም የሚያዘጋጁትና በገንዘብ የሚደግፉት? ለነዚህ ተቋማት ሀገርና ማህበረሰብ ከሸቀጣቸው ማራገፊያነት የዘለለ ትርጉም የላቸውም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የከሳቴ ብርሀን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ‹ሰገጠ› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ክፉ ሰው፤ ሞገደኛ፤ የሰውን ነገር የማይቀበል፤ . . .›› ሲል ይፈታዋል፡፡

🥰1
የሽልማቱ ሲገርመን፣‹‹ሰግጥ - ፈምስ›› የሚባል ሀገራዊ ጉዞ፣ አዶናይን ይዞ፣ ድንቁርናን ተመርኩዞ፣ ሊዘጋጅ ስለመሆኑ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱን ተመለከትኩ፡፡ ‹‹በኤ.አይ የተሰራ ነው በሉኝ›› ብዬ፣ ሰዎች ጋ ደወልኩ፡፡ የተመኘሁት ሳይሆን ቀርቶ እውነት ነው፡፡
ልጆችና ወጣቶች በተለያየ ምክንያት የነዚህ ቲክቶከሮች ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እኔን እንቅልፍ የነሳኝ ፈጽሞ በማልጠብቀው ሁኔታ፣ የጋዜጣዊ መግለጫው ተናጋሪ ወይዘሮና የሰራዊት ፍቅሬ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ሴት ለልጆችዋ፣ ‹ደድቡ፣ ሰግጡ› ትላለች ማለት ነው? በአፍለኛው የሬዲዮ ድራማ አሀዱ ብሎ፣ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ፣ እዚህ የደረሰው ሰራዊት ፍቅሬ፣ የመጣበት የሙያ ትግል ጉዞ ላይ ውሀ ከልሶ፣ ‹ሰግጥ - ፈምስ› የሚል ሀገራዊ ዘመቻ ፊታውራሪ ለመሆን የተነሳው ምን አስልቶ ነው? ለመሆኑ ሰራዊት የዚህ አካል መሆኑ ለልጆቻችን የሚያስተላልፈው መልእክት፣ ‹እዚህ የደረስኩት፣ ‹ደድቤ - ሰግጬ ነው› የሚል እንደሆነ ያውቃል?
የትምህርት ስረአታችን ማጥ ውስጥ ነው!
በሙስና ተጨማልቀናል!
የሀይማኖት ተቋሞቻችን ረክሰው አለማዊ መድረኮችን እየመሰሉ ነው! . . . ይህ ሁሉ አልቆረቆራቸውም፤ ለዘመቻ አላነሳሳቸውም፡፡ ‹‹ወርቅ በወርቅ›› ብሎ ፊልም የሰራበት፣ ሀገራችን የምትታወቅበት አትሌቲክስ ተዋርዶ፣ ከአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለ ወርቅ መመለሳችን እንኳን ሰራዊት ፍቅሬን በቁጭት ለተግባር አላነሳሳውም፡፡ ሰራዊትን ለሀገራዊ ዘመቻ ያነሳሳው የሀገሪቱ የደደቦች፣ የሰገጤዎች ማነስ ነው፡፡
በመጨረሻ
ይህ ጉዞ የሀገራዊና ማህበረሰባዊ ውድቀታችን ይፋዊ አዋጅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት፤
ባህል ሚንስቴር፣ ትምህርትት ሚኒስቴር፣ በወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሚንስቴሮች፣ ካሉ (አሉ ብዬ አምናለሁ) ይህ ጉዞ መታገድ አለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀይማኖት ስም፣ በአነቃቂ ንግግር ስም፣ በይፋ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችንን የሚቃረኑና የዘቀጡ፣ ለማጭበርበር የቀረቡ ይዘቶች በማቅረብ፣ በህዝብ በተለይ ባልተማረው ማህበረሰብ ስነልቦና ላይ የሚጫወቱ የማህበራዊ ሚድያ ይዘት አቅራቢዎች ላይ ህጋዊና ተገቢ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡:

ዜና ችሎት፡
የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደባቸው! 🚨
የቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በእስራት ተቀጡ
አዲስ አበባ - የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የ 7 ዓመት ከ2 ወር ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው።
ዛሬ አርብ፣ ኅዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም.የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት።
አቶ ታዬ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል።

❤4
ቲክቶከሮቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ
ሕዳር 30/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በ3ኛው የጂ ፓወር ክርኤቲቭ አዋርድ ላይ ከሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ መልኩ ሰውነታቸውን ያጋለጠ አለባበስ ለብሰው፤ በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸውን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ ማጣራት መጀመሩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የ"ቲክቶክ ክርኤቲቭ አዋርድ" ላይ "ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ እና ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው፤ በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች" ላይ ምርመራ መጀመሩን ነው የገለጸው።
በዚም መሠረት ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣ በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣ መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣ ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል።
ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ፤ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ይፋ አደረገ
የአውሮፕላን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ የሚቀጥል ሲሆን ፤ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ግን ጭማሪ ተደርጎበታል።
በእዚህም መሰረት ፦
- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር እንዲሸጡ የተወሰነ መሆኑ ታውቋል።

❤5
ዋልያዎቹ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !
የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል ከደቂቃዎች በፊት በግብፅ ካይሮ ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ' ዋልያዎቹ ' በማጣሪያው በምድብ 1️⃣0️⃣ ተደልድለዋል።
የኢትዮጵያ ምድቡ ምን ይመስላል ?
⏩ ኢትዮጵያ
⏩ ሱዳን
⏩ ሞዛምቢክ እና
⏩ ሴኔጋል ጋር በአንድ ምድብ ተደልድለዋል።
የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አራት ከኬንያ ፤ ጊኒ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር ተደልድሏል
የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ በኬንያ ፤ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አዘጋጅነት ይካሄዳል።
ማጣሪያው በመስከረም ፤ ኅዳር እና መጋቢት ወራት በሚኖሩ ሶስት የብሔራዊ ቡድኖች እረፍት ወቅት ይካሄዳሉ።

❤8👍3
ስፔን ፖርቹጋልን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የ16ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስፔን ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ሩብ ፋጻሜውን ተቀላቅላለች።
የስፔንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሜሪኖ ከመረብ አሳርፏል።

❤10