የቴሌብር ዕዳ ያለባችሁ በአስቸኳይ ብትከፍሉ ጥሩ ነው፤ የዲጂታል ዘመን ላይ “ዲጂታል ንቅሳት - Digital tattoo” የሚባል can Sir አለ። የሆነ ቦታ ላይ ከነደፈህ ሁሉንም የሕይወት ክፍልህ ጋር ይዳረሳል፤ በምንም ዐይነት ኬሚካል ወይም ቴራፒ አይጸዳም፤ የቴሌብር ዕዳ አልከፈልክም ማለት መረጃው ትራፊክ ጽሕፈት ቤት, መሬት አስተዳደር, ባንኮች, ፖሊስ ጣቢያ, ሆስፒታል, ትምህርት ቤት, ወዘተ መረጃዎችህን እየሄደ ይበክልብሃል። የምትሠራበት መሥሪያ ቤት ውስጥ ዕቃ ቢጠፋ ቅድሚያ ከሚጠረጠሩትውስጥ የመሆን ዕድልህ ሰፊ ይሆናል፤ ምናልባትም ሥራ ማግኘት ልትቸገር ትችላለህ፣ ዕዳው 20 ብር ሊሆን ይችላል፣ ግን ቀይ ያበራል። የዜግነት ደረጃህና እምነትህ የሚለካው በሚኖርህ የክሬዲት ነጥብ (Credit score) ነው።